Telegram Web Link
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተባለው ምስባክ

“ምድርኒ ወሀበት ፍሬሃ፤
ወይባርከነ እግዚአብሔር አምላክነ።
ወይባርከነ እግዚአብሔር፤
ወይፍርህዎ ኵሎሙ አጽናፈ ምድር።”
[መዝሙር ዳዊት 67: 6-7]

በግእዝ አጨናነኳችሁ አ..?? አይዞን እኔም ምስባክ ላይ በአማርኛ ሲሉት ስሰማ ጥቅሱን ይዤው ነው😁😁

“ምድር ፍሬዋን ሰጠች፤
እግዚአብሔር አምላካችንም ይባርከናል።
እግዚአብሔር ይባርከናል፥
የምድርም ዳርቻ ሁሉ ይፈሩታል።”

ከዝናብ በኋላ ምድር ፍሬዋን ትሰጣለች.. እንዲሁ ከእግዚአብሔር በረከት ወይም ጸጋ በኋላ ከምድር የተዘጋጀን እኛ ደግሞ ፍሬን እንሰጣለን.. ሰው ጌታችን ኢየሱስ ከሚሰጠው ከሕይወት ውኃ ሳይጠጣ ፍሬን ማፍራት አይችልም.. እኛ ደግሞ ከዚህ ውኃ ጠጥተናልና እንደ ምድረ በዳ እሾህና አመኬላን እንደሚያበቅል ምድር አንሁን.. ከኃጢአት ሁሉ እየራቅን ከጸጋው የተነሳ ፍሬን እናፍራ..

“እግዚአብሔር አምላካችን ይባርከናል”

መልካም የጌታ ቀን

@Apostolic_Answers
🕯የቤተ ክርስቲያን ካህን ላንተ እንደ መንፈሳዊ አባት ይሁንልህ:: አንድ ሕመምተኛ ስውር በሽታዎቹን በግልጽ ለሐኪም እንደሚያሳይና ከዛም እንደሚድን ሁሉ አንተም ሚስጥሮችህንለካህን በግልጽ ንገር [ ትድንማለህ ]

•ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ

መልካም የጌታ ቀን (ሰንበት )!

⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
"አባቱ አየውና አዘነለት፤"
(ሉቃ. 15፥20)
***
ይህ ልጅ አባቱ በቁሙ ሳይሞት ገና ንብረት ያወርሰው ዘንድ ጠይቆ የድርሻውን ወስዶ ያባከነ ከንቱ ልጅ ነበር። አባት ሳይሞት ከንብረትህ የድርሻዬን አካፍለኝ ማለት አባት እስኪሞት እንደመቸኮል ያለ ጽኑ በደል ነው፤ የአባቱን ውርስ ወስዶ ማባከን ደግሞ ሌላ በደል!
ግን አንድ ነገር ሕይወቱን መለሰችለት፦ የአባቱን መልካምነት አልዘነጋም፤ በአባቱ መታመኑን አልተወም። ወደ ልቡ ተመልሶ ያደረገው ነገር ጽኑ በደል መሆኑን አምኖ ተጸጸተ፤ ልጅ ሊባል እንደማይገባውም ተናዘዘ። ልጅ ሊባል እንደማይገባው ቢያምንም የአባቱን ቸርነት አልረሳም። ምሕረትን የምትሻ፣ ከሞት ጋር የተካከለች የጎሰቆለች ሕይወቱን ይዞ ወደ አባቱ ቤት ተመለሰ።
አባቱ ከቤቱ በር ሆኖ የልጁን መምጣት እየተጠባበቀ ሩቅ ይመለከታል። የተጎሳቆለ ልጁን ከሩቅ ሲያየው አዘነለት። ልብ ይነካል!
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የአባቱን ቸርነት በዚህ መንገድ ገለጠልን። ከእርሱ ጋር አንድ ፈቃድ ያለውን የአባቱን ልብ ገልጦ አሳየን። ሐዋርያው ጳውሎስ “ዓለም ሳይፈጠር፥ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን፤” በማለት ከዘላለም በአብ ልብ ውስጥ ለእኛ ታስባ የነበረች ቸርነቱን ነገረን። (ኤፌ. 1፥4) ቅዱስ ያዕቆብ ዘእልበረዲ "አባታዊት ርኅራኄ የምትገለጥበት ጊዜ ሲደርስ" ሰው ሆኖ አዳነን ብሎ የገለጣት ይህችን ቸርነት ነው።
ጌታችን ስለ አባቱ ሲነግረን በጽኑ በደል የተለየውን ክፉ ልጁን ከሩቅ አይቶ በሚያዝን እና በመመለሱ ደስታን በሚያደርግ ቸር አባት ምሳሌ ነው። በደለኛ ስለሆነ ዓይኔን እንዳያይ በሚል መራር አባት ምሳሌ አይደለም። ይህን የእግዚአብሔር ቸርነት እና ፍቅር በምልዓት ሊረዳው የሚችል ፍጡር የለም፤ ከእውቀት በላይ ነው።
ኃጢአታችን እጅግ የበዛ የምድር ጎስቋሎች ብንሆን ይህች አባታዊት ቸርነት ትጠብቀናለች፤ ከሩቅ ትመለከተናለች። በአባታቸው ቸርነት አምነው በእውነተኛ ንስሐ የሚመለሱትን ልታቅፍ ዘወትር የተዘጋጀች ናት። ቀድሞ በልጁ ሞት የተደረገች መዳናችን በዚህች ቸርነት ላይ የተመሠረተች ነች። የምንታደስባት ንስሐችንም በዚህች ቸርነት ላይ የተመሠረተች ናት።
መንፈስ ቅዱስ በልባችን የሚያፈሰው አባ አባት ብለን እንድንጮህ የሚያነሣሣ የልጅነት መንፈስ ይህን የእግዚአብሔር አባትነት ከልብ ማመን ነው፤ በዚህች ቸርነት ላይ መደገፍ ነው። (ገላ. 4፥6)
***
ሰማያዊ አባታችን ሆይ፥ ስምህ ይመስገን!

Bereket Azmeraw

⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
ውድ እህቴ ኦርቶዶክሳዊ ኑሮ ለመኖር የምትፈልጊ ከሆነ የምነግርሽን ነገር አድምጪኝ። ሁልጊዜም በተወሰነ ሰዓት የመንቃት ልምድ ይኑርሽ :: በማለዳ በእግዚአብሔር ፊት ለመቆም ከአልጋሽም ለመነሳት ምክንያተኝነትን ከአንቺ አስወግጂ :: ከእንቅልፍሽም በነቃሽ ጊዜ የተሰቀለውን ጌታችንን በመስቀል ላይ እንዳለ አድርገሽ አስቢ :: ራስሽን በብርድ ልብስ ሙቀት አታታይ :: ከመኝታሽ አፈፍ ብለሽ ተነሽ :: በሠራዊት ጌታ በልዑል እግዚአብሐር ፊት ልትቆሚ መሆኑን አስቢ:: ሁልጊዜም የእናትሽን የሔዋንን ውድቀት እያሰብሽ :: አምላክሽን የሚያስብ በጎ ኅሊና እንዲኖርሽ በሥጋም ሐሳብ ተጠልፈሽ እንዳትወድቂ ፈጣሪሽን ለምኝው።

⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
"የእግዚአብሔር ጸጋ የምትሰጠው እምነታቸውን ለሚናገሩት ሳይሆን እምነታቸውን ለሚኖሩት ነው።"
~ ቅዱስ ጎርጎሪዎስ ነባቤ መለኮት

“በተግባርና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት ብቻ አንዋደድ።”
  — 1ኛ ዮሐንስ 3፥18
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
'' ሰው ከተስተካከለ ዓለሙም🌍 ይስተካከላል!''

አንድ የመዋዕለ ህፃናት ርዕስ መምህር እሁድ ጠዋት የሚያስተምሯቸውን ህፃናቶች እና ወላጆቻቸውን ሰብስበው እየተናገሩ እያለ አንድ ህፃን ልጅ ሲያስቸግራቸው የሚጫወትበት ተገጣጣሚ መጫወቻ (puzzle Game) ይሰጠዋል ። ጨዋታው የተበታተነውን የአለም ካርታ ገጣጥሞ የተስተካከለ ዓለም🌍 ማምጣት ነበር።የዓለም ካርታው ውቅያኖስ እንዲሁም የተለያዩ ነገሮችን የያዘ በመሆኑ ህፃኑ ለማስተካከል ቸገረው። ነገር ግን የካርታውን ክፍልፋዮች ሲገለብጥ የሰው አካል ቁርጥራጭ ስእሎችን አገኘ ። ይህ የሰው ስእል የአለሙ ካርታ በትክክል ሥፍራውን ከያዘ በሃላ በእስኪብርቶ የተሳለ ስእል ነበር። ህፃኑ ታድያ ስዕሉን እንዲሁም አባቱን እየተመለከተ የተሳለውን የሰው ስእል ቦታ ቦታውን ያሲዘውና ገልበጥ ሲያደርገው የዓለሙ 🌍 ካርታ ተስተካክሎ አገኘው።

ወዲያውም ለአባቱ ያሳየዋል አባትየውም በመገረም እንዴት እንዲህ በፍጥነት አስተካከልከው ቢለው ህፃኑም ሰውየውን ሳስተካክለው የዓለም ካርታውም ተስተካከለልኝ አለው። ያም ርዕሰ መምህር በነጋታው ጠዋት ባልደረባዎቹን ሰብስቦ ሰው ከተስተካከለ ዓለሙም ይስተካከላል ሲል ተናገረ።

(ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኘ)

⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እግዚአብሄርን በፍፁም ልባናችን ልንወደው ይገባል

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ስንወደው ጓጉተን እንጠብቀዋለን

ወንድም አኬ

⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
'' ለክርስቶስ ከሚኖር ሰው በቀር ነፃ ሰው የለም ! ''

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️

#ለሌሎች_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ🤗
መስቀል ዕፀ ሕይወት ነው። መስቀል ዕፀ መድኃኒት ነው። መስቀል ዕፀ ትንቢት ነው። መስቀል ዕፀ ዕረፍት ነው።

መስቀል ሰይጣንን የሚያጠፋ ምሳር ነው። የአጋንንትንም ራሶች የሚቆርጥ ሰይፍ ነው።

መስቀል ርኵሳን መናፍስትን የሚወጋቸው የእሳት ዘገር ነው። የአመስቴማውያንንም ሠራዊት የሚመታ የመብረቅ ጦር ነው።

መስቀል ማኅተመ ሥላሴየሌለው ሰው ወደእርሱ ሊቀር በው የማይቻለው አምባ መጠጊያ ነው። መስቀል ከግራም ከቀኝም ለሚመጣ ጠላት የጽድቅ ጋሻ ነው። ጳውሎስ ውጊያችሁ ከሥጋና ከደም ጋር አይደለምን እንዳለው መስቀል የጦር መሣርያ ነው።

መስቀል የጦር ውጋት ሊቀድደው፣ የቀስትና የዘንግም ጫፍ ሊበላው የማይችል የሃይማኖት ጥሩር ነው። መስቀል አማሌቃውያንን ለመዋጋት በራፊድ በረሐ በተዘረጋው ስሙሴ እጅ አምሳል የተሠራ ነው።

መስቀል ሰሙሴ እጅ ወደ ውስጥ በተጨመረ ጊዜ መራውን ውኃ በቀር በረሐ ያጣፈጠ ነው። መስቀል የቅድስናና የንጽሕና ማኅተም ነው።

መስቀል ለሚጋደሉ የድል አክሊል፤ ወደ በጉ ሰርግ ለተጠሩትም የሰርግ ልብሳቸው ነው። መስቀል የማይነጥፍ ምንጭ፣ በቁዔትም ጥቅምም የሞላበት የክብር ጉድጓድ ነው።

(ውዳሴ መስቀል - በአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ)

#ለሌሎች_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇🤗
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
+ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ምክር +

☞ ተወዳጆች ሆይ ጊዜ ሳለልን ድኅነታችንን እንፈጽም፡፡ ጊዜ ሳለልን ለመብራታችን ዘይት የተባለ ምጽዋትን እንያዝ፡፡ ጊዜ ሳለልን መክሊታችንን ለማብዛት እንፍጨርጨር፡፡ በዚህ ዓለም ሳለን ይህን ለማከናወን ልል ዘሊል እና ሐኬተኞች ከኾንን በወዲያኛው ዓለም እልፍ ወትእልፊት ጊዜ ወዮ ብለን ብናለቅስ ብንጮህም እንኳን የሚረዳን የለምና፡፡ ያ ባለ አንድ መክሊት ሠራተኛ አንዲቷን መክሊት ሳይቀንስ ለጌታው ቢያስረክብም ከኩነኔ አላመለጠምና፡፡ አምስቱ ሰነፎች ደናግልም ጌታችንን ለምነውት ነበር፤ በሩን አንኳኩተው ነበር፡፡ ነገር ግን ልመናቸውም ማንኳኳታቸውም ከንቱ ነበር፥ ጥቅም አልባ ነበር፡፡

☞ስለዚህ እነዚህን ነገሮች ዐውቀን በሀብታችንም፣ በትጋታችንም፣ ለወንድማችን በምናደርገው ማናቸውም ጠቃሚ ነገርም የዓቅማችንን ያህል እንጣር፡፡ መክሊት የተባለው የእያንዳንዱ ሰው በእጁ ያለውና ማድረግ የሚችለው ነገር ማለት ነውና፡፡ ለአንዱ ወንድሙን መጠበቅ ሊኾን ይችላል፥ ለአንዱ በገንዘቡ ደግ ነገር ማድረግ ሊኾን ይችላል፥ ለሌላው ማስተማር ሊኾን ይችላል፥ ለሌላው ደግሞ ይህን በመሰለ ሌላ ነገር ሊኾን ይችላልና ጊዜ ሳለልን በሞተ ሥጋም ሳንወሰድ መክሊታችንን እናብዛ፡፡ አንድ ሰውስ እንኳን መክሊቴ አንዲት ናት አይበል፡፡ የተሰጠችህ መክሊት አንዲት ብትኾንም አንተ ንቁ ከኾንህ ንዑድ ክቡር ከመባል አትከለከልምና፡፡ ምንም ያህል ድኻ ብትኾንም ከዚያች ኹለት ሳንቲም ከሰጠችው ሴት በላይ ድኻ ልትኾን አትችልምና የተሰጠቺኝ ትንሽ ናት አትበለኝ፡፡ ከቅዱስ ጴጥሮስና ከቅዱስ ዮሐንስ በላይ ያልተማርክ ልትኾን አትችልምና እኔኮ አልተማርኩም አትበለኝ፡፡ እነርሱ ምንም ያልተማሩ ቢኾኑም ባሳዩት ትጋት ርስት መንግሥተ ሰማያትን መውረስ ተችሎዋቸዋልና እኔ አይቻለኝም አትበለኝ፡፡

☞ እግዚአብሔር አንደበትን የሰጠን ለዚህ ነው፡፡ እግዚአብሔር እግርን የሰጠን ለዚህ ነው፡፡ እግዚአብሔር ብርታትን፣ አእምሮን፣ ማሰብን የለገሰን ለዚህ ነው፡፡ እነዚህን ኹሉ የሰጠን ለራሳችን እንድናተርፍባቸውና ለባልጀሮቻችንም እንድንጠቅምባቸው ነውና ኹለት ወይም አምስት መክሊት አልተሰጠኝም አትበለኝ፡፡'

ተርጓሚ፦ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ

#ለሌሎች_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇🤗
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
በመስቀል ጉዳይ ከትውፊታውያን አብያተ ክርስቲያናት የምንጋራቸው ምንባባትና ሥርዓታት

ደብተራ በአማን ነጸረ

--
1.ውዳሴና ክብረ መስቀል
ውዳሴ መስቀል የሚባል የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ድርሰት አለ፡፡ በእንግሊዝኛ ከምናገኘው Exaltation of the Holy Cross የሚል የምሥራቃውያን ትውፊት ተዛምዶ ሊኖረው ይችል ይሆናል፡፡ የነገረ መስቀል ታሪክና ድርሰቶች በምሥራቁም በምዕራቡም ተቀራራቢነት አላቸው፡፡ ከመስቀል ጋራ የተገናኙ ተዛማጅ ምንባባት አሉን፡፡ እንጥቀስ፡- “ለመስቀልከ ንሰግድ ኦ ሊቅነ፣ ወለትንሣኤከ ቅድስት ንሴብሕ ኵልነ፣ ይዕዜኒ፡፡ ወዘልፈኒ - መምህራችን ሆይ! ለመስቀልህ እንሰግዳለን፣ ቅድስት ትንሣኤህን እናወድሳለን፣ ዛሬም ዘወትርም - Before thy Cross, we bow down in worship, O Master, and thy holy resurrection we glorify” ቅዱስ ቴዎፍሎስ ዘእስክንድርያ ‹‹The cross is the helper of the wretched, assisting all the oppressed.›› ሲል የደረሰው ድርሰት በቅ/ያሬድና አባ ጊዮርጊስ ቃል በቃል ‹‹ለአግብርት፡ ግዕዛን፣ ጽንዕ፡ ለድኩማን፡ መስቀል፡፡ - መስቀል ለባሮች ነጻነት፣ ለደካሞችም ረዳት ነው›› በሚል ሰፍሯል፡፡

በበረከት አዝመራው ( Bereket Azmeraw አነጋገር መስቀልን እንደ ግዑዝ ሳይሆን እንደ ሕያውና ሰማኢ ባለግዕዛን አካል አድርጎ መናገር (Personification) በእኛም በሌሎችም አለ፡፡ በፕ/ር ጌታች የተሰባሰበ የነገረ መስቀል ድርሳን፡- ‹‹ወሶበ ተቀኖከ መስቀል ምስለ እደ ክርስቶስ ክቡር፡፡ ሞተ መልአከ ሞት መኰንነ ኵሉ ፍጡር፡፡ ወሙታንሂ ተንሥኡ እምዝህር - መስቀል ሆይ! ከከበረ የክርስቶስ እጅ ጋራ ብትቸነከር፣ የፍጥረታት ሁሉ ገዢ የሆነ የሞት መልአክ ሞተ፣ ሙታንም ከመቃብር ተነሡ›› ይላል፡፡ መስቀልን እንደ ሰው ያናግረዋል፡፡ ግባጻውያን በውዳሴያቸው (Doxology) መስቀልን ግዕዛን ሰጥተው እንዲህ ያናግሩታል፡- ‹‹ We carry you, O Cross, the strength of the Christians, powerfully around our necks, and we proclaim openly. - የክርስቲያኖች ብርታት የምትሆን መስቀል ሆይ! በአንገታችን ዙሪያ አጽንተን እንይዝሃለን፤ በይፋም እንሰብክሃለን፡፡›› እንደ ሰው ያናግሩታል፡፡ ‹‹Hail to you, Praise to You, We bow down - ስብሐት ለከ፣ ንሰግድ ለከ - እናመሰግንሃለን፣ እንሰግድልሃለን›› የሚል መነሻ ያላቸው ድርሰቶች በሁላችንም ዘንድ አሉ፡፡ መስቀል ይከበራል፣ የጸጋ ስግደት ይሰገድለታል! የመስቀል ድርሰቶች ቢነጻጸሩ ዝምድናቸው ሰፊ ነው፡፡

---
2.መታሰቢያ
የመስቀል ከተዳፈነበት በንግሥት ዕሌኒ መውጣት ከሞላ ጎደል ዓለም አቀፋዊ ታሪክ ነው፡፡ አከባበሩና የሚከበርበት ቀን በመጠኑ ሊለያይ ይችል ይሆናል፡፡ መስቀል ሁለት ጊዜ ይታሰባል፡፡ መጋቢት 10 እና መስከረም 17፡፡ የመጋቢቱ ዐቢይ ጾም ወይም የኢየሱስ ጾም (ጾመ ኢየሱስ) ላይ ይውላል፡፡ (አሁን አሁን በንግሥ ዙሪያ ትውፊቱ ቢሸረሸርም) በኢየሱስ ስም በተሠየው ጾም በዓልን ያውም የአደባባይ በዓል ማክበርን ቀኖናችን አይፈቅድም፡፡ (መስቀሉንና የመስቀሉን ጌታ ልዩነት አበጥረን እናውቃለን! ብንል አጉል ትምክሕት አለመሆኑን እዚህ ላይ አስተውል!) በዓሉ የጌታን ጾም ክብር እንዳይጋፋ ተጠቃሎ መስከረም ላይ ይከበራል፡፡ መስቀል በዝክር ብቻ አይቀርም፡፡ በስሙ ቤተ ክርስቲያን ይታነጻል፡፡ ‹‹መስቀለ ኢየሱስ›› የሚባል ቤተ ክርስቲያን አለን፡፡ በወላጆቼ አካባቢ ‹‹ወር/ዕ/ያ መስቀል›› የሚባል ደብር አለ፡፡ በግብፆች፣ በምሥራቆችና በካቶሊኮች ‹‹Holy Cross Church of Coptic Orthodox Church, Holy Cross Greek Orthodox Church, Holy Cross Catholic Church›› በሚል ስም አብያተ ክርስቲያናት መትከል የተለመደ ነው፡፡
---
3.የመከበሩ ፋይዳ
መስቀል ለክርስቲያኖች የስቃይ ታሪክ ብቻ ሳይሆን ከስቃይ በኋላ የሚገኝ ድል አድራጊነት ይዘከርበታል፡፡ ተዘክሮውን Contemplation ሲሉት ሰምቻለሁ፡፡ ነገረ ድኅነት ይታሰብበታል፡፡ የድኅነት መሣሪያ (Instrument of Redemption) ይሉታል፡፡ በተደጋጋሚ እንደምንለው መስቀል የክርስትና አርማ ነው፡፡ ባንዲራ ነው፡፡ ባንዲራውን ስታይ አገርህ ትታሰብሃለች (ከፈለግህ ክልልህም ትዝ ትበልህ! ምሳሌ ነውና)፡፡ ባንዲራው ጨርቅ መሆኑ አይጠፋህም፣ አይጠፋንም፡፡ ውክልናው ግን ከፍ ይላል፡፡ የሚመጣልህ ሐሳብ ጨርቁ ከምን ተሠራ አይደለም፡፡ ለክብሩ የተከፈለው ዋጋ ነው፡፡ መስቀል ክቡር ደም ፈስሶበታል! የሌላ ደም አይደለም፡፡ የፈጣሪ ደም ነው! ‹‹አኮ ደመ ካልዕ፡ አላ ደመ ወልድ ክቡር!›› እንዲል መስተብቊዕ ዘመስቀል፡፡
---
4.ማማተብ
ማማተብን ዕድሜ ለብሔራውያንና ዓለም አቀፍ ስፖርተኞች የክርስትና ቋንቋ አድርገውታል፡፡ ስናማተብ ‹‹በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ›› እያልን ከግንባራችን ጀምረን ወደታች፣ ከዚያም ወደግራና ቀኝ እናማትባለን፡፡ ጸሎትና የእምነት አዋጅ ነው! ‹‹በሥላሴ ሦስትነትና አንድነት አምናለሁ!›› ብሎ እምነትን ማወጅ ነው፡፡ በዚህ አዋጅ ሠይጣንን እንገሥጻለን፡፡ ይህም ድንበር ተሸጋሪ ትውፊት ነው፡፡
--
5.ሥርዓቱና ደመራው
በእኛ ታሪኩ በቃል ብቻ ተነግሮ አይቆምም፡፡ መስቀሉ የወጣበት ሒደት በአደባባይ በተምሳሌት ይገለጻል፡፡ የክርስትናው የአምልኮ ጠባይ ነው፡፡ ከምዕራቡ ለየት ያደርገናል፡፡ የእኛ ከዊንን/ ክዋኔን (Performance) ሲከተል የምዕራቡ ቃላዊ ገለጻን (description) ያዘወትራል፡፡ በመስቀል ዙሪያ ጥቅሶችን እየነካኩ ‹መስቀል የተባለው እንደዚህ ነው፣ እንደዚያ ነው እንጅ ዕንጨት ማለት አይደለም› የሚል ተቃዋሚ ቢነሣ አይገርምም፡፡ ማለፍ ነው! የአምልኮ መንገዳችን ስለሚለያይ፡፡ የተግባሩን ገለጻ ጥሬ ቃልና ጥቅስ በመፍተል ለመዳኘት የሚደረግ የሚዛን መለያየት ያመጣው ጣጣ ነው፡፡ እንለፈው! ላደለው ምልጣኑ ላይ ያለቺው ንሺ (የቅብብሎሽ ዜማ) ‹‹እመኑ ብየ፡ ወእመኑ በአቡየ፡ አበርህ በመስቀልየ - በእኔ እመኑ፣ በአባቴም እመኑ፣ በመስቀሌ አበራለሁ / ጨለማውን እገፋለሁ/›› የሚል ነው፡፡
በመስቀሉ ያብራልን!


#ለሌሎች_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇🤗
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
መንፈሳውያን ነን ብለው የሚያስቡ ሰዎች ኃጢአተኛ ነው ብለው ያሰቡትን ሰው አጠገባቸው ሲደርስ በእነርሱ ንጽሕና እንዲደናገጥ እና ጓደኛቸው ሁኖ መኖር እንደማይገባው እንዲያስብ በማድረግ ከአጠገባቸው ያርቁታል። እውነተኛ መንፈሳዊነት ግን እንደ ማግኔት ተቃራኒውን ይስባል ፡፡ የተቀደሱ ሰዎች በሃጢአት ለወደቁ ሰዎች ዕረፍት ይሰጣሉ። እግዚአብሔርን እንዲያስታውሱ ይረዷቸዋል መንፈሳዊ ነገር እንዴት መጀመር እንዳለባቸው ያማክሯቸዋል።

እመኑኝ ተወዳጆች የእግዚአብሔር ንጽሕና ኃጢአተኞችን የማቀፍ እና የማቅረብ እንጂ የማስበርገግ ፍላጎት የለውም ፡፡" ክርስቶስ ለኃጢአተኞች ያለውን ፍቅር እንዳትረሱ አደራ ልላችሁ እፈልጋለሁ። በቻላችሁት ሁሉ ከእግዚአብሔር የራቁትን የምታግዙ ኦርቶዶክሳዊያን ሁኑ ብዬ እለምናችኋለሁ ። ሰውን የምታቀኑበት የክርስቶስን ፍቅር በዙሪያችሁ ላሉ ሰዎች የምታደርሱበት መልካም ቀዳሚት ሰንበት ይሁንላችሁ🙏


#ለሌሎች_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇🤗
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
የተወደደ_ቀን_የተወደደ_ዓመት(128k)
@m_ezmur21
አምሽቶ የመጣ አይገባም አትበሉ
አባክኖ የመጣ አይገባም አትበሉ
ፍቅር ስለሆነ እግዚአብሔር ለሁሉ
ልጅ ቤቱን ይወርሳል እንደ ተስፋ ቃሉ 🥰

⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
ደብተራ በአማን ነጸረ የተደረገለት ቃለ መጠይቅ ላይ የተናገረው ነው ። እኛም እንደ እሱ መጻሕፍትን ለሚጽፉልን መጸለይ ቢለምድብን ጥሩ ነው

መልካም ዕለተ ሰንበት 🤗🤗

⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
"ላለማመን እንጂ ለማመን በዙሪያችን ብዙ ምስክሮች አሉልን"

ዓይነ ሥውሩ ቅዱስ ዲዲሞስ በአንድ ወቅት የእግዚአብሔርን መኖር የሚክዱ ተመራማሪዎች የራሳቸውን እውቀት መነሻ በማድረግ የእግዚአብሔርን አለመኖር ከነገሩት በኋላ "እስኪ አንተ እግዚአብሔር መኖሩን በተጨባጭ አስረዳን?" ሲሉ ጠየቁት። ቅዱስ ዲዲሞስ ተመራማሪዎቹ ጭልጥ ብለው መሳሳታቸውን ቢያውቅም በጥሞና ያዳምጣቸው ነበር እንጂ አልተበሳጨም። ለጠየቁት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት "ምሽት ተመልሳችሁ ኑ" አላቸው።

እነርሱም የቀጠሮአቸውን ሰዓት አክብረው ምሽት ተመልሰው መጡ። ቅዱስ ዲዲሞስም "እስኪ ወደላይ አንጋጣችሁ የሰማዩን ገጽታ ተመልከቱ" አላቸው። እነርሱም እንዳላቸው ሰማዩን ተመለከቱ። እርሱም "በሰማይ ላይ ምን ምን ይታያችኋል?" አለ። እነርሱም "ከዋክብት" ብለው መለሱለት። እርሱም "በስጋዊ አይናችሁ የማየት ችሎታ እነዚህን ክዋክብት በቀን ማየት ትችላላችሁን?" አላቸው። እነርሱም "አንችልም" አሉት። እርሱም "ለምን ማየት ያቅታችኋል?" ሲል ጥያቄውን በጥያቄ ደገመላቸው። እነርሱም "ምክንያቱም ከዋክብትን ለማየት የግድ መምሸት አለበት" አሉት። እርሱም "በእርግጥ ትክክል ናችሁ የመለሳችሁት ምላሽ ትክክል ነው። ይሁን እንጂ በተፈጥሮ እንደምናውቀው የተሰወረውን ነገር ለማግኘት ብርሃን ያስፈልጋል እነዚህን የምታዩአቸው ከዋክብት ለማየት ግን ብርሃን ሳይሆን ጨለማ ሊኖር የግድ ነው። እንደዚሁ ሁሉ እግዚአብሔርንም ለማየት ቁሳዊ ነገርን ማየት በሚቻልበት በሳይንስ መሳሪያና ፍልስፍና ሳይሆን በእምነት ብቻ ማረጋገጥ እንደሚቻል ልነግራችሁ እወዳለሁ።" በማለት አስረዳቸው።

 በድጋሚ "በሰማያት ገጽታ ላይ ከዋክብት እንደሚታዩ ነግራችሁኛል። ይሁን እንጂ እኔ ዓይነ ሥውር ስለሆንኩ በምን ታረጋግጥሉኛላችሁ?" ሲል አዲስ የጥያቄ ርዕስ ከፈተላቸዉ። እነርሱም ግራ ተጋብተው ምላሽ አጡ፤ እናም ከመናገር ይልቅ ዝምታን መረጡ። እርሱ ግን የእኔ ዓይነ ስውርነት የከዋክብቱን አለመኖር አያረጋግጥም፤ እኔ አየሁም አላየሁም ከዋክብቱ ዘወትር አሉ። እኔም ምንም ዐይነ ሥውር ብሆንም እንኳን ከዋክብቱን ሳልመለከት እናንተ አይታችሁ በነገራችሁኝ ምስክርነት ብቻ የከዋክብቱን መኖር አምኜ ተቀብየዋለሁ አላቸው። እኔ አንዳች ከዋክብት ሳልመለከት የከዋክብቱን መኖር እንዳመንኩ እናንተም በሥጋዊ አይናችሁ ባትመለከቱም እንኳን በእምነት እግዚአብሔር መኖሩን አታምኑምን? ብታምኑ መልካም ነው።" ሲል በትሕትና ጠየቃቸው። እነርሱም በጥያቄ መልክ ያቀረበላቸውን አስተሳሰቡን እና ምስክርነቱንም ተቀብለው የእግዚአብሔርን መኖር በእምነት አረጋገጥን አሉት። በዚህ የክርክርና የውይይት ሁኔታ ዓይነ ሥውሩ ቅዱስ ዲዲሞስ (በትሕትናውና በድክመቱ) የተናገሩትን አድምጦ የእነርሱን ዕውቀታቸውንና አስተሳሰባቸውን ተጠቅሞ ክብራቸውን ሳይጋፋ የእግዚአብሔርን መኖር በማሳመን ረታቸው። ክርክራቸውም በዚህ ተደመደመ።

(#ብፁዕ_ወቅዱስ_አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ "የሕይወት መንገድ" በመምሕር ሰለሞን በቀለ ከተተረጎመ መጽሐፍ የተወሰደ)

#ለሌሎች_ተደራሽእንዲሆን_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇🥰🤗

⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
2024/11/15 18:23:37
Back to Top
HTML Embed Code: