Telegram Web Link
ሰበር ዜና! አቋርጠው ወጡ

"ቤተክርስቲያን ስትፈርስ መዶሻ አላቀብልም"

ትናንት በዋለው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ ለሹመት በተመረጡ ኤጲስ ቆጶሳት ዙሪያ በተጀመረው ውይይት ከፍተኛ ውዝግብ ያስተናገደ ሲሆን ከጅምሩ በነበረው የአካሄድ ክፍተትና የቀኖና ጥሰት ቅሬታ የነበራቸው ብፁዓን አባቶች ባለ መገኘታቸው የምልዓተ ጉባዔው አባላት ሳይሟሉ እንዲቀጥል ተደርጓል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በምልዓተ ጉባዔው ተገኝተው እየተሳተፉ ያሉ ብፁዓን አባቶች በግንቦቱ ለተሰየሙ አስመራጭ ኮሚቴ አባላት ለሚቀርብላቸው ጥያቄ ቀጥተኛ ማብራሪያና ምላሽ ባለመስጠታቸው አሁንም ግልጽነት የጎደለውና ከስርዓተ ቤተ ክርስቲያን ውጭ የሆነ አካሄዳቸውን በመቃወም አቋርጠው ለመውጣት ተገደዋል።

ከእነዚህም ብፁዐን አባቶች ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል የከፋ ሸካ ቤንች ማጂ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ሓላፊ ቤተክርስቲያን ስትፈርስ መዶሻ አላቀብልም በማለት አቋርጠው መውጣታቸውን ለማወቅ ተችሏል።
እስኪ ፀልዩ አባቶቻችን ምን ነካቸው ?
"…ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ከምዕራብ ሸዋ ሃገረ ስብከት፣ ከምሥራቅ አፍሪካ፣ የኬሠኒያ፣ ኡጋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ሩዋንዳ ሃገረስብከት ሊቀጳጳስነት በተጨማሪ የሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት አደራጅ ሊቀ ጳጳስ ተብለው ተሹመዋል ተብሏል።

• ሹመት ያዳብር…!
መዝሙር 21
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ አቤቱ፥ በኃይልህ ንጉሥ ደስ ይለዋል፤ በማዳንህ እጅግ ሐሤትን ያደርጋል።
² የልቡን ፈቃድ ሰጠኽው፥ የከንፈሩንም ልመና አልከለከልኸውም።
³ በበጎ በረከት ደርሰህለታልና፤ ከክቡር ዕንቍ የሆነ ዘውድን በራሱ ላይ አኖርህ።
⁴ ሕይወትን ለመነህ ሰጠኸውም፥ ለረጅም ዘመን ለዘላለሙ።
⁵ በማዳንህ ክብሩ ታላቅ ነው፤ ክብርንና ምስጋናን ጨመርህለት።
⁶ የዘላለም በረከትን ሰጥተኸዋልና፥ በፊትህም ደስታ ደስ ታሰኘዋለህ።
⁷ ንጉሥ በእግዚአብሔር ተማምኖአልና፥ በልዑልም ምሕረት አይናወጥም።
⁸ እጅህ ጠላቶችህን ሁሉ ታግኛቸው፥ ቀኝህም የሚጠሉህን ሁሉ ታግኛቸው።
⁹ በተቈጣህም ጊዜ እንደ እሳት እቶን አድርጋቸው፤ እግዚአብሔር በቍጣው ያጠፋቸዋል፥ እሳትም ትበላቸዋለች።
¹⁰ ፍሬአቸውን ከምድር ዘራቸውንም ከሰው ልጆች ታጠፋለህ።
¹¹ ክፋትን በአንተ ላይ ዘርግተዋልና፥ የማይቻላቸውንም ምክር አሰቡ።
¹² ወደ ኋላቸው ትመልሳቸዋለህ፤ ፍላጻን በፊታቸው ላይ ታዘጋጃለህ።
¹³ አቤቱ፥ በኃይልህ ከፍ ከፍ በል፤ ጽናትህንም እናመሰግናለን እንዘምርማለን።
ሰላም ለልደትከ ከመ ገብርኤል አደሞ
ስድስተ አውራኃ ለልደተ ክርስቶስ እንተ ቀደሞ
ዮሐንስ ስኂን ወምዑዝ እምቀናንሞ 😍
ለለነበብኩ በፅሒቅ ለመልክእከ ሰላሞ
ከመ ከላስት በሕፅንከ ሲሞ 😍
ግዛቱ የተሽፋፋለት የሸገር ሃገር ስብከት አዲስ ጣጣስ 😡
+ የበረሃው መናኝ +

መጥምቁ ዮሐንስ በሕፃንነቱ የመነነ የምድረ በዳ ሰው ነበር፡፡ የቀን ሐሩሩን የሌሊት ቁሩን ታግሦ በማይመቸው በረሃ ውስጥ ይኖር ነበር፡፡ የምድረ በዳው ሰው የዮሐንስ ድምፅ ታዲያ ከአይሁድ ሸንጎ እስከ ሔሮድስ ቤተ መንግሥት ድረስ ዘልቆ ይሰማ ነበረ፡፡

የምናኔን ኃይል ተመልከቱ! በምድረ በዳ ለመኖር የጨከነ ባሕታዊ ድምፅ ግርማው በከተማ ይሰማል፡፡ እርሱ በዋሻ ውስጥ እያደረ በቤተ መንግሥት በምቾት አልጋ የሚያድሩትን ሰዎች ያንቀጠቅጥ ነበር፡፡

‘ያን ጊዜ ኢየሩሳሌም ይሁዳም ሁሉ በዮርዳኖስም ዙሪያ ያለ አገር ሁሉ ወደ እርሱ ይወጡ ነበር’ (ማቴ. 3፡3) መናኙ ዮሐንስ ለስብከት ወደ ከተማ መምጣት አላስፈለገውም፡፡ ሕዝቡ ‘ወደ እርሱ ይወጡ ነበር’ ባሕታዊ ዮሐንስ ምድረ በዳውን አልለቀቀም፡፡ ሕዝቡን ለማምጣትም ወደ ሕዝቡ ገብቶ አብሮ መኖር አላስፈለገውም፡፡ ሕዝቡ ለነፍሳቸው ዕረፍት ፍለጋ ወደ ዮሐንስ ይሔዱ ነበር፡፡

ወደ ዮሐንስ ያልሔደ ማን አለ? ወታደሩ ፣ ባለ ሥልጣኑ ፣ ፈሪሳውያኑ ፣ ሰዱቃውያኑ ሁሉ ከሚመጣው ቁጣ ሊሸሹ ወደ ዮሐንስ ይመጡ ነበር፡፡

እውነተኛው መናኝ ዮሐንስ ሰዎችን ፈልጎ ወደ ዓለም የሚመጣ ሳይሆን ዓለማውያኑ ፈልገውት ወደ እርሱ የሚሔዱለት ነበር፡፡ አባ መቃርስን አባ እንጦንስን ፈልገው ወደ አስቄጥስ በረሃ ሰዎች እንደገሰገሱ ፣ አባ ሳሙኤልን ፈልገው ወደ ዋልድባ እንደተጓዙ ፣ አባ አረጋዊን ብለው ወደ ደብረ ዳሞ እንደገሰገሱ ሰዎች የዮሐንስን ፈለግ የተከተሉ የምድረ በዳ መናኞች ዓለምን ወደ እነርሱ ይስባሉ እንጂ እነርሱ በዓለም አይሳቡም፡፡

ዮሐንስ ምግቡ አንበጣና የበረሃ ማር ፣ ልብሱ የግመል ጠጉር ነበረ፡፡ ሰውነት የሚኮሰኩስ ቆዳን የሚረብሽ ልብስ ለብሶ ነበር፡፡ የግመል ጠጉር ዕርቃንን ከመሸፈኑ ውጪ ለብርድም ለሙቀትም የማይመች ዓይነት ልብስ ነበር፡፡ ዮሐንስን በሕይወቱ ከሚመስለው ከኤልያስ በስተቀር እንዲህ ዓይነቱን ልብስ ሊለብሰው የሚወድ ሰው አልነበረም፡፡

ጌታ ወደ ዮሐንስ የመጡትን ሰዎች ‘ምን ልታዩ ወጣችሁ? ቀኝን ልብስ የለበሰ ሰውን? እነሆ ቀጭን ልብስ የለበሱ በነገሥታቱ ቤት አሉ’ ብሎ ነበር፡፡ ማቴ. 11፡8 እውነት ነው ዮሐንስ አለባበሱን ለማየት የሚጓጓለት ሰው አልነበረም፡፡ ምን ዓይነት ልብስ ለብሶ ይሆን ብላችሁ ልታዩ ከመጣችሁ የሚያምር ልብስ የሚለብሱት ሰዎች ያሉት በነገሥታቱ ቤት ነው፡፡ ዮሐንስ ልብሱ የግመል ጠጉር ነው፡፡

የግመል ጠጉር ሰውነት ይኮሰኩሳል:: ለልብስነት አይመችም ለአገልግሎት ግን ይመቻል:: ልብስህ ግመል ምግብህ አንበጣ ቤትህ ምድረ በዳ ከሆነ ያለሃሳብ ታገለግላለህ:: እንደ በረሃው መናኝ እንደ ምድረ በዳው ባሕታዊ እንደ ቅዱስ ዮሐንስ ቤቴ ሚስቴ ድስቴ ልብሴ ምግቤ ሳትል ዝም ብለህ ለጌታህ መንገድ ትጠርጋለህ:: የማታጥበው የማትተኩሰው የግመል ጠጉር ከለበስህ ቃሉን ከመስበክ በቀር ምን ያሳስብሃል?

ዮሐንስ የስብከቱ ኃይል ምድርን ያንቀጠቀጠውም ለዚህ ነው፡፡ ነገሥታቱን ለመገሠፅ ያልከበደውም ለዚህ ነው፡፡ ምን አጣለሁ ብሎ ይፈራል? ምን እበላለሁ እንዳይል ቀድሞውንም ምግቡ አንበጣ ነው፡፡ ምን እለብሳለሁ? ብሎ እንዳይሰጋ የሚለብሰው የግመል ጠጉር ነው፡፡ ሰውነቱን ምቾት ስላላስለመደ ዮሐንስ እንዳያጣው የሚፈራው ምንም ነገር አልነበረም፡፡ ቤቴን እንዳይቀሙኝ ብሎ እንዳይፈራም እርሱ የምድረ በዳ መናኝ ነው፡፡

ባሕታዊው ዮሐንስ ሆይ ያማረ በፍታና ቀጭን ልብስ የለበስን ፣ ያማረ የምንበላ የምንጠጣ ፣ ባማረ አልጋ የምንተኛ ሰባኪያን አንተ መንገድ የጠረግህለትን ጌታ መንገድ ስንዘጋበት ስታይ ምንኛ ትታዘበን ይሆን? ሔሮድስ ከሔሮድያዳ ቢጋባና ቢወልድ ትንፍሽ የማንል ይልቁንም ሰርጉን ለመባረክ የምንሮጠው ለምን ይመስልሃል? ሔሮድስ እንኳን እናቲቱን ልጅትዋንም ጨምሮ ቢያገባ ሰምተን እንዳልሰማ የምንሆነው ልብሳችን እንዳንተ የግመል ጠጉር ፤ ምግባችንም የበረሃ አንበጣ ስላልሆነ ነው::

ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ ዛሬ "ለጌታ መንገድ አቅኑ ተራራው ዝቅ ይበል" ልትለን የሚገባህ የሐዲስ ኪዳን ፈሪሳውያንን በዝተናል:: በክርስቶስ የምናምን ሰዱቃውያንን የሔሮድስ ሰርግ ደጋሾች የሔሮድያዳ ጠጅ አሳላፊዎች እልፍ አእላፋት ሆነናል:: በልደትህ ቀን ወደ እኛ ተመልከት::

እኛ እንዳንተ "ዳዕሙ ከመ ያእምርዎ እስራኤል" (እስራኤል ያውቁት ዘንድ ነው) ማለት የምንችል አይደለንምና የምድረ በዳው መናኝ ሆይ ጌታህን እኛ እንድናውቀው አድርገን::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሰኔ 30 2015 ዓ.ም.
የመናኙን ምልጃ ለመማጸን የተጻፈ

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን አጥብቃችሁ ስለ እኔ ጸልዩልኝ!
በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ [ዋጋን በምድር የሚያስቀር ውዳሴም ሆነ ሌላ] ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)
"አንተ ራስህ ለገዛ ወንድምህ ጨካኝና ይቅር የማትል ኾነህ ሳለስ እግዚአብሔር እንዲራራልህና እንዲምርህ እንዴት መለመን ይቻልሃል?

"ባልንጀራህ ምናልባት ንቆህ ሊኾን ይችላል፡፡ አዎ! አንተ ግን እግዚአብሔርን ኹልጊዜ እንደናቅኸው ነው፡፡ በባልንጀራና በእግዚአብሔር መካከልስ ምን ንጽጽር አለ? ባልንጀራህ ምናልባት ጉዳት ሲደርስበት ሰድቦህ ይኾናል፤ አንተም በዚህ ተበሳጭተህ ይኾናል፡፡ አንተ ግን ምንም ሳይጎዳህና በአንተ ላይ ክፉ ሳያስብ ይልቁንም ዕለት ዕለት በረከቱን እየተቀበልክ እያለ እግዚአብሔርን ሰድበኸዋል፡፡ እንግዲህ ተመልከት! ነቢዩ፡- “እመሰ ኃጢአተኑ ትትዐቀብ እግዚኦ መኑ ይቀውም - አቤቱ ኃጢአትንስ ብትጠባበቅ ማን ይቆማል?” ብሎ እንደ ተናገረ እግዚአብሔር በእርሱ ላይ የምንፈጽመውን በደል ቢመረምር ኖሮ አንዲት ቀንስ እንኳን በሕይወት መቆየት አንችልም ነበር (መዝ.129፡3)፡፡

እያንዳንዱ በደለኛ ሰው ለራሱ የሚያውቀውንና ሌላ ሰው የማይመሰክርበትን እግዚአብሔር ብቻዉን ግን የሚያውቀውንስ ይቅርና የተገለጠውና ሰው ኹሉ የሚያውቀው ኃጢአታችንን እንኳን እግዚአብሔር ቢቈጣጠር ኖሮ ከእነዚህ ኃጢአቶች በኋላ የምንጠብቀው ምንድን ነው? እግዚአብሔር ንዝህላልነታችንንና ጸሎት ስናደርስ የምናሳየው ግድየለሽነታችንን፣ ሠራተኞች ለአሠሪዎቻቸው ወታደሮችም ለአለቆቻቸው ጓደኛሞች ለጓደኞቻቸው የሚያሳዩትን ፍርሐትና ክብር ያህልስ እንኳን ለጸሎትና ለልመና በፊቱ በቆምን ጊዜ አለማሳየታችንን ቢቈጣጠር ኖሮ ምን ነበር የምንኾነው?

አንተ ከጓደኛህ ጋር ስትነጋገር ለምታደርገው ማንኛውም ነገር ትጠነቀቃለህ፡፡ ስለ በደሎችህ እግዚአብሔርን ስትጠብቀው፣ ለብዙ መተላለፎችህ ይቅርታን ስትጠይቀው፣ ሥርየትን ለማግኘት ስታሳስበው ግን [በፊቱ ላይ] ኹልጊዜ ግድየለሽ ትኾናለህ፡፡ ጉልበትህ በምድር ላይ ተንበርክኮ ሳለ ልቡናህ ግን እዚህም እዚያም፣ በገበያ ሥፍራም፣ በቤት ውስጥም ይዋልላል፤ ከንፈርህ በከንቱና እንዲሁ ያነበንባል፤ ይህን የምንፈጽመው ደግሞ አንዴ ወይም ኹለቴ ሳይኾን ኹልጊዜ ነው።

እንግዲህ እግዚአብሔር ይህን ብቻ እንኳን ቢመረምር ይቅርታን ወይም ምሕረትን እንደምናገኝ ታስባለህን? በእውነት አይመስለኝም!"

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

#ትምህርት_በእንተ_ሐውልታት_መጽሐፍ
ገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተረጎመው
#ሩማ ክብር ለቅድስት ድንግል ማርያም

ይህ ፎቶ በዓለም መነጋገሪያ የሆነው የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ነው። በሩማ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ የቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ብቻ ሲቀር ህንፃው ሙሉ ለሙሉ ወድሟል።

ክብር ለእናታችን
ከዛሬው የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርስቲ ተመራቂዎች መሓል የምንኩስና ሕይወቷን በመንፈሳዊ እውቀት ለማጠንከር በማዕረግ የተመረቀች መነኮሳይት።
ሲኖዶስን እንደ መጅልሱ የጎሣ ማድረግና ከቀኖና ውጭ የፖለቲካ አገልጋይ ማድረግ ከትልቁ የዓለም አቀፍ ሤራ ጋር ትሥሥር ይኖረው ይሆን? ያድምጡት https://fb.watch/lGDtZnbMNY/?mibextid=WPBo4E68yvx9pgQK
እማሆይ ዜና ማርያም 💚💛

በመንፈሳዊ ትምህርት የቅኔ መምህርነት አስመስክረዋል ፣ አቋቋም ተምረዋል ፣ በረካታ የቤተክርስቲያን ትምህርቶችን ተምረዋል። ከልጅነት እስከምንኩስና በርካታ የችግር ጊዜዎችን አልፈዋል። እማሆይ ዜና ማርያም በዲማ ጊዮርጊስ ቅኔ ተምረዋል ፣ በባህርዳር የአብነት ትምህርት ቤት አቋቋም ተምረዋል። በዘመናዊ ትምህርት የመጀመርያ ድግሪ ተምረው ተመርቀዋል ፣ በዚህ አመት በ2014 ደግሞ በከፍተኛ ማዕርግ የማስተር ድግሪያቸውን ይዘዋል። በአሁኑ ሰዓት በቅድስት ሰላሴ መንፈሳዊ ዩኒበርስቲ በማስተማር ላይ ይገኛሉ።

እማሆይ ዜናማርያም በልጅነታቸው ከሰንበት ትምህርት ቤት የጀመራቸው የእግዚአብሔር ቃልና ለእግዚአብሔር ራስን የመስጠት ፍቅር እንዲሁም በእግዚአብሔር ቃል የመጠራት ጥበብ በሴትነታቸው የደረሰባቸውን ባህላዊና ቤተሰባዊ ጫና በትዕግስትና በእግዚአብሔር ጥበብ በማለፍ ለዚህ ክብር የበቁ እናት ናቸው። በታላቁ ገዳም በደብረ ሊባኖስ የምንኩስናን ተቀብለው የመንፈሳዊ ህይወት ሰባኪ ሆነው ቀጥለዋል።

እማሆይ ዜናማርያም ለሴቶች የሚከብድ የሚመስለውን ህይወት ኖረው አሳይተዋል እየኖሩትም ነው። የዕማሆይ ፅናታቸውና እምነታቸው ገራሚ ነው። በወጣትነታቸው የገቡበትን መንፈሳዊ ህይወትና ውጣ ውረድ አልፈው በሁለት የተሳለ ሰይፍ የመሆን ምስጢርን አሳይተዋል።
2024/09/29 21:35:07
Back to Top
HTML Embed Code: