Telegram Web Link
Audio
ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊነት
        
Size:-35.6MB
Length:-1:42:08

በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
በዓለ ቅድስት ሥላሴ

እንኳን ለቅድስት ሥላሴ ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ!

ውድ አንባብያን! እንደምን ሰነበታችሁ? አሜን! የአምላካችን የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን! የሐምሌ ሰባት በዓለ ቅድስት ሥላሴን በተመለከተ አጭር ጽሑፍ አቅርበንላችኋል፤ ተከታተሉን!

በዚህችም ቀን ልዩ የሆኑ ሦስቱ አካላት ቅድስት ሥላሴ በኦሪት መጽሐፍ እንደ ተጻፈ ወደ አብርሃም ቤት ገቡ ያቀረበላቸውንም ተመገቡ። የይስሐቅንም ልደት አበሠሩት ባረኩት፤ አከበሩትም። (መጽሐፈ ስንክሳር ዘሐምሌ ሰባት)

አብርሃም አባታችን በተመሳቀለ ጎዳና አራት በር ያላት ግንብ ሠርቶ ያለፈውን ያገደመውን የወጣውን የወረደውን ሲቀበል ይኖር ነበር:: ሰይጣን በዚህ ቀንቶበት ግንባሩን ገምሶ፣ ልብሱን፣ ገፎ፣ አጥንቱን ከስክሶ፣ ልብሱን በደም ለውሶ ሄዶ፡፡ ወደ አብርሃም ቤት መሄጃ መንገድ ላይ ተቀምጦ ወደ አብርሃም ቤት እንግዳ ሲመጣ “ወዳጄ ወዴት ትሄዳለህ?” ይለዋል፤ “ወደ አብርሃም ቤት” ይለዋል:: “አይ አብርሃም የቀድሞው አብርሃም መሰለህ? እኔ ያጎርሰኛል፤ ያለብሰኛል ብዬ ብሄድ ይኼው እንደምታየኝ ግንባሬን ገምሶ፣ ደሜን አፍሶ ሰደደኝ፤ እኔን ያገኘ መከራ እንዳያገኝህ ይቅርብህ፤ ባትሄድ ይሻልሃል” እያለ እንግዳ መለሰበት::

ከዚህ በኋላ አብርሃም “ማዕደ እግዚአብሔር ያለ ምስክር እንዴት ይቀርባል?” ብሎ ሦስት ቀን ጾሙን አደረ። ቅድስት ሥላሴ ርኅሩኃን ናቸውና በእንግዳ ልማድ ሄደው ከደጁ ከመምሬ ዛፍ ተቀምጠው አያቸው፤ እርሱም ሊቀበላቸውም እየሮጠ ወጣ፤ በቀረበም ጊዜ ወደ ምድር ሰገደ፤ “አቤቱ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ ባርያህን አትለፈኝ ብዬ በእውነት እለምንሃለሁ፤ ከቤቴ ገብታችሁ ዕረፉ” አላቸው:: “በፊትህ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ ባርያህን አትለፈኝ” ብሎ መናገሩ አንድነቱን፣ ጥቂት ውኃ ይምጣላቸሁ እግራችሁን ታጠቡ ብሎ መናገሩ ሦስትነታቸውን ለመግለጽ ነው:: ይህ ምሳሌ ነው፤ ዛፏ የእመቤታችን ምሳሌ ናት፤ ሥላሴ በዛፏ ሥር ተቀምጠው እንደ ታዩ አብ ለአጽንዖ፣ መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ፣ ወልድ ለተዋሕዶ በእመቤታችን የማደራቸው ምሳሌ ነው:: ይህቺ ዛፍ በአብርሃም ደጃፍ ተተክላ፣ ቅርንጫፎቿን አንሰራፍታ ቅድስት ሥላሴን ለመቀበል እንደበቃች፣ እመቤታችንም ከአብርሃም ዘር ተወልዳ፣ ጸጋዋ ተንሰራፍቶ፣ ክብሯ፣ ልዕልናዋ ሰፍቶ የሥላሴ ማደሪያ ለመሆን በቅታለችና፡፡ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ “አንቲ ውእቱ ዕፀ ድርስ ዘለአብርሃም በርስአኒሁ ዘብኪ አጽለለ እግዚአብሔር በሥላሴሁ፤ለአብርሃም በእርጅናው ወቅት እግዚአብሔርን በሦስትነት ያስጠለለብሽ የወይራ ዛፍ አንቺ ነሽ” በማለት ገልጾታል:: (እንዚራ ስብሐት)

ቅድስት ሥላሴም “አዝለህ አግባን” አሉት ጽንዐ ፍቅሩን ለማጠየቅ ነው፡፡ አብርሃምም አንዱን አዝሎ ሲገባ ሁለቱን ገብተው አግኝቷቸዋል! አብርሃም ሣራን “ሦስት መስፈሪያ ዱቄት አምጥተሸ በአንድ አድርገሽ ጋግሪ” አላት፤ እርሷም እንዳዘዛት አደረገች፤ “ወአቅረበ ሎሙ መዓረ ወዕቋነ ወእጓለ ላህም ስቡሓ፤ ድፎ ዳቦ አቅርቦላቸዋል፤ ላህም ሠውቶላቸዋል” ባርከው አስነሥተውለታል! ሕያዋን እንደሆኑ ለማጠየቅ ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ልጅ እንደሚወልድ ነግረውት ሲሄዱ ከሦስቱ አንዱ “የዛሬ ዓመት በእውነት ወደ አንተ እመጣለሁ፤ ሚስትህ ሣራም ልጅ ትወልዳለች” ብሎ ተስፋውን ነግሮት ሄደዋል:: (ዘፍ.፲፰፥፲)

ቅድስት ሥላሴ በእንግዳ አምሳል የገቡት በቤተ አብርሃም መስተናገዳቸውን ቅዱስ ያሬድ ሲናገር “አብርሃም ርእየ ሠለስተ እደወ በዛቲ ዕለት ምሥጢረ ሥላሴ ዜነወ እትነሣእ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ውእቱ ኀይልየ አምላኪየ ረዳእየ ወመድኀንየ፤ አብርሃም ሦስት አረጋውያንን ተመለከተ፤ በዚያች ዕለት የሥላሴን ምሥጢር ተናገረ፤ አብና ወልድ መንፈስ ቅዱስ ኀይሌ፣ አምላኬና መድኀኒቴ ነው ብዬ እነሣለሁ” በማለት የሥላሴ አንድነትና ሦስትነት ተገልጦለት እንደተናገረ ሊቁ በዜማው መስክሯል:: (ድጓ ዘሥላሴ ኆኅተ ሰብከት ዘቅዱስ ያሬድ ቅጽ ፪ ገጽ ፭፻፰፯)

ይስሐቅን ሳይወልድ አብራም ይባል ነበር፣ አበ ውሁዳን ማለት ነው፡፡ ይስሐቅን ከወለደ በኋላ ግን አብርሃም ተብሏል አበ ብዙኃን ማለት ነው፡፡ (ዘፍ.፲፯፥፮ አንድምታ ትርጓሜ)

አባታችን አብርሃም ይስሐቅን ሳይወልድ “አብራም” ይባል ነበር፤ “አበ ውሁዳን” ማለት ነው፡፡ ይስሐቅን ከወለደ በኋላ ግን “አብርሃም” ተብሏል፤ “አበ ብዙኃን” ማለት ነው፡፡ ባሕረ ጥበባት ቅዱስ ያሬድ እግዚአብሔር ለአብርሃም ምሥጢር እንደገለጠለት ሲናገር “አብርሃምን መረጠው ወዳጄም አለው፤ የተሰወሩ ምሥጢራትን ሁሉ ገለጠለት፤ አብርሃም እንደ ፀሐይና እንደ ንጋት ኮከብ ብሩህ እንደሆነ በመንፈስ ቅዱስ ሁሉንም ነገር ነገረው” ሲል ዘምሯል፡፡ (ድጓ ዘሥላሴ፣ ኆኅተ ሰብከት ዘቅዱስ ያሬድ ቀጽ ፪ ገጽ ፭፻፰፯)

ስለዚህ በአብርሃም በኩል ምሥጢሩን ለገለጡለት ለቅድስት ሥላሴ ምስጋና እንደሚገባ ሲናገር “ንግሩ ምሕረቶ ለሥላሴ ወዜንዉ ሠናይቶ ለሥላሴ መሃይምናን ንግሩ ምሕረቶ ለሥላሴ፤ የሥላሴን ምሕረቱን ንገሩ፤ የሥላሴ በጎነቱን መስክሩ! እናንተ ምእመናን የሥላሴ ምሕረቱን ተናገሩ” በማለት ያሳስባል።

አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም በአካል በግብር ሦስትነት በባሕርይ በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው። በዚህ ጊዜ ተገኙ፤ በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም፤ መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸው። እንግዲህ ሥላሴ ስንል፦

*ሥላሴ ዋሕድ* በአንድ እግዚአብሔር ከሚገኝ ከሦስቱ አካላት ከአብ ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ በቀር፥ ቅድመ ዓለም ቢሆን ፣ ድኅረ ዓለማት ቢሆን ፈጽሞ ሌላ መንቲያ ወይም ተመሳሳይ የሌለውና ብቻውን የሚኖር ልዩ ሦስት "ሦስትነት" መሆኑን የሚያረጋግጥ አብነት ነው።

ሃሌ ሉያ ለአብ ፥ሃሌ ሉያ ለወልድ፥ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ ሥላሴ ዋሕድ።

*ሥላሴ ዘለዓለም (ዘለዓለም ሥላሴ)* ይህ ሲባል የሥላሴ መጠሪያ ስም ከጊዜ በኋላ የተገኘ ሳይሆን ከዘለዓለም በሥላሴነቱ የነበረ ያለ የሚኖር መሆኑን የሚታወቅበት ገለጻ ነው። እምቅድመ ዓለም ወእስከ ለዓለም ሀሎ እግዚአብሔር በትሥልስቱ፤ እግዚአብሔር ከዓለም በፊት እስከዘለዓምም ድረስ እግዚአብሔር በሦስትነቱ አለ፡፡ (ቅዳሴ ዘዲዮስቆሮስ)

*ሥሉስ ቅዱስና ልዩ ሦስትነት* ይህ ሦስትነት አንድነት ያለው በመሆኑ ሥሉስ ቅዱስ ይሰኛል ማለት ሦስት አካላትን የያዘ ቅዱስ የተለየ ባሕርይ ያለው እግዚአብሔር ወይም መለኮት ማለት ነው።

*ልዩ ሦስትነት* የእግዚአብሔር ልዩ ሦስት ሲባል በሦስትነት በአንድነት የሚገኙ ልዩ ምሳሌዎች አሉና ከዚያ ለይቶ ለማስገንዘብ ነው። ከእነዚህም አንዱ የአካል ሦስትነት ቢኖራቸውም የባሕርይና የህልውና አንድነት የላቸውም። ለምሳሌ “አብርሃም፣ ይስሐቅ፣ ያዕቆብ” ብለን የምንጠራቸው ሦስት ስሞች ናቸው።

እንደዚሁም ደግሞ በአንድ የአካል ስም ሲጠሩ በኩነታት ሦስትነት ያላቸው አሉ። እነርሱም ፀሐይ፣ እሳት፣ ቀላይ፣ ባሕር፣ ተክልና ንፋስ ናቸው። የሰው ነፍስ ብትሆንም እንኳን የኩነት፣ የግብር ሦስትነት አላት እንጂ የአካል ሦስትነት የህልውና አንድነት የላትም።
ሥላሴ ግን የአካል፣ የግብር፣ የኩነት ሦስትነት፥የመለኮት የባሕርይ የህልውና አንድነት አላቸው። ልዩ ሦስት "ቅድስት ሥላሴ" ይባላሉ።

ዳግመኛም ሥላሴ፡-
ወላድያነ ዓለም “ቅዱስ” ሥላሴ ማለት ትተን “ቅድስት” ሥላሴ ብለን በሴት አንቀጽ እንጠራቸዋለን፤ የምንጠራበት ምክንያት ምንድን ነው? ስንል ስለ ብዙ ምሥጢር ነው፤ እንደ ሊቃውንቱ ትንታኔ ሴት ርኀርኅተ ልብ ናት፤ ሥላሴም ለፍጥረታቸው ርኅሩኃን ናቸውና፡፡ አንድም ሴት ከባሕርይዋ ልጅ ትወልዳለች! ሥላሴም ወላድያነ ዓለም ናቸው፤ ይህን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር ካለመታየት ወደ መታየት አምጥተው የፈጠሩ ፈጥረውም የሚያስተዳድሩ ቅድስት ሥላሴ ናቸውና:: አንድም ጽኑዕ፤ ንጹሕ፣ ክቡር፣ ልዩ ሲል ነው፡፡ ሰውን ጽኑዕ ቢሉት እስከ ጊዜው ነው፤ እንጂ ኋላ በሕማም በሞት ይለወጣል:: ቅድስት ሥላሴ ግን መቼም መች ሕልፈት ውላጤ ድካም ሕማም የለባቸውም፡፡

አምልኮት መሠረት

ቅድስት ሥላሴ የአምልኮታችን መሠረት ነው፤ ይህ ማለት ምስጋናም ሆነ አምልኮት የሚጀመረው በቅድስት ሥላሴ ነው፤ የማንኛውም አገልግሎት መክፈቻም ሆነ መዝጊያ የቅድስት የሥላሴ ስም ነው! ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አገልግሎቷን “በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ” ብላ ጀምራ “ስብሐት ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ” ብላ ትዘጋለች::

ባሕረ ጥበባት ቅዱስ ያሬድ ሲናገር “ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ አአትብ ወእትነሣእ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ሠለስተ አስማተ ነሚእየ እትመረጐዝ እመኒ ወደቁ እትነሣእ ወእመኒ ሖርኩ ውስተ ጽልመት እግዚአብሔር ያበርህ ሊተ በእግዚአብሔር ተወከልኩ፤ ቅድመ ዓለም የነበረ ዛሬም ያለ ወደ ፊትም ዓለም አሳልፎ የሚኖር በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ተነሥቼ አማትባለሁ፤ እነዚህን ሦስት ስሞች ይዤ እመረኮዛለሁ፤ ብወድቅ እነሣለሁ፤ ወደ ጨለማ ብሔድ እግዚአብሔር ያበራልኛል፤ በእግዚአብሔር ታመንኩ” ሲል የሃይማኖታችን መነሻና መድረሻ ቅድስት ሥላሴ መሆኑን መስክሯል:: (ድጓ ዘሥላሴ ኆኅተ ስብከት ዘቅዱስ ያሬድ ቅጽ ፪ ገጽ ፭፻፹፰)

ዳግመኛም ቅድስት ሥላሴ የአምልኮታችን መሠረት የእምነታችን ምንጭ እንድሆነ ሊቁ ግልጥ አድርጎ ሲነግረን “ነአምን ወናመልክ በአሐዱ እግዚአብሔር ዘእምቅድመ ዓለም ሀሎ ወነአምን በካልዑ እግዚአብሔር ዘበምልክናሁ ለአብ ይመስሎ ወነአምን በሣልሱ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ዘይመልዕ፤ ቅድመ ዓለም በነበረ በአንዱ በእግዚአብሔር አብ እናምናለን እናመልካለን፤ አብን በጌትነት በሚመስለው በሚተካከለው በእግዚአብሔር ወልድ እናምናለን እናመልካለን፣ በዓለም ምሉዕ በሆነው በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ እናምናለን እናመልካለን” ሲል ቅድስት ሥላሴ የአምልኮታችን ማዕከል መሆናቸውን ተናግሯል፡፡ (ድጓ ዘሥላሴ)
የሚሠዋው መሥዋዕት፤ የሚጸለየው ጸሎት፣ የሚታጠነው ዕጣን የሚቀርበው ቁርባን ሁሉ የሚያርገው ወደ ቅድስት ሥላሴ ነው:: ሊቁ እንዲህ እንዳለ “አንትሙሰ ከመ ዕብነ ሕይወት ተሐነጹ ቤቶ ለመንፈስ ቅዱስ ወለክህነቱ ቅዱስ ከመ ታዕርጉ መሥዋዕተ ወትንግሩ ሠናይቶ፤ ለቅዱስ አገልግሎት ሕያው መሥዋዕትን ታሣርጉ ዘንድ በጎነቱን ትነግሩ ዘንድ፣ እናንተ እንደ ሕይወት ድንጋይ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ሆናችሁ ታነጹ” በማለት ዘምሯል፡፡ (ድጓ ዘሥላሴ ኆኅተ ስብከት ዘቅዱስ ያሬድ ቅጽ ፪ ገጽ ፭፻፹፰)

ሙሴ የያዛቸው ሦስት ስሞች

ሊቀ ነቢያት ሙሴ ሕዝበ እስራኤልን እየመራ ወደ ከነአን ሲጓዝ ለጉዞው መሳካት የእግዚአብሔርን ረድኤት የሚጠይቅበትና ሕዝቡ ሲበድሉ የእግዚአብሔርን ምሕረት የሚማፀንበት ሦስት ስሞች ነበሩ፡፡ እነዚህን የያዛቸው ሦስት ስሞች ደጋግሞ መጥራት የፈጣሪውን ምሕረትና ረድኤት አግኝቷል፤ እነዚሀ ሙሴ የያዛቸው ስሞች ምንድን ናቸው? ሙሴ በአብርሃም፣ በይስሐቅ፣ በያዕቆብ ስም ፈጣሪውን ይማጸን እንደነበር ተናግሯል፡፡ እነዚህ ሦስት ስሞች የሥላሴ ምሳሌ ናቸው፤ እነዚህ ስሞች የቃል ኪዳን ማስታወሻ ናቸው፤ እግዚአብሔር ለጊዜው ምድራዊቷ ርስት ከነአንን እንደሚያወርስ፣ ለፍጻሜው ደግሞ ሰማያዊቷን ርስት ወደ መንግሥተ ሰማያትን እንደሚያወርስ ከሕዝቡ በረድኤት እንደማይለይ ቃል ኪዳን ይገባ የነበረው በእነዚህ ስሞች ነበር፤ ሕዝቡም ለአብርሃም ለይስሐቅ ለያዕቆብ የገባውን ቃል ኪዳን አስቦ የእግዚአብሔር ልብ እንዲራራላቸው ያደርጉ ነበር።

ሊቁ ቅዱስ ያሬድ እንዲህ ይገልጠዋል “መፍቀሬ ሰብእ ክርስቶስ ፈኑ ሣህለከ ወምሕረተከ ዘአንተ ታርኁ ክረምተ በጸጋከ ወትሴሲ እመዝገብከ ስብሐት ለከ ወዐቢይ ኀይልከ ዘሠራዕከ ሰንበተ ለሰብእ ዕረፍተ ዘሠርዐ ለአብርሃም ወመሐለ ለይስሐቅ ወዐቀመ ስምዐ ለያዕቆብ ንስእለከ ወናስተበቊዐከ እስመ ኵሉ ዘሥጋ ያንቃዓዱ ኀቤከ፤ ሰው ወዳጅ ክርስቶስ ሆይ ይቅርታህንና ምሕረትህን ላክ፤ አንተ ክረምትን የምትከፍት፣ ከመዝገብህ በጸጋህ ትመግባለህ፤ ምስጋና ለአንተ ይገባል፤ ኀይልህ ታላቅ ነውና፤ ለዕረፍት ሰንበትን የሠራህ፤ ለአብርሃም ለይስሐቅ የማልክ፤ ለያዕቆብ ምስክርነትን ያቆምክ” ሲል ዘምሯል፡፡ እነዚህ ሦስት ስሞች (አብርሃም ይስሐቅና ያዕቆብ) የእግዚአብሐር ሕዝብ የመሆን ምልክት ነበሩ፤ ሥላሴም የሃይማኖት ምልክት ናቸውና፡፡ (ድጓ ዘሥላሴ ኆኅተ ስብከት ዘቅዱስ ያሬድ ቅጽ ፪ ገጽ ፭፻፹፱)

ቅዱስ ያሬድ ሲናገር “ነሡእየ ማዕተበ ዘወልደ እግዚአብሔር አአትብ በሥላሴ እመኒ ወደቁ አቲብየ እትነሣእ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ኀይለ መስቀሉ እትመረጐዝ፤ የወልደ እግዚአብሔርን የኢየሱስ ክርስቶስ ምልክት የኾነውን ቅዱስ መስቀል ይዤ በሥላሴ ስም አማትባለሁ፤ ብወድቅ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አማትቤ እነሣለሁ፤ በመስቀሉም እመረኮዛለሁ” ሲል ዘምሯል:: (ድጓ ዘሥላሴ ኆኅተ ስብከት ዘቅዱስ ያሬድ ቅጽ ፪ ገጽ ፭፻፹፱ )

በአጠቃላይ ምሥጢረ ሥላሴን በሚገባ መርምሮ መረዳት ለማንም ቢሆን አይቻለውም። እርሱ ባወቀ ግን በብዙ አይነት በብሉይ ኪዳንም ይልቁንም በሐዲስ ኪዳን ምሥጢረ ሥላሴን እራሱ ባለቤቱ በጥምቁቱ ገልጦልናል፡፡ ይህንንም በዓል ሰናከብር እግዚአብሔር (ሥላሴ) በአብርሃም ቤት ተገኝተው፣ የአብርሃምን ቤት በርከው ሊመጣ ያለውን የሐዲስ ኪዳን ነገረ ድኅነት በግልጥ ነገሮናል። እኛም በዓሉን ሰናከብር እምነታችን በቅድስት ሥላሴ ላይ በማድረግ በቀናች ሃይማኖት ልንጸና ይገባናል!

እንደ አብርሃም ንጹሕ ልብ ይዘን፣ ከኀጢአት ርቀን እንግዶችን እንድንቀበል አምላካችን እግዚአብሔር ይርዳን፤ አሜን!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ምንጭ፦ ኆኅተ ስብከት ዘቅዱስ ያሬድ በሊቀ ጉባኤ ጌታሁን ደምፀ
አምስቱ አዕማደ ምሥጢር በምኑን በኀበ ሰብእ
ሃይማኖተ አበው ተስፋ ገብረ ሥላሴ
ምሥጢረ ምሥጢራት በገብረ መድኅን እንየው እና መዝገበ ቃል ገ/ሕይወት

Mahebere kidusan
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እግዚአብሔርን የኢትዮጵያ ብቻ አምላክ ማድረግ አደገኛ ነው

#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
ነገረ ሃይማኖት 101
***
በአመክንዮአዊነት የታጠረ፣ በተወሰኑ ፎርሙላዎች ላይ የቆመ፣ ወጥ በሆነ መንገድ በቀላሉ ማብራራት የሚቻል (coherently explainable) ነገረ-ሃይማኖታዊ ሐተታ ስታይ የሆነ የጎደለ ነገር እንዳለ ተረዳ። የክርስትና ነገረ-ሃይማኖት ከአመክንዮ ጋር የሚቃረን ባይሆንም ከሰው መረዳት የሚያልፍ እና በጥቂት አመክንዮአዊ ሐተታዎችና ፎርሙላዎች የማይጠቃለል ምሥጢር አለው። መለኮታዊ ስለሆነ!
በመሆኑም ሰዎች በአመክንዮአቸው ልክ ቀንሰው የሰፉት (reductionist) ትምህርት የሚቀረው ብዙ ነገር አለ፤ ስህተትን ያስከትላል።
የምዕራቡ ዓለም ክርስትና በመካከለኛው ዘመን ክርስትናን በአርስቶትላዊ አመክንዮ ውስጥ ለመቀመር ሞክሮ ብዙ ተጎድቷል። የእኛም ሊቃውንት በዚህ አልተፈተኑም ማለት ይከብዳል። በተለይ በአንዳንድ 'ሊቃውንት' ነገረ-ክርስቶስ የሚብራራበት የመገናዘብ ሐተታ (communication of idioms) የተለጠጠ እና አመክንዮአዊ ትምክህት የሚታይበት ነው። ይህ ወደ ችግር እንጂ ድኅነት የሚወስድ አይደለም። ነገረ-ክርስቶስ የመዳን ምሥጢር ነው። ክብር ይገባዋል።

Bereket Azmeraw
የመዳን_ትምህርት_በዘመናት_ሂደት_ውስጥ_አጭር_ዳሰሳ_በዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ.pdf
204.5 KB
የመዳን ትምህርት በዘመናት ሂደት ውስጥ - አጭር ዳሰሳ

* የነገረ ድኅነት ትምህርት በምዕራቡ አለም
* ስኮላስቲሲዝም (scholasticism)
* የትሬንት ጉባኤ
* የፕሮቴስታንቶች አጸፌታ
* ኦርቶዶክሳዊ የመዳን ትምህርት

++++++++ ~ +++++++

መዳን ከኃጢአት ይቅርታ ባሻገር ብዙ ነገሮችን የያዘ ሰፊና ጥልቅ ነገር ነው፡፡ ስለዚህም አንደኛውንና የመጀመሪያውን ሥጦታ (የኃጢአትን ይቅርታ ማግኘትን) ብቻ ሌላውን እስከሚያስረሳ ድረስ ማጉላትና ከዚያ ያለፈ ነገር የሌለ ማስመሰል እግዚአብሔር የሰጠውን ጸጋ ማሳነስና የተጠራንበትን ከፍ ያለውን የእግዚአብሔርን ጥሪ ማስረሳት ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱሳዊውና በአበው ቀደምት አስተምህሮ መሠረት መዳን ስንል ሥርየተ ኃጢአት ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔርን ማወቅን፣ ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት ማግኘትን፣ ብርሃናዊነትን ገንዘብ ማድረግን፣ ከባርነት ነጻ መውጣትን፣ አዲስ ተፈጥሮንና የጸጋ አምላክነትን ገንዘብ ማድረግን ሁሉ የሚጨምር ሰፊና ጥልቅ ነው::

++++++++ ~ ++++++++

ኦርቶዶክሳውያን አባቶቻችን የጸጋው ሥጦታ ነጻ (እንዲሁ) የሚሰጥ መሆኑን በአንድ በኩል፣ የሰውን ነጻ ፈቃድ (ነጻነት) ደግሞ በሌላ በኩል አስተባብረው በመያዝ ለሰው መዳን የሁለቱ መስተጋብር (በግሪኩ Synergy) አስፈላጊ መሆኑን በአጽንኦት ያስተምራሉ፡፡ ይህም በቅዱስ ጳውሎስ “ከእርሱ ጋር አብረን የምንሠራ ነንና” ተብሎ የተገለጸው ነው፡፡ 1 ቆሮ. 3:9


#መድሎተ_ጽድቅ

#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
"እኛ መና አለን ይህ መና እስራኤላውያን በምድረ በዳ የተመገቡት መና አይደለም። እኛ መንፈሳዊ መጠጥ አለን፤ ይህ መጠጥ እስራኤላውያን ከዐለት ውስጥ ፈልቆ የጠጡት መጠጥ አይደለም።አሁን እኛ የአንድነትን (ገዳማዊ) አኗኗር እየኖርን ነው።አሁንም ያለነው በገዳም ውስጥ ነው። በምድረ በዳ ያለቅድስና መኖር ማለት በአካል ከሰው ከመነጠል በቀር ምንም ትርጉም የለውም። ያ በረሃ እንዲህ አስፈሪ የሆነበት ምክንያት ምንድነው? ጊንጡ ወይስ ሐሩሩ ነው? ወይስ ነቢዩ ሙሴ፦ "እባብና ጊንጥ ጥማትም ባለባት ውኃም በሌለባት በታላቂቱና በምታስፈራው ምድረ በዳ የመራህን"(ዘዳ.8፡15) እንዲል እንዲሁም ነቢዩ ኤርሚያስ "ማንም በማያልፍበትና ማንም በማይቀመጥበት ምድር" (ኤር.2፡6) ያላትን ነውን? ይህ ገዳም ነውን የሚያስፈራው? አይደለም። ከእርሱ ይልቅ የጽድቅ ፍሬን ከመስጠት የመከነ የሰው ገዳም አያስፈራምን? በዚህ ምሳሌ ምን ያህል ጊንጦችና መርዛም እባቦች በዚህ ገዳም (ዓለም) ውስጥ አሉ? ምን ያህል እባቦችና የእፉኝት ልጆች በዚህ ገዳማችን (ዓለም) ውስጥ ይኖራሉ? (ማቴ.3፡7) እኛ በእነዚህ መካከል የምንኖር አይደለንምን? እንዲህ ቢሆንም ግን እንፈራቸው ዘንድ አይገባንም ምክንያቱም እኛን ከእነዚህ እባቦች የሚያድነን ሙሴ ሳይሆን ከእርሱ የበረታው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ ነው"


St. John Chrysostom, Homilies on Ephesians.Homily XXlll.P.165
በእንተ_ሥጋዌ_በዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ.pdf
147.8 KB
በእንተ ሥጋዌ

ለተማሪዎቹ የሚያስብ ርኀሩህ አስተማሪ አንዳንዶቹ ተማሪዎቹ ረቀቅና መጠቅ ያለው ትምህርት እንዳልገባቸው ሲያይ ወደ እነርሱ ደረጃ ዝቅ ብሎ እነርሱ በሚገባቸው በማንኛውም ሁኔታ እንደሚያስተምራቸው ሁሉ የእግዚአብሔር ቃልም እንዲሁ አደረገ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም እንዲህ እንዳለ፡- በእግዚአብሔር ጥበብ ምክንያት ዓለም እግዚአብሔርን በጥበብዋ ስላላወቀች በስብከት ሞኝነት የሚያምኑትን ሊያድን የእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ ሆኗልና፡፡»"

#ቅዱስ_አትናቴዎስ_ሐዋርያዊ_ህይወቱና_ትምህርቱ

#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
#እግዚአብሔርን_ጠብቅ

እግዚአብሔርን የሚጠብቅ ሰው እርሱን በተስፋ፤ በእምነት፤ በተሞላ ሙሉ ልብና ያለምንም ድካም ይጠብቀዋል። ይህ በመሆኑም እንደዚህ ዓይነቱ ሰው እግዚአብሔር በመካከል ገብቶ እንደሚሰራና ሁሉም ነገር ለበጎ እንደሚሆን ያምናል። "እግዚአብሔር ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።" [ሮሜ 8፥28] "እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ አይታክቱም ይሄዳሉ አይደክሙም።" [ኢሳ 40፥31] ኃይላቸው በመከራ የተናወጠባቸው ሁሉ እግዚአብሔርን በተስፋ በመጠባበቅ ኃይላቸውን ያድሳሉ ማለት ነው። "ጎልማስነትሽን እንደ ንስር ያድሳል" የሚል ቃል ተጽፏል [መዝ 102፥5] ስለሆነም ማንም ቢሆን እግዚአብሔር እምነት በተሞላ ብርቱ ልብና በእርሱ ላይ በመተማመን ይጠብቀዋል።

ነገር ግን አንድ ሰው እግዚአብሔር እርምጃ እንደሚወስድና እርምጃውም ግልጽና ኃያል እንደሆነ መተማመን አለበት። ከዚሁ ጋር እርምጃው በተመቻቸ ሰዓት ፍሬያማ በሆነ መንገድ የሚከናወን ነው። እግዚአብሔር አንድ የሆነ እርምጃ ለመውሰድ ከወደደ ምንም የሚጠባበቀው ሰዓት አይኖርም። ኢየሱስ ክርስቶስ " ... አብ በገዛ ሥልጣኑ ያደረገውን ወራትንና ዘመናትን ታውቁ ዘንድ ለእናንተ አልተሰጣችሁም አላለምን ? [ሐዋ 1፥7] አንተ ችግርህን እግዚአብሔር እንደሚያቃልልህ በማመን መቼ ለችግርህ መፍትሔ እንደሚሰጥህ ሳታስብ በእርሱ እጅ ላይ ብቻ ጣለው።

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል

“ይህንም ብሎ፡ በታላቅ ድምፅ፦ አልዓዛር ሆይ፥ ወደ ውጭ ና፡ ብሎ ጮኸ።”
[ዮሐንስ 11:43]

ከሞተ አራት ቀን ወደ ሆነው “ይሸታል” ወደተባለው ሙት ጌታችን መጥቶ አስነሳው.. መግነዙን ፍቱት አለ.. እና አባ ሲያስተምሩ ምን አሉን በኃጢአት ብትተሳሰሩ እንኳ ጌታን ተስፋ አድርጉት እርሱ ከታሠራችሁበት ማሰሪያ ፈትቶ ነጻ ያደርጋችኋል.. እርሱን ብቻ ተስፋ አድርጉ.. የሞተውን አበቃለት የተባለውን እንኳ አስነስቷልና..

እርሱ የትኛውንም ልብ ሳይጸየፍ በልዩ ፍቅሩ በዛ ሊኖር ይመጣልና እናንተ ደግሞ ጌታን የሚቀበል ልብ ይኑራችሁ.. ጌታችሁ የልባችሁን በር ዘወትር ያንኳኳልና ክፈቱለት እርሱ ይግባ..

መልካም የጌታ ቀን

@Apostolic_Answers
ሱባዔ

ሱባዔ ምንድን ነው ?
ሱባኤ በሰዋሰው ትርጉሙ "ሰባት"ማለት ሲሆን በመንፈስ አተረጋጎም አንድ ሰው ከዚህ ቀን እስከ ዚህ ቀን በጸሎት ከፈጣሪየ ጋር እገናኛለሁ ብሎ የሚያቅደው መንፈሳዊ ዕቅድ ነው ፡፡ ሰባት ቁጥር በእስራኤላውያን ዘንድ በሥራም በቃልም የሚገለጥ ፍጹም ቁጥር ነው፡፡ ለምሳሌ ፦ ፈጣሪ አለማት እግዚአብሔር በሰባተኛው ቀን ሥነ ፋጥረትን ከመፋጠር ማረፋ ፥ለጸሎት የሚተጉ ምዕመናን በቀን ለሰባት ጊዜ ማመስገናቸው የሰባት ቁጥር ፋጹምነት ያመለክታል ፡፡ (ዘፍ 2፥2 , መዝ 118፥164) አንድ ሰው 7 ቀናት ቢጾም "አንድ ሱባኤ ጾመ" ይባላል ፡፡

ሱባኤ መቼ ተጀመረ?
የተጀመረው ከውድቀት በሓላ በመጀመርያው ሰው በአዳም ነው፡፡ ቅዱሳን መላእክት አዳምን ጸሎት እንዳስተማሩት የቤተ ክርስቲያናችን መዛግብት ያስረዳሉ በምላሹም ከልጅ ልጅህ ተወልጄ ስጋን ለብሼ ከ 5 ቀን ተኩል በኋላ አድንሃለሁ የሚለውን ቃል ኪዳን የሰማው ሱባኤ በመግባቱ ነው፡፡

ሱባዔ ለምን ይጠቅማል?
የሰው ልጅ ሓጢአት በሚስማማው የሥጋ ሰውነቱ ዘወትር ፈጣሪውን ይበድላል፡፡ በፈፀመው በደል ህሊናው ይወቅሰዋል ይጸጸታል፡፡ በመጀመርያ ደፋሮ በሰራው ሀጥያት በኋላ ይደነግጣል ይህ በማንኛውም ሰብአዊ ፋጥረት ኀሊና ውስጥ የሚፈራረቅ ክስተት ነው ፡፡ በዚህ ግዜ የፈጣሪውን ይቅርታ ለማግኝት ያስባል ይተክዛል፡፡ ሰው በደፋርነቱ የኃያሉን አምላክ ትእዛዝ ተላልፎ አለም ሲያስጨንቀው  ሸክሙን የሚያቃልልበትና የሚያስወግድበት  መንፈሳዊ ጥበብ ከቸሩ ፈጣሪ ተሰጥቶታል፡፡ ይህውም በጥቂት ድካም ሥጋ ያልተወሰነ ጸጋ እግዚአብሔር የሚያገኝበት ሥርዓት ሱባዔ ነው፡፡

1- እግዚአብሔርን ለመማጸን፦
ማንኛውም ሰው ሱባኤ ሲገባ በቁርጥ ወደ ፈጣሪው የሚያቀርበው ተማፅኖ ሊኖረው ይገባል፡፡ ምንም የምንጠይቀው ( የምንማፀነው) ነገር ሳይኖር ሱባዔ ብንገባ የምናገኝው መልስ አይኖርም፡፡ ስለዚህ ሱባኤ ከመግባታችን በፊት፦ ሱባዔ የምንገባው ለምንድን ነው ?  በማለት እራሳችንን መጠየቅ ይኖርብናል ፡፡

2- የቅዱሳንን በረከት ለመሳተፍ
ቅዱሳን አባቶችና እናቶች የተጋደሉትን ተጋድሎ በማዘከር ቃል ኪዳን በተሰጣቸው ገዳማትና አድባራት የሚገባ ሱባኤ የቅዱሳን በረከት ተካፋይ ያደርጋል፡፡ በጾመ ነብያት የነብያትን፣ በጾመ ሀዋርያት የሀዋርያትን፣ በጾመ ፋልሰታ የእመቤታችንን በረከት ለመሳተፋ ሱባኤ መግባት የነበረ ነው፡፡

የሱባዔ አይነቶች፦
1- የግል ሱባኤ ( ዝግ ሱባዔ)፦
አንድ ሰው ብቻውን አመች ቦታ ማንም ሳያየው በግሉ የጸሎት በአቱን ዘግቶ በሰቂለ ኀሊና ሆኖ ፈጣሪው ብቻ እንዲያየው በኀቡዕ የሚፈፅመው ሱባኤ ነው ፡፡

2- የማህበር ሱባዔ፦
ካህናት ምዕመናን ወንዶች ሴቶች ሽማግሌወች ፤ወጣቶች ፤በአንድ ሆነው በቤተ ክርስትያንና አመች በሆኑ ቦታወች ሁሉ ተሰብስበው የሚገብት ሱባዔ ነው፡፡

3- የአዋጅ ሱባዔ፦
በሀገር  ላይ ድንገተኛ አደጋ ፤ አባር ቸነፈር ጦርነት ሲነሳ እንዲሁም በማህበረ ምዕመናን ላይ አስጊ የሆነ መቅሰፋት ሲከሰት እግዚአብሔር መዓቱን በምህረት ቁጣውን በትዕግስት እንዲመልስ የሚያዝ የሱባዔ አይነት ነው፡፡

ለሱባዔ የሚደረግ ቅድመ ዝግጅት፦
ሱባኤ ከመግባታችንም ሆነ ከገባን ግዜ እንዲሁም ከጨረስን በኋላ ምእመናን ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ይገባናል፡፡

➢ ሱባኤ ከመግባት አስቀድሞ
በመጀመርያ ሱባዔ የምንገባበትን ምክንያት ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል ፡፡
፪ ሱባኤ ለመግባት የወሰንበትን ምክንያት ከለየን በኋላ ምክንያታችንን ይዘን የንስሃ አባታችንን ማማከር ያስፈልጋል፡፡
፫ ለምን ያህል ቀናት መቆየት እንዳለብን መወሰን ያስፈልጋል ፡፡ሱባኤ ከዚህ እስከዚህ እቆያለሁ ብለን ዕቅድ የምንይዝበት ነው፡፡
፬ ወቅትና ቦታ መምረጥ ተገቢ ነው፡፡ በቤተክርስቲያናችን በአብዛሀኛው ግዜ ሱባዔ የሚገባው በአጽዋማት ወቅት በመሆኑ ይህንን መለየት ነው፡፡ ምክንያቱም በጾም ወቅት ብዙ አባቶች ጸሎት የሚይዙበት ስለሆነ ፀሎታችን ከእነርሱ ጋር አብሮ ያርግልናልና ነው፡፡ እዚህ ላይ በማንኛውም ግዜ ሱባኤ አይያዝም ለማለት አይደለም በማንኛውም ግዜ ፈተና ያጋጠመው ሰው ሱባዔ ሊይዝ ይችላል፡፡

➢ በሱባዔ ግዜ 
ሀ. በጸሎት ሰአት ዓምድና ግድግዳ ሳይደገፉ መቋሚያ ሳይዙ በሁለት እግር ቀጥ ብሎ በመቆም መጸለይ ይኖርብናል፡፡ እንዲሁም ፊትን ወደ ምስራቅ መልሶ መቆም ወደ ግራ ወደ ቀኝ አለመዟዟር በሰቂለ ህሊና ኾኖ መጸለይ ይገባል፡፡
ለ . በቅደም ተከተል መፀለይ ይገባል በመጀመርያ አአተብ ከሚለው ተጀምሮ አቡነ ዘበሰማያትን ጠቅሶ ጸሎተ ሀይማኖትን መጨረስ ፡፡ሰግዱ እና ስለ መስቀል በሚያነሳው ላይ እየሰገዱና እያማተቡ መጸለይ ፡፡ በማስቀጠል አቡነ ዘበሰማያት ፤መዝሙረ ዳዊት ውዳሴ ማርያም ሌሎችንም ማስከተል ከዚያ 41 ግዜ ኪራላይሶ ይባላል ፡፡
ሐ.  በሱባዔ ግዜ ከተሐራሚው የሚጠበቀው ነገር ሐጢአቱን እያሰበ ማዘን ማልቀስ ለእያንዳንዱ በደል ማልቀስ ማዘን ይገባዋል ፡፡
መ.  በመጨረሻም ሱባዔ የገባው ሰው ሱበዔውን ሳይጨርስ ወይም አቋርጦ ከማንኛውም ሰው ጋር ፈፅሞ መገናኝት የለበትም ፡፡

3- ከሱባዔ በኋላ
ላቀረብነው ተማፅኖ እግዚአብሔር የሚያደርግልንን ነገር  መጠበቅ ይኖርብናል። ሱባዔ የገባ ሰው ሁሉ ራዕይ ላያይ ይችላል፡፡ ምክንያቱም የእግዚአብሔር መልስ አሰጣጥ ለማንም ግልጽ አይደለም፡፡ ከሱባዔ በኋላ መጀመሪያ የምናገኝው የህሊና ሰላም ነው፡፡ ይህ ትልቅ የአምላክ ስጦታ ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር ሱባኤ ገብተን ያሰብነውን  ካላገኝን ዳግመኛ ተዘጋጅተን እስከ መጨረሻው ሰዓት በመማፀን መጽናት ይኖርብናል፡፡፡

መጭው ጾመ ፋልሰታ (የመቤታችን ጾም ) በመባል የሚታወቀው እና ቤተ ክርስቲያናችን አበይት አጽዋማት ብላ ከደነገገቻቸው ወስጥ አንዱ ነው ፡፡ በዚህ ወራት ብዙዎቹ አባቶቻችንና እናቶቻችን በረከተ ስጋ ወነፍስ ያገኙበት የበረከት ጾም ነው እኛም ቢቻለን በሱባኤ ባይቻለን አቅማችን የፈቀደውን እየጾምን በጸሎት አምላካችንን መጠየቅ እንዲሁም እመቤታችን በምልጃዋ  ታስበን ዘንድ መማፅን ያስፈልገናል ፡፡


(ቃለ ተዋሥኦ ቁጥር 2 )
🕊

† እንኳን ለቅድስት ጾመ ፍልሠታ ለማርያም  በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †

†  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !  †

†  🕊 ቅድስት ጾመ ፍልሠታ ለማርያም  🕊

† ቸር እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ከሰጠው ጸጋ አንዱ ጾም ነው:: የሰው ልጅ ከፈጣሪው ክብር እንዲደረግለት ክፋትን መስራት የለበትም:: መልካም መሆንም ይጠበቅበታል:: ለዚህ ምንጮቹ ደግሞ ጾም: ጸሎትና ስግደት ናቸው:: ያለ እነዚህ ምግባራት መቼም ወደ ጽድቅ መድረስ አይቻልም::

ይቅርና እኛ ክፉዎቹ የሰማይና የምድር ፈጣሪ: የክብር ሁሉ ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋችንን በተዋሐደ ጊዜ የመጀመሪያ ሥራው ያደረገው ጾምን ነው:: ስለዚህም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ፯ [ 7 ] አጽዋማትን በጉባዔ ሠርታ: በአዋጅ እንዲጾሙ ታደርጋለች:: ከእነዚህም አንዱ ጾመ ፍልሠታ ነው::

"ፈለሠ" - ሔደ: ተጉዋዘ እንደ ማለት ሲሆን "ፍልሠታ" ማለት የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን የዕርገት ጉዞ የሚያዘክር ቃል ነው:: እመ ብርሃን በዚህ ዓለም ለ ፷፬ [64] ዓመታት ኑራ ካረፈች በሁዋላ ሥጋዋ እንደ እኛ አልፈረሰም::

ለጊዜው በዕጸ ሕይወት ሥር ቆይታ እንደ ልጇ ትንሳኤ ተነስታ ዐርጋለች:: እርሷ በሁሉ ነገሯ ቀዳሚና መሪ ናትና:: ጾመ ፍልሠታን የጀመሩት አበው ሐዋርያት ሲሆኑ እንድትጾምም ሥርዓት የሠሩ ራሳቸው ናቸው:: ከ፯ [7] ቱ አጽዋማትም እጅግ ተወዳጅና እየተናፈቀች የምትፈጸም ናት::

ካህናትና ምዕመናንም ጾሟን እንደየአቅማቸው ክብር በሚያሰጥ መንገድ ይፈጽሟታል::
- የቻሉ ወደ ገዳማት ሔደው ጥሬ እየቆረጠሙ: ውሃ እየተጐነጩ ክብርን ያገኛሉ::
- ሌሎቹ ደግሞ ባሉበት ደብር አካባቢ እያደሩ ሌሊት ሰዓታቱን: በነግህ ኪዳኑንና ውዳሴ ማርያም ትርጉዋሜውን: በሰርክ ደግሞ ቅዳሴውን ይሳተፋሉ::
- የኔ ብጤ ደካማ ደግሞ ጠዋት ማታ ወደ ደጇ እየተመላለሰ "አደራሽን ድንግል" ይላታል::

† በእርሷ አምነን አፍረን አናውቅምና ነጋ መሸ ሳንል እንማጸናታለን::

🕊

† ጽንዕት በድንግልና: ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኚልን:: አእምሮውን: ልበለብዎውን: ጥበቡን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን::
- ጾሙን የፍሬ: የትሩፋትና የበረከት ያድርግልን::


🕊                        💖                     🕊
Audio
ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ ዘረቡዕ
Audio
ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ክፍል 1
2024/09/28 22:24:58
Back to Top
HTML Embed Code: