Telegram Web Link
Forwarded from ዘ ተዋህዶ
#ቅድስት_ሥላሴ

"ሥላሴን " "ቅድስት ሥላሴ እያልን የመጥራታችን ምስጢር ምንድን ነው?

◉አንዲት ሴት ወይም እናት ልጆቿን አልወለደችም ተብላ አትጠረጠርም ፤ ሥላሴም ይህንን
ዓለም ፈጥረዋል እናም አልፈጠሩም ተብለው አይጠራጠሩም ።

◉አንዲት ሴት በባሕሪይዋ ልጅን ታስገኛለች ፤ ሥላሴም ይህንን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር
አምጥተው ስለፈጠሩት በሴት አንጻር # ቅድስት ተብለው ይጠራሉ ።

◉አንድም ሴት አዛኝ ናት ፤ ለታናሹም ይሁን ለታላቁ ትራራለች ሥላሴም እንደዚሁ ለፍጥረት
ሁሉ ያዝናሉ ፥ ይራራሉ ፥ ምህረት ይሰጣሉ ። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንዲህ ይላል ።
ምህረታችሁ ከልክም በላይ የበዛ በሴት አንቀጽ ቅድስት ተብላችሁ የተጠራችሁ ሥላሴ " በማለት ያመሰጥራል።
ስለዚህ ቅድስት ለምን ተባሉ ቢባል በረከታቸው ፥ ርህራሄያቸውና ፥
ይቅር ባይነታቸው መሆኑን ማወቅ አለብን ።

◉አንድም ሴት ልጇ ቢታመምባት አትወድም ፤ ሥላሴም አንድም ልጅ በዲያብሎስ እጅ ተይዞ
በኃጢአት እንዲታመሙ አይወዱም ፥ አይፈቅዱም በመሆኑም
#ቅድስት ይባላሉ ።

◎አንድም ሴት ልጅ የልጇን ነውር አትጠየፍም ልጄ ቆሽሿል ፥ ተበላሽቷል ብላ ፊቷን አታዞርም ።
ሥላሴም የሰውን በኃጢአት መቆሸሽ ሳይፀየፉ በቸርነታቸው ጎቦኝተው ለንስሐ ያደርሱታል ።

◎ይህንን የፅድቅ አየር የምንምገው ያማረውንም ብርሃን የለበስነው ስለ ፅድቃችን ሳይሆን
በሥላሴ ቸርነት ነውና ስለዚህም ሥላሴን በሴት አንቀፅ # ቅድስት እንላቸዋለን ።

◉አኔድም ሴት ልጆቿን ፈጭታና ጋግራ ትመግባቸዋለች ሥላሴም እንደዛው ናቸው ። በዝናብ
አብቅለው በፀሐይ አብሥልው ፍጥረታትን ሁሉ ይመግባሉ ። ስለዚህ ሥላሴ እንደ እናት
ሁሉንም ይመግባሉና በሴት አንቀጽ #ቅድስት ይባላሉ ።


----- Share---&---Join

👇👇👇👇👇
@tewhodox
@tewhodox
👆👆👆👆👆
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቆይ አትለፉት እንኳን ለእመቤታችን ለኪዳነ ምህረት ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

#መሐርኒ_ድንግል
#አስደሳች_ዜና

#create_post

*create post ለመስራት የምትፈልጉ በኦርቶዶክሳዊ bot አብሶ ግሩፕ እና ቻናል ያላችሁ ለማስተዋወቅ በጣም ይጠቅማችኋል !

👇👇👇👇👇👇
@Orthodox_hegere_bot
@Orthodox_hegere_bot
@Orthodox_hegere_bot
ውድ የቻናላችን ተከታዮች መሐርኒ ድንግል ከዛሬ ጀምሮ የእለቱን ምስባክ እና ገድለ ቅዱሳን ያቀርብላችኋል እና ደግሞ አንዳንዴ መንፈሳዊ ጥያቄ፣ ምክረ አበው በሁለት ሳምንት ውስጥ ያቀርብላችኋል !

የመብታችን የድንግል ማርያም ልጅ ሀገራችን ይጠብቅልን !
የሐዋርያት የቅዱስ ጴጥሮስ ደቀመዝሙር ማን ነበር ?
Anonymous Quiz
21%
ቲቶ
38%
ጢሞቴዎስ
24%
ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ
17%
ፊሊምን
በነገው ዕለት ነሐሴ 18/12/2015 ዓ.ም

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ
መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ

ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፵፬፥፱(44፥9)
ወትቀውም ንግሥት በየማንከ
በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኁብርት
ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምኢ እዝነኪ


📖ወንጌል
ወንጌል ዘሉቃስ ፩፥፴፱-፶፯(1፥39-57)
ወተንሥአት …



ምንባባት ዘቅዳሴ

👉 ዲያቆን
📖ኀበ ሰብአ ፊልጵስዩስ ፫፥፩-፮(3፥1-6)
ወይእዜኒ አኃውየ ተፈሥሑ በእግዚእነ…


👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ዮሐንስ ፩ ም ፪፥፩-፳(2፥1-20)
ደቂቅየ ዘንተ እጽሕፍ ለክሙ…


👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፳፦፳፰-፴፩(20፥28-31)
ወይእዜኒ ዕቀቡ ርእሰክሙ…


📜ምስባክ ዘቅዳሴ

አጽንዕዋ ለጥበብ ከመ ኢይትመዓዕ እግዚአብሔር
ወኢትትኀጎሉ እምፍኖተ ጽድቅ
ሶበ ነደት ፍጡነ መዓቱ


ትርጉም

መዝሙረ ዳዊት ም. ፪ ቊ. ፲፪

፲፪ ተግሣጹን ተቀበሉ ጌታ እንዳይቈጣ እናንተም በመንገድ እንዳትጠፉ፥ ቍጣው ፈጥና ትነድዳለችና። በእርሱ የታመኑ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው።


📜ምስባክ ዘቅዳሴ ተለዋጭ

ዘዐበያ ለበረከት ወትርኀቅ እምኔሁ።
ወለብሳ ለመርገም ከመ ልብስ።
ወቦአ ከመ ማይ ውስተ አማዑት።


ትርጉም

መዝሙረ ዳዊት ም. ፻፱ ቊ. ፲፯ - ፲፰

፲፯ መርገምን ወደደ ወደ እርሱም መጣች፤ በረከትንም አልመረጠም ከእርሱም ራቀች።

፲፰ መርገምን እንደ ልብስ ለበሳት፥ እንደ ውኃም ወደ አንጀቱ፥ እንደ ቅባትም ወደ አጥንቱ ገባች።



📜ወንጌል ዘቅዳሴ

የማቴዎስ ወንጌል ም. ፲፭ ቊ. ፮ - ፳፩

፮ አባቱን ወይም እናቱን አያከብርም ትላላችሁ፤ ስለ ወጋችሁም የእግዚአብሔርን ቃል ሻራችሁ።

፯ እናንተ ግብዞች፥ ኢሳይያስ ስለ እናንተ።

፰ ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፥ ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው፤

፱ የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል ብሎ በእውነት ትንቢት ተናገረ።

፲ ሕዝቡንም ጠርቶ። ስሙ አስተውሉም፤

፲፩ ሰውን የሚያረክሰው ወደ አፍ የሚገባ አይደለም፥ ከአፍ የሚወጣው ግን ሰውን የሚያረክሰው ይህ ነው አላቸው።

፲፪ በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ቀርበው። ፈሪሳውያን ይህን ቃል ሰምተው እንደ ተሰናከሉ አወቅህን? አሉት።

፲፫ እርሱ ግን መልሶ። የሰማዩ አባቴ ያልተከለው ተክል ሁሉ ይነቀላል።

፲፬ ተዉአቸው፤ ዕውሮችን የሚመሩ ዕውሮች ናቸው፤ ዕውርም ዕውርን ቢመራው ሁለቱም ወደ ጉድጓድ ይወድቃሉ አለ።

፲፭ ጴጥሮስም መልሶ። ምሳሌውን ተርጕምልን አለው።

፲፮ ኢየሱስም እንዲህ አለ። እናንተ ደግሞ እስካሁን የማታስተውሉ ናችሁን?

፲፯ ወደ አፍ የሚገባ ሁሉ ወደ ሆድ አልፎ ወደ እዳሪ እንዲጣል አትመለከቱምን?

፲፰ ከአፍ የሚወጣ ግን ከልብ ይወጣል፥ ሰውንም የሚያረክሰው ያ ነው።

፲፱ ከልብ ክፉ አሳብ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ ዝሙት፥ መስረቅ፥ በውሸት መመስከር፥ ስድብ ይወጣልና።

፳ ሰውን የሚያረክሰው ይህ ነው እንጂ፥ ባልታጠበ እጅ መብላትስ ሰውን አያረክሰውም።

፳፩ ኢየሱስም ከዚያ ወጥቶ ወደ ጢሮስና ወደ ሲዶና አገር ሄደ።



📜ቅዳሴ


ዘእግዝእትነ አው ግሩም

የዕለቱን ምስባክ ሁልጊዜ ለማግኘት join በሉት
👇👇👇👇
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
18 nehasa zeabeyalebereket.wma
694.4 KB
በነገው ዕለት ነሐሴ 18/12/2015 ዓ.ም

ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፵፬፥፱(44፥9)
ወትቀውም ንግሥት በየማንከ
በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኁብርት
ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምኢ እዝነኪ

📜ምስባክ ዘቅዳሴ

አጽንዕዋ ለጥበብ ከመ ኢይትመዓዕ እግዚአብሔር
ወኢትትኀጎሉ እምፍኖተ ጽድቅ
ሶበ ነደት ፍጡነ መዓቱ

📜ምስባክ ዘቅዳሴ ተለዋጭ

ዘዐበያ ለበረከት ወትርኀቅ እምኔሁ።
ወለብሳ ለመርገም ከመ ልብስ።
ወቦአ ከመ ማይ ውስተ አማዑት።


📜ቅዳሴ


ዘእግዝእትነ አው ግሩም

የዕለቱን ምስባክ ሁልጊዜ ለማግኘት Join
በሉት
👇👇👇👇
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
በነገው ዕለት የማቀርበውን ምስባክ በፅሁፍ አና በድምፅ አቅርበናል የነገው ዕለት ገድለ ቅዱሳን እናቀርባለን ይጠብቁን ! ቅሬታችሁን እዳረካን እርግጠኛ ነን ! አስተያየት ስለሰጣችሁን እናመሰግናለን ! አሁንም አስተያየት (ቅሬታ) ካላችሁ አናግሩን እናስተካክላለን 👉 @mehereni_dngl_bot
††† እንኳን ለሊቁ ቅዱስ እለእስክንድሮስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ እለእስክንድሮስ ሊቅ †††

††† ቅዱሱ ታላቅ የሃይማኖት ጠበቃ ሲሆን ሃገረ ሙላዱ (የተወለደባት) ግብጽ ናት:: የተወለደው በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ሲሆን በምግባሩ: በትምሕርቱ ለምዕመናን ጥቅም ሆኗቸዋል:: ቅዱስ እለእስክንድሮስ ገና ልጅ ሳለ ምሥጢረ ክርስትናን ይማር ዘንድ ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት ሔዷል::

††† ቅዱስ ጴጥሮስ የግብጽ አሥራ ሰባተኛ ፓትርያርክና ሊቅ ሲሆን በታሪክ የዘመነ ሰማዕታት መጨረሻ ተብሎ ይታወቃል:: ከዚህ ሰማዕት ሥር የሚማሩ ብዙ አርድእት ቢኖሩም ሦስቱ ግን ተጠቃሽ ነበሩ::
1.ቅዱስ እለእስክንድሮስ (ደጉ)
2.አኪላስ (ውዳሴ ከንቱ ወዳጅ)
3.አርዮስ (የቤተ ክርስቲያን ጠላት)

ከእነዚህም አርዮስ ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት ሲታትር ነበር:: አኪላስ ደግሞ ሆዱ ዘመዱ: ስለ ምንም የማይጨንቀው ሰው ነበር:: ቅዱስ እለእስክንድሮስ ግን በጾምና በጸሎት እየተጋ መምሕሩን ቅዱስ ጴጥሮስን ለመተካት (ለመምሰል) ይጥር ነበር::

ወቅቱ ዘመነ ሰማዕታት እንደ መሆኑ ቅዱሱ ከመምሕሩ ጋር ብዙ ነገሮችን አሳልፏል:: አርዮስ ክዶ: ቅዱስ ጴጥሮስ ካወገዘው በኋላ እንደ ባልንጀራ ገስጾ ሊመልሰውም ሞክሮ ነበር:: ነገር ግን የአርዮስን ክፋት ከጌታ ዘንድ የተረዳው ቅዱስ ጴጥሮስ ደቀ መዝሙሩን እለእስክንድሮስን ጠርቶ መከረው::
"እኔ ከሞትኩ በኋላ አኪላስ ይተካል:: ከአርዮስ ጋር ስለሚወዳጅ በስድስት ወሩ ይቀሠፋል:: አንተ ግን ከአርዮስ መርዝ ተጠበቅ::" አለው:: ይህንን ካለው በኋላ ወታደሮች የቅዱስ ጴጥሮስን አንገት ቆረጡ:: ይህ የተደረገውም እ.ኤ.አ በ311 ዓ/ም ነው::

ወዲያውም አኪላስ ተሾመ:: እንደ ተባለውም ከአርዮስ ጋር ስለተወዳጀ በስድስት ወሩ ተቀሰፈ:: በዚያው ዓመትም ቅዱስ እለእስክንድሮስ የእስክንድርያ (ግብጽ) አሥራ ዘጠነኛ ፓትርያርክ (ሊቀ ጳጳሳት) ሆኖ ተሾመ::

ሊቁ ሲሾም መልካም አጋጣሚ የነበረው ያ የመከራ ዘመን ማለፉ ሲሆን በጣም ከባዱ ግን የአርዮስ ተከታዮች ከተገመተው በላይ መብዛታቸው ነው:: ቅዱሱ ሊቅ በጵጵስና መንበሩ ለአሥራ ሰባት ዓመታት ሲቆይ ዕንቅልፍም ሆነ ዕረፍት አልነበረውም::

በዚህ እየጾመ: እየጸለየ: ሥጋውን እየጐሰመ ለፈጣሪው ይገዛል:: በዚያ ደግሞ ሕዝቡን ነጋ መሸ ሳይል ያስተምራል:: ምዕመናንን ከአርዮስ የኑፋቄ መርዝ ለመታደግ በአፍም: በመጣፍም (በደብዳቤ) አስተማረ::

ብርሃን የሆነ ደቀ መዝሙሩ ቅዱስ አትናቴዎስ እያገዘው: አርዮስን ከነአበጋዞቹ አሳፈሩት:: ለእያንዳንዷ የኑፋቄ ጥያቄ ተገቢውን መንፈሳዊ ምላሽ ከመስጠቱ ባለፈ አርዮስን ከአንዴም ሁለቴ: ሦስቴ በጉባኤ አውግዞታል::

ነገሩ ግን በዚህ መቋጨት ባለመቻሉ ንጉሡ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ጉባኤ ኒቅያ እንዲደረግ አዋጅ ነገረ:: እ.ኤ.አ በ325 ዓ/ም (በእኛ በ318 ዓ/ም) ከመላው ዓለም ለጉዳዩ ሁለት ሺ ሦስት መቶ አርባ ስምንት የሚያህሉ ሰዎች ተሰበሰቡ:: ከእነዚህ መካከል ሦስት መቶ አሥራ ስምንቱ ሊቅነትን ከቅድስና የደረቡ: ስለ ቀናች ሃይማኖት ብዙ መከራ ያሳለፉ ነበሩ::

ይህንን የተቀደሰ ጉባኤ እንዲመራ ደግሞ መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ እለእስክንድሮስን መረጠ:: ሊቁም አበው ቅዱሳንን አስተባብሮ በሺ የሚቆጠሩ ተከታዮች ያሉትን አርዮስን ተከራክሮ ረታው::

በጉባኤው መጨረሻ አርዮስ "አልመለስም" በማለቱ እርሱን አውግዘው: ጸሎተ ሃይማኖትን ሠርተው: ሃያ ቀኖናዎችን አውጥተው: መጽሐፈ ቅዳሴ ደርሰው: አሥራው መጻሕፍትን ወስነው: ቤተ ክርስቲያንን በዓለት ላይ አጽንተው ተለያይተዋል::
የዚህ ሁሉ ፍሬ አበጋዙ ደግሞ ቅዱስ እለእስክንድሮስ ነው::

እርሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን "ወልድ ዋሕድ: አምላክ: ወልደ አምላክ: የባሕርይ አምላክ" መሆኑን መስክሮ ክብርን አግኝቷል:: የእምነታችንም መሠረቱ ይሔው ነው:: ክርስቶስን "ፈጣሬ ሰማያት ወምድር: የባሕርይ አምላክ: ዘዕሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ (ከአባቱ ጋር በመለኮቱ የሚተካከል)" ብለው ካላመኑ እንኳን ድኅነት ክርስትናም አይኖርም::

ከጉባኤ ኒቅያ በኋላ ቅዱስ እለእስክንድሮስ በመልካሙ ጐዳና ሲጋደል: ምዕመናንንም ሲያጸና ኑሯል:: ዘወትር ወንጌልን በፍቅር ያነብ ነበርና ሲጸልይ የብርሃን ምሰሶ ይወርድለት ነበር::

ስለ ውለታውም ቤተ ክርስቲያን በግብጽ ካበሩ አምስቱ ከዋክብት ሊቃውንት እንደ አንዱ ታከብረዋለች:: ቅዱሱ ሊቅ በ328 ዓ/ም (በእኛ በ320 ዓ/ም) በዚህች ቀን ዐርፎ በክብር ተቀብሯል::

††† ቸር አምላከ ቅዱሳን ቤተ ክርስቲያንን ከነጣቂ ተኩላ ይጠብቅልን:: ከቅዱሱ ሊቅም በረከትን ይክፈለን::

††† ነሐሴ 18 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ተዝካረ ፍልሠታ ለማርያም ድንግል (ሦስተኛ ቀን)
2.ቅዱስ እለእስክንድሮስ ሊቅ
3.ቅዱስ እንድራኒቆስ ዲያቆን
4.አባ ዘክርስቶስ ዘወሎ (ኢትዮጵያዊ ጻድቅ)

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ፊልጶስ ሐዋርያ
2.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሰባኬ ሃይማኖት (ረባን)
3.አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ
4.ማር ያዕቆብ ግብጻዊ
5.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ከሰባ ሁለቱ አርድእት)

††† ". . . ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኳችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ::" †††
(ይሁዳ. ፩፥፫)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
ምስባክ እና ገድለ ቅዱሳን መልቀቁን እንቀጥልበት ?
Anonymous Poll
89%
Yes
11%
No
ምስባክ የምንለቀው ቀደም ብለን ነው ማለቴ የነገ ምስባክ ከሆነ ዛሬ ነው የምንለቀው ።
በነገው ዕለት ነሐሴ 20/12/2015 ዓ.ም

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ

ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፵፬፥፱(44፥9)
ወትቀውም ንግሥት በየማንከ
በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኁብርት
ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምኢ እዝነኪ


📖ወንጌል
ወንጌል ዘሉቃስ ፩፥፴፱-፶፯(1፥39-57)
ወተንሥአት …



ምንባባት ዘቅዳሴ

👉 ዲያቆን
📖ኀበ ሰብአ ቆሮንቶስ ፩ ም ፲፭፥፴፫-፶፩(15፥33-51)
ኢያስሕቱክሙ አኃዊነ ነገር እኩይ…


👉ንፍቅ ዲያቆን
📖ያዕቆብ ፬፥፲፩-፲፯(4፥11-17)
አትሕቱ ርእሰክሙ ወያሌዕለክሙ…


👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረሐዋርያት ፳፫፥፳፪-፴፭(23፥22-35)
ወእምዝ ፈነወ መልአክ ለውእቱ ወልድ…




📜ምስባክ ዘቅዳሴ

ነጽረኒ ወስምዐኒ እግዚኦ
አምላኪየ አብርሆን ለአዕይንትየ ከመ ኢይኑማ ለመዊት
ወከመ ኢይበሉኒ ጸላእትየ ሞእናሁ


👉ትርጉም

መዝሙረ ዳዊት ም. ፲፫ ቊ. ፫ - ፮

፫ አቤቱ አምላኬ፥ እየኝ ስማኝም፤ ጠላቴ። አሸነፍሁት እንዳይል፥

፬ የሚያስጨንቁኝም እኔ ብናወጥ ደስ እንዳይላቸው፥ ለሞትም እንዳልተኛ ዓይኖቼን አብራ።

፭ እኔ ግን በቸርነትህ ታመንሁ፥ ልቤም በመድኃኒትህ ደስ ይለዋል።

፮ የረዳኝን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፥ ለልዑል እግዚአብሔር ስምም እዘምራለሁ።



📜ወንጌል ዘቅዳሴ

የማቴዎስ ወንጌል ም. ፳፪ ቊ. ፳፫ - ፴፬

፳፫ በዚያን ቀን። ትንሣኤ ሙታን የለም የሚሉ ሰዱቃውያን ወደ እርሱ ቀረቡ፥

፳ እንዲህም ብለው ጠየቁት። መምህር ሆይ፥ ሙሴ አንድ ሰው ልጅ ሳይወልድ ሲሞት ወንድሙ ሚስቱን አግብቶ ለወንድሙ ዘር ይተካ አለ።

፳፭ ሰባት ወንድማማች በእኛ ዘንድ ነበሩ፤ ፊተኛውም ሚስት አግብቶ ሞተ፥ ዘርም ስለሌለው ሚስቱን ለወንድሙ ተወለት፤

፳፮ እንዲሁ ደግሞ ሁለተኛው ሦስተኛውም፥ እስከ ሰባተኛው ድረስ።

፳፯ ከሁሉም በኋላ ሴቲቱ ሞተች።

፳፰ ሁሉ አግብተዋታልና በትንሣኤ ቀንስ፥ ከሰባቱ ለማናቸው ሚስት ትሆናለች?

፳፱ ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው። መጻሕፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ትስታላችሁ።

፴ በትንሣኤስ እንደ እግዚአብሔር መላእክት በሰማይ ይሆናሉ እንጂ አያገቡም አይጋቡምም።

፴፩-፴፪ ስለ ትንሣኤ ሙታን ግን። እኔ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ ነኝ የሚል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ እናንተ የተባለውን አላነበባችሁምን? የሕያዋን አምላክ ነው እንጂ የሙታን አይደለም።

፴፫ ሕዝቡም ይህን ሰምተው በትምህርቱ ተገረሙ።

፴፬ ፈሪሳውያንም ሰዱቃውያንን ዝም እንዳሰኛቸው በሰሙ ጊዜ አብረው ተሰበሰቡ።



📜ቅዳሴ


👉ዘእግዝእትነ


@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
20 nehasa netsereni.wma
1021.2 KB
በነገው ዕለት ​ነሐሴ 20/12/2015 ዓ.ም

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ

ዘነግህ
📖ምስባክ
መዝ ፵፬፥፱(44፥9)
ወትቀውም ንግሥት በየማንከ
በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኁብርት
ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምኢ እዝነኪ

📜ምስባክ ዘቅዳሴ

ነጽረኒ ወስምዐኒ እግዚኦ
አምላኪየ አብርሆን ለአዕይንትየ ከመ ኢይኑማ ለመዊት
ወከመ ኢይበሉኒ ጸላእትየ ሞእናሁ

📜ቅዳሴ


ዘእግዝእትነ


@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
@mehreni_dngl
2024/06/30 21:48:35
Back to Top
HTML Embed Code: