#ስለ_ወንድማችን_አክሊል_አንዳንድ_ነገሮች!
#ወንድማችን_አክሊል_ጌታችን_ካረገ_በኋላ_አብን_ያመልካል_አላልኩም_የሚል_መልእክት_ስለላከልኝ_ዋናው_ጉዳይ_መስተካከሉ_ስለ_ኾነ_አንሥቼዋለሁኝ🙏
በመጀመሪያ አክሊልን ያወኩት በቲክቶክ ሲያስተምርና ለመ*ና*ፍ*ቃን መልስ ሲሰጥ ነው። በዚህ ረገድ በጣም የሚበረታታ ሥራን ሠርቷል፤ እየሠራም ይገኛል። በሚያቀርባቸው የሃይማኖት ትምህርቶች በቲክቶክ የሚከታተሉትን በውጭም በሀገር ውስጥም ያሉ ብዙ ምእመናንን አጽንቷል፤ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እንዲረዱ ረድቷቸዋል። ይህም ብቻ ሳይኾን በኑ*ፋ*ቄ እሳት የነደዱትን መ*ና*ፍ*ቃንንም ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲመለሱ የበኩሉን አስተዋጽዖ አበርክቷል፤ አሁንም እያበረከተ ይገኛል። ይህን አገልግሎቱን የተረዳ ሰው ይጸልይለታል፤ እግዚአብሔር ከክፉ እንዲጠብቀው ያስበዋል።
እንደሚታወቀው አንድ ሰው አንድ መልካም ሥራ ሊሠራ ሲነሣ ብዙ ፈተናዎች ሊገጥሙት እንደሚችል ግልጽ ነው። ይህ ፈተና በመጀመሪያ ከራስ የሚመነጭ ነው። ይኸውም ስለ ራስ ያለ ቦታና ደረጃ ለወጥ እያለ የመሄድ ፈተና ቀዳሚው ነው። ይህ በእንዲህ ዓይነት ትጉህ አገልግሎት ላይ ባሉ ኹሉም ላይ ማለት እስኪቻል ድረስ የሚመጣ ፈተና ነው። ይህን ፈተና ተፈታኞቹ አንዳንዴ ላይረዱት ኹሉ ይችላሉ፤ አደገኛ የሚያደርገው ደግሞ ይህ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ በምናቀርበው ነገር የተደሰቱ አካላት የሚያቀርቡልን ገነን ያለ ምስጋናና አክብሮት ሌላው የሕይወት ፈተና ይኾናል። ከእነዚህ ጋር ተያይዞ ደግሞ የበጎ ነገር ኹሉ ጠላት የኾነ ሰይጣን የሚያመጣብን ሰወር ያለ ወይም ግልጽ የኾነ ፈተና ይኖራል። ይህን መረዳት ተገቢ ነው። እንግዲህ ይህን በአጭሩም ቢኾንም ከግምት ውስጥ በማስገባት በአገልግሎት ላይ ላሉ ወንድሞቻችን ልንጸልይና ከእኛ እንደ ክርስቲያን የሚጠበቅብንን ልናደርግ ይገባል።
ኹለተኛው ነጥቤ - የወንድሜን አኬን አካሄድ ማዕከል ያደረገ ይኾናል። ይኸውም በአንድ በኩል አንድን ነገር ለማስረዳት የሚገልጽበት መንገድ ጸነን ማለት ሲኾን በሌላ በኩል ተደጋጋሚ ጊዜ ያቀረባቸውን የስሕተት ትምህርቶችን የሚመለከት ነው። እኔ ከእርሱ ጋር በአካል በተደጋጋሚ ጊዜ ባወራን ጊዜ ያገኘኹትና እንደ ወንድም ደጋግሜ መክሬው ግን እስካሁን አቋም አድርጎ የያዛቸው የስሕተት ትምህርቶችን በቅደም ተከተል ላስቀምጥ፦
1) ነገረ ክርስቶስን በተመለከተ ያቀረበው ስሕተት ነው።
ይኸውም ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋው ወራት አብን አምልኳል የሚለው ነው። ይህን በተመለከተ እጅግ ስላስደነገጠኝ በጣም ለምኜዋለሁኝ። እባክህን ይህ ክሕደት ነው ተስተካከል ብዬዋለሁኝ በጓደኞቹ ፊት በጉዳዩ የምችለውን ኹሉ ለማለት ሞክሬያለሁኝ። እርሱ ግን ሚዲያ ላይ ከእንግዲህ ወዲህ አላነሣውም ቢኾንም ግን አቋሜ ነው ብሎኝ ነበር። ለዚህ ስሕተት መነሻ ያደረገውም ዮሐ 4፥21-22 ላይ ቅዱስ ቄርሎስ ያብራራውን እና አምብሮስ ዘሚላን ያለውን ነበር። በአቅሜ ለማስረዳት ሞክሬ ነበር። ያልኩትን አሁን አሻሽሎት ከኾነ ተመስገን ነው የምለው። ካልሆነ ግን በፍቅርና ክርስቲያናዊ በኾነ መንገድ እንዲያስተካክል ተማኅጽኖዬን በትሕትና በአደባባይ አቀርባለሁኝ።
2) ለኢየሱስ ክርስቶስ ከተዋሕዶ በኋላ አብ አምላኩ ነው የሚል አንዲት አጠር ያለች ቪዲዮ ሠርቶ ያ ቪዲዮ በብዙዎች ዘንድ ውዝግብን ፈጥሮ እንደ ነበር አስተውሳለኹኝ። ሙስሊሞችም አኬ ማለት ባልፈለገው መንገድ አጣመው ሲያራግቡት ነበር። ወንድማዊ በኾነ መንገድ በተደጋጋሚ ይህንም ጉዳይ በተመለከተ አውርተናል። ቪዲዮውንም እንዲያጠፋ ጽኑ ልመናዬን ከተግሣጽ ጋር በአካል አቅርቤለታለሁኝ። ኋላ ሌሎች መምህራንም ኾነን ተሰብስበን መክረነው ያን ቪዲዮ እንዳጠፋ ነግሮኝ ነበር። አቋሙ ግን እንደ ጸና ቀጥሏል። አብ ለኢየሱስ ከተዋሕዶ በኋላም አምላኩ ነው ማለት ምን ማለት ነው? ሥግው ቃል አንድ ከኾነና ሥጋን በመዋሐዱ ምክንያት ሥግው ቃል ፍጡር ነው የማይባል ከኾነ እንዴት ለሥግው ቃል አብ አምላኩ ሊባል ይችላል? በመጻሕፍት አምላኩ የተባለውን በጥንቃቄ ኾነን ቃል የተዋሐደው ሥጋ ፍጡር መኾኑንና ከተዋሕዶም በኋላ ያ ሥጋ አለመለወጡን ለማስረዳት መኾኑን እንገልጻለን እንጂ ከተዋሕዶ በኋላ ቃል የተለየው ዕሩቀ መለኮት የኾነ ሥጋ እንዳለ አድርገን አናምንም።
ወንድሜ አክሊል ግን "ቃል የተዋሐደው ሥጋ ስላልተለወጠ አሁንም ያንሳል" ብሎ እንደሚያምን ነግሮኝ ነበር። አምላኬም ያለው በሥጋው ነው፤ ሥጋው ያንሣልና ብሎኝ ነበር። ይህ ደግሞ ምንታዌ ነው። ሥጋ ምንም እንኳን ፍጡርነቱን ባይለቅም ከተዋሕዶ በኋላ ከቃል ስለማይለይ ያንሣል አይባልም። ያንሣል የሚለውን ስሑት ትምህርት አባቶቻችን አውግዘዋል። አባ ጊዮርጊስ በመጽሐፈ ምሥጢር፤ ሊቃውንት በመዝገበ ሃይማኖት ይህ ትምህርት የልዮናውያን እንደ ኾነና በኛ ዘንድ ተቀባይነት እንደ ሌለው አንሥተዋል። ሥጋው ያንሣል ማለት በአንድ በኩል ከመለኮቱ ተለይቷል የሚያሰኝ ሲኾን በሌላ በኩል ያመልካል እንጂ አይመለክም የሚያሰኝ ነው። ይህ ደግሞ ተቀባይነት የለውም። በቀጥታ ምንታዌን የሚያስረዳ ነውና ይልቅስ በአበው ትምህርት ያለው ሥጋ ያለመለያየት በተዋሕዶ ከቃል ጋር አንድ ስለ ኾነ ይመለካል የሚል ነው።
3) ከመ*ና*ፍ*ቃን ጋር ሲወያይ "ለሥግው ቃል አንድ ፈቃድ እንዳለው ነገር ግን የሥጋ ፈቃድ ለመለኮት ፈቃድ ለዘላለም ሲገዛ እንደሚኖር" በተደጋጋሚ ጊዜ አንሥቶ ስምቼዋለሁኝ። ይህም የምሥራቅ ኦርቶዶክሶች ትምህርት ነው። እነርሱ ኹለት ፈቃድ አለ፤ አንዱ ገዥ (የመለኮት ፈቃድ) ሌላኛው ተገዥ (የትስብእት ፈቃድ) ብለው ያምናሉ። መነሻቸው የባሕርይ ተዋሕዶ ስለሌለ ከኹለት ባሕርይ ኹለት ፈቃድና ኹለት ግብር ይመነጫል የሚል አቋም ስላላቸው እንዲያ ብለው ያምናሉ። እኛ ግን ከኹለት ፈቃድ የተገኘ አንድ ፈቃድ ብለን ስለምናምን በሥግው ቃል ውስጥ የምንከፋፍለው ፈቃድ የለም። ፈቃዱ ከኹለት የተገኘ አንድ ነው። ይሄ የመለኮት ይህ ደግሞ የትስብእት ተብሎ ተለያይቶ ፈጽሞ አይነገርም። ይህን አድማሱ ጀንበሬና በመድሎተ አሚን፤ አለቃ አያሌው መች ተለመደና ከተኩላ ዝምድና በሚል መጽሐፋቸው አንሥተውታል። አንዳንድ ቅዱሳን ሊቃውንት በጥንቃቄ የሥጋ ፈቃድ እንዳልጠፋ ለማስረዳት ያነሡት እንጂ እንደ ኬልቄዶናውያን ከፋፍሎ አንዱ ገዥ ሌላው ተገዥ በሚያሰኝ መንገድ እንድንረዳ ለማድረግ ፈጽሞ አይደለም።
4) "ቃል የተዋሐደው የጎሠቆለ ሰውነትን ነው" ብሎ አውርተንበት ነበር። ይህን የሚመስል አገላለጽ ያቀረቡ ሊቃውንትን ሐሳብ እንዴት መረዳት እንዳለብን አስረድቼው በጊዜው ከዲያቆን ብርሃኑ አድማስም ጋር እንዲያወሩ አድርጌ መ/ር ብርሃኑ በዚህ እና በእመቤታችን ጉዳይ (የጎሠቆለ ሰውነትን ለብሳለች አልለበሰችም በሚለው) ጽሑፍ ጽፎ በቴሌግራም ልኮለት ነበር። እኔም ከመ/ር ብርሃኑ አስቀድሜ ተው አክሊል አካሄድህ ጥሩ አይደለም ብዬ ረዘም ያለ የማብራሪያ ጽሑፍ ከዓመት ከስድስት ወር በፊት ልኬለት ነበር፤ በተጨማሪ መምህር ግርማ ባቱን ጉዳዩን ነግሬያቸው ተገናኝተው እንዲነጋገሩ አሳስቤ የላኩለትንም ጽሑፍ ለመምህር ግርማ አያይዤ ልኬ አሳይቼው ነበር። ወንድሜ አክሊል ግን እስካሁን ከአቋሙ አልተንቀሳቀሰም።

👍2
ሌላውን ለጊዜው እንተውና እንዲህ ዓይነት መሠረታዊ ትምህርቶች ላይ ስሕተት ተፈጥሯል። እነዚህን ስሕተቶች ቢያርም መልካም ነው። እግዚአብሔር ወንድማችንን ከክፉ ነገር ኹሉ ይጠብቅልን። እንዲህ ዓይነት ስሕተቶችንም እንዲያርም እግዚአብሔር ኃይሉን ያድልልን። ምናልባትም አሁን ላይ እነዚህን ስሕተቶቹን አርሟቸውም ሊኾን ይችላል። ከኾነም እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነው። እንዲህ አላልኩም ቢል እንኳን ደስታዬ ወደር የለውም። ዋናው ጉዳይ መስተካከሉ ነውና። አኹንም አቋም ኾኖ የተያዘ ከኾነ ግን ትልቅ ችግር ነው። ወንድም እኅቶቻችን ሆይ በአገልግሎት ተሠማርተን ላለነው ለኹላችንም ከወደዳችሁን ከልብ ጸልዩልን፤ ክፉ ሰይጣን ቀስ አድርጎ እንዳይጥለንና እንዳያጠፋን የእውነት የኾነ ልባዊ ጸሎት ያስፈልገናልና። ፍቅራችሁን እኛን ሊያድንና ሊጠቅመን በሚችል መንገድ ግለጹ እንጂ ሊጎዳን በሚችል መንገድ አታድርጉት።
ቸር ሰንብቱ!
Yohannes Getachew
ቸር ሰንብቱ!
Yohannes Getachew
በአርሹ ላይ የእስልምናው ነብያት ከእስራኤል ነቢያት ጋር ስለመመሳሰላቸው እንድንማማር መጥቻለሁ ።
አቅሙ እውቀቱ እና በጀቱ ያላችሁ ሙስሊሞች እንድትመጡ ይበረታታል ።

አኃት አብያተ ክርስቲያናት የአንድነት አገልግሎት ፈጸሙ !
የካቲት 11 ቀን 2017 ዓ.ም(ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ጨምሮ ስድስቱ ኦሬንታል አኃት አብያተ ክርስቲያናት በአንድነት በአንድ መቅደስ ሥርዓተ ቅዳሴ አከናውነዋል::
የካቲት 8 ቀን 2017( Feb.15/2025) በፔንስልቫኒያ ግዛት ፊላደልፊያ ከተማ ደብረ ገነት ቅዱስ አማኑኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የተፈጸመው ይህ የአንድነት አገልግሎት ቅዳሴን ጨምሮ መዝሙር ትምህርትና ሃይማኖታዊ መልእክቶች የተላለፈበት ነበር ::
የዘንሮው የአንድነት አገልግሎቱ አዘጋጅ የሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በመሆኗ የቅዳሴው አገልግሎት በዋናነት የተመራው በቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ( ዶ/ር) ነበር ::
በአገልግሎቱ ላይ የግብፅ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፣ የሶሪያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እና በአሜሪካ የምትገኘው የኤርትራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በጳጳሳት የተመራ ልዑክ ይዘው የተገኙ ሲሆን የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እና የአርመንያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ደግሞ ካህናት እና ዲያቆናት ተገኝተዋል::
ይህ ዓይነቱ የአንድነት አገልግሎት ከረጅም ዘመን በፊት ይደረግ እንደነበር የገለጹት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ እንዳሉት ከሆነ ላለፉት 50 ዓመታት በተለያየ ምክንያት ተቋርጦ የኖረ ሲሆን ከባለፈው ዓመት ጀምሮ እንደገና መቀጠሉን አንስተዋል ::

👍6❤1🥰1
የዘንድሮው አገልግሎት በመጠንም ሆነ በይዘት ደረጃ ከፍ ብሎ የተደረገ መሆኑን የገለጹት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የአብያተ ክርስቲያናቱ አንድነት በዚህ ብቻ የተገደበ እንዳልሆነ ተናግረዋል :: በየሀገራቱ ያሉ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ችግሮችን ለመፍታት እና በጎ ሚና ለመጫወት አንድነት ወሳኝ መሆኑን በማንሳት በቀጣይ በትምህርትና ሥልጠና ፣ በተተኪ ትውልድ ማፍራትና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ለመፍታት እንደሚንቀሳቀሱም ጠቁመዋል::
ከአገልግሎቱ በኋላ ሐሳባቸውን የሰጡ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በአንድነት በማገልገላችን አንዳችን ስለሌላችን የበለጠ እንድናውቅ እድል ከመፍጠሩም ባለፈ ግንኙነታችን እንድጠናከር እና ወደፊት ለሁላችንም የሚጠቅሙ የጋራ ሥራዎችን ለመሥራትም ይረዳናል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል ::
©ማኅበረ ቅዱሳን

👍3
The statement "God does not exist because theists have no evidence" is a logical fallacy called an argument from ignorance (also known as "appeal to ignorance")
because it assumes that something is false simply because no evidence has been presented to prove it true; in this case, it wrongly concludes that God doesn't exist just because no definitive proof has been shown to support his existence.

+ + ከባድ ሰበር መረጃ! (እና የትብብር ጥሪ)
(ትኩረታችሁን ሰብስባችሁ አንብቡኝ!)
***
ትናንት፡ ጥቂት ተቺዎቼ፡ " አንቺ መቼም፡ ስለ ኢሉሚናቲ፣ ስለ 666፣ ምናምን... ነው እንጂ፡ መጻሕፍትንና ሊቃውንትን ጠቅሰሽ፡ ስለ ጥንተ አብሶም ይኹን ስለ ነገረ መለኮት ማስተማር አትችዪም" ብለው ሊወቅሱኝ ሞከሩ።
እኔ ዓቅሜን የማውቅ ጨዋ ምዕመን ስለኾንኩ፡ ጠለቅ ብዬ ሊቃውንትን እየጠቀስኩ የነገረ መለኮት ክርክርአላደርግም። በቃሌ መሳቴ ስለማይቀር። መጻሕፍትንና ሊቃውንትን አላውቅም ማለት ግን አይደለም። የነቢያት፣ የሐዋርያትና የሊቃውንት የምን ጊዜም ተማሪያቸው ነኝ።
የኔ ስጦታ፡ መሠረታዊው የሃይማኖታችን አስተምህሮ፡ በአገራዊና በማኅበረሰባዊ አካኼዳችን ላይ ያለውን በጎ ተጽዕኖ መመርመርና ተጻራሪዎቹን ደግሞ ማጋለጥ ነው። ሙያዬ በማኅበረሰብ ሳይንሱ ዘርፍ በኩል ነውና።
ስለዚህ፡ በበጎው በኩል፡ ተዋሕዶ፡ እንዴት የኅዳሴ፣ የኢትዮጵያዊነት (utopian) ፣ የአብርኖት፣ የጤናማ ሥርዓተ መንግሥትና ሥርዓተ ማኅበር መሠረት እንደኾነች መግለጥ፤
በተጻራሪው በኩል ደግሞ፡ ስለኢሉሚናቲና ስለ666፣ ስለ ደቂቀ እስጢፋና ስለመሳሰሉት ቡድኖች አፍራሽ (dystopian) ሥራዎች ማጋለጥ ነው የኔ ሥራ።
***
እና፡ ዛሬ፡ ከጥቂት ዓመታት በፊት፡ ከአንድ አገር ወዳድ መንፈሳዊ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሰምቼ ለራሴ የያዝኩትን፡ ነገርግን ተጨማሪ መረጃዎች ለማግኘት ውሉ የጠፋኝን አንድ መረጃ አካፍላችኋለሁ።
ተቺዎቼ '' ስለ666 ስታወሪ አንድም ነፍስ ሳታድኚ፡ እነ አኬ ትናንት መጥተው ስንት ነፍሳት ወደ ቤተክርስቲያን ስለጨመሩ ቀንተሽ'' ምናምን እያሉ፡ ለግብፅ የጥንተ አብሶ ትምህርት ሊያግባቡኝ ሲሞክሩ ነበር።
እኔ ግን፡ ወደ 666ቱ እና ወደ ኢሉሚናቲው ነው የምመለስላችሁ! አጀንዳዬን አልረሳም። ሞኛችሁን ፈልጉ!
***
ስለግብጻውያን የአሞን ካህናት (The Amun priesthood) ሰምታችሁ ታውቃላችሁ? የግብፅ እና የውጪ አገርምሑራን፡ በየድረ ገጹ እንደሚሉት፡ የጥንት የግብፅ አምልኮ ካህናት ናቸው እንጂ፡ አሁን የሉም። አሁን ያሉት፡ "በጥንት ግብጽ (Kemet) አምልኮ ዙርያ የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ቡድኖች ናቸው እንጂ፡ ከነዚያ የጥንቶቹ የአሞን ካህናት ጋር፡ ምንም ግንኙነት የላቸውም" ይላሉ። እነዚህ ያሁኖቹ ቡድኖች፡ ተራ ዜጎች ኾነው፡ በራሳቸው ጊዜ የጥንቱን የግብፅ ፍልስፍናና የአምልኮ ሥርዓት (rituals) ለማጥናት፡ ብሎም ለመመለስ የተቋቋሙ እንደኾኑ ተደርጎ ነው የሚታሰበው። እነዚህ በግል ተነሣሽነት የተቋቋሙ ቡድኖች፡ kemetic reconstructionists ይባላሉ።
ታድያ፡ መቼም ኢትዮጵያውያን የጸሎት ሰዎች የዋዛ ሰዎች አይደሉም አይደል? ከተወሰኑ ዓመታት በፊት አንድ መረጃ አቀበሉኝ። ፍንጭ ብቻ እንጂ ዝርዝር አላገኘሁም። ያም ምን መሰላችሁ? እነዚህ የአሞን ካህናት የሚባሉት ግብጻውያን፡ ጥንት ብቻ ሳይኾን፡ አሁንም ከነሙሉ አምልኮዋቸው በምሥጢር ማኅበረሰብ መልክ እንዳሉ እና፡ ኢትዮጵያን አስመልክቶ፡ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ላይ ሤራ እንደሚሠሩ ነበር የነገሩኝ። በተለይደግሞ፡ "በኢትዮጵያ ትንሣኤ" እና "ይነሣል" በተባለው ንጉሥ ቴዎድሮስ ዙርያ፡ የተወዛገቡ ነገሮችን ስፖንሰርበማድረግና፡ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ብዙ ወግዘትና ስሕተት እንዳለባት ወሬ በማስነዛት ወጣቱ ጥሏት እንዲወጣ ፕሮፓጋንዳ ውስጥ ለውስጥ በመንዛት በኩል፡ ረዥም እጅ እንዳላቸው፡ በወቅቱ ወሬው ደርሶኛል።ትናንትና፡ አስተያየት መስጫዬ ላይ፡ አንዳንዶች፦ "የግብፅ ቤተክርስቲያን፡ ከኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ተረት ተረት አውጥታ፡ እውነተኛ ክርስቲያን አደረገችኝ፤ የጥንቶቹ የአኀት አብያተ ክርስቲያናት ሊቃውንት፡ ትክክለኛውን ትምህርት ይዘዋል። እነ አኬ ዓይናችንን ገለጡልን፤ 2000 ዓመት ሊቃውንት አስተምረው ምንም ነፍሳት ወደቤተክርስቲያን ያልጨመሩትን፡ አሁን የቲክ ቶክ ወጣቶች መጥተው ስንቶችን አዳኑ..." ዓይነት እንቶ ፈንቶ ሲያወሩብኝ፡ ይኽ ወሬያቸው፡ ከነ አቡነ ሽኖዳና ከእነ እማሆይ ኄራን ቤተክርስቲያን የፈለቀ ሳይኾን፡ "ከአሞን ካህናት ፕሮፓጋንዳ ክፍል የመጣ ሊኾን ይችላል" የሚል ሃሳብ መጣብኝ። ዓይናቸው ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች ላይ እንደኾነ ከጥቂት ዓመታት በፊት ሰምቼያለሁና። በኪሴ የያዝኩትን መረጃ፡ አሁን አውጥቼ መጠቀም ልጀምር ነው።
እናም፡ ባለፉት ዓመታት፡ ስለ አሙን ካህናት አድራሻና ሥራ ለመመርመር በመጠኑ ሞክሬያለሁ። ውላቸው ግን አይያዝም። ስለጥንቶቹ የአሙን ካህናት፡ ከበቂ በላይ መረጃ አግኝቼያለሁ። ስለአሁኖቹ ግን፡ በየድረ ገጹ፡ ምንም የለም። እንዳልኳችሁ፡ አሁን እንደሌሉ ተደርጎ ነው በየቦታው የሚጻፈው።
ይኽን ነገር አብረን እንመርምረው! ጥሪዬም ይኽ ነው፦
ባለፈው፡ '' ስለ ደቂቀ እስጢፋ መረጃ አቀብሉኝ'' ብዬ ጥሪ ስላደረግሁ፡ ወሳኝ ዓይን ከፋች መረጃዎችን አግኝቼያለሁ። አሁንም፡ ስለ አሞን ካህናትና በኢትዮጵያ ስላላቸው ሚና መረጃ ያላችሁ ሰዎች ካላችሁ፡ በተመቻችሁ መንገድ እንድታቀብሉኝ በእግዚአብሔር ስም እጠይቃችኋለሁ። ጥቂት ፍንጮች ከተገኙ፡ ነጥቦቹን ማያያዝ አይከብድም።
እና ልጆቹ ያሾፉብኝ መስሏቸው፡ ለሌላ አጀንዳ በር ከፈቱ ማለት ነው። "በለፈለፉ በአፍ ይጠፉ'' እንዲሉ። ኹሉ ነገር ለበጎ ነው። እግዚአብሔር እንድናየውና እንድናስተውለው የሚፈልገውን ነገር፡ በጊዜው፡ በውድም፥ በግድም ዞረን እንድናየው ማድረጉ አይቀርም። ክብር ምሥጋና ለርሱ ይኹን!
ስለትብብራችሁ በቅድሚያ አመሰግናለሁ።
መልካም ውሎ!
+++
ምንጭ:-መስከረም ለቺሳ youtube channel

👍1
ጥንተ_ተፈጥሮቱ_ለአዳም_prelapsarian_and_postlapsarian_1.pdf
975.2 KB
እያነበባችሁ ሼር አድርጉ!🙏
#ዋዜማ_የኪነ_ጥበብ_መርሐ_ግብር
ቅዳሜ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በወልድ ዋህድ ሰንበት ትምህርት ቤት አዳራሽ ይከናወናል ።
በመርሐ ግብሩ ላይ ከወልድ ዋህድ እና ከሌሎች እህት ሰንበት ትምህርት ቤቶች በተጋበዙ ወጣቶች
👉ቅኔ
👉ስነ ግጥም
👉ወጎች እንዲሁም
👉ጭውውት ይቀርባል ።
በመርሐ ግብሩ ላይ ትሳተፉ ዘንድ ጠርተነዎታል ።
መግቢያ ዋጋ :- #ሰዓት_ማክበር_ብቻ

ኪዳነምህረት በአባቶች ውዳሴ
[የእመቤታችን የየካቲት 16 ቃል ኪዳኗን አስመልክቶ በሊቃውንት የቀረበላት ውዳሴ (ቅዱስ ያሬድ፣ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ፣ አባ ዘመለኮት፣ አባ ጽጌ ድንግል)]
✍️ አዘጋጅ፡- መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
💥 ቅዱሳን ሊቃውንት የአምላክን እናት አመስግነው በቃኝ አይሉም ነበር በተለይ ከኢትዮጵያ ሊቃውንት ቅዱስ ያሬድ፣ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ፣ አባ ጽጌ ድንግልና አባ ዘመለኮትን በዚህ ክፍል ላይ ስጠቅሳቸው በተለይ የክብር ባለቤት ልጇ በጎልጎታ የምሕረት ቃል ኪዳንን የገባላትን የየካቲት 16 ክብረ በዓሏን አስመልክቶ ከጻፉት ከብዙው በጣም ጥቂቱን የእመቤቴን በረከት ለመሳተፍ ስል አስፍሬዋለሁ፡፡
💥በቅዱስ ያሬድ💥
❤ ቅዱስ ያሬድ በድጓው በተለይ በዐጫብር ድጓ ዘኪዳነ ምሕረት ውስጥ ከተጻፈው፡-
✍️ “ለብእሲ ዕሩቅ እምልብሰ ምግባር
ታዕድዊዮ እምገሃነም ባሕር
ኦ ድንግል በኪዳንኪ ሐመር”
(ድንግል ሆይ በቃል ኪዳንሽ መርከብ ከምግባር ልብስ የተራቈተውን ሰው ከገሃነመ እሳት ባሕር ታሻግሪዋለሽ)
✍️ “ብእሲ ቅሩብ ለሙስና
ለድንግል በኪዳና
በመንግሥተ ሰማይ ዘኢይጸልም ብርሃና
ይረክብ ሕይወተ ዕረፍት ወጥዒና”
(ለጥፋት የቀረበ ሰው ለድንግል በተሰጣት ኪዳን፤ ብርሃኗ በማይጨልም በመንግሥተ ሰማይ ዕረፍትና ጤንነትን ያገኛል)
✍️ “ክነፈ ርግብ በብሩር ዘግቡር ወገበዋቲሃኒ በሐመልማለ ወርቅ
አንቲ ምሥራቅ ወወልድኪ ፀሐየ ጽድቅ
አማን ኪዳንኪ ኢየሐልቅ”
(በብር የተሠራች የርግብ ክንፍ ጐኖቿ በወርቅ ዐመልማሎ የተሸለመች አንቺ በምሥራቅ ስትመሰዪ ልጅሽ የእውነት ፀሐይ ነው፡፡ በእውነት ቃል ኪዳንሽ አያልቅም)፡፡
✍️ “አዕረግዋ መላእክት እምድር ውስተ ሰማያት በክብር ወበስብሐት
በእንቲኣነ ከመ ትስአል እምወልዳ ኪዳነ ምሕረት”
(ስለ እኛ ከልጇ የምሕረት ኪዳንን ትለምን ዘንድ በክብር በምስጋና መላእክት ከምድር ወደ ሰማያት አሳረጓት፡፡)
✍️ “ይቤላ ለእሙ ማርያም እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ተካየድኩ ምስሌኪ ኪዳነ ምሕረት ከመ አድኅን ዘተአመነኪ መሐልኩ ለኪ በርእስየ ዘመሐልኩ አነ ለኖኅ ገብርየ ወለአብርሃም ፍቁርየ፤ ዘመሐልኩ አነ ለዳዊት ኅሩይየ ብእሲ ምእመን ዘከመ ልብየ መሐልኩ ለኪ በርእስየ በቅዱስ ሥጋየ ወበክቡር ደምየ መሐልኩ ለኪ በርእስየ ከመ ኢይሔሱ ማእኰትየ”
(ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ ማርያምን እንዲኽ አላት በምልጃሽ ያመነብሽን አድን ዘንድ ካንቺ ጋራ የምሕረት ቃል ኪዳንን ተጋባኊ፤ ለአገልጋዬ ለኖኅና ለወዳጄ ለአብርሃም ቃል የገባኊ እኔ በራሴ ማልኹልሽ፤ እንደ ልቤ ለምለው ለታመነው ለዳዊት የማልኊ እኔ በራሴ ማልኹልሽ፤ በቅዱስ ሥጋዬና በክቡር ደሜ የማልኊ እኔ ምዬ እንደማልከዳ ማልኹልሽ)
💥💥💥
💥 አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ💥
✍️ድካመ ጌጋይየ ትማእ ማርያም ጽድቀ ዚኣኪ በጽንዓ
መዳልወ ጥበብ ሶበ መልኣ ሰማኒተ ነፍሳተ ወሰብዓ
ሕፍነ ማይ ኀየለ ወሞአ”
(ማርያም የአንቺ ጽድቅ የበደሌን ድካም ድል ትነሣ ዘንድ የጥበብ (የምስጢር) ሚዛኖች በመሉ ጊዜ እፍኝ ውሃ ሰባ ስምንት ነፍሳትን ፈጽሞ ድል ነሣ፡፡)
✍️ “በከመ ልማድኪ በሊ ኀበ ወልድኪ ከሃሊ
ኦ ርኅሩኅ ኢተበቃሊ
ያጠፍኦኑ ለሥዕሉ ሠዓሊ
ኪነተከ ዘትካት ኀሊ”
(እንደ ልማድሽ ኹሉን የሚችል ወደሚኾን ልጅሽ የማትበቀል ቸር ሆይ፤ ሠዓሊ ሥዕሉን ያጠፋዋልን? የቀድሞ ፍጥረትኽን ዐስብ በዪ)።
✍️ “ጊዜ ጸልዮትኪ በጽሐ ከመ ኢይሙት ገብርኪ
ቅድሜሁ ስግዲ ወአስተብርኪ
እንዘ ታዘክሪዮ እምጻማ ንግደትኪ
ርግብየ የዋሂት ለየዋህ ወልድኪ”
(ደገኛዪቱ ርግቤ ለደገኛው ልጅሽ የእንግድነትሽን ድካም እንደ እናት እያሳሰብሺው፤ በፊቱ ፍጹም ስገጂ፤ አገልጋዪሽ እንዳይሞት የጸሎትሽ ጊዜ ደረሰ)።
✍️ “እሙ በሊዮ በእንቲኣየ ለፍሬ ከርሥኪ እብኖዲ
ላዕሌሁ ምሕረተ ኢታጐንዲ
እመ አሕዘነከ ብእሲ አባዲ
ቤዛ ነፍሱ ንጽሕየ እፈዲ”
(የጌታዬ እናት የማሕፀንሽ ፍሬ እብኖዲን ስለ እኔ እንዲኽ በዪው በርሱ ላይ ይቅርታን አታዘግዪ፤ ሰነፍ ሰው ቢያሳዝንኽም የነፍሱን ምትክ ንጽሕናዬን ዋጋ አድርጌ እከፍልለታለኊ)።
✍️ “አንቲ ውእቱ ለእግዚአብሔር አትሮኑሱ
ለአዳም ክብረ ሞገሱ
በኪዳንኪ ኃጥኣን መንግሥተ ሰማያት ይወርሱ"
(የእግዚአብሔር አትሮንሱ (ዙፋኑ) የአዳም የግርማው ክብር አንቺ ነሽ፤ ኃጥኣንም በቃል ኪዳንሽ መንግሥተ ሰማያትን ይወርሳሉ)።
💥💥💥
💥 አባ ጽጌ ድንግል 💥
✍️ “ሚ ሠናይ ከመ ጼና ጽጌ ልሑይ
በኲሉ ጊዜ ምሒረ ነዳይ
በእንተ ኪዳንኪ ድንግል ለበላዔ ሰብእ ጊጉይ
ሶበ ዐብየ እምኀጢአቱ ክበደ መድሎቱ ለማይ
ለተአምርኪ በሰማይ ተገብረ ግናይ”
(ኹል ጊዜ ለደኻ መራራት መመጽወት እንደ ለመለመ አበባ ያማረ ነው (ምን ያምር?) ድንግል በቃል ኪዳንሽ ምክንያት ከበላዔ ሰብእ ኀጢአት የውሃ ሚዛን በልጦ በመታየቱ ለተአምርሽ በሰማይ ምስጋና ኾነ)።
✍️ “በከመ ይቤ መጽሐፍ ማእከለ ፈጣሪ ወፍጡራን
ለዕረፍት ዘኮንኪ ትእምርተ ኪዳን
ሰንበተ ሰንበታት ማርያም ዕለተ ብርሃን
ብኪ ይትፌሥሑ ዘገነተ ጽጌ ጻድቃን
ወብኪ ይወጽኡ ኃጥኣን እምደይን”
(መጽሐፍ እንደተናገረ በፈጣሪና በፍጡራን መካከል ለዕረፍት የኪዳን ምልክት የሆንሽ የብርሃን ዕለት የሰንበታት ሰንበት ማርያም በአንቺ የገነት አበባ ጻድቃን ይደሰታሉ፡፡ ኃጥአንም በአንቺ ምልጃ ከሲኦል ይወጣሉ)፡፡
💥💥💥
💥የመልክአ ኪዳነ ምሕረት ደራሲ አባ ዘመለኮት💥
✍️ “ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘአስተማሰልዎ በኮከብ
ሶበ ብርሃኖ ተከድኑ ጽልሙታነ ራእይ ሕዝብ
ኪዳነ አምላክ ማርያም ወተስፋ መድኀኒት ዘዐርብ
ተናዘዘ ብኪ አኮኑ ኅሊና ቀዳማይ አብ
አመ እምገነቱ ተሰደ በሐዘን ዕጹብ”
(ለጨለመባቸው ወገኖች ብርሃኑን ባሳየ ጊዜ በኮከብ የመሰሉት ለኾነ ለስም አጠራርሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ የዐርብ የመድኀኒት ተስፋ የአምላክ ኪዳን ማርያም ሆይ በሚያስጨንቅ ሐዘን ከገነቱ በተሰደደ ጊዜ የመዠመሪያው ሰው ኅሊና ባንቺ ተረጋጋብሽ እኮን)።
✍️ “ሰላም ለአእዛንኪ እለ ተበሥራ ኪዳነ
እምአፈ ፈጣሪ ወልድኪ ዘባሕርየኪ ተከድነ
አምሕለኪ ማርያም ከመ ኢታርእዪኒ ደይነ
እንበለ ምግባር ባሕቱ እመ ኢይጸድቅ አነ
ቦኑ ለከንቱ ኪዳንኪ ኮነ”
(ባሕርይሽን ከተዋሐደ ከፈጣሪ ልጅሽ አንደበት የኪዳን ምሥራችን ለተበሠሩ ጆሮዎችሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ ያለምግባር የማልጸድቅማ ከኾነ በውኑ ኪዳንሽ ለከንቱ ይኾናልና ማርያም ሆይ ፍርድን እንዳታሳዪኝ አምልሻለኊ)።
✍️ “ማርያም ኅሪት እምነ መላእክት ወሰብእ
ተዝካረኪ ለእመ ገብረ በተአምኖ ጽኑዕ
በመንግሥተ ሰማይ ምስሌኪ ይነግሥ ኃጥእ”
(ከመላእክትና ከሰዎች ይልቅ የተመረጠሸ ማርያም ሆይ መታሰቢያሽን በብርቱ መታመን ያደረገ በመንግሥተ ሰማይ ካንቺ ጋር ይነግሣል) በማለት አወድሰዋታል፡፡
💥 እኛም በረከቷ ይደርብን ጸሎቷ ይጠብቀን፡፡ በአስተያየት መስጫው ላይ የአምላክ እናት በተሰጣት ቃል ኪዳን ትጠብቃችሁ ዘንድ በምትወዱት መዝሙር ግጥም ወይም በምትወዱት የምስጋና ጸሎት አመስግኗት።
✍️ መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ (በድጋሚ የተለጠፈ)

❤5👏1😁1