Telegram Web Link
በከፋ ሀገረ ስብከት ቦንጋ ከተማ ለሚገነባው አዳሪ የአብነት ት/ቤት የመሰረት ድንጋይ የማስቀመጥ መርሐ ግብር ተከናወነ።

የካቲት ፴/፳፻፲፯ ዓ.ም

የከፋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ፣ የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ሃይማኖት ቀሲስ ዘውዴ ገብረ ጻድቅ ፣ የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ሥራ አስፈፃሚ መምህር ዋሲሁን  በላይ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የአካባቢው ምእመን በተገኙበት በኬያ ኬላ ደብረ መንክራት አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።

ብፁዕነታቸው በመልእክታቸው  የሚገነባው አብነት ትምህርት ቤት ለከፋ ሀገረ ስብከት ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ለደቡብ ክልል ለሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት አገልጋዮችን የሚያፈራ ታላቅ ኘሮጀክት ነው ብለዋል።

አብነት ትምህርት ቤት ከሌለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልትኖር አትችልም ያሉት ብፁዕነታቸው  አክለውም ይህ ጉባኤ ቤት እናተ የዓለም ብርሃን ናችሁ የተባሉ ደቀ መዛሙርቱ የሚወጡበት የቤተ ክርስቲያን ማኅጸን የሚሆን ነው በማለት ተናግረዋል።

የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ሃይማኖት ቀሲስ ዘውዴ ገ/ፃድቅ በበኩላቸው "ማኅበረ ቅዱሳን ፕሮክቱን በዚህ ለመተግብር ይህን የመሰረት ድንጋይ ሲያስቀምጥ ለተዘጋችው ቤተ ክርስቲያን ሲል በጎ አድራጊዎችን አስተባብሮ በመሆኑ የተሰጠንን ዕድል በአግባቡ መጠቀም ይጠበቅብናል በማለት በመርሐ ግብሩ ላይ ለታደሙ ምእመናን መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከ 100,000 ሺህ በላይ ደቀመዛሙርት ያሏት ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን ስትሆን ምእመናንን በሃይማኖትና በምግባር በማጽናት የመንግሥተ ሰማያት ዜጋ ለማድረግ እየተጋች ነው ያሉት ደግሞ የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ሥራ አስፈፃሚ መምህር ዋሲሁን በላይ አክለውም አብነት ትምህርት ቤቶቿ ደግሞ በዕውቀትና በመልካም ሥነ ምግባር የታነፁ ከዲያቆናት ጀምሮ እስከ ሊቃነ ጳጳሳት የሚያፈሩ የትምህርት ተቋማት ናቸው በማለት ተናግረዋል።

ማኅበረ ቅዱሳን በ2017 ዓ.ም ከሚተገብራቸው ፕሮጀክቶች ውስጥ በከፋ ሀገረ ስብከት በቦንጋ ከተማ የሚገነባው አዳሪ አብነት ትምህርት ቤት አንዱ ፕሮጀክት መሆኑን በመጥቀስ የፕሮጀክቱ ዓላማ በሀገረ ስብከቱ  መሰረታዊ የክህነት ትምህርት እና ሥልጠና በመስጠት ቀሳውስት ፣ዲያቆናት ፣ ሰባኪ እና አስተዳዳሪ ደቀመዛሙርትን በማፍራት የተዘጉ አብያተ ክርስቲያናት እንዲከፈቱ እና የተሟላ መንፈሳዊ አገልግሎት የማይሰጡትም እንዲሰጡ በማድረግ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ተልዕኮ ማፋጠን ነው በማለት መምህር ዋሲሁን በላይ አክለዋል።

ማኅበሩ በተለያዪ አህጉረ ስብከት ከሚተገብራቸው ፕሮጀክቶች በተጨማሪ በ171 ለተመረጡ  የአብነት ትምህርት ቤቶች ለ239 መምህራን እና ለ2230 ደቀመዛሙርት  በዓመት ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ ድጎማ እያየረገ እንደሚገኝ መምህር ዋሲሁን በላይ ጠቁመዋል።

ማህበረ ቅዱሳን ትኩረት ሰጥቶ ከሚሰራቸው  ተግባራት መካከል የአዳሪ አብነት ት/ቤቶችን በመገንባት የሐዋርያዊት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ሳይበረዝ እና ሳይከለስ ለትውልድ ለማስተላለፍ እየሰራ እንደሚገኝ ይታወቃል።

ማኅበሩ ከዚህ ቀደም በየአህጉረ ስብከት ያስገነባቸው ጉባኤ ቤቶች መልካም ውጤት እያስመዘገቡ ሲሆን  ይህ ፕሮጀክትም ተገንብቶ ሲጠናቀቅ በቋንቋ አገልግሎት ያለውን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

አዳሪ አብነት ትምህርት ቤቱ 32 ደቀመዛሙርትን በአዳሪነት ፣ ለሁለት መምህራን ማደሪያ ፣ መማሪያ ጉባኤ ቤት ፣ መጸዳጃ ቤት እንዲሁም መመገቢያ አዳራሽን ያካተተ ሲሆን ለፕሮጀክቱ የተያዘለት በጀት 11, 852,172  ብር እንደሆነ ተገልጿል።
“He went into their synagogue” (Matthew 12:9)
The third week of “The Great Lent” is known as “Synagogue” according to the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church education. Our Lord and Savior Jesus Christ entered to this synagogue, which served as the temple of Jews. Whilst in His teaching age in Jerusalem, there were synagogues in which the apostles also thought the gospel. 
On the Sabbath known as “synagogue”, Our Lord rebuked the changers, threw out those who made the temple cattle drive and sells of gold along their things. It is stated in the gospel of John as, “He found in the temple those who sold oxen and sheep and doves, and the money changers doing business. When He had made a whip of cords, He drove them all out of the temple, with the sheep and the oxen, and poured out the changers’ money and overturned the tables.” (John 2:14-15)
He also thought them saying “my house is a prayer place;” but you have made it a ‘den of thieves.” (Luke 19:46) The hymn of Saint Jared for this Sabbath, all the lyrics, songs and readings are correlated with our Lord’s teachings, preaching and miracles.
Epistles: – (Colossians 2:16 up to the end) (James 2:14 up to the end)
Gospels, (John 2:12 up to the end)
(Acts 10:1-8)
“Mesebak” Prophets David’s words in rhyme; “for the zeal of thine house has eaten me up; and the reproaches of them that reproached thee are fallen upon me.” (Psalm 68:9)
May God’s mercy be upon us and Glory be to Him!
ዜና ገዳማት
  ማኅበረ ቅዱሳን በገዳማትና በአብነት ት/ቤቶች ላይ እየሰራቸው የሚገኙ ተግባራት ሪፖርት ወር በገባ የመጀመሪያው ማክሰኞ መጋቢት 2 ቀን 2017 ዓ.ም  ልዩ መርሐ ግብር ይቀርባል።
የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤያት  ተመራቂ ተማሪዎች በስጦታ የተበረከተላቸውን ሽልማት  ለማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል ማስረከባቸውን ጅግጅጋ ማእከል አስታወቀ

መጋቢት ፩/፳፻፲፯ ዓ.ም 

በማኅበረ ቅዱሳን የጅግጅጋ ማእከል በዩኒቨርሲቲው ግቢ ጉባኤያት ተማሪዎች በ2016 እና 2017 የትምህርት ዘመን ለማኅበራቸው በስጦታ ያስረከቧቸውን ሦስት ዋንጫዎችና አንድ ሜዳሊያ የግቢ ጉባኤው እና የማእከሉ ሥራ አስፈጻሚ ተወካዮች በጋራ በተገኙበት የካቲት 30/2017 ዓም ለዋናው ማእከል አስረክበዋል።

ዲ/ን መንግሥቱ አዲስ የጅግጅጋ ጽ/ቤት ኃላፊ፣  ዲ/ን አሳልፍ  የግቢ ጉባኤው ም/ሰብሳቢ   ማእከሉን እና ግቢ ጉባኤውን ወክለው ዋንጫዎቹን እና ሜዳሊያውን ያስረከቡ ሲሆን የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ማእከለን በመወከል በግቢ ጉባኤው  ጽ/ቤት በመገኘት ስጦታዎቹን  የተረከቡት መጋቤ ብርሃናት  ቀሲስ ሙሉቀን ብርሃኑ ናቸው ተብሏል።

መጋቤ ብርሃናት  ቀሲስ ሙሉቀን አባታዊ መልእክታቸውን ያስተላለፉ ሲሆን በመልእክታቸውም የግቢ ጉባኤ  ተማሪዎቹ  ለዘመናት በዓለማዊ ትምህርት ጠንከረው ለመሥራታቸው ምስክሮች የሆኑትን  እነዚህን ዋንጫዎች እና ሜዳሊያዎች ለማኅበረ ቅዱሳን ማስረከባቸው እጅግ የሚያስደንቅና ለማኅበራቸው ያላቸውን ፍቅርና ቁርጠኝነት የሚገልጽ ነው ብለዋል።

አክለውም  ማኅበሩ  በቅዱስ  ሲኖዶስ የተሰጠውን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን መንፈሳዊ ትምህርት የማስተማር ኃላፊነት ወደ ፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸው ለስኬቱም ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጠይቀዋል።
በተጨማሪም  ተማሪዎች በተማሪነት ዘመናቸው የሚያሳዩትን የአገልግሎት ትጋት ወደ ሥራ ዓለም ከተቀላቀሉ በኋላም እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።
በባሌ ሮቤ ማእከል ሥር ለሚገኙ ወረዳ ማእከላት እና ግንኙነት ጣቢያዎች የአባላት ማትጊያ መርሐ ግብር ለሦስት ተከታታይ ቀናት መካሄዱ ተገለጸ።

መጋቢት ፩/፳፻፲፯ ዓ.ም

በማኅበረ ቅዱሳን ባሌ ሮቤ ማእከል ሥር ለሚገኙ ወረዳ ማእከላት እና ግንኙነት ጣቢያዎች የአባላት ማትጊያ መርሐ ግብር ከየካቲት 28 እስከ 30 ቀን 2017 ዓ.ም በሮቤ ፈለገ ብርሃን ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን መካሄዱ ተገልጿል።

በመርሐ ግብሩ አቶ ታምራት ዴቢሳ የማኅበረ ቅዱሳን ሐዋሳ ማእከል ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፣ ዶ/ር ሙሉቀን ገዝሙ የባሌ ሮቤ ማእከል ሰብሳቢ፣ የማእከላት ፣ የወረዳ ማእከላት እና ግንኙት ጣቢያዎች ሥራ አስፈጻሚ አባላት ተገኝተውበታል።

የማኅበረ ቅዱሳን ሐዋሳ ማእከል ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ታምራት ዴቢሳ  በአዲሱ የማኅበረ ቅዱሳን መዋቅራዊ ለውጥ፣ የማኅበሩ ባሕል፣ መንፈሳዊ መሪነት እና ባሕርያት በሚሉ ርዕሰ ጎዳዮች ላይ ለተሳታፊዎች ሰፋ ያለ ሥልጠና የተሰጠ ሲሆን ትምህርተ ወንጌል፣የበገና ዝማሬ፣ ስለ ኦሮቶዶክሳዊ መዝሙራት፣ስለተከለሰው የግቢ ጉባኤያት ስርዓተ ትምህርት መሠረታዊ ጉዳዮች እና አባላትን እንዴት በማትጋት ለአገልግሎት ልናበቃ እንችላለን በሚሉ ርዕሶች በተለያዩ የማእከሉ የክፍላት ኃላፊዎች ሥልጠና እና ውይይት ተካሄዷል።

በቀጣይ ተሳታፊዎቹ በወረዳ ማእከላቸው እና በግንኙት ጣቢያቸው ላሉ አባላት ይህን የአባላት ማትጊያ እና ስለማኅበሩ ተቋማዊ ለውጥ ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ እንደሚያከናውኑ አስተያየታቸውን ለግሰዋል ።
2025/03/15 19:59:29

❌Photos not found?❌Click here to update cache.


Back to Top
HTML Embed Code: