Telegram Web Link
#በበረሃው በሀሩሩ

በመሐርኒ ድንግል

በበረሃው በሀሩሩ
በሚያስፈራው በባህሩ
እስራኤልን የታደገው
በክንፎቹ የጋረደው ሚካኤል ነው
=======================

ሚካኤል ነው አፅናኝ ደጋፊዬ
" " በዱር በበረሃ
" " ነፍሴን ያረካልኝ
" " ከአለቱ ውሃ
የፊቴ ፈገግታ የውስጤ ፍስሐ
ከአምላክ የተሰጠኝ በረከት አምሐ
======================

ሚካኤል ነው መብረቅ ያወረደው
" " ጠላት ድል የነሳው
" " የባህራን ወዳጅ
" " ሀዘኑን ያስረሳው
ቤቱን የሰራለት በእግሮቹ ያቆመው
እንደ እናት እንደ አባት ደግሶ የዳረው

= = = = = = = =
ሚካኤል ነው ክሴን ያስቀደደ
" " የበደሌን እዳ
" " በአማላጅነቱ
" " ያዳነኝ ከፍዳ
በመንገዴ ሁሉ እኔን እየረዳ
ፍቅሩን ጽፎት አልፏል በልቤ ሰሌዳ

መሐርኒ ድንግል
Join & share
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
እግዚኦ ረሰዮ ለውእቱ ሚካኤል እምኲሎሙ መላእክት ይትለአል መንበሩ።

እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል ለአመታዊ በዓል በሰላም፣ በጤና እና በፍቅር አደረሳችሁ አደረሰን !

ቅዱስ ሚካኤል ሀገራችንን ኢትዮጵያን ይባርካት።

መሐርኒ ድንግል
Join & share
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
Forwarded from ዘ ተዋህዶ
አረጋዊው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ !!!

የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከትን ከ30 ዓመታት በላይ የመሩት አረጋዊው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ።
ብፁዕነታቸው ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን የሀገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎች ለተሚማ አረጋግጠዋል።

በሦስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ እድ፣ ጥር 14 ቀን 1972 ዓ.ም. ከተሾሙት 15 ብፁዓን አባቶች አንዱ የኾኑት ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም፤ እስከ ዕርግና ዘመናቸው ከቆዩበት ደብረ ብርሃን ቀደም ብሎ፣ በአርሲ እና በመቐለ አህጉረ ስብከት ተመድበው ጉልሕ ሐዋርያዊ አገልግሎት አበርክተዋል፡፡

በረከታቸዉ ይደርብን
🌹ዘተዋህዶ🌹
💐@tewhodox💐
💐@tewhodox💐
💐ለወዳጅ ለዘመድ ለጓደኛ ያጋሩ 💐
በዚኽ ቻናል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የተዘጋጁ መዝሙራት እንዲሁም ሥዕለ ቅዱሳን እና ምርጥ እና የሚመቹ ደስ የሚሉ ፎቶዎች ይለቀቅበታል
ማንኛውንም ሀሳብ አስተያየት ካለ እንዲሁም አንዲለቀቅ የምትፈልጉትን ፎቶዎች እና መዝሙሮችን በዚህ ሊንክ አድርሱን 👉👉👉 @Mtrsetbot👈👈👈
https://www.tg-me.com/mertephoto
ኦርቶዶክሳዊ የወጣቶች ህይወት !

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡

👉 @mehereni_dngl

#ማግባትን_ለምትሹ !

👉 @mehereni_dngl

" ከምንም በፊት የጋብቻ ዓላማን ማወቅ አለባችሁ ፡፡ በሕይወታችን ለምን ጋብቻ እንደሚያስፈልገን መረዳት አለባችሁ፡፡ ከዚህ ውጪ ሌላ ነገርን አትጠይቁ፡፡ እናስ የጋብቻ ዓላማው ምንድነው ? ለምንድነው እግዚአብሔር ጋብቻን የሰጠን ? ብጹዕ ጳውሎስን እናድምጠው ፤ እንዲህ ያለውን ፦ "ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑሮው ፤ ለእያንዳንዲቱ ደግሞ ለራሷ ባል ይኑራት" [ ፩ኛ ቆሮ.፯፥፪ ]

" ከድህነት ይወጣ [ ትወጣ ] ዘንድ " ነው የሚለውን ? ወይስ " ሀብት ለማግኘት ሲባል " ነው የሚለውን ? አይደለም ! ታዲያ ምንድነው የሚለው? ከዝሙት እንጠበቅ ዘንድ ፤ ራሳችንን መቆጣጠር እንችል ዘንድ ፤ ንጽህናን ገንዘብ እናደርግ ዘንድ ፤ በትዳር አጋራችን ደስ ተሰኝተን እግዚአብሔርን እናመሰግን ዘንድ፡፡ አያችሁ ይኼ ነው የጋብቻ ስጦታው ይኼ ነው የጋብቻ ፍሬው ፤ ይኼ ነው የጋብቻ ጥቅሙ፡፡

ስለዚህ ልጆቼ ! እማልዳችኋለሁ ፦ ትልቁን ጥቅም ዘንግታችሁት ዓይናችሁን በትንሹ ላይ አታሳርፉ፡፡የትዳር አጋርን ስትመርጡ የሀብት ጉዳይ የእናንተ ትልቅ አጀንዳ ሊኾን አይገባም፡፡ ስለ ሀብት ብሎ የትዳር አጋርን መምረጥ ድንቁርና ነው ፤ ሀብት ነገ ሊጠፋ ይችላልና፡፡ ስለዚህ ለትዳር የምትመርጡት ሰው ከምንም በላይ መንፈሳዊ ሀብቱን ተመልከቱ፡፡ በዚህም ዓለም በወዲያኛውም ዓለም ይበልጥ የሚጠቅማችሁ ይኼ ነውና፡፡

አባቶች ሆይ ! አብርሃምን ምሰሉት፡፡ አብርሃም ለልጁ ለይስሐቅ ሚስትን ሲፈልግለት ፦ ሀብትን አላየም ፤ የንጉሣውያን ቤተሰብን አልተመለከተም ፤ አፍአዊ ውበትን መመዘኛ አላደረገም ፤ ወይም ይህን የመሰለ ሌላ መስፈርትን አልደረደረም፡፡ የነፍስ ንጽህናን እንጂ፡፡

እናቶች ሆይ ! ሴት ልጆቻችሁን እንደ ርብቃ አሳድግዋቸው፡፡ እናንተ ማግባትን የምትሹ ወጣቶች ሆይ ! ይስሐቅን ምሰሉት ፦ ዘፈንን ፣ ዳንኪራን ፣ ሳቅና ስላቅን ፣ የከበሮንና የዋሽንት ጫጫታን ፣ ሌላውንም የዲያብሎስ ትርኢት በሰርጋችሁ ቀን አታስቡ፡፡ ከዚህ ይልቅ በምታደርጉት ኹሉም ላይ እግዚአብሔር እንዲቀድማችሁ ለምኑት፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ ትዳራችሁ ፍቺ ፣ ዝሙት ፣ ቅናት ፣ ጭቅጭቅ ፣ ንትርክ የሌለበት ኾኖ ይፀናላችኋል፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ ፥ ሌላው በረከትም ተትረፍርፎ ይመጣላችኋል፡፡ የአውሎ ነፋስ ዓይነት በዙሪያችሁ ቢነፍስም ፥ አትነዋወፁም፡፡

እናንተ ልጃገረዶች ሆይ ! ርብቃን ምሰሏት፡፡ የትዳር አጋራችሁን ፍጹም ለማፍቀር የተዘጋጃችሁ ኹኑ፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ ቤታችሁ ፍጹም ሰላማዊ ባሎቻችሁ የምትልዋቸውን የሚያደርጉና በፍቅራችሁ የሚንበረከኩ ይኾናሉ፡፡ ትዳር እንዲህ ኾኖ ሲጀመር ፥ እግዚአብሔርንና ወላጆቹን ደስ የሚያሰኝ ልጅ ይገኝበታል፡፡

የቤት ዕቃዎችን መግዛት ስንፈልግ ፥ በጣም እንጠነቀቃለን፡፡ የሻጮቹን ማንነት አይተን ፣ የዕቃዉንም ጥንካሬ አገላብጠን ተመልክተን ነው የምንሸምተው፡፡ ሚስት ስናገባም ከዚህ የበለጠ ልንጠነቀቅ ይገባናል፡፡ የገዛነው ዕቃ ችግር ቢኖርበት ለሸጠልን ሰው መመለስ እንችላለን፡፡ ሚስት ስናገባ ግን ወደ ቤተሰቦቿ መመለስ አንችልም ፤ እስከ ዕድሜአችን ፍጻሜ ድረስ ከእኛ ጋር ነው የምትኾነው፡፡ ክፉ ናት ብለን ብንመልሳት ፥ በሕገ እግዚአብሔር መሠረት አመንዝራ እንኾናለን፡፡ ስለዚህ ፥ ሚስት ስትመርጡ የሀገራችሁን ሕገ መንግሥትን ብቻ አታንብቡ ፤ ከኹሉም በፊት ሕገ ቤተ ክርስቲያንን አንብቡ እንጂ፡፡"


(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

Join & share
👉 @mehereni_dngl
👉 @mehereni_dngl
👉 @mehereni_dngl
Enter a caption here!
Enter a caption here!
#የማንቂያ_ደውል

🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔
የምንፈራውም የማይቀረውም ሞት ነው። ዕለት ዕለት ስለሞት እየሰማንና እያየን ብንኖርም ቤተኛ አድርገን ልንወዳጀው ያልቻልነው ሞት ብቻ ነው።
ሞት ሁልጊዜ አዲስ ነው። እንደምንሞት አምነን እድር ብንመዘገብም እንደምንሞት አምነን ግን ንሰሐ ለመግባት አንፈጥንም። ሁልጊዜ እየቀበርን እንደምንኖር እንጂ አንድ ቀን እኛም ሞተን የምንቀበር አይመስለንም። ምክንኛቱም ሞት ማለት አዳምና ሄዋን ያመጡብን ድፍርስ ውሃ እንጂ ስንፈጠር ያልነበረ እንግዳ ነገር በመሆኑ ነው።
ስለዚህ ለዘለዓለም ሕይወት የተፈጠረ የሰው ልጅ ሞትን አሜን ብሎ መቀበል አለመፈለጉ እውነት ነው። ይሁን እንጂ ብንቀበለውም ባንቀበለውም እናታችን እንኳን የማትቀይረን ሞት ከፊታችን አለ። ነገር ግን ይህንን ንሡምና ምሁሩ ባዕለጠጋውና ደሀው ባለ ዝና ሆኖ ዓለም ያወቀውና ያላወቀው ሰው የሆነ በሙሉ የሚፈራውና የሚጨነቅለት ሞት በክርስቶስ ኢየሱስ ሙት ሆኗል።
እርሱ አምላካችን ሞትን በሞት ውጦታል። መድኃኒት ገዳዩን በሽታ ገሎ እንደሚያድን ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስም ገዳዩን ትገድሎ ከፍርሃትና ከባርነት ነጻ አውጥቶናል። ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሞተና እንደተነሳ ያመነ ሁሉ እርሱም ይነሳል መርፌው ባለፈበት ሁሉ አብሮ የተጣበቀው ክር ያልፋል።
ክርስቶስ በሄደበት ሁሉ ክርስቲያን ይሄዳል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞተ ተነሳ ንጽህት ቅድስት እናቱ ድንግል ማርያምም ሞተች እሷም እንደልጇ ተነሳች። ሌሎችም በመቃብር ልብ ያሉ ክርስቲያኖች በሙሉ ከሞት ለመነሳት የጌታን ቀን እየጠበቁ ነው።አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ያደረገ ሄኖክ አልሞተም። ነቢዩ ኤልያስም ሞትን ሳያይ በክብር አርጓል ብሎ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያለውን እውነት አምናለው የሚል ሰው እንዴት የአምላክ እናት ከሞት በመነሳት አርጋለች ሲሉት ለማመን ይቸገራል?ለማንኛውም ማስተዋሉን ይስጣቸው።

🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔
🔔Join🔔 @mehereni_dngl 🔔
🔔Join🔔 @mehereni_dngl 🔔
🔔Join🔔 @mehereni_dngl 🔔
🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔
Forwarded from ዘ ተዋህዶ
እንኳን ለሆሳዕና በዓል በሰላም አደረሳቹ? አደረስን
🌹ዘተዋህዶ🌹
💐@tewhodox💐
💐@tewhodox💐
💐ለወዳጅ ለዘመድ ለጓደኛ ያጋሩ 💐
2024/10/01 22:38:56
Back to Top
HTML Embed Code: