Telegram Web Link
ትላንት በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በተከሰተው ጉዳይ ቤተክርስቲያን መግለጫ ሰጠች

በኢ/ኦ/ተ/ ቤ/ ክ/ የአ/አ ሀገረ ሰብከት በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች አማካኝነት ተፈጽሟል ባለው ሕገ ወጥ ድርጊትን አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።

የቅ/ጊዮርጊስ ክብረ በዓል ለማክበር ህዝቡ ከየቤቱ ተሰባስቦ ከጠዋቱ 3:15 ላይ በሰሜን በኩል ከመንግሥት የጸጥታ አካላት 2 ጊዜ በተተኮሰ አስለቃሽ ጭስና በቅጥሩ በተፈጠረው ረብሻ እስከአሁን ባለው መረጃ የ1 ምዕመን "በአስለቃሽ ጭስ ታፍነው" ህይወታቸው ማለፉን ገልጿል።

በተጨማሪም አገልጋይ ካህናት፣ ምእመናንና ምእመናት ከፍተኛ የሆነ አካላዊ እና ሥነ ልቡናዊ ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ ከ15 ያላነሱ የሰንበት ትምህርት ቤት አገልጋይ ተማሪዎች በደረሰባቸው ጉዳት ምክንያት ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸው ተጠቅሷል፡፡ 

የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ቢሮ በዓሉን አስመልክቶ በዕለቱ ያወጣውን መግለጫም ከነበረው እውነታ በእጅጉ የራቀ በሚል የተገለጸ ሲሆን መንግሥት ችግሩን ለማረምና መፍታት ፍላጎት የሌለው መሆኑን ያመለከተ ነውም ብለዋል።

መንግሥት የቤ/ክርስቲያንን ክብርና ልዕልና በሚዳፈር መልኩ በተፈጸመው ሕገ ወጥ ተግባር ላይ የተሳተፉና ይህን ድርጊት የፈጸሙና ያስፈጸሙ፤ እንዲፈፀም ያዘዙ የመንግሥት ኃላፊዎችን በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ለይቶ በሕግ እንዲጠየቁ እንዲያደርግ" ተጠይቋል።

በተለመደው የሀሰት ውንጀላ በዓላችንን በማክበር ላይ እያሉ የመንግሥት የፀጥታ አካላት በፈፀሙት ሕገ ወጥ ተግባር ምክንያት በተፈጠረው ግርግር መነሻት የታሰሩ ምእመናንን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ፤ ይህ የማይሆን ከሆነ ቤ/ክርስቲያን መብቷን ለማስከበር ወደ ቀጣይ እርምጃዎች የምትገባ ገልጻለች።

ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፬ኛው
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
፩ኛ ዓመት መታሰቢያ  በመንበረ ጸባዖት ቅድስት
ሥላሴ ካቴድራል ተከናወነ።
******
የካቲት ፳፭ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም
""""""""""""""""""""""""""""
አዲስአበባ -ኢትዮ
******

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ፬ኛ ዓመታ መታሰቢያ በመንበረ ጸባዖት ቅድስ ስላሴ ካቴድራል ብፁዕአን ሊቃነ ጳጳሳት የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የሥራ ኃላፊዎች፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎች ሊቃውተ ቤተክርስቲያን ወዳጆቻቸው እና የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው በተገኙበት  በድምቀት ተከብሯል።

ቅዱስ አባታችን የካቲት ፳፭ ቀን ፳፻ ፲ወ፬ዓ.ም ነው ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉት ቅዱስነታቸው በአገር ውስጥና በስደት ቆይታቸው ቅድስት ቤተክርስቲያንን ማዕከል ያደረጉ በርካታ ሥራዎችን ያከናወኑ፣በንጽሕናና በቅድስና የኖሩ ወደ አገራቸው ከተመለሱ በኋላም በአርምሞና በጸሎት ቅድስት ቤተክርስቲያናችንንና አገራችንን የጠበቁ ታላቅ አባት ነበሩ።

++++
2024/10/01 22:31:29
Back to Top
HTML Embed Code: