Telegram Web Link
Forwarded from ዘ ተዋህዶ
🌿ሆሳዕና_ማለት_ምን_ማለት_ነው ??
🌿በሆሳዕና_ለምን_ቀለበት_እናስራለን ?
🌿በሆሳዕና_ጌታችን_ለምን_በአህያ_ላይ_ተቀመጠ .
🌿በሆሳዕና_ለምን_ዘንባባ_አነጠፉ ?
................................................................
እና ሌሎች በደንብ ይነበብ ሼር!
=> ሆሳዕና ማለት ምን ማለት ነው??
ሆሳዕና ማለት፦ የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ ‹‹እባክህ አሁን አድን አሁን ባርከን›› ማለት ነው፡፡በሰሙነ ሕማማት ጸሎተ ፍትሃት ጸሎተ አስተስርዮ ስለማይፈጸም ጸሎተ ፍትሃትና አስተስርዮ
የሚደረገው በዚሁ ዕለት ነው::

=> በሆሣዕና ዕለት በእጃችን እደ ቀለበት ማሰራችን የምን ምሳሌ ነው??
1.ጌታ ለአዳም የሰጠው ቃል ኪዳን ለማስታወስ፡-ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድነሃለሁ ያለውን የተስፋ ቃል ለማስታወስ፡፡
2.ጌታ ለእመቤታችን የገባላትን ቃል ኪዳን ተምሳሌት ነው።
3.ጌታ ለእስራኤላውያን የሰጣቸው ቃል ኪዳን ተምሳሌት ነው።
4.ጌታ ለአዳም ከሰይጣን ግዛት ነጻ እንዳወጣው ሁሉ እኛም ከሰይጣን ግዛት ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ከክፋት ከኃጢአት አውጣን ማረን ለንስኃ ሞት አብቃን ከቤትህ አትለየን እንደ ቸርነትህ ይቅር በለን ስንል ለጌታ ዳግም ላናጠፋ ቃል የምንገባበት ነው፡፡

=> ጌታችን በዕለተ ሆሳዕና ለምን በፈረስ ላይ አልተቀመጠም??
ትንቢቱንና ምሳሌውን ለመፈጸም ነው፡፡ "
አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፤ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ
ግልገል በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።(ትንቢተ ዘካርያስ 9:9)
=> በአህያ መቀመጡ፦

•ትህትናን ለማስተማር
•የሰላም ዘመን ነው ሲል
•ለፈለጉኝ ሁሉ የቅርብ አምላክ ነኝ ሲል በንጽህና በየዋህነት ለሚኖሩ ምዕመናን አድሬባቸው እኖራለሁ ሲል፡፡

•አህያዎች ትሁታን ናቸው ረጋ ብለው ነው
የሚሄዱት፤በቀላሉ ትወጣበታለህ፤በቀላሉ
ትይዘዋለህ፤እንደፈለክም ታዝዋለህ።
ጌታችን ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ ዘባባ የመነጠፉ ሚስጢር የምን ምሳሌ ነው???
1.ዝንባባ፡- ይስሃቅ በተወለደ ጊዜ ደስ ብሎት አብርሃምን ዘንባባ ይዞ እግዚአብሔር አመስግነዋል፡፡
2.ዝንባባ ደርቆ እንደገና ሂይወት ይዘራል፡- የደረቀ የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
3.ዝንባባ የሰላም ምልክት ነው፡- የሰላም አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
4.ዝንባባ የደስታ መግለጫ ነው፡- አንተ ደስ የምታሰኝ ሃዘናችንም የምታርቅልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
5.ዝንባባ እሾሃማ ነው፡- አንተ ህያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
6.ዝንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጂ፡፡ ጌታም አንተ ባህሪህን የማይመረመር ነው ሲሉ ነው፡፡
ህዝቡ ከልብሳቸው ሌላ ስንት አይነት ቅጠንል አነጠፉለት ምን ምን??

ልብሳቸውን ማንጠፋቸው፡-
ለክብሩ መግለጫ ነው፡፡
ሌሎችም ሦስት አይነት ቅጠል አነጠፉለት ዘንባባ፤የቴመር ዛፍ፤የወይራ ዛፍ አነጠፉለት፡፡
ትልቅዋ አህያ በምን ትመሳለለች ውርን ጭለዋስ???
ትልቅዋ አህያ የኦሪት ምሳሌ ነው።
1.ትልቅዋ አህያ ሸክም የለመደች ናት ህገ ኦሪትም የተለመደች ህግ ናትና፡፡
2.የእስራኤል ምሳሌ ነው፡-ትልቅዋ አህያ ሸክም እንደለመደች ሁሉ እስራኤልም ህግ ለመፈጸም በህግ ለመራመድ የለመዱ ናቸው፡፡
3.የአዳም ምሳሌ ነው፡- አዳም ሸክም የበዛበት ነበርና።

ውርጭላዋ
1.በህገ ወንጌል ትመሰላለች፡-ምክንያቱም ወንጌል ኢየሱስ ክርስቶስ የመሰረታት የሰራት አዲስዋ ህግ ናትና፡፡
2.በአህዛብ ትመሰላለች፡-ትንሽዋ አህያ ሸክም የለመደች አይደለችም እንዲሁም አህዛብም ህግህን የመቀበል የመቀበል የለመደ አይደሉም፡፡ ለህግህ አዲስ ናቸውና፡፡
3.የእመቤታችን ምሳሌ ናት፡- የዓለም ሸክም አቅልላለችና በእመቤታችን ትመሰለላለች፡፡ እመቤታችን ድህነተ ምክንያታችን ጌታን የተሸከመች ንጽህት እንከን የሌላት እናት ናትና፡፡

ወስበሐት_ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ_ድንግል ወለመስቀሉ_ክቡር አሜን አሜን አሜን
🌹ዘተዋህዶ🌹
💐@tewhodox💐
💐@tewhodox💐
💐ለወዳጅ ለዘመድ ለጓደኛ ያጋሩ 💐
እንኳን ለበዓለ ትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ! አደረሰን!


✝️ መልካም በዓል ✝️

Join & share
👇👇👇👇👇👇
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
መሐርኒ ድንግል pinned «🌿ሆሳዕና_ማለት_ምን_ማለት_ነው ?? 🌿በሆሳዕና_ለምን_ቀለበት_እናስራለን ? 🌿በሆሳዕና_ጌታችን_ለምን_በአህያ_ላይ_ተቀመጠ . 🌿በሆሳዕና_ለምን_ዘንባባ_አነጠፉ ? ................................................................ እና ሌሎች በደንብ ይነበብ ሼር! => ሆሳዕና ማለት ምን ማለት ነው?? ሆሳዕና ማለት፦ የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ ‹‹እባክህ አሁን አድን…»
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼መልካም አዲስ አመት🌼🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ሉቃስ አሸጋገራችሁ !

መልካም አዲስ አመት
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼👇👇👇👇👇👇🌼
🌼 @MEHERENI_DNGL 🌼
🌼 @MEHERENI_DNGL 🌼
🌼 @MEHERENI_DNGL 🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

✝️🌼✝️ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ! ✝️🌼✝️

መሐርኒ ድንግል
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
✝️ @MEHERENI_DNGL ✝️
✝️ @MEHERENI_DNGL ✝️
✝️ @MEHERENI_DNGL ✝️
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

@MEHERENI_DNGL
በስመአብ በወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን

#ጥያቄ

የዘብዴዎስ ልጅ ማነው?

#ምርጫ

⚫️ቅዱስ በርቶሎሜዎስ
🔴ቅዱስ ያዕቆብ
🔵ቅዱስ እስጢፋኖስ
⚪️ቅዱስ ሐናንያ

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ጥያቄ እና መልስ ለማግኘት
👉 @mehereni_dngl
👉 @mehereni_dngl
👉 @mehereni_dngl
Audio
🌹ዘተዋህዶ🌹
💐@tewhodox💐
💐@tewhodox💐
💐ለወዳጅ ለዘመድ ለጓደኛ ያጋሩ 💐
+እንደ አርዮስ ሐሳብ መድኃኒታችን ክርስቶስ የባሕርይ አምላክ አይደለም (ሎቱ ስብሐት!!) ማለት ክርስትናን ከሥሩ ፈንቅሎ መጣል ነው::
+ስለ ክርስቶስ እግዚአብሔርነት ብሉይም ሐዲስም እየመሰከሩ:-
(ኢሳ. 9:6, መዝ. 46:5, 77:65, ዘካ. 14:4, ዮሐ. 1:1, 10:30, ራዕይ. 1:8, ሮሜ. 9:5 . . .)
አርዮስና የዛሬ መሰሎቹአንዲት ጥቅስ ይዘው ክርስትናን ከመሠረቱ ለመናድ መሞከራቸው በእርግጥም ከሰይጣን መላካቸውን ያሳያል::

+በወቅቱም በመወገዙ አርዮስ ወደ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ሔዶ ከሰሰ:: ቅዱሱ ንጉሥም የጉዳዩን ክብደት ተመልክቶ የዓለም ሊቃውንት ይሰበሰቡ ዘንድ አዘዘ::

+በ325 ዓ/ም (በኛው በ318 ዓ/ም) ለ40 ቀናት የሚቆይ ሱባኤን ያዙ:: ሱባኤውን ሲጨርሱም በ4ቱ ፓትርያርኮች (እለእስክንድሮስ: ሶል ዼጥሮስ: ዮናክንዲኖስና ኤዎስጣቴዎስ) መሪነት: በእለእስክንድሮስ ሊቀ መንበርነት: በአትናቴዎስ ጸሐፊነት ጉባኤው ተጀመረ::

+በጉባኤው ሙሉ ስልጣን በሰማይ ከፈጣሪ: በምድር ከንጉሡ የተሰጣቸው አበው አርዮስን ተከራክረው ከነ ጀሌዎቹ ምላሽ አሳጡት:: ክርስቶስ አምላክ ወልደ አምላክ: ሥግው ቃል: ራሱም እግዚአብሔር መሆኑን አስረዱት::

+በጉባኤው መጨረሻም አልመለስም በማለቱ አርዮስን አወገዙ: ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እንደሚገባ አደራጁ:: አባቶችም ሥራቸውን ከጨረሱ በሁዋላ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስን ባርከው ወደየ ሃገረ ስብከታቸው ተመልሰዋል::

+ቅዱስ ሶል ዼጥሮስም ከጉባዔው ከተመለሰ በሁዋላ በጐ ጐዳናውን አቅንቶ ቀጥሏል:: ብዙ ድርሳናትን ደርሶ: በድካም ሰብኮ ኢአማንያንን መልሷል:: ፈላስፎችንም ድል ነስቶ አሳምኗል:: መናፍቃን ደግሞ ፈጽመው ይፈሩት ነበር:: ሊቀ ዽዽስናን በተሾመ በ11 ዓመቱም በዚህች ቀን ዐርፏል::

=>የሥላሴ ቸርነት ከሁላችን ጋር ይሁንና ጥር 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.በዓለ ሥሉስ ቅዱስ
2.ቅዱስ ሶል ዼጥሮስ
3.ቅዱስ ኤፍሬም
4.ቅዱስ ሰሎሞን

=>ወርሐዊ በዓላት
1.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
2.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ)
3.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
4.አባ ባውላ ገዳማዊ
5.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
6.ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ)

=>+"+ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ: የእግዚአብሔርም ፍቅር: የመንፈስ ቅዱስም ሕብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን:: አሜን:: +"+ (ቆሮ. 13:14)

   <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
እጅግ አሳዛኝ ዜና!

ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የምስካየኅዙናን መድኃኒአለም ገዳም የበላይ ጠባቂ በዛሬው ዕለት እራሳቸውን ፓትሪያርክ በማድረግ 25 ኤጲስ ቆጶሳትን ሾመዋል!!!

በዛሬው ዕለት በወሊሶ መድኃኒአለም ቤተክርስቲያን ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ እራሳቸውን ፓትሪያርክ በማድረግ ለስልጣን ጥማት ያደረባቸውን 25 ኤጲስ ቆጶሳት አድርገው ሾመዋል።

ከአንድ የቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ የማይጠበቅ እና ህገ ቤተክርስቲያንን የሚፃረር ድርጊት ይፈፅማሉ ብለን የማንጠብቃቸው አቡነ ሳዊሮስ ይሄንን አድርገዋል።

ቤተክርስቲያኒቷ በራሷ ስርዓት እና ህግ የምትገዛ ሆኖም ሲኖዶሳዊት የሆነችውን ይቺ ሀገር የሆነችውን ቤተክርስቲያን ብትንትኗን ለማውጣት ይሄን ያህል መንገድ መራመዳቸው እጅግ የሚያሳዝን ተግባር ነው።

በአስቸኳይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ለምመናኗ መፍትሔ ሊሰጥ እንደሚገባ በታላቅ ትህትና እንጠይቃለን ።

@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
🌹ዘተዋህዶ🌹
💐@tewhodox💐
💐@tewhodox💐
💐ለወዳጅ ለዘመድ ለጓደኛ ያጋሩ 💐
2024/10/01 18:38:07
Back to Top
HTML Embed Code: