“ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ” በሚል መሪ ቃል የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር መካሄዱን የአቡዳቢ የግንኙነት ጣቢያ ገለጸ
የካቲት ፳፭/፳፻፲፯ ዓ.ም
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/ በሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የአቡዳቢ ልዩ ግንኙነት ጣቢያ 5ተኛውን የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር “ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ” (ኤፌ ፭፥፲፮) በሚል መሪ ቃል ቅዳሜ የካቲት 22 ቀን 2017 ዓ.ም በአቡዳቢ ምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም መከናወኑ ተገልጿል።
ጸባቴ አባ ፍ/ማርያም ተከስተ (ቆሞስ) የአቡዳቢ ምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ወአቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም አስተዳዳሪ፣ መላከ ፀሐይ ቀሲስ ኪሩቤል ይገዙ የራስ አልኬማ ደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ፣ የገዳሙ ቀሳውስት፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም የተስፋ ስዱዳን ሰንበት ትምህርት ቤት አባላትና ምእመናን በተገኙበት ዝግጅቱ ተካሂዷል።
በመርሐ ግብሩ መዝሙር በማኅበሩ፣ በተስፋ ስዱዳን ሰንበት ትምህርት ቤትና በግቢ ጉባኤ አባላት የቀረበ ሲሆን መምህር እስጢፋኖስ “ከእርሱም በተደረገው ድንቅ ነገር ሕዝቡ ሁሉ ደስ አላቸው” በሚል የዕለቱን ወንጌል ሰጥተዋል።
የዋናው ማእከል የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዲ/ን ሲሳይ ብርሃኑ የማኅበሩ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን በማስከተልም ስለ ግንኙነት ጣቢያው አጠር ያለ የስራ ሂደት በግንኙነት ጣቢያው የሕዝብ ግንኙነት ተወካይ መቅረቡ ተገልጿል።
በመጨረሻም በአባቶች ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ተሰጥቷል።

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Ready for an Epic Gathering, yet again?
Calling all incoming freshmen, college students, and recent grads! Join us for our 7th in-person General Assembly this July in Atlanta! Don’t miss out – register now to secure your spot using the link below. Let’s embark on this spiritual journey of connection and enlightenment together.
We can’t wait to see you!
Registration form:
https://forms.gle/cqgiQz4tcv8SwNhU6

"ምንጮች እንዳይደርቁ ጉባኤ ቤቶችን እንገንባ" በሚል መሪ ቃል የምክክርና የዉይይት መርሐ ግብር መካሔዱን ማኅበረ ቅዱሳን የባሕር ዳር ማእከል ገለጸ
የካቲት ፳፰/፳፻፲፯ ዓ.ም
ማኅበረ ቅዱሳን የባሕር ዳር ማእከል ከባሕር ዳርና ሰሜን ጎጃም አኅጉረ ስብከቶች ጋር በመተባበር የአብነት ጉባኤ ቤቶች ልዩ የምክክርና የውይይት መርሐ ግብር ከየካቲት 26 እስከ 27/6/2017 ዓ.ም ማካሔዱን ተልጿል፡፡
በጉባኤው የባሕር ዳርና የሰሜን ጎጃም አኅጉረ ስብከቶች፣ የወረዳ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጆች፣ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ የሰበካ ጉባኤ ተወካዮች፣ የአብነት ጉባኤ ቤት መምህራን ተወካዮችና ከ130 በላይ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል፡፡
የባሕር ዳር ማእከል ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አይሸሹም የኔው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን በጉባኤው መክፈቻ መርሐ ግብር ክቡር መልአከ ሰላም ኤፍሬም ሙሉዓለም የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ተገኝተው መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ በመልእክታቸውም ጉባኤ ቤቶች መሠረቶቻችን መሆናቸውን አንስተው “ሁላችንም በጉባኤ ቤቶቻችን ላይ በትኩረት ልንሠራ ይገባል” ብለዋል፡፡
መርሐ ግብሩ የአብነት ት/ቤቶችን የሚመለከት ዳሰሳዊ ጽሑፍ በዲ/ን ግሩም መሠረትና የአብነት ት/ቤቶች ሚና ትናንት፣ ዛሬና ነገ የሚል ጽሑፍ በመ/ር አስተርዓየ ገላው ቀርበው ሰፊ ዉይይት የተደረገባቸው ሲሆን በውይይቱም የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበው የቀጣይ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል፡፡
በዝግጅቱ የግብጽ ኮፕቲክ ቤተ ክርስቲያን ተሞክሮ በመ/ር ኃይለማርያም ዘውዱና የአብነት ት/ቤቶችን አስተዳደር ለማዘመን የተዘጋጀው የመረጃ ቋት መተግበሪያ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሶፍትዌር ባለሙያ፣ የገዳማትና መንፈሳዊ ት/ቤቶች አገ/ት ዋና ክፍል አባል በሆኑት ወንድም ጌትነት መቅረቡ ተጠቁሟል።

በጉባኤው የመፍትሔ ሐሳቦችን የሚያመላክት አጭር መነሻ ሐሳብ በዲ/ን አዲሱ ሙሉጌታ በማንሳት በቡድን በውይይቱ የተደረገ ሲሆን የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት የትምህርት መምሪያ ኃላፊ ሊቀ ጉባዔ ሙሉጌታና የሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት ትምህርት ክፍል ኃላፊ መ/ገነት መልአከ የማጠቃለያ ሃሳብ ሰጥተዋል፡፡
ከሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት ተወክለው የተገኙት መልአከ ምህረት ግሩም አለነ የሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ አገልግሎት ክፍል ኃላፊ ጉባኤውን ያዘጋጀውን ማእከሉን አመስግነው ሁሉም የቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅር ለጉባኤ ቤቶች ልዩ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በመጨረሻም ጉባኤዉን በተመለከተና በቀጣይ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር መሥራት በሚቻልባቸዉ ጉዳዮች ዙሪያ የማኅበሩን አቅጣጫዎች የማአከሉ ጽ/ቤት ኃላፊ በሆኑት አቶ አይሸሹም የኔው ቀርበው መርሐ ግብሩ ተጠናቋል፡፡

ምኵራብ
የቤተ ክርስቲያን እንዚራ ቅዱስ ያሬድ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ምኵራብ መግባት አይቶ በወንጌል የተጻፈውን ተርጒሞ ሳምንቱን በዜማ ያንን ቤተ መቅደስ የገባበትንና ቤተ መቅደሱ ውስጥ ይሸጡ ይነግዱ የነበሩ ወንበዴዎችን ያባረረበት ቅጽበት አንሥቶ ለጾሙ ሳምንት ምኵራብ ብሎ አርእስት ሰጥቶታል።
ምኵራብ “ቤተ አዳራሽ፣ ኮረብታ፣ ተራራ የሚያህል ታላቅ ሕንጻ፣ ሰቀላ መሰል አዳራሽ” ማለት ሲሆን ናቡከደነጾር ኢየሩሳሌምን ወርሮ ቤተ መቅደሱን ባፈረሰበት ሰዓት እና ሕዝቡንም በምርኮ ወደ ባቢሎን በአግአዘ (በአፈለሰ) ወቅት በምርኮ ሀገር ሆነው እግዚአብሔርን የሚያመልኩበት፣ ለጸሎት እና መሥዋዕት ማሳረጊያ ይሆናቸው ዘንድ ባገኙት ቦታ ድንኳን ይተክሉ (የጸሎት ቤት ይሠሩ)ነበር። (ሕዝ.፲፩፥፮፣ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ገጽ ፷)
በዚያ ምኩራብም መጻሕፍትን ያነቡ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ይማሩ፣ የአምልኮ እና የጸሎት ሥርዓት ይፈጽሙ ነበር፤ ከሕግና ከነቢያት፣ ከዳዊት መዝሙራትም ይዘምሩ ነበር፥ ስብከት እና ቡራኬም ነበር፤ሕግ ያፈረሱትን በፍርድ የሚቀጡበትም ቤት ነው። ይህም የሚሆነው በሰንበት ቀን ነበር። (ማቴ.፬፥፳፫፣ ሐዋ.፮፥፱፣ ፱፥፪፣ ዮሐ.፱፥፴፬፣ ፪ኛ ቆሮ. ፲፩፥፳፬፣ ሉቃ.፬፥፲፮)
ጌታችንም በሰንበት ቀን እየሄደ ሕዝቡን ያስተምር፣ ድውያንን ይፈውስ፣ አንካሳውን እንዲራመድ ያደርግ ነበር፤ ሽባውን ይተረትር፣ ለምጻሙንም ያነጻ ነበር። ከነቢያት መጻሕፍትን ከመዝሙርም እየጠቀሰ ያስተምራቸው ነበር። (ማቴ.፳፩፥፲፬፣ ማር.፩፥፳፩፣ ፭፥፴፭፣ ሉቃ.፬፥፲፮)
ይህን አይቶ ቅዱስ ያሬድ በድጓው እንዲህ አለ፤ "ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ ወመሐረ ቃለ ቃለ ሃይማኖት ለአይሁድ ወይቤሎሙ ምጽዋተ አበድር እመሥዋዕተ፤ አነ ውእቱ እግዚኣ ለሰንበት ወአቡሃ ለምሕረት እግዚኣ ውእቱ ለሰንበት ወልደ እጓለ እመሕያው ኢትግበሩ ቤተ አቡየ ቤተ ምሥያጥ፤ ቤትየሰ ቤተ ጸሎት ይሰመይ ቦአ ምኩራቦሙ ወገሠጾሙ ያርምሙ አንከሩ ምሕሮቶ ሞገሰ ቃሉ ወጣዕመ ነገሩ ወሣዕሣዓ አፉሁ፤ ኢየሱስ ወደ አይሁድ ምኵራብ ገባ፤ የሃይማኖትም ቃል አስተማረ፡፡ ከመሥዋዕት ይልቅ ምጽዋትን እወዳለሁ፤ የሰንበት ጌታዋ የምሕረት አባትዋ እኔ ነኝ አላቸው፡፡ የአባቴን ቤት የሸቀጥ ቦታ አታድርጉት፡፡ ቤቴ የጸሎት ቤት ተብሎ ይጠራል፡፡ ወደ ምኵራብ ገብቶ ተቈጣቸው፡፡ ዝም እንዲሉም ገሠጻቸው፡፡ እነርሱም ትምህርቱን፣ የቃሉን ግርማ፣ የአነጋገሩንም ጣዕም፣ የንግግሩንም ርቱዕነት አደነቁ፡፡" (ጾመ ድጓ ዘምኩራብ ዘሰንበት)
የሊቁን ሐሳብ ይዘን ብንመረምር ብዙ ጠቃሚ ነገሮችን እናገኛለን። በዋናነት ግን ሁለት ዐምድ የሆኑ ጉዳዮችን እናገኛለን። የመጀመሪያው ጌታችን ወደ አይሁድ ምኵራብ ገብቶ እንዳስተማረ፤ የሃይማኖትንም ቃል እንደነገራቸው ስለ ምጽዋት፣ ስለ ሰንበት ጌትነቱ፣ ስለ ምሕረት እንዳስተማራቸው የምናገኝበት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ አንጽሆተ ቤተ መቅደስ ያደረገበትን ቦታ እናገኛለን። ቅዱስ ያሬድም ጌታችንን ወደ ምኵራብ የገባበትን እና ቤተ መቅደሱን ያነጻበትን ምክንያት በማድረግ ሳምንቱን ምኩራብ ብሎ የጠራው። እስኪ ሁለቱን ሐሳቦች አንድ በአንድ እያነሣን እንመልከታቸው፡-
የመጀመሪያውን በተመለከተ ወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ ወደ ምኵራብ መሄዱን እና የሄደበት ጊዜ ደግሞ ፋሲካቸው መዳረሻ አካባቢ እንደሆነ እንዲህ በማለት ይነግረናል። “ከዚህ በኋላ ከእናቱና ከወንድሞቹ ከደቀ መዛሙርቱም ጋር ወደ ቅፍርናሆም ወረደ፥ በዚያም ጥቂት ቀን ኖሩ። የአይሁድ ፋሲካም ቀርቦ ነበር፥ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ።" (ዮሐ.፪፥፲፪-፲፫)
አይሁድ በምኵራባቸው በሰንበት ቀን እንደ ልማዳቸው መሠረት ጸሎት መጸለይ፣ ትምህርት መማር፣ መጻሕፍትን ማንበብ ያዘወትሩ ነበር። ኢየሱስም የተገኘው በዚሁ ዕለት ነው። ያን ጊዜ ደግሞ የአይሁድ ፋሲካ ነበር። ወንጌላዊው ይህን ፋሲካ ከእግዚአብሔር ፋሲካ ሲለይ የአይሁድ ፋሲካ ብሎ ጠራው። (ዘዳ.፲፪፥፲፩)
ነቢዩ ኢሳይያስ የአይሁድ ፋሲካን ከእግዚአብሔር ፋሲካ መለየቱን እና እግዚአብሔርም እንዳልተደሰተበት የሚነግረን “መባቻችሁንና በዓላቶቻችሁን ነፍሴ ጠልታለች፤ ሸክም ሆነውብኛል፥ ልታገሣቸውም ደክሜያለሁ።" (ኢሳ.፩፥፲፬)
እግዚአብሔርን የኃጢአተኞች ድግስ ደስ አያሰኘውም። የእርሱን ፋሲካ የሚያርጉት ግን እግዚአብሔር ወደዚያ እንዲመለከት ያደርገዋል። መጽሐፍ "ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው። የተቀደሰ ጉባኤ ብላችሁ የምታውጁአቸው በዓላቶቼ፥ የእግዚአብሔር በዓላት፥ እነዚህ ናቸው" የሚለው ለዚህ ነው። (ዘሌ.፳፫፥፪)
በዚህም አይሁድ ከተሠራላቸው ሕግ እንደራቁ፣ ከአምልኮተ እግዚአብሔር ይልቅ በወግ አጥባቂ ሕግ እንደታወሩ መረዳት ይቻላል። ጌታችንም ወደ ምኵራብ በገባ ጊዜ የልቡና ዓይናቸው እንዲገለጥ፣ የዕውቀት ብርሃናቸው እንዲበራ ብሎ ያስተማረውን ትምህርት ነው፤ ቅዱስ ያሬድ "ወደ አይሁድ ምኵራብ ገባ፤ የሃይማኖትን ቃል አስተማረ" የሚለው ነው።
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መጀመሪያ ቤተ መቅደስ የገባው በዐሥራ ሁለት ዓመቱ ነበር። ያን ጊዜ ከመምህራን ትምህርትን ሊማር፣ ሊጠይቅ እንጂ ሊያስተምር አልነበረም። (ሉቃ.፪፥፵፪-፶፪) ከዚያ በኋላም ግን ለማስተማር፣ መጻሕፍትን ያውቁ ዘንድ (ሉቃ.፬፥፲፮) የእውነትን ምሥጢር ይገልጥላቸው ዘንድ ስለ አባቱ ጌትነት፣ ስለ እራሱም የባሕርይ ልጅነት፣ ስለ መንፈስ ቅዱስም የባሕርይ ሕይወትነት ሊያስተምራቸው፣ ከሃይማኖት ይልቅ በወግ አጥባቂ ሕግ ታንቀው ነበርና ያንን ያፈርስ ዘንድ፤ ጾምን፣ ምጽዋትን፣ ወንድማማችነት ሊሰብክ ወደ ምኵራብ ገባ። እነርሱ ግን አላወቁም። የእነርሱንም ድንቁርና አልተረዱም። ይልቁንም የቃሉን ግርማ፣ የአነጋገሩን ጣዕም፣ የንግግሩንም ርቱዕነት ያደንቁ ነበር እንጂ።
አይሁድ ግን የእጁን ተአምር እያዩ፣ የቃሉን ትምህርት እየሰሙ ክፉ ቅንዓት ይዟቸው ነበር። እንዲያውም የምኵራብ መሪዎች እነርሱን እና ቤተ መቅደሱን የሚያዋርድ ይመስላቸውም ነበር። (El Khoury paul Elfaghali: The Gospel of Saint John, The Writhing Syndicate, 1992, page 15)
እግዚአብሔርም ግን በፍቅሩ ስቦ ወደ ቅዱስ መቅደሱ በክብር ያቆመናል። እኛም በእርሱ፣ በአባቱም ፊት ባለሟልነትን እናተርፋለን። ለዚያም ክብር ያብቃን፤ አሜን!
ስብሐት ለእግዚአብሔር፤አሜን!