Telegram Web Link
"የእግዚአብሔር ጸጋ የምትሰጠው እምነታቸውን ለሚናገሩት ሳይሆን እምነታቸውን ለሚኖሩት ነው።"
~ ቅዱስ ጎርጎሪዎስ ነባቤ መለኮት

“በተግባርና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት ብቻ አንዋደድ።”
  — 1ኛ ዮሐንስ 3፥18
የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትን መስማት ቤተ ክርስቲያንን መስማት ነው ምክንያቱም ሊቃውንት የቤተ ክርስቲያን አንደበቶች ናቸውና
መንፈስ ቅዱስ አስቀድሞ በነቢያት በኋላም በሐዋርያት በኩል እንደተናገረ ዛሬም በተለያዩ መምህራን አድሮ ያስተምራል

በዘመናችን ርቱዕ አንደበት ከዕውቀት ጋር
ትሕትና ከትጋት ጋር
ቅንነት ከሊቅነት ጋር የተባበረላቸው አራት ዓይናው ሊቅ ሊቀ ሊቃውንት ዮሴፍ ደሳለኝ
#ዳቤር በሚል የሚዲያ አማራጭ ከኦሪት ዘፍጥረት እስከ ራእየ ዮሐንስ በተከታታይ ሊያስተምሩን መጥተዋል
ስለሆነም ይህንን ከታች የተያያዘውን ሊንክ በመጫን ወይም ዳቤር ብለን #youtube ላይ #search በማድረግ እና #Subscribe በማድረግ ሊንኩን ለሌሎችም በማጋራት እንድንከታተል ተጋብዘናል ።
ሊቃውንቱን ወደ መገናኛ ብዙኃን መረብ በማምጣት እናበረታታ

https://youtube.com/@yosef-daber?si=-jwo1UTiPZRMfOte
ወላዲተ_አምላክ_በዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ.pdf
352.7 KB
ወላዲተ አምላክ

*እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም "ወላዲተ አምላክ" ትባላለችን? ለምን?

* "ወላዲተ አምላክ" የቃሉ ትርጉም

* የቃሉ ነገረ መለኮታዊ ፋይዳ

* የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክነት በመጽሀፍ ቅዱስ ትምህርት

* የእመቤታችን ወላዲተ አምላክነት-በቀደምት አበው ትምህርት

+++++++++~~~+++++++

ቅዱስ ቄርሎስ ንስጥሮስ “ወላዲተ አምላክ” የሚለውን መቃወሙ በነገረ ክርስቶስና በነገረ ድኅነት ላይ የሚያስከትለው ነገር መሠረታዊ የሆነ ኑፋቄ መሆኑን በሚገባ አስረድቷል፡፡ እነዚህን ነገሮችም እንደሚከተለው በሚገባ ለይቶ አውጥቷቸዋል፡-

ከድንግል ማርያም የተወለደው አካላዊ ቃል የእኛን ባሕርይ ነሥቶ (ተዋሕዶ) ሥግው ቃል ካልሆነና ሰው ብቻ (ዕሩቅ ብእሲ) ከሆነ መዳናችን አደጋ ላይ ይወድቃል፡፡ ምክንያቱም ክርስቶስ የተቀበላቸው ሕማማትና መከራዎች የሥግው ቃል (ሥጋን የተዋሐደውና የእኛን ባሕርይ ባሕርዩ አድርጎ ሰው ሆኖ በሥጋ የተገለጠው አካላዊ የእግዚአብሔር ቃል) ሕማማትና መከራዎች ሳይሆኑ የዕሩቅ ብእሲ (የስው ብቻ) ይሆናሉና፡፡ ፍጡር በሆነ በሰው ብቻ መዳን አይቻልምና ስለዚህ ድነናል ማለት አይቻልም፡፡ ስለዚህ ወላዲተ አምላክ የሚለውን ቃል መካድ የአምላክን ሰው የመሆን ምሥጢር (ምሥጢረ ሥጋዌን) እና የሰውን መዳን መካድ ነው፡፡

እንደዚሁም አካላዊ ቃል አዲሱን ሰው ዳግማዊ አዳምን ለመፍጠር አካላዊ ቃል ከእኛ ባሕርይ ጋር ሊያደርግ የሚያስፈልገው ተዋሕዶ፡ ንስጥሮስ እንዳለው ዓይነት አፍኣዊና የጉርብትና ዓይነት ዝምድና ሳይሆን፣ ውሳጣዊና ባሕርያዊ የሆነ ጥብቅ እና አማናዊ የሆነ ተዋሕዶ ያስፈልገው ነበር፡፡ ይህ አይደለም ከተባለ የባሕርያችን መታደስ፡ በሐዲስ ተፈጥሮ የመዳናችን ነገር ሁሉ ከንቱ ይሆናል፡፡

#መድሎተ_ጽድቅ

#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
2. መዳናችንን እንፈጽማለን
3. እንድናለን
«ወንድምህን አትናቀው»

ወዳጄ ሆይ! ክርስቲያን ነህን? እንኪያስ በፍጹም ወንድምህን አትናቀው። እህትህን አትናቃት። ምንም ይሁን ምን ሰው አትናቅ። ይህ የምትንቀው ወንድም በተለይ ክርስቲያን ከሆነ ክርስቶስን እየሰደብከዉ እንደሆን አስተውል። "እንዴት?"  ያልከኝ እንደሆንም ይህ የምትንቀው ወንድምህ የክርስቶስ ሕዋስ (ብልት) ኾኗል። የክርስቶስ ሕዋስ ከኾነ ደግሞ እሱን ናቅኸው ማለት ክርቶስን ናቅኸው ማለት ነው። ወንድምህን የምትንቅ ከሆነም በጲላጦስ አደባባይ ጌታን ከገረፉት፣ እራቁቱን ከሰቀሉት፣ ሐሞትንና ከርቤን ቀላቅለው ከሰጡት፣ በፊቱ ላይም ከተፉበት ሰዎች በምንም አትተናነስም። ስለዘህ ወንድምህን ከመናቅ ተጠንቀቅ።

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
" ካንተ ጋር ተዋህጄ ምሥጢር ከማየት የከለከለችኝ ኃጢያቴን አርቅ ዘንድ ካንተ ጋር አንድነትን ስጠኝ፤ በንጽሐ ሥጋ የሚሰጥ ልዩ ብርሃንህን በመዋሃድ ደስ ይለኝ ዘንድ፣ በንጽሐ ነፍስ በሚሰጥ ልዑል ስፉህ በሚሆን ብርሃን በንጽሐ ልቦና በሚሰጥ በረቂቅ ብርሃንህ ደስ ይለኝ ዘንድ፤ መልክህን ከማየት የሚከለክሉኝ ሰይጣናት እንዳያዩኝ፣ አቤቱ ልቦናዬ በዚህም ዓለም ግብር በማሰብ እንዳይደክም ጌትነትህን ብርሃንህን ለማየት እንድማረክ አድርገኝ፤  አቤቱ ከፍቅርህ ሊለየኝ የሚቻለው አይኑር፤  የመላእክት ክብራቸው ዕውቀታቸው ተድላ ደስታቸው፣  ሁልጊዜ ጌትነትህን የሚያመሰግኑ ሁልጊዜ በፍቅርህ የሚቃጠሉ በፍቅርህ ብርሃን ገጽ ልቡናቸው የሚያሸበርቅ፣ ከሁሉ በምትበልጥ ተዋህዶ ካንተ ጋር በመዋሃድ ፊታቸው የሚያሸበርቅ፣ እውነት ነው፤ አቤቱ ሀብታት ምሥጢራትህን  ካንተ እሻለሁ፤ አንድነትህን ሦስትነትህን የማውቅበትን ዕውቀት በልቡናዬ ትገልጽ ዘንድ እማልድሃለኁ። "

አረጋዊ መንፈሳዊ
ቅዱስ ጳውሎስን በትክክል ስለመረዳት
***
ሐዋርያው በገላትያ እና ሮሜ መልእክቶቹ ስለ 'ኦሪት ሕግ' የተናገራቸው ጉዳዮች አሉ። አነዚህን ነገሮች በትክክል ለመረዳት ሐዋርያው ከማን ጋር እየተነጋገረ እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል። ጉዳዩ ከአይሁድ ዘመም ክርስቲያኖች ጋር ነው። ቅዱስ ጳውሎስ ሕጉ የተሰጠበትን ዓላማ በሚገባ አና በጥልቀት ካልተረዱ ሰዎች ጋር ነው ጉዳዩ። የመጀመሪያው ያልተረዱት ጉዳይ ሕግ እስራኤልን ከሌሎች አሕዛብ ለመለየት የተሰጠው ተግባር ማብቃቱን እና አሕዛብም በአብርሃም በኩል የተገባላቸው ኪዳን መድረሱን ባለመረዳት በክርስቶስ አንድ ሆነው ሲያበቁ ከአይሁድ የመጡት ከአሕዛብ ከመጡት ለመለየት ሕጉን መጠቀም መፈለጋቸው ነው። ያ ተፈጽሞአል። ክርስቶስ እስራኤልን ከአሕዛብ የሚለየው ሕግ ፍጻሜ ነው፤ ለሁሉም መጥቶአልና። ሁለተኛው ደግሞ ሕግ ያለ ክርስቶስ ማዳን እና ጸጋ ብቻውን ሊያድን እንደማይችል በመዘንጋታቸው እና ከክርስቶስ ማዳን ጋር ማፎካከራቸው ነው። ሕግ ኃጢኣትን በመግለጥ እና መርገምን በማምጣት ለሞት አሳልፎ ይሰጣል። ይህ የሆነው ሕጉ መጥፎ ሆኖ ሳይሆን የሰው ልጅ የነበረበት የድካም ሁኔታ ያደረገው ነው። በክርስቶስ ማዳን መንፈሳዊ ጸጋ ሲሰጥ ግን ሕጉ የባርነት መሆኑ ቀርቶ 'የሕይወት እና የእምነት ሕግ' ሆነ። በቀድሞ ሁኔታው 'የሞት ሕግ' ያለውን በአዲሱ ሁኔታ 'የክርስቶስ ሕግ' እያለ መጥራት ጀመረ። በመሆኑም ሕጉ በክርስቶስ አዲስ ኃይል እና ተግባር እንዳገኘ ተናገረ። ሕጉ አሁንም እንደሚጠቅም ግን ደጋግሞ ተናግሮአል። "ኃጢኣት በሕግ ይታወቃልና" በማለት ሰዎች ኃጢኣት የሆነውን ለይተን እናውቅ ዘንድ ሕጉ የግድ እንደሚያስፈልገን ተናግሮአል። (ሮሜ. 3፥20) በመሆኑም የቅዱስ ጳውሎስ ችግር 'ቅዱስ፣ ጻድቅ እና በጎ' ብሎ ከጠራ ከሕግ ጋር ሳይሆን ሕጉን በተሳሳተ እና ግልብ በሆነ መንገድ ከተረዱ ሐሰተኛ ወንድሞች ጋር ነበር። (ሮሜ. 7፥12)
የሚያሳዘው ግን የ15ኛው መ/ክ/ዘመን የተሐድሶ አራማጆችም በዚሁ መሰናክል መውደቃቸው ነው። ቅዱስ ጳውሎስን ከትክክለኛው መልእክታቱን በጻፈበት ዘመን ከነበረው ነባራዊ ዓውድ አንጻር ሳይሆን በመካከለኛቹ ዘመናት በሮም ቤተ ክርስቲያን የነበረው ቀውስ በፈጠረው ሌላ ዓውድ ለመረዳት የመሞከር ስህተት ፈጽመዋልና።
Dn. Bereket Azmeraw

ቤተክርስቲያንን በሁለት መንገድ ማወቅህን አረጋግጥ። እንደ አሕዛብ ጠላቷ እንዳትሆን #በትምህርት_ዕወቃት፤ እንደ ፈሪሳውያን እንዳትሆን #በኑሮ_ዕወቃት። ለሥርዓቷ ታማኝ ሁን፥ አንተ ወደ ሥርዓቷ እደግ እንጅ ሥርዓቷ ወደ አንተ ፈቃድ እንዲወርድልህ አትውደድ፤ ሰማያውይቷን ቤተክርሰቲያን ምድራዊት እንድትሆንልህ አትፍቀድ።

በቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አንድነቶች ካልተሳተፍክ ከቤተክርስቲያን አንድነት እየተለየህ እንደሆነ እወቅ። እሊህም፦ ኪዳን ማስደረስ፥ ማስቀደስና ንስሐ ገብቶ መቁረብ፥ በምህላ ጸሎቶቿ በአዋጅ አጽዋማቷ መተባበር ናቸው።

ከቤት ከሚጸለይ አሥር ጸሎት ይልቅ በቤተክርስታያን የሚደረግ አንድ ጸሎት እንደሚበልጥ አውቀህ  በየቀኑ ወደ እርስዋ ገሥግሥ። በሕይወትህ ሁሉ ቤተክርስቲያናዊ ሁን!

#ርዕሰ_ሊቃውንት_አባ_ገብረ_ኪዳን
እጅህ ላይ ባለው ነገር ከታመንህ እግዚአብሔር አምላክ በእጁ ውስጥ ያለውን ነገር ይሰጥሃል።

በውስጥህ ያለውን አቅም መጠቅም ከቻልህ እግዚአብሔር የአንተ ያልሆነ ተጨማሪ አቅም ይሰጥሃል።

ከእግረኞች ጋር ሳትደክም እኩል መራመድና መቅደም ከቻልህ እግዚአብሔር ፈረስን ለውድድር ይሰጥሃል። ኤር. 12፥5

የሚታዩ ኃጢአቶችን ለመዋጋት ታምነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር የተሸሸጉና የማይታዩ ኃጢአቶችን ድል እንድትነሣ ይሾምሃል።

በሕፃንነትህ በልጅነትህ ለእግዚአብሔር የታመንህ ሆነህ ከተገኘህ እርሱ በወጣትነትህ በምታደርገው ውጊያ ውስጥ ታማኝነትን ያድልሃል።

በሲና ምድረ በዳ ለመቀመጥ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር አምላክ የተስፋይቱን ምድር ከንዓንን ያወርስሃል።

በዚህ በተወሰነና አጭር ሕይወት ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር መጨረሻ የሌለውን ዘላለማዊ ሕይወት ያድልሃል።

ትልቁ ቁም ነገር በእጅህ ውስጥ የገባው ነገር ትንሽም ይሁን ጥቂት በእርሱ መታመን መቻልህ ነው። ስለሆነም ባለህ አንድ መክሊት ታምነህ ስትገኝ እግዚአብሔር አምስት መክሊቶችን በአደራ ይሰጥሃል።

አንተ በሚታዩት ነገሮች ላይ ታማኝ ሆነህ ስትገኝ እርሱ በማይታዩት ነገሮች ላይ ይሾምሃል።በመሆኑም ዓይን ያላየችውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልብ ያልታሰበውን መንግሥቱን ያወርስሃል። 1ኛ ቆሮ 2፥9

(#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ)
በቤተክርስቲያን አስተምሮ በመዳን ዙሪያ ለመዳን እምነት እና ስራ አስተባብሮ መያዝ እንደሚገባን ያስተምረናል…
ማኅበረ ጽዮን
በቤተክርስቲያን አስተምሮ በመዳን ዙሪያ ለመዳን እምነት እና ስራ አስተባብሮ መያዝ እንደሚገባን ያስተምረናል ነገር ግን በእምነት ብቻ የዳኑ እንዳሉ ቅዱስ መፅሀፍ ይነግረናል። ለምሳሌ ፈያታዊ ዘይማን በተመሳሳይ 12 ዐመት ደም ሲፈሳት የነበረችውንም እምነትሽ አድኖሻል ብሏታል። ይሄንን እንዴት እንመለከተዋለን?

ለጥያቄው ምላሽ በዲያቆን ያረጋል አበጋዝ


@eoteLIBRARY
ቅዱስ ጳውሎስ እና ሕግ
***
"መገረዝ ቢሆን አለመገረዝም ቢሆን ከንቱ ነው፥ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መጠበቅ ነው እንጂ።" (1ኛ ቆሮ. 7፥19)
ታላቁ ሐዋርያ ጳውሎስ ሆይ! መገረዝ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ስለመሆኑ ለአንተ እንዴት ይነገራል? ለአብርሃም እና ለዘሩ መገረዝን ያዘዘ ራሱ እግዚአብሔር አይደለምን? መገረዝን ከትእዛዛት ለምን አወጣኸው? ብለን እንጠይቅ። እርሱም እንዲህ ይመልሳል።
የብሉይ ሕግ ልዩ ልዩ ገጽታ አለው። አንደኛው ገጽታው እስራኤል ከአሕዛብ ርኩሰት ይጠበቁ ዘንድ ከአሕዛብ ለመለያነት የተሰጡ ሕጋት ናቸው። እነዚህም የግዝረት፣ የመባልዕት፣ የበዓላት እና የቀናት ሕጋት ናቸው። እስራኤል በሃይማኖት እስኪጎለምሱ ድረስ በመንፈስ ሕጻናት በነበሩበት ዘመን እንደ ሞግዚት ሆነው ይጠብቋቸው ዘንድ በጊዜያዊነት የተሰጡ ሕጋት ናቸው። እነዚህን ሐዋርያው በገላትያ እና በሮሜ መልእክታቱ 'የሕግ ሥራ' እያለ የሚጠራቸው ናቸው። (ገላ. 2፥16፣ 3፥2፣ 3፥5፤ ሮሜ. 3፥20፣ 3፥27 ወ.ዘ.ተ. . . ) በክርስቶስ መምጣት አሕዛብ ሁሉ የአብርሃምን ተስፋ በእምነት የሚካፈሉበት ዘመን ሲደርስ እነዚህ እስራኤልን አጥር ቅጥር ሆነው ከአሕዛብ የሚለዩ ሕጋት ተፈጽመዋል፤ ክርስቶስ የእነዚህ ሕጋት ፍጻሜ ነውና። (ሮሜ. 13፥10)
አሁን በእነዚህ የአይሁድ ሕጋት ሥር ለመሆን መፈለግ ከአዋቂነት ወደ ሕጻንነት፣ ከነጻነት ወደ ባርነት መመለስ ስለሆነ ሐዋርያው ይህን አምርሮ ይቃወማል። በዚህ መንገድ ሆነው አሕዛብ ወደ ወንጌል ለመምጣት የግድ እነዚህን የአይሁድ ሕጋት ፈጽመው 'አይሁድ' መሆን አለባቸው ብለው እዳ የሚጭኑትን አይሁድ-ዘመም መምህራን "ከክርስቶስ ተለይተው ከጸጋው የወደቁ፣ ስለክርስቶስ መስቀል እንዳይሳደዱ የሚሸሹ፣ የመስቀሉን እንቅፋት ለማስወገድ የሚሰሩ" በማለት ይወቅሳል፤ ከክርስትና ወንጌል በተቃርኖ ያቆማቸዋል። (ገላ. 5፥3፣ 11፤ 6፥12)
ሌላኛው የሕግ ገጽታ ደግሞ አይሁድን ከአሕዛብ ያለመለየት ለሁሉም የሰው ልጆች የሚሆነው እና ሕግ ያልተሰጣቸው አሕዛብ ሳይቀር በልቡናቸው የሚያውቁት፣ የእግዚአብሔር ፈቃድ ከኃጢአት ተለይቶ የሚታወቅበት ነው። ቅዱስ ጳውሎስ "መገረዝም ቢሆን አለመገረዝም ቢሆን ከንቱ ነው፤" ካለ በዋላ በተጻራሪ የሚጠቅመው "የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መጠበቅ ነው እንጂ፤" ብሎ የገለጸው ይህን ሰፊውን እና ጥልቁን የሕግ ገጽታ ነው።
በርግጥ ከክርስቶስ መምጣት በፊት ባሕርያችን ደክሞ ኃጢኣት ሰልጥኖ ስለነበር ሰው በሕግ ኃጢኣትን ቢያውቅም በጽድቅ መጽናት አልቻለም ነበር፤ ይልቁንም በገነት ውስጥ እንደሆነው ሕጉ ሲከለክለው እየጎመጀ ኃጢኣትን ይሠራ ነበር። የጉስቁልና ዘመን ነበርና። በዚህም የተነሣ ቅዱሱን ሕግ ራሱ ለመጥፎ መጠቀሚያ ያደርግ የነበረውን ክፉ ውድቀት ለመናገር ሐዋርያው በዚህ በሰፊ ገጽታውም ጭምር ሕጉን "የኃጢኣት ሕግ"፣ "የባርነት ሕግ"፣ "የእርግማን ሕግ"፣ "የሞት ሕግ" እያለ ጠንከር ባሉ አገላለጾች ጠርቶታል። (ሮሜ. 5፥20፣ 8፥2፣ ገላ. )
ነገር ግን ከዚህ ተነሥተው ሰዎች ወደተሳሳተ ድምዳሜ እንዳይሄዱ ደግሞ ፈጥኖ ስለ ሕጉ በጎነት እና ጽድቅ ጥብቅና ይቆማል። (ሮሜ. 7)
ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ መጥቶ የሕግን እውነተኛ ገጽታ (እግዚአብሔርን እና ባልንጀራን መውደድ) በፊደሉ ሳይሆን በጥልቅ ትርጉሙ አስተምህሮ እንዲሁም በተግባር ፈጽሞ ካሳየ በኋላ፣ በሞቱ እና በትንሣኤው ባሕርያችን አድሶ በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ካጠነከረን በኋላ ግን ሕጉ አዲስ ኃይል እንዳገኘ ያስረዳን ዘንድ ሐዋርያው በብዙ መልኩ ይጥራል። በአንድ ቦታ "ሕግ ሁሉ በአንድ ቃል ይፈጸማልና፥ እርሱም፦ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የሚል ነው፤" በማለት ሕጉ በክርስቶስ የፍቅር ትእዛዛት እንደጸና ይናገራል። (ገላ. 5፥14) ይህንኑ ሲያመለክትም "የክርስቶስ ሕግ" እያለ ይናገራል። (ገላ. 6፥2) ቀድሞ ለኃጢኣት ኃይል መጠቀሚያ ሆኖ የነበረው በመንፈስ ቅዱስ ሃይል ለጽድቅ መሆን መጀመሩን ሲናገርም "የመንፈስ ሕግ" ይለዋል። (ሮሜ. 8፥2)
***
ጠቅለል ሲደረግ የቅዱስ ጳውሎስ የሕግ አስተምህሮ ሰፊ እና መልከ ብዙ (differentiated) ነው። በአግባቡ ለመረዳት ሰፊውን ታሪካዊ እና ነገረ-ሃይማኖታዊ ዓውድ ማጤን ይገባል። ዋናው ነገር ግን ታላቁ ሐዋርያ ሕግ የሚባል ነገር አያስፈልግም፤ ተሽሮአል ብሎ አላስተማረም። የሕጉን መንፈስ እና ዓላማ እያሳየ የተፈጸመውን እና የጸናውን በየፈርጁ አስረዳ እንጂ። ሕጉን በተሳሳተ መልኩ የሚረዱትንም አወገዘ እንጂ። በተጨማሪም ሕግ ከሚፈጸምበት ጸጋ እና ሃይል ተለይቶ "ከክርስቶስ እምነት" በተጻራሪ ሊቆም እንደማይገባ በሃይለ ቃል አስተማረ እንጂ። (ገላ. 2፥16)
ቅዱስ ጳውሎስ ሕግን እንደተቃወመ አድርጎ የሚተረጎመው አካሄድ የ15ኛው መ/ክ/ዘመን የሉተር እና የሌሎች ተሐድሶዎች የተሳሳተ መረዳት (distortion) ውጤት ነው። ሉተር ጉዳዩን ይረዳው የነበረው ከቅዱስ ጳውሎስ ዓውድ አንጻር ሳይሆን ከራሱ የግል የሕይወት ቀውስ እና ከሮም ቤተ ክርስቲያን ዘመንኛ ችግር አንጻር ነበር። ይህም ትልቅ ምስቅልቅል አምጥቷል።
Bereket Azmeraw
ብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አባቶቻችን ሐዋርያትን ሰማዕትነት በተቀበሉበት ቀናት በዓላት ሰይማ ታከብራቸዋለች፡፡ እንዲሁም በስማቸው የተሰየመውን ጾም በመጾም አሠረ ፍኖታቸውን ይከተሉ ዘንድ ምእመናንን ታሳስባለች፡፡ በሐምሌ ፭ ቀን ደግሞ የደጋጎቹን ሐዋርያት የቅዱስ ጴጥሮስና የቅዱስ ጳውሎስን በዓል ታደርጋለች፡፡ የእነዚህ ቅዱሳን አባቶቻችን በዓል መደረጉ በአንድ ቀን ሰማዕትነት በመቀበላቸው ነው፡፡

ሁለቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አመራረጣቸው በጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ የጥሪው መንገድ ግን ይለያይ ነበር፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ለሐዋርያነት የተመረጠው ጌታችን በገሊላ ባሕር አጠገብ ሲመላለስ ከወንድሙ እንድርያስ ጋር ሆኖ ዓሣ ለማጥመድ መረባቸውን ወደ ባሕር ሲጥሉ አየ፤ ወደ እነርሱም ቀርቦ “በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ” አላቸው፡፡ ወዲያውም መረባቸውን ትተው ተከተሉት፡፡ (ማቴ.፬፥፲፰‐፳)

በአንጻሩ የቅዱስ ጳውሎስ አመራረጥ ደግሞ በተአምር ነው፤ ይኸውም እንዲህ ነው፡፡ በቀደመ ስሙ ሳውል ተብሎ የሚታወቀው ይህ ሐዋርያ የቤተ ክርስቲያን አሳዳጅ ነበር፡፡ ቀዳሜ ሰማዕት እስጢፋኖስ በአይሁድ እጅ ሲወገር የተስማማ የገዳዮቹንም ልብስ ጠባቂ ነበር፡፡ (የሐዋ. ፯፥፶፰-፷)

ቅዱስ መጽሐፍ “ሳውል ግን ቤተ ክርስቲያንን ያፈርስ ነበር ወደ ሁሉም ቤት እየገባ ወንዶችንም ሴቶችንም እየጐተተ ወደ ወህኒ አሳልፎ ይሰጥ ነበር፡፡ . . . ሳውል ግን የጌታን ደቀ መዛሙርት እንዲገድላቸው እየዛተ . . .” እንዲል፡፡ (የሐዋ.፰፥፫፤፱፥፩) በክርስቶስ አምነው የተጠመቁ ክርስቲያኖችን ለማሳደድ ከሊቁ ካህናቱ ዘንድ የፈቃድ ደብዳቤ ጠየቀ፡፡ ይህን ዓላማውን ለማስፈጸም ወደ ደማስቆ ሲጓዝ በርሱ ዙሪያ ከሰማይ መብረቅ ወረደ፤ ዐይኖቹም ታወሩ፤ ወደ ምድርም ወደቀ፡፡

በዚያም ሳለ “ሳውል ሳውል፥ ስለምን ታሳድደኛለህ” የሚለውን ድምፅ ሰማ፡፡ ያነጋገረው ሳውል የሚያሳድደው ጌታ ነበር፡፡ “አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ፤ የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብኻል” አለው፡፡ ከዚያም በመፍራትና በመንቀጥቀጥ ተነሥቶ ወደ ከተማው ገባ፡፡ ሦስት ቀንም ሳይበላ ሳይጠጣ ተቀመጠ፡፡ ሐናንያ የተባለው ከደቀ መዛሙርት ወገን የሆነ ወደ እርሱ ዘንድ ቀርቦ ጸለየለት፤ ዐይኖቹም ተፈወሱ፤ ተነሥቶም ተጠመቀ፡፡ (የሐዋ.፱፥፩‐፲፰)

ቅዱስ ጳውሎስ በወቅቱ ስለሆነው ነገር ለቆሮንቶስ ምእመናን ሲተረክላቸው “ ከሁሉም በኋላ እንደ ጭንጋፍ ለምሆን ለእኔ ደግሞ ታየኝ፡፡ እኔ ከሐዋርያት ሁሉ የማንስ ነኝና፥ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ስላሳደድሁ ሐዋርያ ተብዬ ልጠራ የማይገባኝ” እንዲል፡፡ (፩ኛቆሮ.፰፥፱)

የቤተ ሰብ ሕይወታቸው
ቅዱስ ጴጥሮስ የተወለደው በቤተ ሳይዳ ነው፡፡ ቤተ ሰቦቹ ደግሞ በቅፍርናሆም ይኖሩ ነበር፡፡ የኦሪት መጻሕፍትን ያልተማረ ከዝቅተኛው የማኅበረሰብ ክፍል የተገኘ ሰው ነበር፡፡ (የሐዋ. ፬፥፲፫) ጳውሎስ ደግሞ በኪልቅያ በምትገኘው በጠርሴስ ተወለደ፡፡ ከአይሁድ ወገን ከብንያም ወገን ነበር፡፡ (ፊል.፫፥፭) በጠርሴስም ሳለ በገማልያል እግር ሥር የኦሪት ትምህርቱን ተማረ፤ በትምህርቱም የተመሰከረለት ነበር፤ (የሐዋ.፳፪፥፫፤፳፮፥፳፬) ይህ የሚያሳየው የእግዚአብሔር መንግሥት ለተማሩትም ላልተማሩትም፣ ለባለጸጎችም ለድሆችም የተዘጋጀ መሆኑን ነው፡፡

ቅዱስ ጴጥሮስ ባለ ትዳር ነበር፡፡ አማቱም ታማ በነበር ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤቷ ገብቶ እንደፈወሳት በወንጌል ተጽፏል፡፡ (ማቴ.፰፥፲፬‐፲፭) ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ድንግል ነበር፡፡ “ሰው ሁሉ እንደ እኔ ሊሆን እወዳለሁና ነገር ግን፥ እያንዳንዱ ከእግዚአብሔር ለራሱ የጸጋ ስጦታ አለው፥ አንዱ እንደዚህ ሁለተኛውም እንደዚያ፡፡ ላላገቡና ለመበለቶች ግን እላለሁ፡- እንደ እኔ ቢኖሩ ለእነርሱ መልካም ነው፤ ነገር ግን፥ በምኞት ከመቃጠል መጋባት ይሻላልና፥ ራሳቸውን መግዛት ባይችሉ ያግቡ” በማለት ለቆሮንቶስ ምእመናን ጽፏል፡፡ (፩ኛቆሮ. ፯፥፯‐፱) ቤተ ክርስቲያን እንደ ጴጥሮስ ያገቡ እንደ ጳውሎስ ያሉ ደናግላንን ይዛ የምትገኘው ጌታችን ሁሉንም ወደ እርሱ ስለጠራ ነው፡፡

የስማቸው መለወጥ
ቅዱስ ጴጥሮስ የዮና ልጅ ስምዖን ተብሎ ይጠራ ነበር፡፡ (ዮሐ.፳፩፥፲፭) ነገር ግን ጌታችን ደቀ መዛሙርቱን “እናንተስ ማን ትሉታላችሁ” ብሎ ሲጠይቃቸው ሐዋርያው ተነሣና፡- “አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ” ብሎ መለሰለት፡፡ ያን ጊዜም ጌታችን “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ፡፡ እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም አለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሏትም” በማለት ጴጥሮስ ብሎ ሰየመው፡፡ (ማቴ.፲፮፥፲፯—፲፰)

ጳውሎስን ደግሞ ጌታችን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲጠራው በመጀመሪያ ስሙ ሳውል ብሎ ጠራው፤ በምስክርነቱ ጊዜ ደግሞ “ጳውሎስ ሆይ፥ በኢየሩሳሌም ስለ እኔ እንደ መሰከርህ እንዲሁ በሮሜም ትመሰክርልኝ ዘንድ ይገባሃልና፥ አይዞህ አለው፡፡” (የሐዋ.፳፫፥፲፩)

አገልግሎታቸው
የቅዱስ ጴጥሮስ አገልግሎቱ በአብዛኛው ሕግ ለተጻፈላቸው፣ ነቢያት ለተላኩላቸው፣ መሥዋዕት ለሚያቀርቡ፣ ግርዛት ለተሰጣቸው ለአይሁድ ነበር፡፡ በአንጻሩ ደግሞ የቅዱስ ጳውሎስ አገልግሎት የነበረው በአሕዛብ መካከል ነበር፡፡ ይህንንም ሲመሰክር “ለተገረዙት ሐዋርያ እንዲሆን ለጴጥሮስ የሠራለት፥ ለእኔ ደግሞ ለአሕዛብ ሐዋርያ እንድሆን ሠርቷልና፡፡” ብሏል፡፡ (ገላ.፪፥፯‐፰) እንዲያውም በአንድ ወቅት ጳውሎስና በርናባስን አይሁድ ትምህርታቸውን በተቃወሟቸው ጊዜ “እነሆ ወደ አሕዛብ ዘወር እንላለን እንዲሁ ጌታ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ለማዳን ትሆን ዘንድ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌሃለሁ ብሎ አዞናልና” ብለው ነበር፡፡ (የሐዋ. ፲፫፥፵፮—፵፯)

በበዓለ ኀምሳ ቅዱሳን አባቶቻችን ሐዋርያት የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ከተቀበሉ በኋላ ጴጥሮስና ዮሐንስ በትምህርታቸው በኢየሩሳሌም ለነበሩ ነፍሳት ደረሱ፡፡ በአንድ ቀን ብቻ ሦስት ሺህ ነፍሳት ወደ ቤተ ክርስቲያን ተጨመሩ፡፡ (የሐዋ.፪) ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ “ከሁላችሁ ይልቅ በልሳኖች እናገራለሁና እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ” በማለት ስለተሰጠው የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ መስክሯል፡፡ (፩ኛቆሮ. ፲፬፥፲፰) ሁለቱም ሐዋርያት በምእመናን ላይ እጃቸውን በመጫን ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ያሳድሩ ነበር፡፡ (የሐዋ.፰፥፲፬፤፲፱፥፭‐፮)

በአገልግሎታቸው ድንቅ ተአምራትን ፈጽመዋል፡፡ ለምሳሌ ስለ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፡፡ “እግዚአብሔርም በጳውሎስ እጅ የሚያስገርም ተአምራት ያደርግ ነበር፤ ስለዚህም ከአካሉ ጨርቅ ወይም ልብስ ወደ ድውዮች ይወስዱ ነበር፥ ደዌያቸውም ይለቃቸው ነበር ክፉዎች መናፍስትም ይወጡ ነበር፡፡” (የሐዋ.፲፱፥፲፩—፲፪) በኢዮጴም ጣቢታ የምትባል አገልጋይን ከሞተች፤ አጥበውም በሰገነት ከአኖሯት በኋላ ቅዱስ ጴጥሮስ ካለበት ተጠርቶ ከጸለየ በኋላ ጣቢታ ሆይ ተነሽ ሲላት ዐይኖቿን እንደከፈተች ተጽፏል፡፡ (የሐዋ.፱፥፴፮—፵፪) በተመሳሳይ ቅዱስ ጳውሎስ አውጤኪስ የሚባል ከሦስተኛ ደርብ ወደ ታች ወድቆ የሞተን ጎልማሳ እንዲነሣ አድርጓል፡፡ (የሐዋ.፳፥፯—፲፪)
መልእክታት
ቅዱስ ጴጥሮስ ሁለት መልእክታትን ለምእመናን ጽፏል፤ ቅዱስ ጳውሎስ በአካል ተገኝቶ ለሰበካቸውና ላጠመቃቸው የሮሜ፣ የቆሮንቶስ፣ የገላትያ፣ የኤፌሶን፣ የፊልጵስዩስ እና የቆላስይስ፣ የተሰሎንቈ፣ ለዕብራውያን ምእመናን መልእክታትን የጻፈ ሲሆን ለመንፈስ ቅዱስ ልጆቹ ለጢሞቴዎስ፣ ለቲቶ እና ለፊልሞና መልእክታትን ሰዶላቸዋል፤ በአጠቃላይ ዐሥራ አራት መልእክታትን ጽፏል፡፡

ሰማዕትነታቸው
ሁለቱም ቅዱሳን ሐዋርያት በሮማው ቄሳር ኔሮን ዘመን ፷፯ ዓ.ም. ሰማዕትነትን ተቀብለዋል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ቁልቁል ተሰቅሎ ሰማዕትነት የተቀበለ ሲሆን ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ አንገቱን ተቀልቶ ሰማዕትነትን ተቀብሏል፡፡
በረከታቸው ይደርብን፤ አሜን!

Mahebere kidusan
እያንዳንዱ እንዴት እንዲያንጽ ይጠንቀቅ /1ኛ ቆሮ 3 ፤ 10/

እንኳን ለበዓለ ጴጥሮስ ወጳውሎስ አደረሰን አደረሳችሁ።

በቅዳሴያችን ወቅት ገባሬ ሠናይ ዲያቆኑ ከጳውሎስ መልእክት ካነበበ በኋላ በዜማ የምንለው መርግፍ እንዲህ ይላል። “ቅዱስ ሐዋርያ ጳውሎስ ሠናየ መልእክት ፈዋሴ ዱያን ዘነሣእከ አክሊለ ሰአል ወጸሊ በእንቲአነ ያድኅን ነፍሳተነ በብዝኀ ሣህሉ ወምሕረቱ በእንተ ስሙ ቅዱስ” – ‘አክሊልን የተቀዳጀህ፣ ድውያንን የምትፈውስ፣ መልእክትህ ያማረ፣ ቅዱስ ሐዋርያ ጳውሎስ ሆይ በይቅርታውና በቸርነቱ ብዛት ስለ ቅዱስ ስሙም ብሎ ነፍሳችንን ያድን ዘንድ [ወደ ጌታ] ስለእኛ ለምንልን፣ ጸልይልንም’ ማለት ነው።

በዚህች አጭር ጸሎት እንዲያደርግልን በምታሳስብ አጭር ልመና ውስጥ የቅዱስ ጳውሎስን ማንነት በአጭሩ የሚገልጹ ሦስት ነገሮች ተቀምጠዋል። ድዋያንን የሚፈውስ፣ መልዕክቱ ያማረ መሆኑና በዚህም አክሊል የተቀዳጀ መሆኑን የሚያሳዩ ወሳኝ መግለጫዎች ናቸው።

ቅዱስ ጳውሎስ በሁለንተናው ፈዋሴ ዱያን ነውና ዛሬም ቤተ ክህነታችን ከተያዘበት፣ የዘረኝነት፣ የጠባብነት፣ የሌብነት፣ የአላዋቂነት፣የፖለቲከኝነት እና ለሹመት የማበድ በሽታ ይፈውስልን።

መልእክቱም በእውነት በእጅጉ ያማረ ነው። በቆሮንቶስ መልእክቱ ላይ “የእግዚአብሔር ጸጋ እንደ ተሰጠኝ መጠን እንደ ብልሃተኛ የአናጺ አለቃ መሠረትን መሠረትሁ፥ ሌላውም በላዩ ያንጻል። እያንዳንዱ ግን በእርሱ ላይ እንዴት እንዲያንጽ ይጠንቀቅ። ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልምና፥ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ማንም ግን በዚህ መሠረት ላይ በወርቅ ቢሆን በብርም በከበረ ድንጋይም በእንጨትም በሣርም ወይም በአገዳ ቢያንጽ፥ የእያንዳንዱ ሥራ ይገለጣል፤ በእሳት ስለሚገለጥ ያ ቀን ያሳያልና፥ የእያንዳንዱም ሥራ እንዴት መሆኑን እሳቱ ይፈትነዋል። ማንም በእርሱ ላይ ያነጸው ሥራ ቢጸናለት ደመወዙን ይቀበላል፤ የማንም ሥራ የተቃጠለበት ቢሆን ይጎዳበታል” /1ኛ ቆሮ 3 ፤ 10 -15/ ሲል የገለጸውን እና እኛ ካለንበት ሁኔታ አንጻር ላለው የሚጠቅም የሚመስለኝን እንኳ ብናየው መልእክቱ ምንኛ ያማረ ነው። 

ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው ሐዋርያት የሠሩት የቤተ ክርስቲያን መሠረት የማይለወጥ ማንም ፈላስፋም ሆነ ፖለቲከኛ፣ ጎልበተኛም ሆነ ሴረኛ ሊለውጠው የማይችል ንጹሕ ሐዋርያዊ መሠረት ነው ያለን። ከእነርሱ በኋላ የመጡት ግን ሐዋርያው እንዳለ በወርቅ በብር እና በከበረ ድንጋይ ያነጹ ቢኖሩም አንዳንዶቹ ደግሞ በገለባ፣ አንዳንዶቹም በሣር ሌሎቹም ደግሞ በእንጨት በጭራሮ የሚያንጹ ነበሩ። እኛ ሀገር በዚህ ወቅት የምናየው የዘር ቤተ ክህነት እና የጎሳ ጵጵስና ጉዳይ በሣር እና በአገዳ ያንጻሉ ያላቸውን የሚያስታውስ ነው። እንዲህ በእንጨት፣ በሣር፣ በአገዳ የሚያንጹት ቢኖሩም ቤተ ክርስቲያን ግን ጸንታ ትኖራለች ። በእግዚአብሔር የፍርድ እሳት ሲመረመር የእነርሱ ይቃጠላል፣ የባለ ብሮቹ እና የባለወርቆቹ የተባለው የንጹሐኑ ሥራ እና ተጋድሎ እና የመሳሰሉት ግን የበለጠ ይጠራል፣ ያበራል፣ ይከብራል። 

በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በየዘመኑ ስለሚኖር እና አሁንም ስላለነው ሲናገርም “በትልቅም ቤት የእንጨትና የሸክላ ዕቃ ደግሞ አለ እንጂ የወርቅና የብር ዕቃ ብቻ አይደለም፥ እኵሌቶቹም ለክብር፥ እኵሌቶቹም ለውርደት ይሆናሉ” /2ኛ ጢሞ 2 ፡ 20/ ሲል የገለጸውም ምንኛ ያምራል። እውነት ለመናገር በትልቋ ቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ የክብር ዕቃ ዓይነት የከበሩ ሰዎች ቢኖሩም ግን ደግሞ መናኛ እና የውርደት ዕቃዎች በተባሉት የምንመሰል ሥራችን ሁሉ ተዋርዶ ማዋረድ የሆንንም እንኖራለን። ዘንድሮ እያየን ያለውም ይህን ይመስለኛል። ተዋርደው የሚያዋርዱ መንደርተኛ ሿሚዎች እና ተሿሚዎች፣ ደጋፊ አሽቃባጭ የጥፋት ቲፎዞዎች እና አጨብጫቢዎች ። ቅዱስ ጳውሎስ የሚለን በተልቅ ቤት ውስጥ ይህ ሁሉ ሊኖር የግድ ነው ነው የሚለን። ይህ ነገር ሁልጊዜም የነበረ እና ያለ ቢሆንም ዘንድሮ የምናየው ግን በትልቁ ቤት በእግዚአብሔር ቤት በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ዕቃው ሁሉ እጅ ሲነካው ቅድድ የሚል፣ ትንሽ ሙቀት የሚያቀልጠው የያዘውን ነገር እንኳ በወጉ የማያደርስ፣ የሽክል ዕቃ ያህል እንኳ ስባሪው የማይገኝ የእኛኑ ዘመን ስስ ፌስታል የሆንን ይመስለኛል። እውነቱን ለመናገር በየቤታችን ያለውን የኬንያን የፕላሲክ ዕቃ ያህል እንኳ ወግ መዓርግ ማጣታችን በእጅጉ ያሳዝናል። እንኳን የወርቅ እና የብር ዕቃ መሆን የሸክላ ዕቃ መሆንን እንዳቃተን ሳስብ እንኳ እገረማለሁ። ነገር ግን መልእክቱ ያማረው ያ ምርጥ ሐዋርያ እንዳለው በትልቁ ቤት በእግዚአብሔር ቤት ግን ይህ ሁሉ ይኖራል ተብሏልና ቢያንስ መደነቅ የለብንም።

ቅዱሱ ሐዋርያ ባዛሬው ዕለት ለእውነት ፣ እውነት ለተባለው ለክርስቶስ ተሰውቶ አክሊል ተቀዳጅቷል። አሁን የእርሱን ሥልጣን የሚፈልጉት ደግሞ የየጎሣ ዘውድ ለመቀዳጀት ይጣደፋሉ፣ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ጥሶ ለመሾም ይሯሯጣሉ፣ ይፎክራሉ፣ ይሸልላሉ። ከሁሉ የሚገርመኝ ደግሞ ይህን በማድረጋቸው ያሸንፉ፣ ያጎዱን፣ በንዴት ያቃጠሉን መስሏቸው ሲደስቱ እና ሲደልቁ ስመለከት  እውነተኛው ዕብደት ምን እንደሚያደርግ እየገባኝ እገረማለሁ። በርግጥ በእብደት ውስጥ ያለ እብደቱ ገብቶት አያውቅም። እንኳን ያበደ፣ ለጊዜው እእምሮውን የሳተም ምን እንደሆነ የሚጠይቀው ከተሻለው በኋላ ነው። እውነቱን ለመናገር አሁን በትግራይ የሚታሰብውን ሳስብ ደም ያሰክራል የሚለው ነው ወደ አእምሮየ የሚመጣው። በተለይ አንዳንዶች ይልቁንም የዚሀ ጉዳይ አቀንቃኞች በርግጥም ተጎድተዋል፣ ደም አስክሯቸዋል። ፈዋሴ ዱያን የተባለው ቅዱስ ጳውሎስ ይፈውሳችሁ ከማለት በቀር ሌላ ምን ይባላል። ሰው ከእግዚአብሔር ቃል እና ሕግ ይልቅ እንዴት ለፖለቲከኞች ጭልጥ ብሎ ያታዘዛል? የእነርሱን ለብቻው የምጽፍበት ስለሚሆን አሁን አልነካካም። ለሁሉም ግን አእምሮው ጨርሶ ያልጠፋበት ካለ ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው ማንም ቢሆን እንዴት እንዲያንጽ ይጠንቀቅ።
Dn. Birhanu Admas
2024/09/28 20:17:38
Back to Top
HTML Embed Code: