Telegram Web Link
Trimmed_22
<unknown>
📕 አቂደቱል ዋሲጥያ
🎤 ሸይህ ዑመር አሊ
📆  ክፍል- የመጨረሻ ክፍል-
👉http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
🎯የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ
ዘርፍ🎯
የዑመር ኢብኑልኸጣብ (ረዐ) 20ምርጥ ምክሮች፤
.
1. ‹የምትጠላውን ሰው ተጠንቀቅ፤›

2. ‹ብልጥ ሰው የእለት ስራዎቹን ከራሱ ጋር ይተሳሰባል፡፡

3. ‹የዛሬን ስራ ለነገ አታሳድር፡፡›

4. ‹ከሰዎች ጥያቄ ተነስተህ አስተሳሰባቸውን መለካት ይቻላል፡፡›

5. ‹ለሌሎች ዳዕዋ በምታደርግበት ወቅት እራስህን አትርሳ፡፡›
.
6. ‹ከዱንያ ትንሽን ብቻ ስትፈልግ ይበልጥ ነፃነትን እያገኘህ ትሄዳለህ፡፡›

7. ‹ወንጀል አለመስራት ከፀፀት ይሻላል፡፡›

8. ‹ታጋሽ ሁን፤ ትዕግስት የእምነት ምሶሶ ነችና፡፡›

9. ‹አሏህን ፈሪ መሆን እድለኛነት ነው፤ ከዚህ ውጭ ያለው እድለቢስ መሆን ነው፤›

10. ‹ወደ አኺራ የሄዱ ሰዎችን ንግግር ጠብቁ፤ እነርሱ የተናገሩት አሏህ እንዲናገሩ ያገራላቸውን ብቻ ነውና፡፡
.
11. ‹አሏህን ፍራ፤ እርሱ ሁሌም ህያው፤ ከርሱ ውጭ ያሉ ሁሉ ጠፊ እና አላቂ ናቸውና፡፡

12. ‹ጥፋቴን በነገረኝ ሰው ላይ የአሏህ እዝነት ይውረድ፡፡

13. ‹እውቀትን ገብያት፤ ከዚያም ለሰዎች አስተምር፡፡›

14. ‹የተከበርክ፣ ታማኝ እና እውነተኛ ሁን፡፡›

15. ‹ትምክህተኛ ምሁር አትሁን፤ ትምክህተኛነት እና እውቀት አንድ ላይ አይሄዱምና፡፡
.

16. ‹ለዚህች አለም ፍቅር ያለው አዋቂ ባየህ ግዜ እውቀቱ አጠራጣሪ መሆኑን ተረዳ፡፡›

17. ‹ትንሽ አውርቶ ብዙ በሚሰራ ሰው ላይ የአሏህ እዝነት ይውረድ፡፡›

18. ‹ታማኝነት ማለት በምትሰራው፣ በተናገርከው እና በምታስበው ነገሮች ልዩነት አለመኖር ማለት ነው፡፡

19. ‹የሰው ልጅ ምንም እንኳ እንደ ቀስት ቀጥ ያለ ስራ ቢሰራ ተቃውሞ አያጣውም፡፡›

20. ‹አዕምሮህ እንዲሰፋ ከፈለግክ፤ ከፈሪሀ አሏሆች ጋር ተቀመጥ፤›

ለወዳጆችዎ ሼር በማድረግ ያካፍሉ

SHARE 🔗SHARE
http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
📌 የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ📌
⭐️ይህ የረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ታላቅ ምክር ነው።

⭐️አንድ ሰው ወደ ነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) መጣና "ለዱንያም ሆነ ለአኼራ የሚጠቅም ንግግር ለመጠየቅ መጣው" አላቸው።
# እሳቸውም ደግሞ "የመጣልህን ጠይቅ" አሉት።

⭐️"ከሰው ሁሉ አዋቂ ለመሆን እፈልጋለው?"
# እሳቸውም "አላህን ፍራ" አሉት

⭐️ "ከሰው ሁሉ ሀብታመ ለመሆን እፈልጋለው?" ሲላቸው።
# "ባለህ ነገር ተብቃቅተ አላህን አመስግን" አሉት

⭐️"ትክክለኛ ፈራጅ እና ታማኝ ሰው ለመሆን እፈልጋለው?" ሲል
# "ለራስህ የምትወደውን ለሰዎች ውደድ"አሉት።

⭐️ "ከሰው ሁሉ ብርቱ ለመሆን እፈልጋለው?" ሲል
# "በአላህ ተወከል"አሉት

⭐️ "በአላህ ዘንድ ብቸኛ ተመራጭ ለመሆን
እፈልጋለው" ሲላቸው?
#"ዚክር አብዛ" አሉት።

⭐️ "ከሰው ሁሉ በላጭ ለመሆን እና ጥሩ ሰው ለመሆን እፈልጋለው?" ሲል
# "ለሰው ጠቃሚ ሁን" አሉት።

⭐️"የተከበረና ቸር ሰው ለመሆን እፈልጋለው?" ሲላቸው
# "ችግርህን ለፍጡር አትንገር" አሉት።

⭐️"ረሱል እና አላህ እንዲወዱኝ እፈልጋለው?" ሲል
#"አንተም እነሱ የወደዱትን ውደድ" አሉት::

⭐️"ከወንጀል የጠራው ሁኜ አላህንመገናኘት እፈልጋለው" ሲል
# "ጀናባህን በደንብ ታጥበ እስቲግፋር አብዛ ማልቀስ መተናነስ መታመም አለብህ" አሉት።

⭐️ "ከበጎ ሰሪወች ለመሆን እፈልጋለው" ሲላቸውም
#"አላህን ልክ እንደምታየው ሁነክ ተገዛው" አሉት።

⭐️"ኢማኔ እንዲ ሞላ እፈልጋለው" ሲል
# "ፀባይህን አሳምር" አሉት።

⭐️"እርዝቄ እንዲሰፋ እፈልጋለው" ሲል
# "ተዋዱዕ አዘውትር" አሉት።

⭐️"ዱዓዬ ሙስተጃብ እንዲሆንልኝ እፈልጋለው?" ሲላቸው
# "ሀራም አትብላ" አሉት::

⭐️ "አላህን ከሚታዘዙ ሰዎች ለመሆን እፈልጋለው?" ሲል
# "ግዴታዎችህን ፈፅም" አሉት።

⭐️"በአላህ ዘንድ ትልቁ ሀሠና ወይም ደግ ሥራ የቱ ነው?" ብሎ ሲጠይቃቸው
# "መልካም ፀባይ መተናነስ እና በበላ ላይ ሰብር ማድረግ ነው" አሉት።

⭐️"በአላህ ዘንድ የትኛው ስርዓት ነው መጥፎ ሥራ?" ሲል ሲጠይቃቸው
# "መጥፎ ፀባይና ፍላጎትን መከተል ናቸው" አሉት

⭐️"በዱንያም ሆነ በአኼራ የአላህን ቁጣ የሚያበርድ ምንድነው" ሲል ጠየቃቸው?
#"ድብቅ ሰደቃ እና ዘርን መቀጠል ናቸው" አሉት።

⭐️ "የቂያማ ቀን በአላህ ኑር ለመሰብሰብ
እፈልጋለው?" ሲል
# "ሰውን አትበድል" አሉት

⭐️"የቂያማ እለት አላህ እንዲያዝንልኝ እፈልጋለው?"
# "ለአላህ ባርያዎች እዘን" አሉት።

⭐️"የቂያማ ቀን የጀሀነም እሳት የሚያጠፋው ምንድነው?" ብሎ ሲጠይቃቸው
# "በችግር ላይ ወይም በሙሲባ ላይ ትህግስት መሰድረግ ነው" አሉት።

⭐️ "የቂያማ እለት ነውሬ እንዲሸፈንልኝ እፈልጋለው?" ሲል
# "የወንድምህን አይብ ሸፍን" አሉት።

⭐️"የቂያማ ቀን ከአላህ ቁጣ ሰላም ለመሆን
እፈልጋለው?" ሲል
# "በአንድም ፍጡር አትቆጣ" አሉት።

*** አላህ ሱብሃን ወተአላህ ባወቅነው. በስማነው የምንስራ ያድርገን አሚን!!!!
👉 http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
SHARE 🔗SHARE
📌የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ📌
#አንብቤው_ከተመቸኝ_ላካፍላችሁ!
#ክፍል_ሁለት

🔙 ሀዘን እና ትካዜ ወደ ኋላ ጣላቸው!


🌱ኢብኑል ቀይም አላህ ይዘንለት እንዲህ ይላል፦
"ሀዘን ቁርኣን ውስጥ በክልከላ መልኩ ወይም በማራቅ መልኩ ቢኾን እንጂ አልተጠቀሰም
ልክ አላህ እንዳለው

{ وَلَا تَهِنُوا وَلَا تَحْزَنُوا }
{አትስነፉ አትዘኑም}


{ فَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ }
{ፍርሃት የለባቸውም፤ እነርሱም አያዝኑም}"

🔵የዚህ ሁሉ ሚስጥሩ
👉🏽 ሸይጣን ከሚያስደስተው ነገር ሁሉ ትልቁ ሙዕሚን የኾነ ሰው አዝኖ ማየቱ ነው። ከዚያም ከመንገዱና ከጉዞው ሊገታው።

🔵በእርግጥም ነብዩ ሙሐመድ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሐዘን ተጠብቀዋል
"اللهم إني أعوذ بك من الهم والحزن"
[አላህ ሆይ እኔ ከሀዘንና ከጭንቀት በአንተ እጠበቃለሁ] በማለት


🌱ኢብኑል ቀይም በድጋሚ እንዲህ ይላል፦
"ሀዘን ብሎ ማለት
ቀልብን ያደክማል፣ ቆራጥነትን ያከሽፋል፣ ፍላጎትን ይጎዳል፣ ወደ ሸይጣንም ምንም ተወዳጅ ነገር የለም ሙዕሚን አዝኖ እንደ ማየት"


💡ስለኾነም፦
🍎ሀዘንን ራቁ!
   መልካምን ከጅሉ!
      በአላህ ላይ መልካም ግምት ይኑራችሁ!
       አላህ ዘንድ ባለው ተማመኑ
          በአላህም ላይ ተመኩ
              በአላህ ፍቃድ በሁሉም ሁኔታ ደስተኞች ትኾናላችሁ


💡ብትመለከት፦
አላህ ብዙ ነገራቶች ሳትጠይቀው ሰጥቶሃል። ስለዚህ አላህ የምትፈልገውን ነገር እንደ ማይከለክልህ እርግጠኛ ሁን። ምን አልባት ግን አለ መሰጠትህ የተሻለልህ ካልኾነ በስተቀር።


🌱ምን አልባት፦
አንተ ተኝተህ ሳለህ የሰማይ በሮች ላንተ ዱዐ በሚያደርጉልህ ሰዎች እየተንኳኩልህ ይኾናል።

👉🏽ድሃ ኾኖ የረዳኸው፣
  👉🏽አዝኖ ያስደሰትከው፣
    👉🏽የተጣበበ ኾኖ ያቃለልክለት፣
       👉🏽እያለፈ ብቻ ፈገግ ያልክለት

🤲እጁን ዘርግቶ እየለመነልህ ሊኾን ይችላል።
👇🏾
👉🏽መልካምን ከመስራት መቼም አትቆጠብ


🌱ከቀደምቶች አንዱ እንዲህ ይላል፦
"አላህ የኾነ ነገር እጠይቀዋለሁ, ያንን ነገር ከሰጠኝ አንዴ እደሰታለሁ፤  ያንን ነገር ካልሰጠኝ ግን አስር ጊዜ እደሰታለሁ፤ ምክንያቱም መሰጠቴ የእኔ ፍላጎት ነበር አለመሰጠቴ ደግሞ የአላህ ፍላጎት ነው።"


🌱ሌላኛው ደግሞ እንዲህ ይላል፦
"ህይወት አጭር ናት።
      👉🏽በሀዘን፣
         👉🏽በጭንቀትና
            👉🏽በጥበት
                👉🏽አታሳጥራት"

🤝በያላችሁበት የአላህ እዝነትና ጥበቃ አይለያችሁ🤲
http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
🎯የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ🎯
ይህን ያውቁ ኑሯል

ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ኢስራ ወል ሚዕራጅ ደርሰው ሲመጡ በየሰማያቱ እነማንን እንዳገኙ...

:➊. 1ኛ ሰማይ ላይ ያገኙት ነብዩላህ አደም (ዐ.ሰ)

➋. 2ኛ ሰማይ ላይ ያገኙት ነብዩላህ የህያ (ዐ.ሰ) እና ኢሳ(ዐ.ሰ)

➌. 3ኛ ሰማይ ላይ ያገኙት ነብዩላህ ዩሱፍ (ዐ.ሰ)

➍. 4ኛ ሰማይ ላይ ያገኙት ነብዩላህ ኢድሪስ (ዐ.ሰ)

➎. 5ኛ ሰማይ ላይ ያገኙት ነብዩላህ ሃሩን ቢን ኢምራን (ዐ.ሰ)

➏. 6ኛ ሰማይ ላይ ያገኙት ነብዩላህ ሙሳ ቢን ኢምራን (ዐ.ሰ)

➐. 7ኛ ሰማይ ላይ ያገኙት ነብዩላህ ኢብራሂም (ዐ.ሰ)……ናቸው፡፡
http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
SHARE 🔗SHARE
📌የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ📌
👉አምስት ነገሮችን ከአምስት ነገሮች በፊት ተጠቀሙባቸው ፡፡

ወጣትነትህን     ከማርጀትህ በፊት
ጤንነትህን       ከመታመምህ በፊት
ሀብትህን         ከመደህየትህ በፊት
ትርፍ ጊዜህን    ከመጨናነቅህ በፊት
ህይወትህን         ከመሞትህ በፊት

የአሏህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)  ሲናገሩ " ሕዝቦች አምስት ነገሮችን በመውደድ ከአምስት ነገሮቺ ይዘናጋሉ"  ካሉ በኀላ ሲዘረዝሯቸው እንዲህ አሉ: ⤵️

   👉ሕይወትን ያፈቅሩና - ሞትን ይረሳሉ:

👉ዱንያን ያፈቅሩና -አኼራን ይዘነጋሉ፡

  👉ህንፃ መገንባት ይወዱና - ቀብር  መኖሩን ይዘነጋሉ፡

  👉ገንዘብ ይወዱና - ከሒሳብ ( በቂያማ ግዜ መተሳሰቡን ) ይዘነጋሉ ፡

👉 ፋጡራንን ያፈቅሩና - ፈጣሪን ይዘነጋሉ ፡፡
አሏህ ከዚህ ተግባር ይጠብቀን ኣሚን ፡፡

http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ
》መዉሊድ 《
በታላቁ ሸይኽ ዱክቱር ሷሊህ አል ፈውዛን من كتاب الخطب المنبرية لمعالي
الشيخ 1الدكتور صالح الفوزان/ج

እናንተ ሙስሊሞች ሆይ ሙውሊድ በብዙ አቅጣጫ ከንቱ እና ሀራም ነው።
①በዲን ላይ ፈጠራ ነው ፈጠራ ሁሉ ጥመት ነው ሙሊድን ማቆም የሚያዩ ሰወች ከሸሪአ ማስረጃን ሊያቆሙለት አይችሉም
②ሙሊድ ነሷራዎችን በኢሳ ልደት ላይ በማክበራቸው ላይ መመሳሰል ነው በነሷራዎች ከመመሳሰል ደግሞ በርግጥ ተከልክለናል
③በመውሊድ ዉስጥ በአብዘሃኛው ግዜ በተወገዙ  እና እርም በተደረጉ ነገሮች ላይ ይወድቃል እርም ከተደረጉ ነገሮች ትልቁ በአሏህ ማጋራት ነው ረሱል ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለምን መጣራት በሳቸዉም እርዳታን መጠየቅ ሽርክ ያለባቸዉን ስንኞችን ነብዩን ማወደስ ላይ መግጠምን ይመስል ቡሩዳ የተሰኘው ስንኝ እና መሰሎቹ(መውሊድ ላይ ይከሰታል)
④በእስልምና ላይ ሁለት በዓል እንጂ የለም ¹ኢዱል_አድሃ እና የተባረከው ²ኢዱል_ፈጥር ሶስተኛ በዓልን የፈጠረ በርግጥም በእስልምና ከርሱ ያላደለን ፈጥሯል
አነስ ኢብኑ ማሊክ ከርሱ የተገኘውን አሏህ ይውደድለትና እንድህ አለ ነብዩ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም መደመዲና ገቡ ለመዲና ሰወችም በነሱ ዉሰጥ የሚጫወቱባቸዉ ሁለት ቀን ነበራቸው ነብዩም እነዚህ ቀኖች ምንድን ናቸው አሉ እነሱም በጃሂልያ ግዜ እንጫወትባቸው ነበር አሉ ነብዩም እንድህ አሉ አሏህ ከነዚህ ቀኖች የተሻለ የሆነን ቀን ለውጦላቹሀል ¹የእርዱ ቀን እና ²የፈጥሩ ቀን
አቡ ዳውድ አህመድ ነሳኢይ ዘግበውታል ሰነዱ በሙስሊም ነስፈርት ነው

እናንተ የአሏህ ባሪያዎች ሆይ አሏህን ፍሩ ቢድአንና ተፃርኖን ተጠንቀቁ ሱናን ሙጭኝ አድርጋቹህ ያዙ ተከተሉ አትፍጠሩ
أعوذ بالله من الشيطان الرجيم
وَأَنَّ هَٰذَا صِرَاطِي مُسْتَقِيمًا فَاتَّبِعُوهُ ۖ وَلَا تَتَّبِعُوا السُّبُلَ فَتَفَرَّقَ بِكُمْ عَن سَبِيلِهِ ۚ ذَٰلِكُمْ وَصَّاكُم بِهِ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ
«ይህም ቀጥተኛ ሲኾን መንገዴ ነው፤ ተከተሉትም፡፡ (የጥመት) መንገዶችንም አትከተሉ፡፡ ከ(ቀጥተኛው) መንገዱ እናንተን ይለያዩዋችኋልና፡፡እነሆ ትጠነቀቁ ዘንድ በርሱ አዘዛችሁ፡፡»
بارك الله لي ولكم في القرآن العظيم
)من كتاب الخطب المنبرية، لمعالي الشيخ الدكتور صالح الفوزان/ج1)·
☞ሸይኽ ሷሊህ አል-ፈዉዛን [አሏህ ይጠብቃቸዉ] እንዲህ አሉ ፦
[ልክ ወደ መልካም ተጣሪዎች እንዳሉት ሁሉ ፡ ወደ መጥፎ ተጣሪዎችም አሉ

☞ሰዎች ደግሞ ከመልካም ተጣሪዎች ይልቅ ወደ መጥፎ ተጣሪዎች የቀረቡ ናቸዉ ፡ ምክንያቱም ነፍሶች ወደ ፊትና እና ወደ ሹብሀ የተዘነበሉ ናቸዉ አሏህ ያዘነለት ሲቀር ]

ምንጭ ☞ሸርህ ኪታብ አል-ፊተን ወል ሀዋዲስ [83]
👉http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
🎯የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ🎯
#ዑስማን #ኢብን #ዐፋን ( ረዲየሏሁ ዐነሁ) የዒባዳን ጥፍጥና በአራት (4 ) ነገሮች አግኘው አሉ :-

➊አላህ ያዘዘውን ግዴታ በመፈፀም ::

#አላህ ከከለከለው ሐራም ካደረጋቸው ነገሮች
በመራቅ ::

#አላህ በመልካም ያዘዘውን በመፈፀም ::

➍አላህ የሚጠላውን ነገር መሥራት የአላህን ቁጣ
ስሊሚያመጣ ፈርቶ በመተው ናቸው ::

#ኢብኑ #ዑመር የአላህ መልዕክተኛ :
( ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ) ትከሻዬን ያዝ በማድረግ " በዚህች ዓለም ስትኖር እንደ መንገደኛ ሁን " አሉኝ ማለቱ ተዘግቧል ::

#አራት #ነገሮች አሉ ላዩን ስናያቸው ምንዳ ያላቸው ውስጡን ስንመለከታቸው ግን ግዴታ መሥራት ማድረግ ያለብን ነገሮች ናቸው :: እነሱም :-
➊ከአላህ ሰዎች ጋር አብሮ መኖር

#ቅዱስ #ቁርአንን መቅራት

➌ቀብርን መጎብኘትና

➍የታመመ ሰው መጠየቅ ናቸው ።

ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር
http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
SHARE 🔗SHARE
የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ
ስለ ሰው ልጅ ክህደት የአላህ ፍጥረቶች ምን አሉ?
"
👉 ምድር በየቀኑ እንዲህ በማለት ጌታዋን ትጣራለች፦ «ጌታዬ ሆይ የሰው ልጅን ልዋጠው ፍቀድልኝ እርሱኮ ያንተን ሲሳይ እየበላ አያመሰግንህም»

👉 ተራራም እንዲህ በማለት የጌታዋን ፍቃድ ትጠይቃለች፦ «ጌታዬ ሆይ የሰው ልጅን ላጣብቀው ፍቀድልኝ እርሱኮ ያንተን ሲሳይ እየበላ አያመሰግንህም»

👉 ባህርም በተራዋ «ጌታዬ ሆይ የሰው ልጅን እንዳሠምጠው ፍቀድልኝ ፣እርሱ ያንተን እርዚቅ እየበላ አያመሰግንህም» ትላለች

👉 ሰማይም «ጌታዬ ሆይ የሰው ልጅን አንዳች መቅሰፍት ላውርድበት ፍቀድልኝ እርሱ የአንተን ሲሳይ እየበላ አያመሰግንህም» በማለት ትጣራለች።

⭐️ #አሏህም « ፍጥረቶቼ ሆይ,,,, የሰው ልጅን የፈጠራችሁት እናንተ ናቹህን»? ይላቸዋል

✔️«#ጌታችን #ሆይ አይደለም» ይላሉ ጥራት የተገባው አሏህም እንዲህ ይላል፦ እናንተ ብትፈጥሯቸው ታዝኑላቸው ነበር።

የነሱን ጉዳይ ተውልኝ እስኪ ከነሱ ወደኔ የተመለሰ (የተፀፀተ) እኔ ወዳጁ ነኝ። እኔኮ እናት ለልጇ ከምታዝነው በላይ ለባሮቼ አዛኝ ነኝ። ከነሱ ወደኔ ተፀፅቶ የተመለሰ «አንተ ተውበት አድራጊ ሆይ
እንኳን ደህና መጣህ ብየ ከርቀት እቀበለዋለሁኝ ።

ወንጀል ሰርቶ ከኔ ለሚሸሸው ደግሞ፦ ወደርሱ ቀርቤ ፦ ባርያዬ ወዴት ነው የምትሄደው ከእኔ ውጭ ሌላ ጌታ አገኘህን፤ ከኔ ውጭስ ሌላ አዛኝ የሆነ ጌታ አገኘህን የምትሸሸኝ »በማለት እጠራዋለሁኝ።

👉 ጌታዬ ሆይ ከርቀት የምትቀበለው ወዳንተ ተመላሽ ባርያ አድርገን።አሚን

SHARE 🔗SHARE
http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
👉 የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ👈
"يَا كَثِيرَ القَبَائِح ...
غَدًا تَنطِقُ الجَوَارِح "
አንተ የብዙ መጥፎ ሥራ ባለቤት ሆይ!
ነገ አካላቶቻችን እንደሚናገሩ እወቅ።
ابنُ الجَوزيِّ رَحِمَهُ اللّٰه

🔗SHARE 🔗SHARE
http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
አረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች
ሙዓዝ ኢብኑ ጀበል - ረዲየላሁ ዐንሁ - እንዲህ ይላል :-
" ዕውቀትን ፈልጉ (ተማሩ ) እሱን መማር አላህን መፍራት ነው
"እውቀትን መፈለግ ዒባዳ ነው
መማማሩ አላህን ማጥራት ነው
ብይኖችን ከእውቀት ፈልጎ ማውጣቱ ጂሃድ ነው
ለማያውቀው ማስተማሩ ሰደቃ ነው
ለባለቤቶቹ ማካፈሉ ወደ አላህ መቃረቢያ ነው
ብቸኛ ስትሆን አጫዋችህ ነው
በባዶ ቤት ስትሆን ጓደኛ ነው "
ጃሚዑ በያኒል ዒልሚ ወፈድሊሂ : ( 1/ 54

http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
አረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ
☞የሠዉ ልጂ ሁለት ግዜ አሏህ ፊት ይቆማል

①) የመጀመርያዉ በዱንያ ላይ እያለህ የምትሰግደዉ ሶላት ነው።

②) የሁለተኛዉ የውመል ቂያማህ ነው።

▼☞ የሁለተኛዉ አሏህ ፊት አቋቋምህ ያማረ  እንዲሆን ከፈለክ የመጀመርያዉን ☞አቋቋምህ አሳምር።

ኢብኑል ቀ-ይ'ዩም

SHARE 🔗SHARE
http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ
~ለውጤታማ ስራ~
🚩ፍሬ ያለው መልካም ስራ መስራት ከፈለግክ የሚከተለውን መንገድ ተከተል። ምንዳው የተሟላ፤ ስራውም ስኬታማ ይሆንለሃል።
:የምትሰራውን ስራ አሳንሰህ ተመልክተው። ካሳነስከው ከመኩራራት ትጠበቃለህ፤ ስራውም ይተልቅለሃል።
:የምትሰራውን ስራ ደብቀው። ከደበቅከው ሪያእ/ታይታ/ ስራህን አያበላሸውም።
:የጀመርከውን ስራ አፍጥነው። ካፈጠንከው ከሸይጧን የውስወሳ ወጥመድ ታመልጣልህ። ከመጥፎ ጥርጣሬም ትድናለህ

http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
አረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ
#✍️ኢልም ትልቅ ቦታ አለዉ‼️

♻️قال ابن الجوزي رحمه الله تعالىٰ
🔺
#ኢብኑ ጀዉዚይ አሏህ ይርሀማቿና እንዲ አሉ ‼️
🔘
💢 من أحب أن يكون للأنبياء وارثًا وفي مزارعهم حارثًا فليتعلم العلم النافع وهو علم الدين ففي الحديث : « العلماء ورثة الأنبياء »،
📌
#ለነቢያቶች ወራሽ በማሳቸዉ አራሽ ሊሆን የፈለገ ሰዉ ጠቃሚ እዉቀትን ይማር እሱም ዲንን ማወቅ ነዉ #በሀዲስ ዉስጥ "ኡለሞች የነቢያቶች ወራሽ ናቸዉ" ይላል
وليحضر مجالس العلماء، فإنها رياض الجنة،
📌
#እንዲዉም የኢልም መቀመጮችን ይጣድ እሱዋ የጀነት ጨፌ ናት‼️
🔘
🔘
⭕️ ومن أحب أن يعلم ما نصيبه من عناية الله، فلينظر ما نصيبه من الفقه في دين الله، ففي الحديث : « من يرد الله به خيرًا يفقهه في الدين »،
📌💢
#ከአለህ ትክረት ሆኖ ያለዉን ድርሻ ሊያዉቅ የፈለገ ሰዉ በአለህ ዲን ሆኖ ያለዉን ግንዛቤ ልክ ይመልከት #በሀዲስ ዉስጥ "አሏህ ኸይር ያሻለት ሰዉ በዲን ላይ ግንዛቤን ይሰጣዋል" ይላል‼️
🔘🔘
⭕️ ومن سأل عن طريق تبلغه الجنة، فليمش إلىٰ مجلس العلم، ففي الحديث : « من سلك طريقًا يلتمس فيها علمًا سلك الله به طريقًا إلىٰ الجنة »،
📌💢
#ወደ ጀነት ምታደርሰዉን መንገድ የጠየቀ የኢልም መቀመጫ ይሂድ በሀዲስ ዉስጥ "መንገድን የገባ በሱ ኢልምን ሚፈልግ ሴሆን አሏህ በሱ መሄድ ወደ ጀነት ያለ መንገድ ያስገቧል" ይላል‼️
🔘🔘
💢 ومن أحب ألاّ ينقطع عمله بعد موته فلينشر العلم بالتدوين والتعليم، ففي الحديث : « إذا مات الإنسان انقطع عمله إلاّ من ثلاث صدقة جارية، أو علم ينتفع به، أو ولد صالح يدعو له » .
📌⭕️
#ከሞተ ቦሃላ ኸይር ስራዉ ላይቁዋረጥበት የፈለገ ኢልምን በመፃፍም ና በማስተማር ያሰራጭ በሀዲስ ዉስጥ "ሰዉ የሞተ ግዜ ስራዉ ይቆረጣል ከሶስት ነገር ስቀር #ቀጣይነት ያለዉ ሰደቃ #ወይም ሰዎች ምጠቀሙበት ኢልም ያስቀመጠ #ወይም ጥሩ ልጅ ለሱ ዱዓ ምያደርግለት ልጅ ስቀር" ይላል!!

📚 "التذكرة في الوعظ" (٥٥/١)**
📚{{ምንጭ "አተዝኺረቱ ፊል ወዕዚ" 1/55"}}
////
ኢልም.ኢልም.ኢልም.የዱኒያ.ና.የአኼራ.ብርሃን‼️

⭕️ኢልምን እንዉረስም እናዉርስም አደራ አደራ

http://www.tg-me.com//@arebgendamesjid
አረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ
2024/09/28 20:19:07
Back to Top
HTML Embed Code: