Telegram Web Link
እንኳን አደረሳችሁ

መልካም ፆም
9👍1
ፆም ስጋን ሳይሆን ስጋዌነትን አጥብቆ ይከለክላል ።
🥰6
😂😂

ካፊሮች ይቅር በሉኝ ። ጦምኛ ሁነን ሳለን ዘንድ ይሄንን ሐዲስ ሳልነግራችሁ ባልፍ የፀፅተኛል ብዬ ነው ።
😁2🤣1
+++ ጸልየህ ልታደርገው ትችላለህ? +++

ማልዶ ቤተ ክርስቲያን ተሳልሞ ወደ ሥራ የሚሄድ አንድ መንፈሳዊ ሰው በጉዞው ከሌላ መንገደኛ ሰው ጋር ይገናኛል። ጥቂት እንደ ተጨዋወቱ ይህ በመንገድ ያገኘው ሰው ከደረት ኪሱ የሲጋራ ፓኮ በማውጣት አንዱን መዝዞ እንዲወስድ ይጋብዘዋል። ያም መንፈሳዊ ሰው "አይ ይቅርብኝ" ሲል እምቢታውን ገለጸ። ባለ ሲጋራውም "ኃጢአት ነው ብለህ ስላሰብህ ነው እምቢ ያልከኝ? ማጨስ እኮ ከአስጨናቂዋ ሕይወት ፋታ ለመውሰድና ራስን ዘና ለማድረግ ይረዳል። ግድ የለህም አንዱን ሞክር" እያለ ሊያግባባው ጣረ። በመጨረሻም መንፈሳዊው ሰው "ግድ የለም ለእኔ ይቅርብኝ። ባይሆን አንተ ይጠቅመኛል ካልህ በቃ ሲጋራውን ከመለኮስህ በፊት አንድ "አባታችን ሆይ" ጸልይና ጀምር" አለው። በዚህ ጊዜ ያ መንገደኛ ደንግጦ እንዲህ ሲል መለሰ "ጸሎት ጸልዬማ እንዴት እንዲህ አደርጋለሁ?!"

በጸሎት ልትጀምር የማትችላቸው ማናቸውም ነገሮች ለአንተ መልካም አይደሉም። በልብህ ኃጢአት እንድታደርግ የሚገፉፉህ ክፉ ሐሳብ ሲመጣ "ይህን ጸልዬ ማድረግ እችላለሁ?" ብለህ ራስህን ጠይቅ። ከጸሎት ጋር የማይጣጣም ከመሰለህ እርሱ ኃጢአት ነውና ተወው። ጸልዮ የሚዘሙት፣ ጸልዮ የሚሰርቅ፣ ጸልዮ ባልንጀራውን የሚሳደብ፣ ጸልዮ በወንድሙ ላይ ክፉ የሚያደርግ ማን ነው?

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
አዲስ አበባ
👍1🙏1
came on babe

Lets eat each other 😂
🤣4😁1
በንጽሕና ለመኖር እየታገለ የሚወድቅን እግዚአብሔር አያዝንበትም። ድካሙን እና ያልተቋረጠ ጥረቱን አይቶ ድል የሚነሣበትን መንፈሳዊ ጸጋ ይሰጠዋል እንጂ። እንድትኖር በታዘዝከው ልክ ለመኖር ሞክረህ ስላልሆነልህ በራስህ ተስፋ አትቁረጥ። መሆንህን ብቻ ሳይሆን ፈልገህ መሞከርህን እግዚአብሔር ይቆጥርልሃል። ሰይጣን አቁስሎህ ስለሻረው ጠባሳህ አትቆጭ። ብዙ ጠባሳ እኮ ለሚዋደቅ ጀግና ወታደር የክብር ምልክቱ ነው። አፈ ወርቅ ዮሐንስ እንደሚለው የማይቆስለው የማይዋጋ ብቻ ነው።

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
5👍2
ድኃ ሙስሊምች በተለይ ወንድች ይሄንን ዜና ከሰማችሁ በኋላ እንደምትከፍሩ ርግጠኛ ነኝ ።😳💪

በፎቶዉ ላይ የምታዩት የሳኡዲ ተወላጅ አባወራ በአንድ ጊዜ 3 ሴቶችን አግብቷል። እስከ 4 ሚስት ማግባት በሚፈቀድባት ሳኡዲ ‘ታዲያ ይህ ምን ይገርማል?’ ልትሉኝ ትችላላችሁ። አስገራሚዉ ነገር ሶስቱም ሚስቶቹ በአንድ የትምህርት ተቋም ዉስጥ ያሉ መሆናቸዉ ነዉ! ከሶስቱ ሴቶች አንዷ የተቋሙ ተማሪ፣ ሌላኛዋ መምህርት፣ ሶስተኛዋ ደግሞ የተቋሙ ኃላፊ ናቸዉ። ይበልጥ የሚገርመዉ ደግሞ ግለሠቡ ቀደም ሲል ያገባት የመጀመሪያ ሚስቱም በተመሳሳይ የትምህርት ተቋም ዉስጥ በሱፐርቫይዘርነት በማገልገል ላይ መሆኗ ነዉ።

እኔ የምለዉ ግን … ይሔ ሠዉዬ ከትምህርት ተቋሙ ጋር ያለዉ ግንኙነት መጣራት ያለበት አይመስላችሁም? 😀
😁5👎1🤯1
Forwarded from J.CHRISTIAN
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
They might have horses and chariots but we will be great by the name of God YHWH
ቼ ቼ ቼቼ to the heaven
Forwarded from ልባም ሴት 😍
😁3
መልካም ረረረረረረ #መዳን
በእንግሊዝ ሆፕ ከተማ የሚገኝ የፕሮቴስታንት ቤተ ክርስቲያን መሪዎችን ጨምሮ ሙሉ ጉባኤያቸው ወደ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተጨመሪ

ይህ መልካም ዜና የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እምነት ትክክለኛነትና ሐዋርያዊነትን በማሳየት ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነው።

ስለዚህ የምስራች የተነሱ ሀሳቦች :-

🎯የመቀየሪያው ምክንያት : የፕሮቴስታንት ቤተ ክርስቲያን መሪዎች እና ጉባኤያቸው የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ትምህርቶችን፣ ታሪክን እና ሥርዓቶችን በጥልቀት ካጠኑ በኋላ እውነተኛውን የክርስትና እምነት እንዳገኙ በመግለጽ ወደ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ለመቀላቀል ወስነዋል።
🎯የመቀበያ ሥርዓት : ጉባኤው ወደ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የተጨመረው በጸሎት፣ በቅዱስ ቁርባን እና በሌሎችም የቤተ ክርስቲያን ሥርዓቶች አማካኝነት ነው።
🎯የቤተ ክርስቲያኒቱ ስያሜ: ወደ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የተጨመረው ቤተ ክርስቲያን "የቅዱስ ጆን ክሊማከስ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን" ተብሎ እንደተሰየመ ተገልጿል።
🎯የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምላሽ**: የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የዚህን ጉባኤ ወደ እቅፏ መቀላቀል በደስታ ተቀብላለች።

ይህ መልካም ዜና በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እና በሌሎች የክርስትና እምነቶች መካከል ያለውን ግንኙነት በተመለከተ ብዙ ውይይቶችን አስነስቷል። እንዲሁም የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እምነትን እና ታሪክን ለማወቅ ለሚፈልጉ ሰዎች ትኩረት የሚስብ ሆኗል።
👏13👍1😁1
"መምሬ ካሳሁን እንግዳ በአድዋ ጦርነት ጊዜ የቅዱስ ጊዮርጊስን ታቦት ይዘው በባዶ እግራቸው የዘመቱ አባታችን"

አድዋ የካቲት ፳፫ ቀን ፲፰፻፹፰ ዓ.ም በአድዋ ተራራ ላይ ጥቁር ሕዝቦች ለመጀመሪያ ጊዜ የማይቻል የሚመስለውን የቻሉበት፣ አይሆንም የተባለው የሆነበት፣ “ነጮች” “በጥቁሮች” የተሸነፉበት፣ ታላቅ ሁነት የተፈጸመበት፣ የድል በዓል መታሰቢያ ነው።

የአድዋን ድል ልዩ ያደረገው አንድ ሕዝብ በጦር ሜዳ ተዋግቶ ያሸነፈበት ታሪክ ስለ ሆነ ብቻ ሳይሆን በዘመኑ ዓለምን የተቆጣጠረውን “ጥቁር ሕዝብ ተፈጥሮውም፣ ኑሮውም ነጭን ለማሸነፍ አያስችለውም” የሚልና እንኳን ገዥዎችን ተገዥዎችንም ጭምር አሳምኖ የነበረ አስተሳሰብን የሻረ በመሆኑ ነው፡፡ ሁለት ለንጽጽር የማይገቡና ያልተመጣጠነ አሰላለፍ የነበራቸው ሕዝቦችና መንግሥታት ተዋግተው እንደ ጎልያድ በሰይፍ የመጣው ሳይሆን እንደ ዳዊት በእምነት ጠጠር የወነጨፈው ያሸነፈበት የማይታመን እውነታ በመሆኑም ነው፡፡
🥰5
"መምሬ ካሳሁን እንግዳ በአድዋ ጦርነት ጊዜ የቅዱስ ጊዮርጊስን ታቦት ይዘው በባዶ እግራቸው የዘመቱ አባታችን"

አድዋ የካቲት ፳፫ ቀን ፲፰፻፹፰ ዓ.ም በአድዋ ተራራ ላይ ጥቁር ሕዝቦች ለመጀመሪያ ጊዜ የማይቻል የሚመስለውን የቻሉበት፣ አይሆንም የተባለው የሆነበት፣ “ነጮች” “በጥቁሮች” የተሸነፉበት፣ ታላቅ ሁነት የተፈጸመበት፣ የድል በዓል መታሰቢያ ነው።

የአድዋን ድል ልዩ ያደረገው አንድ ሕዝብ በጦር ሜዳ ተዋግቶ ያሸነፈበት ታሪክ ስለ ሆነ ብቻ ሳይሆን በዘመኑ ዓለምን የተቆጣጠረውን “ጥቁር ሕዝብ ተፈጥሮውም፣ ኑሮውም ነጭን ለማሸነፍ አያስችለውም” የሚልና እንኳን ገዥዎችን ተገዥዎችንም ጭምር አሳምኖ የነበረ አስተሳሰብን የሻረ በመሆኑ ነው፡፡ ሁለት ለንጽጽር የማይገቡና ያልተመጣጠነ አሰላለፍ የነበራቸው ሕዝቦችና መንግሥታት ተዋግተው እንደ ጎልያድ በሰይፍ የመጣው ሳይሆን እንደ ዳዊት በእምነት ጠጠር የወነጨፈው ያሸነፈበት የማይታመን እውነታ በመሆኑም ነው፡፡

በአድዋ እንዴት ልናሸንፍ ቻልን?

የቤተ ክርስቲያናችን አስተዋጽኦ የሚገለጠው “እንዴት አሸነፍን?” የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ስንመረምር ነው፡፡ ይህ ዓለምን በብርቱ ጠፍንጎ የያዘና አንዱን ባሪያ ሌላውን ጌታ የሚያደርግ፣ ሰውን ያህል ፍጡር እንደ ከብት ነድቶ፣ እንደ ዕቃ ጎልቶ፣ ለገበያ አቅርቦ የሚሸጥ እኩይ አስተሳሰብ ከመሠረቱ የናደ፣ ነጻነት ማለት ምን ማለት እንደ ሆነ ለሌሎች ያሳየ፣ የአስተሳሰቡ ሰለባ የነበሩ ነጮችንም ያስደነገጠ ድል ኢትዮጵያውያን እንዴት ሊቀዳጁ ቻሉ? ዓቅሙና ብርታቱስ ከየት ተገኘ? ምዕራባውያን ያላቸው የሠለጠነ ወታደር፣ የጦር መሣሪያ ልዩነት እና ዓለምን የተቆጣጠረው “የነጮች” የበላይነት አስተሳሰብ እያለ የመግጠምስ ሞራሉና እምነቱ ከወዴት መጣ? ኢትዮጵያውያንን ከዚህ የአስተሳሰብና የሞራል ከፍታ ያደረሳቸው ገፊ ምክንያትስ ምንድን ነው? የሚሉ ጥያቄዎችን ስንጠይቅ መልሱ ቤተ ክርስቲያናችን ዘንድ ያደርሰናል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀደም ብላ ያስተማረችው ትምህርት፣ በነገሥታቱ እና በሕዝቡ ላይ ያሳደረችው በጎ ተፅዕኖ፣ “የእኔም ጦርነት ነው፤ በህልውናዬ ላይ የመጣ ነው” ብላ በማሰብ ደወል ደውላ፣ ዐዋጅ ነግራ ታቦት ይዛ ቀጥተኛ ተሳታፊ በመሆኗ ለኢትዮጵያውያን የአስተሳሰብ ከፍታ የነበራት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው፡፡

ኢትዮጵያውያን በእግዚአብሔር የሚያምኑ፣ የካህናትን ትእዛዝ የሚቀበሉ፣ እግዚአብሔርን መፍራትንና ንጉሥ ማክበርን የሚያውቁ፣ መመካት ቢገባቸውም ምሕረትን፣ ፍርድንና ጽድቅንም በምድር ላይ በሚያደርገው በእግዚአብሔር እንጂ በጉልበት፣ በሠራዊት ብዛት፣ በመሣሪያ ጥራት እንዳልሆነ ሲሰበኩ የኖሩ፣ ይህን እውነትም በልባቸው የጻፉ ስለ ነበሩ ነው፡፡ (ኤር.፱፥፳፬)

የአድዋ አርበኞች “እኛኮ ዘመናዊ ትጥቅ የለንም፤ እኛኮ “ጥቁሮች” ነን፤ “ነጭን” ማሸነፍ አንችልም፤ እኛኮ እንበርበት አውሮፕላን፣ እንሽከረከርበት አውቶሞቢል የለንም፤ እንዴት እናሸንፋለን? እንዴትስ ይቻለናል?” የሚል ጥያቄ በፍጹም አልጠየቁም፡፡ ምክንያቱም ‹‹ኢይድኅን ንጉሥ በብዝኀ ሠራዊቱ ወያርብኅኒ በብዝኀ ኃይሉ….፤ንጉሥ በሠራዊቱ ብዛት አይድንም፤ ኀያልም በኃይሉ ብዛት አያመልጥም›› የሚል ትምህርትን ያስተማረችው፣ የእምነት ስንቅም ያስቋጠረችው ቤተ ክርስቲያን ናትና፡፡ (መዝ.፴፪፥፲፮) ብዙዎች የሚዘነጉት ጉዳይ ጦርነትን የሚያሸንፈው የሠራዊት ብዛት፣ የመሣሪያ ጥራት ብቻ ስለሚመስላቸው ነው፡፡

ይህ የአስተሳሰብ ችግር በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ረጅም ዘመናትን የተሻገረ፣ አሁንም ድረስ ያልተቀረፈ አስተሳሰብ ነው፡፡ ብዙ ሰው መግደል ማለት ጦርነትን ማሸነፍ ማለት አይደለም፡፡ ብዙ ሠራዊት ያላቸው፣ ብዙ የጦር መሣሪያ የታጠቁ ሁሉ ብዙ ሰው ይገድሉ ይሆናል እንጂ ጦርነትን ያሸንፋሉ ማለት አይደለም፡፡ ምክንያቱም እውነተኛ አሸናፊነት፣ እውነተኛ ድል የሚገኘው እግዚአብሔርን ከሚያምን ንጉሥ፣ እግዚአብሔርን ከሚያምኑ ሠራዊት ወይም ከእውነተኛ ተዋጊዎች ነውና፡፡

ድል የሚነሡት ‹‹ድል መንሣት ዕውቀትም ካንተ ይገኛል፤ ጌትነትም ያንተ ገንዘብ ነው፤ እኔም ያንተ ባሪያ ነኝ›› የሚሉ ነገሥታትና ሠራዊት ናቸውና፡፡ (ዕዝ.ካልእ ፬፥፶፱)

ጣሊያን መካናይዝድ ጦር አሰልፎ፣ የሠለጠነ ሠራዊት አሰማርቶ፣ ዘመኑ ያፈራቸውን ትጥቆች ታጥቆ በባዶ እግራቸው በሚሄዱት፣ ሰይፍና ጎራዴ በታጠቁት ሊሸነፍ የቻለው ኢትዮጵያውያኑ ‹‹ድል መንሣት በእግዚአብሔር ኃይል ነው›› ብለው በመግጠማቸው ነው፡፡(፩ኛ መቃ.፳፩፥፫) ቁም ነገሩ ስለ ጣሊያን ሽንፈት ሳይሆን ስለ ኢትዮጵያውያኑ አሸናፊነትና የሥነ ልቡና የበላይነት ምክንያቱን ማንሣት ስለሆነ ቤተ ክርስቲያን በእምነት፣ በሥነ ልቡና፣ በአብሮነት፣ የገነባችው ሰብእና አድዋ ላይ አሸናፊ ሆኗል፡፡

ባለ ርእይ የነበሩ ሊቃውንቶቿ በጸሎት ተግተው፣ ራእይ አይተው፣ በቅኔያቸውና በስብከታቸው የጦርነቱን አይቀሬነት እየገለጹ፣ ዝግጅት እንዲደረግ እያሳሰቡና የሥነ ልቡና ግንባታ ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ ኢትዮጵያውያን አድዋ ላይ ታሪክ መሥራታቸው ቤተ ክርስቲያን በአማኞቿ ላይ በሠራችው ሥራ በገነባቸው የሥነ ልቡና የበላይነትና የአሸናፊነት መንፈስ ነው፡፡

የሮም ካቶሊክ መሣሪያ ባርካ ለወረራ ልካለች፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ሠራዊቱን በጸሎት ባርካ ራስን፣ ሀገርን፣ ሃይማኖትን ለመከላከል ልካለች፤ ካቶሊክ በመሣሪያ ተማምናለች፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ በጸሎት ተማምናለች፤ እነርሱ በታንክ ሊያሸንፉ መጡ፤ እኛ በታቦት ልናሸንፍ ታቦት ተሸክመን ወጣን፤ እኛም አሸነፍን፤ እነርሱም ተሸነፉ፡፡ ቤተ ክርስቲያን በእግዚአብሔር መታመንን አስተማረች፤ ካቶሊክ በሠራዊትና በመሣሪያ ታምኖ ለወረራ የሚሄድን ባርካ ሸኘች፡፡ እናም ምዕራባውያኑ እስከ ክፉ መሻታቸው ተሸነፉ፡፡ አሸናፊነት ከእግዚአብሔር ነውና፡፡ መጽሐፍ እንደ ተናገረ ‹‹አንተ ከሠራዊታቸው ጋር በከሃሊነትህ አጠፋሃቸው፤ ቤተ መቅደስህን ያጎሳቁሉ ዘንድ የስምህ ጌትነት ማደሪያ የሆነች ደብተራ ኦሪትንም ያሳድፉ ዘንድ መክረዋልና በብረትም የመሠዊያህን ቀንዶች አፍርሰዋልና›› ይላል፡፡ (ዮዲት ፱፥፰)

ሌላኛው የአድዋ ድል ምክንያት ደግሞ ካህናቱ ዘምተዋል፤ ሊቃውንቱ ዘምተዋል፤ ታቦቱ ዘምቷል፤ በየድንኳኑ ሰዓታት እየቆሙ ቅዳሴ እየቀደሱ፣ የሚያቆርቡ ነበሩ፤ የሞቱ እየተፈቱ በጸሎትና በምሕላ፣ በሞራልና በስንቅ ንጉሡንና ሠራዊቱን እየተራዱ ብዙ ሥራ የሠሩ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ናቸው፡፡ የጦርነቱን ፍትሐዊነት፣ ለሃይማኖት፣ ለርስት፣ ለሚስት፣ ለልጅ ተብሎ የሚከፈል መሥዋዕትነት መሆኑን እና አሸነፊነት ደግሞ ከእግዚአብሔር መሆኑን፣ ቤተ ክርስቲያን አስተምራለች፤ አበረታታለች፤ ብዙዎቹም ሊቃውንትና ካህናት ከአርበኞች ጋር በግንባር ተሠውተዋል፤ አጥንታቸውን ከስክሰዋል፤ ደማቸውን አፍስሰዋል፤ ይህም ለተዋጊዎች ኃይልና ብርታት ሰጥቷቸዋል፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ የሚል፤ ታሪክ አለ፡፡ ‹‹ሳሙኤልም የሚቃጠለውን መሥዋዕት ሲያሳርግ ፍልስጥኤማውያን ከእስራኤል ጋር ሊዋጉ ቀረቡ፤ እግዚአብሔርም በዚያች ቀን በፍልስጥኤማውያን ላይ ታላቅ ነጎድጓድ አንጎደጎደ፤ አስደነገጣቸውም፤ በእስራኤል ፊት ድል ተመቱ›› ይላል የሚገርም ነው፡፡ (፩ኛ ሳሙ.
፯፥፲) አድዋ ላይ የሆነውም ይህ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናትም በጦር ግምባር በድንኳን በቅዱስ ጊዮርጊስ ታቦት ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ሲያሳርጉ፣ ንጉሡም ቅዳሴውን ሲያስቀድሱ፣ የልዳው ኮከብ የፋርሱ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ በጣሊያኖቹ ላይ አንጎደጎደባቸው፤ አስደነገጣቸውም፡፡ በእነዚያ ልበ ሙሉዎች ጎራዴ ይዘው በመድፍ ፊት በሚቆሙ ደፋሮች ኢትዮጵያውያን ድል ተመቱ፡፡

የአድዋ ድል ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በገነባችው የመንፈሳዊ ሥነ ልቡና ብርታትና ለሀገርና ለሃይማኖት እስከ ሞት የመጋደል ወኔ የተገኘ መሆኑ ከድሉ እኩል መነገር ያለበት ነው። ኢትዮጵያውያን የኢጣሊያን ወረራ በሀገረ እግዚአብሔር ላይ እንደ ተደረገ ሰይጣናዊ ጥቃት ነበር የቈጠሩት።

እነሆ ዛሬ እኛ የድል አድራጊዎች ልጆች ተባልን፤ “ነጭም” “በጥቁር” ተሸነፈ፤ የነጻነትን ጣዕም ጥቁሮች ቀመሱ፤ የነጭ ፍልስፍና ተሻረ፤ ሰውን ያህል ፍጡር ባሪያ የሚያደርገው፣ አንዱን ገዥ ሌላውን ተገዥ የሚያስብለው የቅኝ ገዥዎች አስተሳሰብም ታሪኩ በጥቁር መዝገብ ተጻፈ፤ ይህም ከሆነ እነሆ ፻፳፰ ዓመታት ተቆጠሩ፡፡ አባቶቻችን ድል አድርገው ታሪክ ሠሩ፤ እኛ ደግሞ ድል ማድረግ፣ ታሪክ መሥራት ቀርቶ ታሪክን መሸከም ከብዶን ለመውደቅ እንፍገመገማለን፡፡

አድዋ አንድነት ነው፤ አድዋ እኩልነት ነው፤ አድዋ ነጻነት ነው፡፡ አድዋ የድሉ ባለቤቶችን መዘከር ነው፡፡ እነዚህን ዘንግቶ፣ የድሉ ፊታውራራዎችን በማንኳሰስ፣ የቤተ ክርስቲያንንም ሚና በመዘንጋት የሚከበር የአድዋ በዓል ትርጉም አልባና ታሪክን የማጥፋት ሴራ ነው፡፡

ለሀገርና ለሃይማኖት የተሠዉትን ሁሉ ነፍሳቸውን ይማርልን።

ጽሑፉን ለማሰናዳት የማኅበረ ቅዱሳንን ድረገጽ እንዲሁም ሐመር መጽሔትን ተጠቅመናል።
ገራሚ ጥያቄ ነው ለሸኪ የቀረበው ሙስሊም ክርስቲያኑም ቢሰማ ይጠቀምበታል 🙏
😁4
ሾይጧን ታስሯል ተብሎ የለ እንዴ 😂😳
😁3
የመግሪብ አዛን ውስጥ ነው 😂😍🫠😋
😁1🫡1
2025/07/12 04:05:23
Back to Top
HTML Embed Code: