Telegram Web Link
#እዳታልፉት_ይጠቅማችኋል

#ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_ምን_ማለት_ነው?

1 ኦርቶዶክስ የሚለው ስም ከየት የመጣ ነው?
2 ተዋህዶ የሚለውስ ከየት የመጣ ነው?
3 ክርስትያን ማለትስ ምን ማለት ነው???

1 ኦርቶዶክስ የሚለ ስም ከየት የመጣ ነው?
ኦርቶዶክስ ማለት ቃሉ የግሪክ ሲሆን አማርኛው
ትርጉሙ እውነተኛ፤ቀጥተኛ መንገድ የሆነች ሃይማኖት
ማለት ነው፡፡
ቀጥተኛዋ መንገድ ጠይቁ በእርሷም ላይ ሂዱ
ለነብሳቹሁም እረፍት ታገኛላቹሁ፡፡[ኤር 6÷16]
ነብዩ ኤርምያስ እንዳለው እዚህ ላይ እንግዲህ ቀጥተኛ
ማለት ኦርቶዶክስ ማለት ሲሆን መንገድ ማለት ደግሞ
ሃይማኖት ማለት ነው፡፡
ኢየሱስም ክርስቶስም አለ እኔ መንገድ እውነት
ሕይወት ነኝ ብልዋል፡፡[ዮሐ 14÷6]
ይህ ማለቱም የሃይማኖት መሰረታ ቹሁ እኔ ነኝ ማለቱ
ነው፡፡
ከሰማያዊው ጥሪ ተከፋዮች የሆናቹሁ ቅዱሳን ወንድሞች
ሆይ የሃይማኖታችንን ሊቀ ካህን የሆነውን ኢየሱስ
ክርስቶስን ተመልከቱ፡፡[ዕብ 3÷1]
ስለዚህ ኦርቶዶክስ ማለት ይህ ነው፡፡

2 ተዋህዶ ማለትስ ከየት የመጣ ነው?
ተዋህዶ ማለት ተዋሃደ ከሚለው የግእዝ ግስ
የተወሰደ ሲሆን ትርጉሙ አንድ ሆነ መለኮትና ስጋ አንድ
ሆነ ማለት ነው፡፡ ከሁለት አካል አንድ አካል ፤ከሁለት
ባህሪ አንድ በህሪ ሆነ ማለት ነው በሌላ አካሄድ ደግሞ
ተዋሃደ ማለት መለኮት ስጋ ለበሰ ከድንግል ማርያም
ከስጋዋ ስጋ ከነብሷ ነብስ ነሳ ማለታችን ነው፡፡
ይህም ደግሞ ግልፅ የሆነ እውነት ነው፡፡
በጀመርያ ቃል ነበረ ፤ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ
ነበረ፤ቃልም እግዚአብሔር ነበረ፡፡[ዮሐ 1÷1]
ቃልም ስጋ ሆነ፤ፀጋንና እውነትን ተመልቶ በእኛ አደረ
እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡[ዮሐ1÷14]
ስለዚህ ተዋህዶ ስንል ቃል ስጋ ለበሰ ማለታችን ነው፡፡
በበለጠ ደግሞ ብርሃናዊው የሆነ የዓለም ብርሃን
ቅዱስ ጳውሎስ ቃል በቃል ተዋህዶ የሚለው ፅፎልናል፡፡
ክርስቶስ እርሱ ሰላማችን ተውና፤ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ
የተነገረለት በራሱ አዲስ ሰውን ይፈጥር ዘንድ ሰላምም
አደረገ፡፡[ኤፌ 2÷14-15]
ስለዚ ተዋህዶ ማለትም ይህን ይመስላል፡፡

3 ክርስቲያን የሚለውስ ከየት የመጣ ነው?
ክርስትያን ማለት ከክርስቶስ ስም የተወሰደ ሲሆን
ክርስቶስ ተከታዮች፤አማኞች ማለት ነው፡፡
ክርስቶስ አምላክ ነው፤ጌታ ነው፤ፈጣሪ ነው፤ፈራጅ ነው
ብለን የምናምን ክርስትያን ተብለን እንጠራለን፡፡
የክርስቶስ ሐዋርያትም በአንጾክያ ምክንያት ክርስቲያን
ተባሉ፡፡[ሐዋ 11÷26]
በትዕቢት ተነፍቶ በዲያብሎስ ፍርድ
እንዳይወድቅ፤ሰው ሁሉ አዲስ ክርስቲያን አይሁን፡፡
[1ኛ ጢሞ 3÷16]
ክርስቲያን እንደሚሆን ግን መከራን ቢቀበል ስለዚህ ስም
እግዚአብሔርን ያመስግን እንጂ አይፈር፡፡
[1ኛ ጴጥ 4÷16]
ስለዚህ ሁሉም ከመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተነሳ ነው፡፡
ኦርቶዶክስ ነው ሃይማኖቴ ስን ቀጥተኛ ናት
ሃይማኖታችን እያልን ነው፡፡
=>የተዋህዶ ልጆች ነን ስንልም የክርስቶስ ልጆች ነን
እያልን ነው፡፡
=>ክርስቲያን ነን ስንልም ክርስቶስን የምናመልክ
የምናምን ክርስቲያን ነን፡፡
ማለታችን ነው፡፡
ሌላው እምነት ፤ሃይማኖት ግን ጴንጤ ፤ፕሮቴስንት
፤ካቶሊክ፤ጆባዊስትን ክርስቲያን ነን ቢሉም እነዚህ
የመሳሰሉ ግን ከጥንትም ያልነበረ ስም አዲስ ድርጂት
ነው በመፅሐፍ ቅዱስም አንድም ቦታ ላይ የለም፡፡
ከግዜ ቡሃላ ከኦርቶዶክስ ወጥተው ወደ ምንፍቅና
የተመሩ ድርጅቶች ናቸው፡፡
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ግን ከጥንት የነበረች የነብያት
የሃዋርያት የቅዱሳን ሰማዕታት ሃይማኖት ናት ፡፡አሁን እስከ
ልጅ ልጅ ለዘላለም ትኖራለች፡፡

አንድ ጌታ እንዲት ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር አሜን

(ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር)

@mehereni_dngl✝️
✝️@mehereni_dngl✝️
✝️@mehereni_dngl✝️
በነገው ዕለት ​ነሐሴ 24/12/2015 ዓ.ም

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ

ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፹፫፥፮(83፥6)
እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ
ወየሐውር እምኃይል ውስተ ኃይል
ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን


📖ወንጌል
ወንጌል ዘዮሐንስ ፲፥፩-፳፪(10፥1-22)
አማን አማን እብለክሙ ዘኢቦአ እንተ…


ምንባባት ዘቅዳሴ

👉 ዲያቆን
📖ኀበ ሰብአ ሮሜ ፰፥፴፭-፴፱(8፥35-39)
መኑ የኀድገነ ፍቅሮ ለክርስቶስ…


👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ጴጥሮስ ፩ ም ፭፥፩-፮(5፥1-6)
ወለእለኒ ይትለሐቁ እምኔክሙ አስበቍ…


👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፳፥፳፰-፴፩(20፥28-31)
ወይእዜኒ ዕቀቡ ርእሰክሙ…


📜ምስባክ ዘቅዳሴ

እስመ በእንቲአሁ ይቀትሉነ ኩሎ አሚረ
ወኮነ ከመ አባግዕ ዘይጠብሁ
ንቃህ እግዚኦ ለምንት ትነውም


👉ትርጉም

መዝሙረ ዳዊት ም. ፵፬ ቊ. ፳፪ - ፳፫

፳፪ ስለ አንተ ሁልጊዜም ተገድለናል፥ እንደሚታረዱም በጎች ሆነናል።

፳፫ አቤቱ፥ ንቃ፤ ለምንስ ትተኛለህ? ተነሥ፥ ለዘወትርም አትጣለን።



📜ወንጌል ዘቅዳሴ

የማቴዎስ ወንጌል ም. ፲ ቊ. ፲፮ - ፵፪

፲፮ እነሆ፥ እኔ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ።

፲፯ ነገር ግን ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፥ በምኩራቦቻቸውም ይገርፉአችኋልና ከሰዎች ተጠበቁ፤

፲፰ ለእነርሱና ለአሕዛብም ምስክር እንዲሆን፥ ስለ እኔ ወደ ገዥዎች ወደ ነገሥታትም ትወሰዳላችሁ።

፲፱ አሳልፈውም ሲሰጡአችሁ፥ የምትናገሩት በዚያች ሰዓት ይሰጣችኋልና እንዴት ወይስ ምን እንድትናገሩ አትጨነቁ፤

፳ በእናንተ የሚናገር የአባታችሁ መንፈስ ነው እንጂ፥ የምትናገሩ እናንተ አይደላችሁምና።

፳፩ ወንድምም ወንድሙን፥ አባትም ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፥ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ይነሣሉ ይገድሉአቸውማል።

፳፪ በሁሉም ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።

፳፫ በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ፤ እውነት እላችኋለሁና፥ የሰው ልጅ እስኪመጣ ድረስ የእስራኤልን ከተማዎች አትዘልቁም።

፳፬ ደቀ መዝሙር ከመምህሩ፥ ባሪያም ከጌታው አይበልጥም።

፳፭ ደቀ መዝሙር እንደ መምህሩ፥ ባሪያም እንደ ጌታው መሆኑ ይበቃዋል። ባለቤቱን ብዔል ዜቡል ካሉት፥ ቤተሰዎቹንማ እንዴት አብዝተው አይሉአቸው!

፳፮ እንግዲህ አትፍሩአቸው፤ የማይገለጥ የተከደነ፥ የማይታወቅም የተሰወረ ምንም የለምና።

፳፯ በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን ተናገሩ፤ በጆሮም የምትሰሙትን በሰገነት ላይ ስበኩ።

፳፰ ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ።

፳፱ ሁለት ድንቢጦች በአምስት ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ከእነርሱም አንዲቱ ያለ አባታችሁ ፈቃድ በምድር ላይ አትወድቅም።

፴ የእናንተስ የራሳችሁ ጠጉር ሁሉ እንኳ ተቈጥሮአል።

፴፩ እንግዲህ አትፍሩ ከብዙ ድንቢጦች እናንተ ትበልጣላችሁ።

፴፪ ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤

፴፫ በሰው ፊትም የሚክደኝን ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ።

፴፬ በምድር ላይ ሰላምን ለማምጣት የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ሰይፍን እንጂ ሰላምን ለማምጣት አልመጣሁም።

፴፭ ሰውን ከአባቱ፥ ሴት ልጅንም ከእናትዋ፥ ምራትንም ከአማትዋ እለያይ ዘንድ መጥቻለሁና፤

፴፮ ለሰውም ቤተ ሰዎቹ ጠላቶች ይሆኑበታል።

፴፯ ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔ ይልቅም ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤

፴፰ መስቀሉንም የማይዝ በኋላዬም የማይከተለኝ ለእኔ ሊሆን አይገባውም።

፴፱ ነፍሱን የሚያገኝ ያጠፋታል፥ ነፍሱንም ስለ እኔ የሚያጠፋ ያገኛታል።

፵ እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል።

፵፩ ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል።

፵፪ ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋው አይጠፋበትም።


📜ቅዳሴ


👉ዘሰለስቱ ምዕት (ግሩም)

@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
24 nehasa esmebenetiahu.wma
711.9 KB
በነገው ዕለት ነሐሴ 24/12/2015ዓ.ም

ዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ

ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፹፫፥፮(83፥6)
እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ
ወየሐውር እምኃይል ውስተ ኃይል
ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን

📜ምስባክ ዘቅዳሴ

እስመ በእንቲአሁ ይቀትሉነ ኩሎ አሚረ
ወኮነ ከመ አባግዕ ዘይጠብሁ
ንቃህ እግዚኦ ለምንት ትነውም

📜ቅዳሴ


👉ዘሰለስቱ ምዕት (ግሩም)


@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
††† እንኩዋን ለታላላቁ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ሃይማኖት: ቅድስት ክርስቶስ ሠምራና ቅዱስ ቶማስ ዘመርዓስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ †††

††† ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ሐዋርያዊ †††

*ልደት*

@mehereni_dngl

=>መልካም ዛፍ መልካም ፍሬን ያፈራልና ተክለ ሃይማኖትን የወለዱት ደጋጉ: ጸጋ ዘአብ ካህኑና እግዚእ ኃረያ ናቸው:: እርሱ በክህነቱ: እርሷ በደግነቷ: በምጽዋቷ ጸንተው ቢኖሩ እግዚአብሔር ጣፋጭ ፍሬን ሰጥቷቸዋል::

+በዳሞቱ ገዢ በሞተለሚ አደጋ ቢደርስባቸው ቅዱስ ሚካኤል: ጸጋ ዘአብን ከሞት: እግዚእ ኃረያን ከትድምርተ አረሚ (ከአረማዊ ጋብቻ) አድኗቸዋል:: በሁዋላም የቅዱሱን መወለድ አብስሯቸዋል::

+ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የጸነሱት መጋቢት 24 ቀን በ1206 ዓ/ም ሲሆን የተወለዱት ደግሞ ታሕሳስ24 ቀን በ1207 ዓ/ም ነው:: በተወለዱበት ቀንም ብዙ ተአምራት ተገልጸዋል:: ቤታቸውም በበረከት ሞልቷል::

*ዕድገት*

=>የጻድቁ የመጀመሪያ ስማቸው "ፍሥሃ ጽዮን" ይሰኛል:: ይሕንን ስም ይዘው: አባታቸው ጸጋ ዘአብን ተከትለው አድገዋል:: በተለይ ቅዱሳት መጻሕፍትን (ብሉያት: ሐዲሳትን) ተምረዋል:: በሥጋዊው ጐዳናም ብርቱ አዳኝ እንደ ነበሩ ይነገራል:: ዲቁናም ከወቅቱ ዻዻስ አባ ጌርሎስ ተቀብለዋል::

*መጠራት*

=>አንድ ቀን ፍሥሃ ጽዮስ ለአደን ወጥቶ ሲያነጣጥር ድንገት ከሰማይ አስደንጋጭ ድምጽ ተሰማ:: የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አእላፍ መላእክት እያመሰገኑ በሚካኤል ክንፍ ተቀምጦ ወረደ::

+የወጣቱን አዳኝ ፍርሃቱን አርቆ ጌታችን ተናገረ:: "ከዛሬ ጀምሮ ስምህ ተክለ ሃይማኖት (ተክለ ሥላሴ) ይሁን:: ከዚህ በሁዋላ አራዊትን ሳይሆን ነፍሳትን ታድናለህ:: ዘወትር ካንተ ጋር ነኝ" ብሎ በግርማ ዐረገ:: ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዚህ ጊዜ በሁዋላ ሰዓትን አላጠፉም:: ንብረታቸውን ለነዳያን በትነው በትር ብቻ ይዘው ቤታቸው እንደ ተከፈተ ወደ ምናኔ ወጡ::

*አገልግሎት*

=>ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዻዻሱ ቅስና ተቀብለው የወንጌል አገልግሎትን ጀመሩ:: በመጀመሪያ ስብከታቸው እዚያው ሽዋ (ጽላልሽ) አካባቢ ብቻ በ10ሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን አሳምነው አጠመቁ:: ያን ጊዜ ኢትዮዽያ 2 መልክ ነበራት::

+1ኛ ዮዲት (ጉዲት) በፈጠረችው ጣጣና በእስላሞች ተጽዕኖ ወደ ደቡብ አካባቢ ያለው ነዋሪ አንድም ሃይማኖቱን ክዷል: ወይም በባዕድ አምልኮ ተጠምዷል::
+2ኛው ደግሞ በዛግዌ ነገሥታት ጥረት ክርስትናና ምናኔ ተነቃቅቶ ነበር::

+ግማሹ ሃገር በጨለመበት ወቅት የደረሱት ሐዲስ ሐዋርያ አባ ተክለ ሃይማኖት በወጣት ጉልበታቸውና በኃይለ መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቦታዎችን አደረሱ:: ሕዝቡን: መሣፍንቱን ወደ ሃይማኖት መልሰው: ማርያኖችን (ጠንቁዋዮችን) አጥፍተዋል::

*ገዳማዊ ሕይወት*

=>ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት በወንጌል ብርሃን ኢትዮዽያን ከማብራታቸው ባለፈ ገዳማዊ ሕይወትንም አስፋፍተዋል:: እርሳቸው ከሁሉ የተሻሉ ሳሉም በ3 ገዳማት በረድዕነት አገልግለዋል::

+እነዚህም በአቡነ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ለ12 ዓመታት: በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ ገዳም ለ7 ዓመታት: በደብረ ዳሞ ከአቡነ ዮሐኒ ጋር ለ7 ዓመታት: በአጠቃላይ ለ26 ዓመታት አገልግለዋል::

+በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ከመነኮሱ በሁዋላም ወደ ምድረ ሽዋ (ዞረሬ) ተመልሰው በአንዲት በዓት ውስጥ ለ22 ዓመታት ቆመው ጸልየዋል:: በተሰበረ እግራቸውም 6 ጦሮችን በግራና በቀኝ ተክለው ለ7 ዓመታት ጸልየዋል::

*ስድስት ክንፍ*

=>ኢትዮዽያዊው ጻድቅና ሐዋርያ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከኢትዮዽያ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዘው ከቅዱሳት መካናት ተባርከዋል:: ጻድቁ ምድረ እሥራኤል የገቡት በየመንገዱ መንፈሳዊ ዘርን እየዘሩ: እያስተማሩና እያሳመኑ ነበር::

+የወቅቱ ሊቀ ዻዻሳት አባ ሚካኤል ጋርም ተገናኝተው ቡራኬን ተሰጣጥተዋል:: ዋናው ጉዳይ ግን ከዚህ በሁዋላ ነው:: ጻድቁ እመቤታችንና ጌታችን ከጽንሰታቸው እስከ ዕርገታቸው የረገጧቸውን ቦታዎች ሲመለከቱ በፍጹም ተደሞ እንባቸው ይፈስ ነበር::

+ምክንያቱም እግዚአብሔር ስላበቃቸው ተክለ ሃይማኖት የሚያዩት ቦታውን አልነበረም:: በገሃድ:-
-በቤተ መቅደስ ብስራቱን
-በቤተ ልሔም ልደቱን
-በቤተ ዮሴፍ ግዝረቱን
-በፈለገ ዮርዳኖስ ጥምቀቱን
-በቤተ አልዓዛር ተአምራቱን ይመለከቱ ነበር::

+የጉብኝታቸው የመጨረሻ ክፍል ወደ ሆነው ቀራንዮ ደርሰው ጌታቸውን እንደ ተሰቀለ ሆኖ ቢመለከቱት ከዓይናቸው ይፈስ የነበረው ቁጡ እንባ መልኩን ቀየረና ዓይናቸው ጠፋ::
በዚያች ቅጽበት ስም አጠራሯ የከበረ እመቤታችን ድንግል ማርያም ፈጥና ደርሳ ተክልየን ወደ ሰማይ አሳረገቻቸው::

+በዚያም:-
-የብርሃን ዐይን ተቀብለው
-6 ክንፍ አብቅለው
-የወርቅ ካባ ላንቃ ለብሰው
-ማዕጠንተ ወርቁን ይዘው
-ከ24ቱ ካህናተ ሰማይም ተደምረው
-ሥላሴን በአንድነቱና ሦስትነቱ ተመልክተው
-"ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ ይደሉ" ብለው መንበረ ጸባኦትን አጥነው ወደ መሬት ተመልሰዋል::

*ተአምራት*

=>የተክልየ ተአምራት እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ነው::
*ሙት አንስተዋል
*ድውያንን ፈውሰዋል
*አጋንንትን አሳደዋል
*እሳትን ጨብጠዋል
*በክንፍ በረዋል
*ደመናን ዙፋን አድርገዋል::

+ብዙ ደቀ መዛሙርትን አፍርተው ደብረ ሊባኖስን መሥርተዋል:: በዚያም ሴትና ወንድ መነኮሳት እንደ ሕጻናት አብረው ኑረዋል:: በዘመናቸው ሰይጣን ታሥሯልና::

*ዕረፍት*

=>ጻድቅ: ሰማዕትና ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ብርሃን ሆነው መከራን በብዙ ተቀብለው: እልፍ አእላፍ ፍሬን አፍርተው: በተወለዱ በ99 ዓመት: ከ8 ወር: ከ1 ቀናቸው ነሐሴ 24 ቀን በ1306 ዓ/ም ዐርፈዋል:: ጌታ: ድንግል ማርያምና ቅዱሳን ከሰማይ ወርደው ተቀብለዋቸዋል:: 10 ትውልድ የሚያስምር ቃል ኪዳንም ተቀብለዋል::

††† ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ †††

=>እጅግ የከበረችና የተመሰገነች እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራን እናመሰግናታለን:: እርሷ በሁሉ ጐዳና ፍጹምነትን ያሳየች ኢትዮዽያዊት እናት ናት:: ገና ከልጅነት የነበራት የትሕትናና የመታዘዝ ሕይወት እጅግ ልዩ ነበር:: እናታችን ቅድስናን ያገኘችው ገና በትዳር ውስጥ እያለች ነው::

+ከተባረከ ትዳሯ 12 ልጆችን አፍርታ: ምጽዋትን የዕለት ተግባሯ አድርጋ ኑራለች:: በዚህ ደግነቷም ሙት እስከ ማንሳት ደርሳለች:: አብያተ ክርስቲያናትን አንጻ አንድ ልጇን (ዳግማዊ ቂርቆስን) አዝላ ምናኔ ወጥታልች::

+በደብረ ሊባኖስ ውስጥ የቆየችው ቅድስት እናት ተጋድሎዋን የፈጸመችው ግን ጣና ሐይቅ ውስጥ ነው:: በተለይ ለ22 ዓመታት ሐይቁ ውስጥ አካሏ አልቆ: አሣ በሰውነቷ ውስጥ እስከሚያልፍ ድረስ ተጋድላለች:: በቀኝና በግራ 12 ጦሮችን ተክላም ጸልያለች::

@mehereni_dngl

+ብዙ ኃጥአንን አማልዳ: 12 ክንፎችን አብቅላ: ከፍ ከፍ ብላለች:: ከርሕራሔዋ ብዛት የተነሳ ሰይጣንን እንኩዋ ለማስታረቅ ሞክራለች:: ጌታም ከሲዖል ነፍሳትን እንድታወጣ ፈቅዶላታል:: ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ያረፈችው በዚህ ዕለት ሲሆን አ
ጽሟ ዛሬ በራሷ ገዳም (ጣና ዳር) ይገኛል::

+" ቅዱስ ቶማስ ዘመርዓስ "+

=>ቅዱስ ቶማስ "መርዓስ" በምትባል ሃገር የፈለቀ የንጋት ኮከብ: ጻድቅ: ገዳማዊ: ዻዻስ: ሐዋርያ: ሰማዕትና ሊቅ ነው:: የዚህን ቅዱስ ተጋድሎ እንደ እኔ ያለው ሰው አይቻለውም:: የእርሱ ሕይወት ክርስትና ምን እንደ ሆነ ያሳያል::

+" ቅዱስ ቶማስ "

*ከልጅነቱ ቅዱሳት መጻሕፍትን የተማረ
*ገና በወጣትነቱ መንኖ ገዳም የኖረ
*መርዓስ በምትባል ሃገር ዽዽስና ተሹሞ በእረኝነት ያገለገለ
*በሐዋርያዊ አገልግሎት ብዙ አሕዛብን ወደ ክርስትና የመለሰ
*በዘመነ ሰማዕታት ብዙ መከራን የተቀበለ አባት ነው::

+ጨkegdlatካኞቹ ቅዱሱን ለ22 ዓመታት አካሉን እየቆራረጡ ለጣዖታቸው ያጥኑ ስለ ነበር 2 እግሮቹ: 2 እጆቹ: 2 ጀሮዎቹ: 2 አፍንጫዎቹ: 2 ዐይኖቹ: ሁሉ አልነበሩም:: ነገር ግን እንዲህም ሆኖ አልሞተም ነበር::

+በመጨረሻም በዘመነ መናፍቃን አርዮስን ካወገዙት 318ቱ ሊቃውንት እንዳንዱ ተቆጥሯል:: ቅዱስ ቶማስ ዽዽስና በተሾመ በ40 ዓመቱ በዚህች ቀን ዐርፏል:: የጻድቃንን: የሰማዕታትን: የሐዋርያትንና ሊቃውንትን አክሊልም ተቀብሏል::

††† የጻድቁ አባታችን ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት የቅድስናና የክብር ስሞች †††

1.ተክለ አብ: ተክለ ወልድ: ተክለ መንፈስ ቅዱስ
2.ፍስሐ ፅዮን
3.ሐዲስ ሐዋርያ
4.መምሕረ ትሩፋት
5.ካህነ ሠማይ
6.ምድራዊ መልዐክ
7.እለ ስድስቱ ክነፊሁ (ባለ ስድስት ክንፍ)
8.ጻድቅ ገዳማዊ
9.ትሩፈ ምግባር
10.ሰማዕት
11.የኢትዮዽያ መነኮሳት አለቃ
12.ፀሐይ ዘበፀጋ
13.የኢትዮዽያ ብርሃኑዋ
14.ብእሴ እግዚአብሔር (የእግዚአብሔር ሰው)
15.መናኒ
16.ኤዺስ ቆዾስ (እጨጌ)

††† እነዚህ የአባታችን ስሞች እንደዘመኑ ሰው ለመሞጋገስ የወጡ ሳይሆኑ ሁሉም በትክክል ሥራዎቹንና ለቤተ ክርስቲያን የሆነላትን የሚያዘክሩ ናቸው:: †††

=>አምላከ ቅዱሳን በወዳጆቹ ምልጃ ክብራቸውን ያድለን:: በረከታቸውም በዝቶ ይደርብን::

=>ነሐሴ 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት (መምሕረ ትሩፋት)
2.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ (ጻድቅት)
3.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ
4.አበው አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ

=>ወርኀዊ በዓላት
1.አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ ዘክብራን
2.ቅዱስ አጋቢጦስ (ጻድቅ ኤዺስቆዾስ)
3.ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ
4."24ቱ" ካኅናተ ሰማይ (ሱራፌል)
5.ቅዱስ አባ ሙሴ ጸሊም

=>††† ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል:: ጻድቅን በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል:: ††† (ማቴ.10:40)

<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>

@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
እንኳ ለአባታችን ለአቡነ ተክለሃይማኖት ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ !

#መልካም_በዓል

@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
"አርስተ አበው አብርሃም ይስሃቅ እና ያዕቆብ"

"አብርሃምንና ይሳሃቅና ያዕቆብንም የብያትንም ሁሉ በእግዚአብሔር መንግሥት ባያቹ ጊዜ፣ እናንን ግን ወደ ውጪ ተጥላችሁ ስትቀሩ፣ በዚህ ልቅሶና ጥርስ ማፏጨት ይሆን" (ሉቃ ፲፫፥፳፰)

በረከታቸው ይደርብን!!
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
Forwarded from ኦርቶዶክስ bot
Wallpaper & profile picture ይፈልጋሉ ?
Forwarded from ኦርቶዶክስ bot
ኦርቶዶክስ በመሆንህ/ሽ ታፍራለህ/ሪያለሽ ?
🌻🌼 @MEHERENI_dNGL 🌻🌼

🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 🌻
በመጀመሪያ እንኳን ለዘመን መለወጫ በዓል አደረሳችሁ !
🌻🌻🌻🌻🌻 🌻🌻🌻

በነገው ዕለት መስከረም 01/01/2016 ዓ.ም

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ

ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፷፬፥፲፩(64፥11)
ወትባርክ አክሊለ ዓመተ ምሕረትከ
ወይጸግቡ ጠላተ ገዳም
ወይረውዩ አድባረ በድው


📖ወንጌል
ወንጌል ዘሉቃስ ፬፥፲፮-፳፫(3፥16-23)
ወሖረ ናዝሬተ ኀበ ተሐፅነ…


ምንባባት ዘቅዳሴ

👉 ዲያቆን
📖ኀበ ሰብአ ቆሮንትስ ፪ ም ፮፥፩-፲፩(6፥1-11)
ወናስተበቍዕሂ ኀቤክሙ…


👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ያዕቆብ ፭፥፰-፲፫(5፥8-13)
ተአገሡኬ ወአጽንዑ ልበክሙ…


👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፭፥፲፪-፲፯(5፥12-17)
ወበእደዊሆሙ ለሐዋርያት…


📜ምስባክ ዘቅዳሴ

አድኅነኒ እምእለ ሮዱኒ እስመ ይኄይሉኒ
ወአውጽኣ እምቅሕ ለነፍስየ
ከመ እግነይ ለስምከ እግዚኦ

👉ትርጉም

መዝሙረ ዳዊት ም. ፻፵፪ ቊ. ፮ - ፯

፮ እጅግ ተቸግሬአለሁና ወደ ልመናዬ አድምጥ፤ በርትተውብኛልና ከሚያሳድዱኝ አድነኝ።

፯ አቤቱ፥ ስምህን አመሰግን ዘንድ፤ ነፍሴን ከወህኒ አውጣት፤ ዋጋዬን እስክትሰጠኝ ድረስ ጻድቃን እኔን ይጠብቃሉ።


📜ወንጌል ዘቅዳሴ

የማቴዎስ ወንጌል ም. ፲፩ ቊ. ፩ - ፳

፩ ኢየሱስም አሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርቱን ማዘዝ በፈጸመ ጊዜ በከተሞቻቸው ሊያስተምርና ሊሰብክ ከዚያ አለፈ።

፪ ዮሐንስም በወህኒ ሳለ የክርስቶስን ሥራ ሰምቶ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለት ላከና።

፫ የሚመጣው አንተ ነህን? ወይስ ሌላ እንጠብቅ? አለው።

፬ ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው። ሄዳችሁ ያያችሁትን የሰማችሁትንም ለዮሐንስ አውሩለት፤
፭ ዕውሮች ያያሉ አንካሶችም ይሄዳሉ፥ ለምጻሞችም ይነጻሉ ደንቆሮችም ይሰማሉ፥ ሙታንም ይነሣሉ

፮ ለድሆችም ወንጌል ይሰበካል፤ በእኔም የማይሰናከለው ሁሉ ብፁዕ ነው።

፯ እነዚያም ሲሄዱ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ ሊናገር ጀመረ እንዲህም አለ። ምን ልታዩ ወደ ምድረ በዳ ወጣችሁ?

፰ ነፋስ የሚወዘውዘውን ሸምበቆን? ወይስ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ቀጭን ልብስ የለበሰ ሰውን? እነሆ፥ ቀጭን ልብስ የለበሱ በነገሥታት ቤት አሉ።

፱ ወይስ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችኋለሁ፥ ከነቢይም የሚበልጠውን።

፲ እነሆ፥ መንገድህን በፊትህ የሚጠርግ መልክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ

፲፩ ተብሎ የተጻፈለት ይህ ነውና። እውነት እላችኋለሁ፥ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም፤ በመንግሥተ ሰማያት ግን ከሁሉ የሚያንሰው ይበልጠዋል።

፲፪ ከመጥምቁም ከዮሐንስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ መንግሥተ ሰማያት ትገፋለች፥ ግፈኞችም ይናጠቋታል።

፲፫ ነቢያት ሁሉና ሕጉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናገሩ፤

፲፬ ልትቀበሉትስ ብትወዱ፥ ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይህ ነው።

፲፭ የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።

፲፮ ነገር ግን ይህን ትውልድ በምን እመስለዋለሁ? በገበያ የሚቀመጡትን ልጆች ይመስላሉ፥ እነርሱም ባልንጀሮቻቸውን እየጠሩ።

፲፯ እንቢልታ ነፋንላችሁ ዘፈንም አልዘፈናችሁም ሙሾ አወጣንላችሁ ዋይ ዋይም አላላችሁም ይሉአቸዋል።

፲፰ ዮሐንስ ሳይበላና ሳይጠጣ መጣ፥ እነርሱም። ጋኔን አለበት አሉት።

፲፱ የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ መጣ፥ እነርሱም። እነሆ፥ በላተኛና የወይን ጠጅ ጠጭ፥ የቀራጮችና የኃጢአተኞች ወዳጅ ይሉታል። ጥበብም በልጆችዋ ጸደቀች።

፳ በዚያን ጊዜ የሚበዙ ተአምራት የተደረገባቸውን ከተማዎች ንስሐ ስላልገቡ ሊነቅፋቸው ጀመረ እንዲህም አለ።



📜ቅዳሴ


👉ዘሐዋርያት (ዘበደኃሪ)


@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
01 meskerem wetebarek.wma
2 MB
🌼በነገው ዕለት መስከረም 01/01/2016 ዓ.ም🌻

ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፷፬፥፲፩(64፥11)
ወትባርክ አክሊለ ዓመተ ምሕረትከ
ወይጸግቡ ጠላተ ገዳም
ወይረውዩ አድባረ በድው


📜ምስባክ ዘቅዳሴ

አድኅነኒ እምእለ ሮዱኒ እስመ ይኄይሉኒ
ወአውጽኣ እምቅሕ ለነፍስየ
ከመ እግነይ ለስምከ እግዚኦ

📜ቅዳሴ


👉ዘሐዋርያት (ዘበደኃሪ)


@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼መልካም አዲስ አመት🌼🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

እንኳን ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ በሰላም እና በጤና አሸጋገራችሁ !

ዘመነ ዮሐንስን ሀገራችንን ኢትዮጵያ ከዘረኝነት የጸዳች ያድርግልን ፣ ጥሩ ነገር የምንሰማበት ያድርግልን ፣ የሰላም፣ የፍቅር፣ የጤና ያድርግልን !


መልካም አዲስ አመት
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼👇👇👇👇👇👇🌼
🌼 @MEHERENI_DNGL 🌼
🌼 @MEHERENI_DNGL 🌼
🌼 @MEHERENI_DNGL 🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
††† መስከረም 4 ቀን የሚከበሩ የቅዱሳን በዓላት †††

@MEHERENI_DNGL

††† እንኳን ለታላቁ ነቢይ ቅዱስ ኢያሱ እና ለቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ ኢያሱ ነቢይ ወመስፍን †††

††† ቅዱሱ የተወለደው በምድረ ግብፅ በባርነት ከነበሩ እሥራኤላውያን ሲሆን የቀደመ ስሙ #አውሴ ይባላል:: ዘመኑ #እግዚአብሔር ሕዝቡን ከ215 ዓመታት ባርነት ሊያወጣ የተቃረበበት ነውና #ሊቀ_ነቢያት_ሙሴ ከምድያም ሲመለስ ከመረጣቸው ተከታዮቹ ዋነኛው ኢያሱ ነበር:: እሥራኤል ከባርነት ሲወጡ ሙሴ 80 ዓመቱ: ኢያሱ ደግሞ 40 ዓመቱ ነበር::

ሕዝቡ አንገተ ደንዳና ነበርና ለ40 ቀን የታሠበላቸውን መንገድ 40 ዓመት እንዲሆን አደረጉት:: በዚህ ጊዜ ኢያሱ ከመምሕሩ ከሙሴና ከሕዝቡ አልተለየም:: አውሴን ኢያሱ ብሎ ስም የቀየረለት ሙሴ ሲሆን ይሔውም በፈቃደ እግዚአብሔር ነው::

ኢያሱ ማለት " #መድኃኒት" ማለት ነው:: ለዚሕም ምክንያቶች አሉት:-
1.ለጊዜው አማሌቃውያንን ድል ነስቶ ሕዝቡን አድኗል: ምድረ ርስትን አውርሷል::
2.ለፍጻሜው ግን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ (ጥላ) እንዲሆን ነው::

ቅዱስ ኢያሱ በበርሃው ለዘመናት እግዚአብሔርን አምልኮታል:: ሊቀ ነቢያትን ታዞታል (አገልግሎታል): እሥራኤልንም የጦር አለቃ ሆኖ ከአሕዛብ እጅ አድኗቸዋል:: በዚህም በእግዚአብሔርና በሕዝቡ ዘንድ ሞገስን አግኝቷል:: ቅዱስ ሙሴ #ደብረ_ናባው ላይ ባረፈ ጊዜ ሕዝቡን: ካሕናቱንና ታቦተ ጽዮንን ተረከበ:: ይህን ጊዜ ዕድሜው 80 እየሆነ ነበር::

††† እግዚአብሔርም ኢያሱን "ከአንተ ጋር ነኝ" ብሎ በሕዝቡ ላይ ነቢይና መስፍን (አስተዳዳሪ) እንዲሆን ሾመው:: ቅዱሱም ሰላዮችን ልኮ አስገምግሞ:
¤ባሕረ ዮርዳኖስን ከፍሎ:
¤ሕዝቡን አሻግሮ:
¤የኢያሪኮን ቅጥር 7 ጊዜ ዙሮ:
¤በኃይለ እግዚአብሔር አፍርሶ:
¤የኢያሪኮን ነገሥታት አጥፍቶ:
¤ለሕዝቡ ምድረ ርስትን አወረሰ::

የገባዖን ሰዎች "አድነን" ብለው በላኩበት ጊዜ ነገሥተ አሞሬዎንን ይወጋ ዘንድ ኢያሱ ወጣ:: እነዛን ግሩማን ነገሥታት በፈጣሪው ኃይል: በጦርና በተአምራት ድል ነስቶ የእግዚአብሔር ስሙ ከፍ ከፍ አለ:: በዚሕች ዕለትም ለ12ቱ ነገደ እሥራኤል ርስትን ሲያካፍል ፀሐይን በገባዖን: ጨረቃን ደግሞ በቆላተ ኤሎም (በኤሎም ሸለቆ) አቆመ::

ሰባት #አሕጉራተ_ምስካይ(የመማጸኛ ከተሞችን) ለየ:: ነቢይና መስፍን ሆኖ ሕዝቡን ለ40 ዓመታት አገለገለ:: በመጨረሻም ለሕዝቡ:- "እኔና ቤቴ እግዚአብሔርን እናመልካለን:: (ኢያ. 24) እናንተስ?" አላቸው:: እነርሱም "እኛም እንዳንተ ነን" አሉት:: ለዚህም ምልክት ይሆን ዘንድ 3 ገጽ ያላት ሐውልትን በመካከላቸው አቆመ::

ይህችውም የቅድስት #ድንግል_ማርያም ምሳሌ ናት:: ሐውልቷ 3 ገጽ እንዳላት እመቤታችንም በ3 ወገን (በነፍስ: በሥጋ: በልቡና) ድንግል ናት:: አንድም በ3 ወገን (ከኃልዮ: ከነቢብ: ከገቢር ኃጢአት) ንጽሕት ናት:: ለዚህም ነው #አባ_ሕርያቆስ
"ሐውልተ ስምዕ ዘኢያሱ" (የኢያሱ የምስክር ሐውልት አንቺ ነሽ) ሲል ያመሰገናት::

ታላቁ ነቢይ ኢያሱ ግን ከግብጽ በወጡ በ80 ዓመት: በተወለደ በ120 ዓመቱ (ጥሬው መጽሐፍ ቅዱስ በ110 ዓመቱ ይላል) በወገኖቹ መካከል ዐርፎ በያዕቆብ መቃብር ተቀበረ:: እሥራኤልም ለ30 ቀናት አለቀሱለት::

††† ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ †††

††† አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌሉ እንደነገረን በመንግስተ ሰማያት ታላቁ ሰው ወንጌላዊው ዮሐንስ ነው::

ቅዱሱ ሐዋርያ ከዘብዴዎስና ከማርያም ባውፍልያ ተወልዶ: በገሊላ አካባቢ አድጐ: ገና በወጣትነቱ መድኃኔ ዓለምን ተከትሎታል:: ቅዱስ ዮሐንስ ከሐዋርያት ቀድሞ ጌታን ከመከተሉ ባሻገር በምንም ምክንያት ከጐኑ አይጠፋም ነበር:: ስለ ንጽሕናውና በጐ የፍቅር ሕሊናው ሕጻን ሳለ በወንድሞቹ ሐዋርያት ዘንድ ሞገሱ ከፍ ያለ ነው::

ጌታችንን እስከ እግረ #መስቀሉ ድረስ በመከተሉ ድንግል እመቤታችንን ተቀብሏል:: ከእርሷ ጋር ለ15 ዓመታት ቢቀመጥ መዝገበ ምሥጢር ሆነ:: ስንኩዋን ከሰው ልጆች ይቅርና ከልዑላኑ መላዕክትም ማዕረጉ ከፍ አለ:: ሰው ቢበቃ መላእክትን ሊያይ ይቻለዋል:: ቅዱስ ዮሐንስን ግን መላእክት ሊያዩት ይከብዳቸዋል:: ከፍጥረት ወገን ከእመ ብርሃን ቀጥሎ ክቡር እርሱ ነው።

ቅዱሱ ከጌታችን ዕርገት በሁዋላ ለ70 ዓመታት በዚህ ምድር ሲኖር አብዛኛውን ጊዜውን ያሳለፈው በኤፌሶን አካባቢ ነው:: ሕዝቡን ወደ ክርስትና ለማምጣት በአፍም በመጽሐፍም ደክሟል::

ሶስት መልዕክታት: ራዕዩንና ወንጌልን ጽፎላቸዋል:: ሕይወትን ስለ ሰበከላቸው በፈንታው ብዙ አሰቃይተውታል:: ከእሳት እስከ ስለት: እስከ መጋዝም በስተእርጅና ደርሶበታል:: እርሱ ግን በትእግስቱ ገንዘብ አድርጉዋቸዋል::

††† እናት ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ዮሐንስን ስትጠራው እንዲሕ ነው:-
¤ወንጌላዊ
¤ሐዋርያ
¤ሰማዕት ዘእንበለ ደም
¤አቡቀለምሲስ (ምሥጢራትን ያየ)
¤ታኦሎጐስ (ነባቤ መለኮት)
¤ወልደ ነጐድጉዋድ
¤ደቀ መለኮት ወምሥጢር
¤ፍቁረ እግዚእ
¤ርዕሰ ደናግል (የደናግል አለቃ)
¤ቁጹረ ገጽ
¤ዘረፈቀ ውስተ ሕጽኑ ለኢየሱስ (ከጌታ ጎን የሚቀመጥ)
¤ንስር ሠራሪ
¤ልዑለ ስብከት
¤ምድራዊው መልዐክ
¤ዓምደ ብርሃን
¤ሐዋርያ ትንቢት
¤ቀርነ ቤተ ክርስቲያን
¤ኮከበ ከዋክብት

††† በዚህች ዕለት ቅዱሱ ሐዋርያ ከእናቱ #ማርያም_ባውፍልያ: ከአባቱ #ዘብዴዎስ መወለዱን ቤተ ክርስቲያን ታስተምራለች::

††† አባ ሙሴ ዻዻስ †††

እሥራኤላዊ ሲሆኑ ከአቡነ #ሰላማ ቀጥለው የመጡ የሃገራችን ዻዻስ ናቸው:: ፍጹም ገዳማዊና ትጉህ: ባለ ረዥም ዕድሜ ጻድቅም ናቸው::

ገዳማቸው #ወሎ ውስጥ ቢገኝም አስታዋሽ ያጣ ይመስላል:: መናንያኑ ለዕለት እንኩዋ የሚቀምሱት አጥተው ሲቸገሩ መመልከቱ እጅግ ያማል::

††† በቅዱስ ዮሐንስ ላይ ያደረ የእመቤታችን ድንግል ማርያምና የአንድ ልጇ ፍቅር በእኛም ላይ ይደር:: ቸሩ ጌታ ስም አጠራራቸው ካማረና ከከበረ ወዳጆቹ በረከትን ያሳትፈን::

††† መስከረም 4 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ኢያሱ ወልደ ነዌ (ነቢይና መስፍን)
2.ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ (ልደቱ)
3.ቅዱሳን ዘብዴዎስና ማርያም ባውፍልያ
4.አባ መቃርስ ሊቀ ዻዻሳት
5.አባ ሙሴ ዻዻስ

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ
2.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
3.ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ (ሰማዕት)

††† "አሁንም እግዚአብሔርን ፍሩ:: በእውነተኛም ልብ አምልኩት . . . እግዚአብሔርን ማምለክ ክፉ መስሎ ቢታያችሁ . . . የአሞራውያንን አማልክት ታመልኩ እንደ ሆነ: የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ:: እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን::" †††
(ኢያሱ. 24:14)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

በየዕለቱ ገድለ ቅዱሳን ፣ ምስባክ ፣ ምክረ አበው እና የተለያዩ ኦርቶዶክስ ነክ ነገሮች ለማግኘት ከታች ያለው Link ይንኩት ከዛን join በሉት እግዚአብሔር ሀገራችን ከከፉ ነገሮች ይጠብቅልን !

#መሐርኒ ድንግል
👇👇👇👇
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
በነገው ዕለት የሚነበበውን ምስባክ እና ገድለ ቅዱሳን እናቀርባለን ይጠብቁ !
‹‹‹‹ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፤፤››››

መስከረም 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

@MEHERENI_DNGL

+" ቅድስት ሐጊያ ሶፍያ "+

+ዘመነ ሰማዕታት በሚል በሚታወቀው 3ኛው መቶ ክ/ዘመን ብዙ ቅዱሳት እናቶቻችን ስለ ፍቅረ ክርስቶስ አንገታቸውን ሰጥተዋል:: አንዳንዶቹ ደግሞ ሕይወታቸው እጅግ የሚያምር ነበር:: ከእነዚህ ቅዱሳት እናቶቻችን አንዷ ዛሬ የምናከብራት ሐጊያ ሶፊያ ናት::

+በዚህ ስም ከሚጠሩት አንዷ ስትሆን በቀደመ ሕይወቷ ክርስቶስን አታውቅም ነበር:: ጣዖትን የሚያመልኩ ወላጆቿ አሳድገው አጋቧት:: ከትዳሯም 2 ቡሩካት ሴቶች ልጆች ወልዳለች:: ስማቸውም አክሶስናና በርናባ ይባላል:: ልጆቿ ልብ እያገኙ በሔዱ ጊዜ ቅድስት ሶፍያ ስለ እውነተኛው አምላክ ትመራመር ገባች::

+በወቅቱ የነበሩ ብዙ ሃይማኖቶችን መዘነች:: ከክርስትና በቀር ግን ሌሎቹ ሚዛን እንደማይመቱም አስተዋለች:: "እውነኘተኛው አምላክ ሆይ! ምራኝ: እርዳኝም" ስትል ጸለየች:: መድኃኔ ዓለም ለጠሩት አያሳፍርምና ፈጥኖ በጐውን ጐዳና አሳያት::

+ድኅነት ለልጆቿም ይሆን ዘንድ ሁለቱንም ጠርታ ስለ ክርስትና አማከረቻቸው:: ደስ ብሏቸው ተቀበሏት:: እርሷም ጊዜ ሳታጠፋ ወደ ዻዻስ ሒዳ ማሕተመ ክርስትና: ሃብተ ውልድናን ትቀበል ዘንድ ከልጆቿ ጋር ተጠመቀች:: በቅድስናና ደስ በሚያሰኝ አኗኗርም እስከ መከራ ቀን ቆየች::

+የመከራ ጊዜ ሲደርስም ልጆቿን ጠርታ "ስለ ክርስቶስ ፍቅር እንሙት" አለቻቸው:: ቡሩካቱ አክሶስናና በርናባም ደስ እያላቸው "እሺ" አሏት:: ወዲያውም በመኮንኑ ፊት ቀርበው ክርስቶስን ከመካድና ከስቃይ ሞት የትኛውን እንደሚመርጡ ቢጠየቁ እነርሱ መሞትን መረጡ:: ወደ እሥር ቤትም ከተቷቸው::

+ቅድስት ሶፍያ 2 ልጆቿ ይጸኑላት ዘንድ አዘውትራ ገድለ ሰማዕታትን እና ክብራቸውን ትተርክላቸው ነበር:: በተለይ የታላቁዋን አንጌቤናይት (እመቤት) ሶፍያንና የ3 ልጆቿን (ዺስጢስ: አላዺስና አጋዺስ) ተጋድሎ እየነገረች ታጸናቸው ነበር::

+ከእሥር በኋላ ግርፋት ታዞባቸው እናት ራቁቷን ስትገረፍ መልአክ ወርዶ ሲጋርዳት ልጆች በማየታቸው ደስ አላቸው:: ቅድስት ሐጊያ ሶፍያና 2 ልጆቿ እጅግ የበዛ ስቃይን ስለ ቀናች እምነት ተቀበሉ:: ምላስ እስከ መቆረጥም ደረሱ:: በመጨረሻ ግን በዚህች ቀን ተገድለው አክሊለ ሰማዕታትን ገንዘብ አደረጉ::

+የመከራ ዘመን ካለፈ በኋላ ታላቁ ንጉሥ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ የሁሉን ቅዱሳን ቤት ሠርቶ የእርሷን በመዘንጋቱ ለራሱ ባሰራው ቤተ መንግስት ላይ ተአምር ታይቷል:: ለ3 ያህል ጊዜ ስሙን ሲያስቀርጽ መልአክ እየወረደ ይፍቀው: የሶፍያንም ስም ይጽፈው ነበር::

+በመጨረሻም ንጉሡ ልጁን እስከ መገበር ደርሶ ቤተ መንግስቱ የቅድስት ሶፍያና የ2 ልጆቿ ቤተ ክርስቲያን ለመሆን በቅቷል:: ምንም ለ3 ጊዜያት ያህል ሙሉ እድሳት ቢደረግለትም ዛሬ አሕዛብ የያዙትን ይህንን ቅርስ ንጉሡ የሠራው ከ1700 ዓመታት በፊት ነው::

+" ቅዱስ ማማስ ሰማዕት "+

+የሰማዕቱ ወላጆች ቴዎዶስዮስና ታውፍና ሲባሉ ማማስ የሚለው የስሙ ትርጉም 'ዕጉዋለ ማውታ - እናት አባቱ የሞቱበት' ማለት ነው:: ለምን እንደዚህ ተባለ ቢሉ:- በዘመነ ሰማዕታት ስደት በሆነ ጊዜ ወላጆቹ ይዘውት ተሰደው ነበር:: ማምለጥ ባይችሉ ይዘው አሠሯቸው::

+በእሥር ቤትም ከስቃዩ ብዛት 2ቱም ልጃቸውን ማማስን እንዳቀፉት ሕይወታቸው አለፈች:: ሕጻኑ ሲያለቅስ የተመለከተች አንዲት ሴትም ራርታ እነርሱን አስቀብራ: እርሱን አሳድጋዋለች:: ስሙንም 'ማማስ' ብላዋለች::

+ቅዱሱ ባደገ ጊዜ የወላጆቹን ጐዳና በመከተሉ ተይዞ ለፍርድ ቀረበ:: ክርስቶስን አልክድም በማለቱም ብዙ ስቃይን አሳልፎ በዚህች ቀን ሰማዕት ሆኗል:: ቅዱስ ማማስ ከዐበይት ሰማዕታት አንዱ ሲሆን በአንበሳ ጀርባ ላይም ይቀመጥ ነበር::

+" አቡነ አሮን መንክራዊ "+

@MEHERENI_DNGL
+ኢትዮዽያውያን ጻድቅ አቡነ አሮን በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበሩ ኢትዮዽያዊ ሲሆኑ በገዳማዊ ሕይወታቸው: በሐዋርያዊ አገልግሎታቸውና ነገሥታቱን ሳይፈሩ በመገሰጻቸው ይታወቃሉ:: በተለይም ሕይወታቸው በተአምር የተሞላ ስለነበር 'አሮን መንክራዊ' (ድንቅ አባት) ተብለው ይጠራሉ::

+አንዳንድ ጊዜም 'አሮን ዘመቄት /ዘደብረ ዳሬት/' በሚልም ይጠራሉ:: የአቡነ አሮን ወላጆች ገብረ መስቀልና ዓመተ ማርያም የሚባሉ ሲሆን ከልጅነታቸው ጀምረው በቅዱስ ቃሉ የታነጹ ነበሩ:: ምናኔን በደብረ ጐል: ከአቡነ በጸሎተ ሚካኤል ጀምረው ብዙ ገዳማትን መሥርተዋል:: በርካታ ደቀ መዛሙርትንም አፍርተዋል::

+ለወንጌል አገልግሎት በወጡበት ጸሐይን አቁመው: ሕዝቡን ድንቅ አሰኝተዋል:: እንኳን ሰዉ ይቅርና አጋንንትም ያደንቁዋቸው ነበር:: ነገሥታቱንም ስለ ኃጢአታቸው በገሰጹ ጊዜ ራቁትነት: እሥራት: ግርፋትና ስደት ደርሶባቸዋል::

+ጻድቁ ከብዙ ተጋድሎ በኋላ በዚህች ቀን ወሎ መቄት ውስጥ በሚገኘው ገዳማቸው ዐርፈው ተቀብረዋል:: ገዳሙ እስካሁን ያለ ሲሆን ድንቅ ጥበበ እግዚአብሔር የሚታይበት ነው:: ጣራው ክፍት ሲሆን ዝናብ አያስገባም::

+" አፄ ልብነ ድንግል "+

+እኒህ ንጉሥ ኢትዮዽያን ለዓመታት (ከ1500 እስከ 1532 ዓ/ም) ቢያስተዳድሩም 15ቱ ዓመት ያለቀው በስደት ነው:: ከደጋጉ አፄ ናዖድና ንግሥት ወለተ ማርያም ተወልደው: በሥርዓቱ አድገው ቢነግሡም: በክፉ መካሪዎች ጠንቅዋይ ወደ ቤታቸው ገብቶ ሃገሪቱን ለመከራ ዳርጉዋታል::

+ዛሬም ድረስ ጠባሳው ያለቀቀው የግራኝ ወረራ ለ15 ዓመታት ሃገሪቱን ያለ ካህንና ቤተ ክርስቲያን አስቀርቷት ነበር:: ብዙ ክርስቲያኖችም ሰልመው ቀርተዋል:: አፄ ልብነ ድንግል ግን ደብረ ዳሞ ገዳም ውስጥ ገብተው ንስሃ ጀመሩ: አለቀሱ: ተማለሉ::

+እመቤታችን ተገልጣም "ይቅርታን በነፍስህ እንጂ በሥጋህ አታገኝም" አለቻቸው:: እርሳቸውም ሱባኤውን ቀጥለው: 'ስብሐተ ፍቁርን': 'መልክአ ኤዶምን' የመሰሉ መጻሕፍትን ደርሰው በዚህች ቀን በ ዓ/ም ዐርፈዋል:: እኛ ክርስቲያኖችም እናከብራቸዋለን::

+የቅዱሳኑ አምላክ የወዳጆቹን ፈተና አስቦ ሃገራችንን ከጥፋት: ሕዝቡንም ከስደት ይሰውርልን:: ከበረከታቸውም አይለየን::

+መስከረም 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
2.ቅዱሳት አክሶስናና በርናባ
3.ቅዱስ ማማስ ሰማዕት
4.ቅዱሳን ቴዎዶስዮስና ታውፍና
5.አቡነ አሮን መንክራዊ
6.አፄ ልብነ ድንግል

++"+ ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን: ትንሳኤውን በሚመስል ትንሳኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን:: ከእንግዲህስ ወዲያ ለኃጢአት እንዳንገዛ የኃጢአት ሥጋ ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከእርሱ ጋር እንደ ተሰቀለ እናውቃለን:: +"+ (ሮሜ. 6:5)

‹‹‹‹ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ››››

@mehereni_dngl
@mehereni_dngl

Follow
👇👇👇
http://tiktok.com/@mehereni_dngl
2024/06/28 15:21:56
Back to Top
HTML Embed Code: