Telegram Web Link
ነብይነት እናሰለጥናለን እንሾማለን።
ማስቀደስ እየቻልን ሳናስቀድስ በቤታችን ብንጸልይ ጉዳቱ ምንድን ነው?

“ወደ ቤተ ክርስቲያን ሳንኼድ በቤታችን ኾነን መጸለይ እንችላለን” የሚ ሉ ሰዎች አሉ፡፡

ሰው ሆይ! ራስህን አታስት! እርግጥ ነው, አንድ ክርስቲያን በቤቱ ውስጥ መጸለይ _ ይችላል፡፡ ነገር ግን _ ጸሎቱ በቤተ ክርስቲያን እንደሚደረገው ጸሎት በፍጹም እኩል አይኾንም፡፡ በቤተ ክርስቲያን የሚጸልዩት ጸሎት በአንድነት ኾነው የሚያደርሱት እንደዚሁም እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ኾነው እየጮኹ ልባቸውን ወደ እግዚአብሔር የሚሰቅሉ ብዙ ሰዎች ናቸውና ያሉት፡፡ ብቻህን በቤትህ ኾነህ የምታደርሰው ጸሎት ከወንድም እኅቶችህ ጋር በአንድ ነት በቤተ ክርስቲያን ኾነህ የምትጸልየውን ያህል በእግዚአብሔር ዘንድ የመሰማት ኃይል የለውምና፡፡ ለምን ቢሉ በቤትህ ውስጥ ካለው ይልቅ በቤተ ክርስቲያን ከፍ ያለ አንድነት፣ የፍቅር ገመድ፤ ከምንም በላይ ደግሞ የካህናት ጸሎት አለና፡፡

ካህናት በፊታችን ይቆማሉ፡፡ ስለዚህ የሕዝቡ ጸሎት ደካማ ቢኾን እንኳን ከእነርሱ ኃያል ጸሎት ጋር ይዋሐዳል፣ ወደ ሰማያትም ያርጋል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ከውኅኒ ቤት ነጻ የወጣው በቤተ ክርስቲያን ስለ ተደረገለት ጸሎት ነው፡፡ … እንግዲህ ንገረኝ! የቤተ ክርስቲያን ጸሎት ለሐዋርያው ጴጥሮስ እንኳን አስፈላጊው ከነበረ፣

እንደዚህ ያለ የእምነት ዓምድ የኾነውን ቅዱስ ከወኅኒ እንዲወጣ ካደረገው ለምን እንደዚህ ያለውን ኃይል ትንቃለህ? ለዚህ የምታመጣው አመክንዮስ እንደ ምን ያለ አመክንዮ ነው?

ሰዎች በአንድነት ኾነው ሲጸልዩ እግዚአብሔር እንዲራራ ምሕረቱም እንዲያበዛ እንደሚያደርጉት እርሱ እግዚአብሔር ራሱ የተናገረውን አድምጥ፤ ለነቢዩ ዮናስ እንዲህ ብሎታልና፡- “ከመቶ ሃያ ሺሕ የሚበልጡ ሰዎችና ብዙ እንስሶች ላሉባት ለታላቂቱ ከተማ ለነነዌ አላዝንምን?” (ዮና.4፡11)፡፡

የሕዝቡን ቍጥር ጠቅሶ የተናገረው እንዲሁ ለከንቱ አይደለም፤ በአንድነት የሚደርስ ጸሎት እጅግ ኃያል እንደ ኾነ ታውቅ ዘንድ ነው እንጂ።


ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ❤️
ንግስታቸው የሩጫ ውድድር አድርጋለች😂

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ተደረገ በተባለው ወድድር ንግስቷ በመሰናክል ይሁን በማራቶን የተወዳደሩት የተገለጠ ነገር የለም😂

ዘንድሮ ሃይማኖታዊ ቀልደኞች የበዙበት ጊዜ ነው
✝️እንደዚህ ነዉ መታደል 🙏ሸር🙏Shet🙏✝️

👉ወጣቶች ፣ነጋዴዎች ፣ማህበራት እና ሰራተኞችን የሚያስተምር ተግባር 🙏✝️

👉 ቤተ ክርስቲያንን እወዳታለሁ ላንች እሞታለሁ ከማለት ባሻገር እንደዚህ በጉብዝና ወራት ክርስትናን የማስቀጠያ ሀዲድ የሰዉ ፊት ሳያሳፍራቸዉ ክብራቸዉ ሳያስጨንቃቸዉ እንደዚህ በአደባባይ ስለ ቅድስት ሥላሴ ብሎ ለምኖ አብያተ ክርስቲያናት የሚያሳንፁ ወጣቶች መሆን ይጠበቃል ።
👉 የደብረኝነት እና የጎጥ አጥር ሳይከልላቸዉ አሀቲ ቤተ ክርስቲያን ብለዉ ከተወለዱበት አካባቢ ዉጭ እንደዚህ ሰዉ በሌለበት አስታዋሽ ባጣዉ በደሳሳ ጎጆ ፈጣሪያችን መጋቢያችን ቅድስት ሥላሴ አይቀመጥም በማለት የቤቱ ቅናት ቢያቃጥላቸዉ እነሆ ይህን የመሰለ አብያተ ክርስቲያን እያሳነፁ ይገኛሉ ።
👉ከደሴ 89 ኪ/ሜ እርቀት ላይ ጊምባ ጭሮ የሚገኝዉ ጥቂት ክርስቲያኖች ብቻ ያሉበት የጭሮ ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን እዚህ ደረጃ ደርሶ በቀጣይ ለማስመረቅ እንደዚህ በህብረት ደጆችሽ አይዘጉ ዘ ወሎ እና አብይ ኮሚቴ በጋራ እየተንቀሳቀሱ ነዉ ።
✝️እርስዎም የበኩልዎን በማድረግ ከቅድስት ሥላሴ ረድኤት በረከት ይሳተፉ።🙏🙏🙏
👍ቅዱሳን ስዕላት ጌጥ አይደሉ

አዎ ስዕላት የአምልኮ ንዋያት እንጂ መዋቢያ ወይም ደግሞ ቦታ ማሟያ አይደሉም ።
በየመኪና የሚለጣጠፋ ቅዱሳን ስዕላት እንዲቀሩ መንግስት የተንኮል አዋጅ ቢያውጅም። የእግዚአብሔር ሐሳብም እንዳለበት ማስተዋል ችያለሁ ። በየህዝብ መጓጓዣዎች የተለጠፋ ቅዱሳት ስዕላት የተሳፋሪዎች ፣የረዳቱን እንዲሁም የዘዋሪ ሹፊሮችን ስድድብ እና ክፋታዊ ተግባር እንጂ ለስዕላቱ ላይ ለሚገለጥ የእግዚአብሔር ፀጋ ምስጋናን አልጠገቡም ።

ቀያፋ በጊዜ ትንቢት ሳያውቅ የክርስቶስን የማዳን ስራ እንደተናገረው ሁሉ ባለ ስልጣናቱን ለበጎ ያላይደለ ለክፋ የወሰኑት ውሳኔ በድፍረታችን ይሁን ባለማወቅ በየቦታው በማይመጥናቸው ሁኔታ የሰቀልናቸውን ስዕላት ማስከበሩ ደስ ያሰኛል ።
Forwarded from ልባም ሴት 😍
🦋 ለእህቴ . . .🦋

🥛እርጎ ውስጥ እደገባችዋ ዝንብ ህይወትሽ በጠ
ጪው እጅ አይወሰን 🙅‍♂


አንቺ ሴት ነሽ👸 የእናትሽ ልጅ 🤱 ሴት !!

👉አንቺ ውብ ነሽ ምክንያቱም ሴት ነሽ
👉አንቺ ብልህ ነሽ ምክንያቱም ሴትነሽ
👉አንቺ  ሴት ነሽ ያውም ጀግና ሴት

🌹 ምንም ማረግ ትችያለሽ ዓለም 🌍 ያላንቺ ጨረቃ 🌘 ያኮረፈቻት ፀሃይ 🌥 የተቀየመቻት ጨለማ 🖤 ናት

🌹ሁሉም ቀን ቀንሽ ነው 🌹

🎙የአብስራ ተስፋዬ 📩 @yeabm
መንግስት ለዚህም የሚሆን አዋጅ አምጣ 😡
የ9ኙ መነኮሳት ምርጫ ተጠናቋል

ቅዱስ ሲኖዶስ የዘጠኝ ኤጲስ ቆጶሳት ምርጫን አካሔደ

* ሲመታቸው ሐምሌ 9 ይከናወናል፤
* ከነገ ሰኔ 29/2015 ዓ.ም ጀምሮ ሥልጠና ይገባሉ፤

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፣ ዛሬ ረቡዕ፣ ሰኔ 28 ቀን 2015 ዓ.ም. በአካሔደው ልዩ ስብሰባ፣ በኦሮሚያ እና በደቡብ ክልሎች፣ በተደራቢነት ተይዘው ለቆዩ፣ ክፍት በኾኑና አንገብጋቢ ችግር ባለባቸው ዘጠኝ አህጉረ ስብከት ላይ የሚመደቡ ዘጠኝ ኤጲስ ቆጰሳትን ምርጫ አካሒዷል፡፡

በዚኽም መሠረት፡-
ለኦሮሚያ ክልል ሰባት አህጉረ ስብከት፤
1. አባ ሣህለ ማርያም ቶላ - ምዕራብ አርሲ - ሻሸመኔ ሀገረ ስብከት
2. አባ ወልደ ገብርኤል አበበ - ምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት
3. አባ ጥላሁን ወርቁ - ምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት
4. አባ ዓምደ ሚካኤል ኀይሌ - ሆሮ ጉድሩ ወለጋ - ሻምቡ ሀገረ ስብከት
5. አባ ኀይለ ማርያም ጌታቸው - ድሬዳዋ ሀገረ ስብከት
6. አባ ተክለ ሃይማኖት ገብሬ - ምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት
7. አባ እስጢፋኖስ ገብሬ - ቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት

ለደቡብ ኢትዮጵያ ኹለት አህጉረ ስብከት፤
8. አባ ክፍለ ገብርኤል ተክለ ሐዋርያት - ጌድኦ አማሮ እና ቡርጂ ልዩ ወረዳዎች ሀገረ ስብከት
9. አባ ስብሐት ለአብ ወልደ ማርያም - ዳውሮ እና ኮንታ ሀገረ ስብከት
በቅዱስ ሲኖዶስ የጸደቀው የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ውጤት ይፋ ተደረገ

ምንጭ: EOTC TV
2024/09/28 19:28:44
Back to Top
HTML Embed Code: