Telegram Web Link
በዚህ መዝገብ ማኖር ማንም ሊወስደው በማይችል ቦታ ሰማያዊ ሃብትን በምድራዊ ገንዘብ ማከማቸት ነው። ዝግ የማያዝገው ሌባም የማይሰርቀው ለፈጣሪ የሆነ ብድራት።

የቆመ ለመጣል ብዙ ትግል ውስጥ ባለንበት ዓለም የወደቀ ለማንሳት የሚታገሉ ወንድሞችን ማግኘት ድንቅ ነገር ለሁሉ ምሳሌም የሚሆን ተግባር ነው።

ያወቅነውን ካወቅንበት ማትረፊያ እውቀት ዝናም መጠቀሚያ መሆኑን እንዲህ በእሸቱ እናያለን ጎበዝ ከሆን መቃረም ነው።

ጌታ በነገር ሁሉ መከናወንን ይስጣችሁ🙏!
https://www.facebook.com/biruk.tesfaye.3367?mibextid=ZbWKwL

https://www.tg-me.com/+P797aZHA38IxYzU0
ቦረና ዝናብ እንደጣለ ሰምታችኋላ 😍
+++‹አውጡ› እንጂ ‹ውጡ› አላለም+++

ሁሉ የሚቻለው፣ የሚሳነውም የሌለ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቃና መንደር በታደመበት ሰርግ ቤት ውኃውን በተወደደው በእናቱ ምልጃ ወደ ወይንነት ከለወጠ፣ ሐዋርያቱም ይህን ድንቅ ተአምር አይተው ካመኑበት በኋላ ከእናቱ እና ከወንድሞቹ ከደቀ መዛሙርቱም ጋር ወደ ቅፍርናሆም ወረደ፡፡ በዚያም ለአሥራ አንድ ቀናት ያህል ተቀመጡ፡፡ ወቅቱ የእስራኤላውያን ከግብጽ ባርነት መውጣት የሚታሰብበት የፋሲካ በዓል የደረሰበት በመሆኑ ብዙ ሰዎች ይህንን ታላቅ በዓል ለማክበር መቅደስ ወደ ታነጸባት ቅድስቲቱ ኢየሩሳሌም ይወጡ ነበር፡፡ አምላካችንም እርሱ እግዚአ በዓላት (የበዓላት ጌታ) ሆኖ ሳለ በዓልን ለማክበር በትሕትና ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ፡፡

ራሱ ባለቤቱ እግዚአብሔር በማይዋሽ ቃሉ "የተቀደሰ ጉባዔ ብላችሁ የምታውጁአቸው በዓላቶቼ የእግዚአብሔር በዓላት እነዚህ ናቸው" ሲል ለሙሴ እንደነገረው በዓላት የእግዚአብሔር ገንዘቦች ናቸው (ዘሌዋ 23፡2)፡፡ በበዓላት የሚከረው እግዚአብሔር እግዚአብሔር ሲሆን፣ የሚከናወነው ደግሞ አንዱ የአምላክ ፈቃድ በመሆኑ "ቀንን የሚያከብር ለጌታ ብሎ ያብራል" (ሮሜ 14፡6)፡፡ በዮሐንስ ወንጌል የተጠቀሰው የ‹ፋሲካ በዓል›ም የእግዚአብሔር ንብረት እንደሆነ ‹እርሱ የእግዚአብሔር ፋሲካ ነው› ተብሎ የተቀመጠው የኦሪት ጽሕፈት ምስክር ነው (ዘጸ 12፡11)፡፡ ታዲያ ቅዱስ ዮሐንስ ‹የአይሁድ ፋሲካ› በማለት አይሁድን የበዓሉ ባለቤት አድርጎ ለምን ጠራቸው ? የዚህ ምክንያት በወቅቱ የነበሩት አይሁድ በበዓለ ፋሲካ አምላካቸውን ከማክበር ይልቅ እነርሱ የሚከብሩበትን ተግባር በመፈጸም ተጠምደው ስለሚውሉ፣ እግዚአብሔር ከአዘዘው እና ከፈቃዱ ርቀው ስለሚያከብሩት በዓልነቱን ለእግዚአብሔር ሳይሆን ለአይሁድ ሰጥቶ ይናገራል፡፡ በርግጥም የእርሱ ገንዘብ በሆኑት በዓላቶቹ የገዛ ፈቃዳቸውን እየፈጸሙ ለሚያስቀይሙት አይሁድ እግዚአብሔር ‹መባችሁን በዓላቶቻችሁን ነፍሴ ጠልታለች፤ ሸክም ሆነውብኛል ልታገሳቸውም ደክሜያለሁ› ሲል በነቢዩ አድሮ ይገስጻቸዋል (ኢሳ 1፡14)፡፡

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተጠምቆ አገልግሎቱን ከጀመረ በኋላ እስከ ተሰቀለበት ጊዜ ድረስ አራት የፋሲካ በዓላት የተከበሩ ሲሆን ይህም በዓል የመጀመሪያው ፋሲካ ነው፡፡

መቅደሱን ላነጸ ሰሎሞን ‹በፊቴ የጸለይኸውን ጸሎትህንና ልመናህን ሰምቻለሁ፣ ለዘላለምም ስሜ በዚያ ያድር ዘንድ ይህን የሠራኸውን ቤት ቀድሻለሁ፣ ዓይኖቼና ልቤም በዘመኑ ሁሉ በዚያ ይሆናሉ› ብሎ ቃል የገባ እግዚአብሔር በዘመን መካከል በሥጋ በተገለጠበት ወራት የፋሲካን በዓል ለማክበር በመቅደሱ ተገኘ (1ኛ ነገ 9፡3)፡፡ በዓላትን ለማክበር የእግዚአብሔር መቅደሱ ወደ አለበት የማይገሰግሱ፣ ለጸሎትም ‹ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች› ወዳላት ቅዱስ ስፍራ መምጣት የማይፈልጉ ወገኖች በየትኛው በሐዋርያቱም ሆነ በጌታ ባልተሰበከ ወንጌል ስተው ይሆን ? ስለ ሕንጻ መቅደስ አስፈላጊነት ራሱ ጌታችን በመቅደስ መገኙትን አብነት ከማድረግ የተሻለ ከዚህ የሚበልጥ ምን ምስክር ሊጠቀስ ይችላል? ፡፡ የሰውነታችን ‹መቅደስ› መሰኘት ሕንጻ መቅደስን ያስቀረው ይመስል ‹እኛ ነን የእግዚአብሔር መቅደሶች!› ይሉናል፡፡ ነገር ግን መድኃኒታችን ሰውነቱን ‹መቅደስ› ያለው በሕንጻ ቤተ መቅደስ ውስጥ ተገኝቶ መሆኑን ይዘነጉታል፡፡

ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ጌታችን የፋሲካ በዓል ወደሚከበርበት መቅደስ በገባ ጊዜ በሕንጻ መቅደሱ ካሉት በአንደኛው ክፍል የተመለከተው ድርጊት ቅንዓትን የሚያጭር ነበር፡፡ የመንፈስ ብልጽግና በሚታደልባት ቅድስት ስፍራ ሥጋዊ ብዕልን ለማካበት የሚተራመሱ ብዙ ነጋድያን ሞልተዉባት ነበር፡፡ መቅደሱንም እንዲያገለግሉ የተሾሙ የኦሪት ካህናት ኃላፊነታቸውን ቸል በማለት ትርፍ በሚገኝበት ንግድ ራሳቸውን ጠምደው ነበር፡፡ የክፋት ሁሉ ሥር በሆነው በገንዘብ ፍቅር ልባቸው ስለታወረም ከሃይማኖት ተሳስተው በወቅቱ የነበሩት ብዙ እረኞች የወይን ቦታ የተባለ የእግዚአብሔርን መቅደስ አጥፍተውት ነበር (1ኛ ጢሞ 6፡10 ፣ኤር 12፡10)፡፡ ስለዚህም ‹የሌዊን ልጆች የሚያጠራ› የቤቱ ባለቤት እርሱ ቤቱን ሊያጸዳ ወደ መቅደስ ገባ (ሚል 3፡3)፡፡

እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት አምላካችን ‹አንጽሖተ ቤተ መቅደስ› ያደረገው ሁለት ጊዜ ነው፡፡ የመጀመሪያው አሁን እየተመለከትነው ባለነው ወንጌል እና ምዕራፍ ውስጥ የተጠቀሰው አገልግሎቱን በወጠነባት የመጀመሪያዪቱ ፋሲካ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ የስቅለቱ መቃራቢያና የሥራው መገባደጃ በሆነው በአራተኛው ፋሲካ ነው (ማቴ 21፡12 ፣ሉቃ 19፡45)፡፡ ይህ ምን ያስተምረናል? የእግዚአብሔር የሥራው መጀመሪያም ሆነ መጨረሻ ቤቱን ማጽዳት

መሆኑን ነው፡፡ ብዙዎች ራሳቸውን ‹ከባለቤቱ ያወቁ› ሲያደርጉ ‹እግዚአብሔርማ ቤቱን ማጽዳት ትቷል!› ይላሉ፡፡ ይህ ሐሳብ ግን መጠን ካለፈ ድፍረት እና የእግዚአብሔርን ሥራ ካለመረዳት የሚመጣ ጎጂነት ያለው ቁጭት ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያንን በሰላም የሚመራ አምላክ የሥራው መጀመሪያም ሆነ መጨረሻ የክብሩ ማረፊያ የሆነችውን ቤተ ክርስቲያንን መጠበቅና ማጽዳት ነው፡፡ ስለዚህ እንዲህ ላሉት ሰዎች እለወጥበታለሁ በማለት ቢሰሙን ‹አትታበዩ በኩራትም አትናገሩ እግዚአብሔር (ከእናንተ ይልቅ ለቤቱ) አዋቂ ነውና!!!› ብለን የምክርን ቃል እንለግሳቸዋለን፡፡

ጌታችን ከዚህ በፊት መቅደስ ውስጥ የንግድ ተግባር ይከናወን እንደ ነበር በመቅደስ ተገኝቶ አይቶ ይሆን? ብለን ብንጠይቅ አዎን! ነው መልሳችን፡፡ ጌታ የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅ በነበረ ጊዜ ከእናቱ ከእመቤታችንና ከዮሴፍ ጋር ፋሲካን ለማክበር እንደ በዓሉ ልማድ ወደ ኢየሩሳሌም ወደ መቅደሱ ወጥተው ነበር፡፡ በዓሉንም አክብረው ሲፈጽሙ እናቱ ድንግል እና ዮሴፍ ከመንገደኞች ጋር ይከተላቸው የነበረ ስለመሰላቸው ጥለውት የአንድ ቀን ያህል መንገድ ሄዱ፡፡ የዚያን ጊዜ ብላቴናው መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን በአይሁድ መምህራን መካከል ተቀምጦ ሲሰማቸውና ሲጠይቅ ሦስት ቀን ያህል በመቅደስ ከርሞ ነበር (ሉቃ 2፡46)፡፡ ስለዚህ የለመደባቸውን ንግድ በመቅደሱ ሲያደርጉ ጌታ በአሥራ ሁለት ዓመቱ ወደ መቅደስ በወጣ ጊዜ እንደ ተመለከተ እናስተውላለን፡፡ ነገር ግን በዚያን ወቅት ጅራፍ አንሥቶ አልገሰጻቸውም ነበር፡፡ ይኸውም አንደኛ ለእግዚአብሔር የሥራ ጊዜ እንዳለው የሚያመለክት ሲሆን ሌላው ደግሞ በወቅቱ የአሥራ ሁለት ዓመት ብላቴና በመሆኑ አይሁድ ላይ የአደባባይ ግሳጼን ቢያነሣ ‹ልጅነት ነው እንዲህ የሚያስደርገው› ሲሉ ባልተቀበሉት ነበር፡፡ ስለዚህ ጌታችን የአሥራ ሁለት ዓመት ብላቴና ሳለ በመቅደስ ያገኛቸውን መምህራን ጠየቀ እንጂ ጅራፍ አላነሣም፡፡ ምን ብሎ ጠይቋቸው ይሆን ? ‹በእግዚአብሔር ቤት ለትርፍ መነገድ ይገባልን? በሕግስ ስለ መቅደስ ክብር ተጻፈው ምንድር ነው ? እንዴትስ ታነቡታላችሁ ?› ብሎ ጠይቋቸው ይሆን?
ለአገልግሎት ሙሉ ሰው በሚሰኝበት በሠላሳ ዘመኑ ግን አምላካችን በመቅደሱ በተገኘ ጊዜ እንደ ልጅነቱ ጥያቄን አልጠየቀም፡፡ ወደ ለሊቀ ካህናቱ ገብቶ ለውጥ የማያመጣ አቤቱታን አላቀረበም (ዘኁል 4፡23)፡፡ ቸል ሲሉ የሚሳሳቱ እንደሆኑ የልባቸውን ክፋት ያውቃልና ጅራፍን ገምዶ በሬና በጎቻቸውን እየገረፈ ከመቅደስ እንዲያወጡ አደረጋቸው፡፡ ጅራፍ የሚችሉትን በሬዎችና በጎች ሲገርፍ ጅራፉን የማይቋቋሙ ርግቦችን ግን ከዚህ አንሡ ማለቱ እግዚአብሔር ሁሉን በአቅሙ የሚቀጣ እና ልንቋቋመው ከምንችለው በላይ የሆነን መከራ በሰውነታችን የማያመጣ ርኅሩኅ የሆነ አምላክ መሆኑን ያሳያል፡፡ በዚያውም ላይ ‹የፋሲካ በግ› ከተባለው ከእውነተኛው መሥዋዕት ከእርሱ መምጣት በኋላ በሬ እና በግ የእንስሳትስ መሥዋዕት በመቅደስ ምን ያደርጋሉ ? የሐዲስ ኪዳኑ መሥዋዕት እርሱ መሆኑን በምሥጢር ሲያመለክት የኦሪት መሥዋዕቶች ከመቅደሱ እንዲወጡ አደረገ፡፡

ኃጢአትን የሚጸየፍ የኃጢአተኛውን ሞት ግን የማይፈልግ አምላካችን በመቅደስ ይነግዱ የነበሩትን ሰዎች የሚነግዱትን ንብረት ከመቅደሱ እንዲያወጡ ነው እንጂ፣ እነርሱ ራሳቸው ከመቅደሱ እንዲወጡ አላደረገም፡፡ ‹አውጡ› እንጂ ‹ውጡ!› አላላቸውም፡፡ በእውነት ኃጢአተኞች ከእግዚአብሔር ጋር በንስሓ እርቅን ከሚያገኙባት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ወዴት ይሄዳሉ ? የአምላካቸውንስ ፊት ከሚያዩበት አጸድ ወዴት ይሸሻሉ? ስለዚህ ሰው ወዳጅ የሆነ ጌታችን ክፉ ሥራችሁን ተዉ ‹አውጡ› አላቸው እንጂ ከቤተ ክርስቲያን እንዲወጡ አላዘዛቸውም፡፡ በመሆኑም የአካሉ የቤተ ክርስቲያንም መመሪያ ‹አውጡ› የሚለው ይህ የፈጣሪያችን ቃል ነው፡፡ በኃጢአት በክህደት ውስጥ ላሉ ሁሉ ‹ኃጢአት ፣ክህደታችሁን አውጡ› ትላለች እንጂ ውጡ ብላ ለሞት ለጨለማ አሳልፋ አትሰጣቸውም፡፡ ይሁን እንጂ አንዳንድ ጊዜ ሰው ከኃጢአት ጋር ፍጹም ሲተባበር፣ ከሐዲም ክሕደቱ በእርሱ ላይ ሥግው እስኪሆንበት ድረስ እርስ በእርሳቸው ሲጣመሩ፣ ያን ጊዜ ከሐዲውን ከክሕደቱ፣ በደለኛውንም ከበደሉ ለይቶ ማየት ስለሚያስቸግር አበረው ሊቆረጡ ይችሉ ይሆናል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ግን በኃጢአት ሸክም የጎበጡትን ሁሉ ለማሳረፍ እጆቿን ዘርግታ መዳንን ሲወዱ ወደ እርሷ የሚመጡትን ሁሉ የምትቀበል ናት እንጂ፣ እርሷን አንባ የሚያደርግ ኃጢአተኛን የምትገፋ አልፈልግሽም ብሎ የሚያምጽባትንም በኃይል ተጭና የምታስገድድ አይደለችም።

ይቆየን!

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
[email protected]
አዲስ አበባ

ድረ ገጹን ይጎብኙ
https://dnabel.com

ቴሌግራም
https://www.tg-me.com/Dnabel

(በድጋሚ የተለጠፈ)
Forwarded from RHOBOTH Online shopping
               †               

በሕገወጥ መንገድ የተሾሙት ግለሰቦች በምእራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ስም ሹመትና ዝውውር እያደረጉ እንደሆነ ተገለጸ፡፡

የካቲት 27 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

በሕገወጥ መንገድ የተሾሙት ግለሰቦች በመንግሥት ድጋፍ በምእራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በአሉ አብያተ ክርስቲያናት ዝርፊያ መፈጸሙን መዘገባችን ይታወሳል ለዚህም ምንም አይነት እርምጃ በአለመወሰዱ ምክንያት አሁን ላይ ካህናትን በማፈናቀል እና የወረዳ ቤተ ክህነት የሥራ መደቦቸን የሀገር ስብከቱን ማሕተም በመጠቀም ሹመትና ዝውውር በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በዚህም የተነሳ የምእራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ በማለት በሚጠራው የሕገ ወጡ ቡድን አባል በሆነ ቄስ ታዳሳ ደሪቤ በተጻፈ ደብዳቤ የደብረ ንጉሥ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን የስብከተ ወንጌል ኃላፊና ሒሳብ ሹም የነበሩትን ቄስ ሀሰቤ ታዳሳ በጡሎ እና ዶባ ቤተ ክህነት ወረዳዎች ተዛውረው በሥራ አስኪያጅነት እንዲሠሩ መሾሙን የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት ዘግቧል።

[ TMC ]

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬

Share ያድርጉት @ORTODOX_MERJA
ድሃው ሜንጤ እና ፓስተሮቻቸው ያሉበት ሁኔታ
በሀጂ ኢብርሒም ቱፋ የሚመራው የፌዴራል የእስልምና መጅሊስ ለህገወጡ ቡድን ይፋዊ የሆነ ውግንና እና ድጋፍ በመስጠት ላይ ይገኛል
***

እንግዲህ ለከፋ መከራ መዘጋጀት አይከፋም። ነገሮች በሙሉ ወደ ከባድ ሀዲድ ውስጥ እየገቡ ነው።

ህገወጡ ቡድን ከተሸክመው አስኬማ በቀር ነገረ ሥራው ሁሉ የአጽራራተ ቤተክርስቲያን ኃይላት እንደሆነ እየተገለጠ ነው።

በኦሮሚያ ልዩ ኃይል ይታጀባል፣ ከፕሮ**ታንት ቤተ እምነት ፓስተሮች የገንዘብ ድጋፍ ያገኛሉ፣ ከእስልምና ምክር ቤት አይዞህ ባይነት ቡራኬ ይቀበላሉ። የሃይማኖት ፎረም በሚባል ግዑዝ መዋቅር ቅስቀሳ እና ብርታት ያገኛሉ!

አሁንም ለበለጠ መከራ እራሳችንን እናዘጋጅ።

Kune Demelash kassaye -Arba Minch
ይሄን የማዘል እና መተዛዘል አምልኮ ሳይ ትርጓሜ ዘፍጥረት ላይ ያለው የእባብ እና የከይሲ ጨዋታ ትዝ አለኝ።

በእርግጥ ይሄ ፎቶ በዘመኑ የወንጌሉ አገልጋዮች ነን የሚሉ ሰዎች እና ያገለግሉኛል ብሎ የሚቀልባቸውን ድሃ አማኝ የኑሮ ሁኔታም በጥሩ መልኩ ያብራራል ። ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ የሆነውን
#ኢየሱስንም_ክርስቶስን ንጉሱ ያደረገ አማኝ ወደ ቤተ እግዚአብሔር ሲመጣ ሸክሙን ይጥል እና ያስወግድ ዘንድ እንጂ ተጨማሪ የስጋም የነፍስም እንዲሁም የመንፈስን ሸክም በእራሱ ላይ ለመጨመር አይደለም ። ለዛም ነው በወንጌለ ማቴዎስ 11
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁸
#እናንተ_ደካሞች_ሸክማችሁ_የከበደ_ሁሉ፥ ወደ #እኔ ኑ፥ #እኔም_አሳርፋችኋለሁ
²⁹ ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤
³⁰ ቀንበሬ ልዝብ
#ሸክሜም ቀሊል ነውና። ይላል

ስለዚህ በእግዚአብሔር ቤት እረፍት እንጂ ሸክም የለም እንኳንስ ሸክም ሊኖር የተሸከምነውን የስጋ እና የነፍስ ሸክማ አስወግደን በብርሃኑ እንመላለሳለን እንጂ .... ።

@nubeberhanuenmelales
"ቁጡ ሰው ከመኾን ገር ሰው ወደ መኾን ከተለወጥህ፣ ጨካኝ ሰው ከመኾን ቸር ሰው ወደ መኾን ከተቀየርህ [በተግባር] አሳየኝ እንጂ 'ለአያሌ ቀናት ጾምሁ፤ ይህን ወይም ያን አልበላሁም፤ ወይን አልቀመስሁም፤ መሻቴን ገትቻለሁ' እያልህ አትንገረኝ፡፡ [እስከ አሁን] ቁጣን የተሞላህ ከኾነ ለምን ሥጋህን ታስጨንቃለህ?  ቂምና በቀል በልቡናህ ውስጥ ካሉ፥ [ወይንን ሳይኾን] ውኃ የምትጠጣው ለምንድን ነው?  ረብ ጥቅም የሌለውን ጾም አትጹም፤ ጾም ብቻዋን ወደ ላይ አታርግምና፡፡"

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
የልቤን ጥልቀት መርምሮ ከሚያውቀው ከእርሱ በቀር ማንም ከህመሜ ሊፈውሰኝ ሚችል የለም። ስንት ጊዜ እራሴን ከኃጢያት የሚለይ ድንበርን አበጀሁ፥ ስንት ጊዜስ ከኃጢያት ለመጠበቅ ግንብን ገነባሁ! ሀሳቤ ግን ወደክፋት መንደር ጥሶ ገባ፥ ፈቃዴም ያቆምሁት ግንብ ሳይዘው፤ ያሰመርኩትም ድንበር ሳያቆመው በኃጢያት መንደር አደረ። ያሰመርኩት ወሰን ፈሪሃ እግዚአብሔርን ስላልያዘ፤ ያቆምኩት ግንብም ከልብ በሆነ ንስሐ እና ጸጸት ስላልተመሰረተ ሀሳቤን ከመባከን አልያዘውም።

ደግሞም ነፍሴ መለስ ስትልልኝ፥ ቆም ብዬ አስብና በርህን አንኳኳለሁ፤ ልቤ ያሻውን እስክትሰጠኝ ሳላቆም እጠይቅኻለው፤ ቸርነትህን ያለማፈር እጠይቃለሁ። ከፍ ባለ ድምጽም ወዳንተ እንዲህ እያልኩ ጮኻለው:

“አቤቱ ጌታዬ እና መድኃኒቴ ስለምን ተውኸኝ? ቸር ሰው ወዳጅ ሆይ ቸርነትን አድርግልኝ። በደል ፈጽሞ የሌለብህ ሆይ እባክህ አድነኝ!
ጎድፌ እንዳልቀር ከኃጢያቴ ረግረግ መንጥቀህ አውጣኝ። እንደ አንበሳ ከሚያጋሳው ሊውጠኝም ከሚሻው ከጠላቴ መንጋጋ አድነኝ።

አቤቱ ኃይልህን ይዘህ ተነስ፥ ወደኔም ታድነኝ ዘንድ ና! ጠላቴ ፈርቶ ከፊትህ ይሸሽ ዘንድ አቤቱ የክብርህን መብረቅ አንጎድጉደው፥ በኔም ላይ ያለውን የእርሱን ኃይል በትን! በአንተ እና አንተን በሚወዱ ፊት የመቆም ብርታት የለውምና፥ የጸጋህን በዚህ መኖር ባወቀ ጊዜ ፍርሃት ይይዘዋል፥ እያፈረም ወደ ጉድጓዱ ይሸሻል። አቤቱ ወዳንተ ምሸሽ እኔን አድነኝ፥ ጌታዬ አምላኬም ሆይ አንተን መሸሸጊያዬ አርጌያለሁና በእቅፋትህ አኑረኝ።”

[_ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ_]
› ~ #የማርች_8_ጥያቄዎቼ  ~ ‹
1.
#ሴቶች_በአስተሳሰብ_ከወንድ_ያነሱና_የአዕምሮ ጉድለት ያለባቸው ናቸውን ⁉️
1.1) ሱራ 2:282:- « ከወንዶቻችሁ ሁለትን ምስክሮች አስመስክሩ! ሁለትም ወንዶች ባይሆኑ አንዱ ወንድና አንደኛዋ ስትረሳ አንደኛዋ እንደኛይቱ ሌላዋን
#ታስታውሳት ዘንድ 2 ሴቶች ይመስክሩ »

1.2) ሷሒሕ ቡኻሪ 2658:- «አቡ ስዒድ አልኹድሪ ዘግበውታል; ነቢዩ እንዲህ አለ "የአንዲት ሴት ምስክርነት የወንድ ግማሽ አይደለምን? ሴቶቹም "አዎን" አሉ! እርሱም "ይህም በሴቶች
#አዕምሮ #ጎዶሎነት ምክንያት ነው -- Narrated abu sied alkudri; < the Prophet said "isn't the wittnes of a women equal to half of that of a man?" the women said "yes" he said "this is because of the #deficiency of a womens #mind">

1.3) ሷሒሕ ሙስሊም 142:- «የአላህ መልክተኛም ሴቶቹን "ከናንተ ውጭ በአስተሳሰብም በሃይማኖትም የደከመ አላየሁም" አላቸው! ሴቶቹም "የአስተሳሰባችንና የሃይማኖታችን ድክመት ምንድነው?" ብለው ጠየቁ! ነቢዩም በማስተዋል እንዲህ አሉ "የአስተሳሰባችሁ ድክመት የሚታወቀው የ2 ሴቶች ምስክርነት ከ 1 ወንድ ምስክርነት ጋር እኩል መሆኑ ነው ይህም
#የአዕምሮአችሁን_ድክመት ያሳያል»

1.4) ሷሒሕ ቡኻሪ መጽ6 ሐዲስ 301:-
«የአላህ መልክተኛ እንዲህ አሉ "አብዛኞቹ ወደ
#ሲኦል_የሚገቡት እናንተ ሴቶች ናቸሁ":: እነርሱም "ለምን" ብለው ጠየቁት! እርሱም ለባሎቻችሁ መልካም ስላልሆናችሁና ብዙ ስለምትራገሙ ነው! ከናንተም በላይ በሃይማኖትም በአስተሳሰብም ጎዶሎ የሆነ አይቼ አላውቅም አሏቸው! ሴቶቹም እንዲህ አሉ "በአስተሳሰብም በሃይማኖትም የደከምነው እንዴት ነው? እሳቸውም "የ 2 ሴቶች ምስክርነት ከአንድ ወንድ ምስክርነት እኩል አይደለምን? ሴት በወር አበባዋ ጊዜ መጾምም መጸለይም እንደማትችል እውነት አይደለምን? እነርሱም አዎ አሉ! እርሳቸው: "በሃይማኖትና #በአዕምሮ_ደካማ መሆናችሁም ይሄው ነው" -- the prophet said to the women "I have not seen anyone more #deficient in intellegence and religion than you »

1.5) ተፍሲር ኢብኑ ከቲር 4:34 ገጽ 50
« በዚህ ዓንቀጽ (ሱራ 4:3) ላይ ወንድ የሴት አለቃ እንደሆነና ስሕተት ብትሰራም
#የሚቀጣት_ወንድ መሆኑን አላህ ይናገራል! "አላህ ከፊላቸውን በከፊሉ በማብለጡ ነው" ይሄም የሆነበት ምክንያት ወንዶች ከሴቶች ስለሚበልጡ ወንድም ከሴት ስለሚበልጥ ነው! ስለዚህ ነቢይነትና ንግስነት ለወንዶች ተሰጠ! #ነቢዩ መሐመድም እንዳሉት "ሴትን ልጅ #መሪያቸው አድርገው የሚመርጡ ሕዝቦች #አያሸንፉም - Therefore, prophethood and great kingship were confined to men, as the Prophet said, "A people that choose a woman as their leader will not succeed»

2.
#ሚስቶች_ለባሎቻቸው_እርሻዎችና_የወሲብ ዕቃዎች ናቸውን ⁉️
2.1) ሱራ 2:223:- "ሴቶቻችሁ ለናንተ
#እርሻ ናቸው! እርሻችሁንም በፈለጋችሁት ሁኔታ ድረሱ"

2.2) ሷሒሕ ቡኻሪ መጽ54 ሐዲስ 460:-
«አቡ ሁረይራ ዘግበውታል "የአላህ መልክተኛ እንዲህ አሉ:- ባል ሚስቱን ወደ አልጋ ቢጠራት (ግብረ ስጋ ይፈጽሙ ዘንድ) እርሷም
#እምቢ ብትል በቁጣም ብትናገረው መላኢካ ሌሊቱን ሙሉ እስከ ጠዋቱ ድረስ #ይረግሟታል»
©Binyam ZeChristos የካቲት 29
2024/10/01 19:18:10
Back to Top
HTML Embed Code: