Telegram Web Link
በአሜሪካ ማእከል የአትላንታ ንዑስ ማእከል 6ኛውን የሐዊረ ሕይወት ጉዞ አካሄደ::

በአትላንታ ንዑስ ማእከል ቅዳሜ የካቲት 29 ቀን 2017  የሐዊረ ሕይወት ጉዞ አካሄደ:: ንዑስ ማእከሉ ለ6ኛ ጊዜ ባዘጋጀው ጉዞ፤ መድረሻው ያደረገውን ራዝዌል ቅድስት ማርያም የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ባደረገው  ጉዞ ላይ በርካታ ምእመናንን በአስር አውቶውቡሶች መነሻውን ከአትላንታ መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ካቴድራል ነበር ያደረገው። በዚህ ዙር  ትኩረቱን በክርስትያን መንፈሳዊ ሕይወት እድገትና ማነቆዎች ላይ በማድረግ በተዘጋጀው ሐዊረ ሕይወት ጉዞም ትምህርተ ወንጌል በመምህራን  እንዲሁም  ከምእመናንም ለንዑስ ማእከሉ በተለያየ መንገድ ለቀረቡ ጥያቄዎች በምክረ አበው መርሐ ግብር  በአባቶች በስፋት መልስ ተሰጥቶባቸዋል::
በአጠቃላይ ምእመናን የራሳቸውን መንፈሳዊ ሕይወት እድገት የሚያዩበት እና በመንፈሳዊ ሕይወታቸው አድገው ለልጆቻቸው ምሳሌ መሆን እንዳለባቸው የተማሩበት በመሆኑ ይህንን መሰሉ ጉባኤ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስተያዬታቸውን ሰጥተዋል።

በተጨማሪ በሀገረ አሜሪካ ለተወለዱ ልጆች እና ወጣቶች በሚረዱት ቋንቋ ትምህርት እና ውይይት በተጋበዙ መምህራን ተካሂዷል።  በዚህ ጉዞም እድሜአቸው 18 እና  ከዛ  በላይ  ለሆኑ የሁለተኛ ደረጃ ና የኮሌጅ  ተማሪዎች ከራሳቸው በተሰበሰቡ ጥያቄዎቻቸው ዙርያ ለመጀመርያ ግዜ የምክረ  አበው መርሐ ግብር የተከናወነ ሲሆን  በውይይቱም ተሳታፊ ተኪና አዳጊ ልጆቻችን  እንደተደሰቱበት ለማየት  ተችሏል ::

በዚህ የሕይወት ጉዞ ለመሳተፍ ከ4 ሰዓት በላይ በመንዳት አጎራባች ከሆነው ካሮላይ ከተማ የሚገኙ ምእመናንም ተሳታፊ መሆናቸውን ዘጋቢያችን ከአትላንታ አድርሶናል፡፡ የዜናው ጥንቅር የአሜሪካ ማእከል ሚዲያ ክፍል ነው፡፡
2025/03/15 03:24:43
Back to Top
HTML Embed Code: