ማኅበረ ቅዱሳን ለወጣቶች የሱስ ማገገሚያ ተቋም ለማቋቋም የሚያስችል ጥናታዊ የምክክር ጉባኤ አካሄደ
ግንቦት ፴/፳፻፲፯ ዓ.ም
"ማኅበራዊ ቀውስን በማከም ትውልድን እንታደግ" በሚል መሪ ቃል ግንቦት 30 ቀን 2017 ዓ.ም በተካሄደው ጉባኤ በማኅበረ ቅዱሳን ሙያ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት ከባለድርሻዎች ጋር ሰፊ ጥናታዊ ሰነድን መነሻ ያደረገ ምክክር ተደርጓል።
በአሁኑ ወቅትም በአገራችን ኢትዮጵያ 46 ከመቶ በላይ የሚሆኑ ዜጎች ለሱስ (በአልኮል፣ ጫት ወይም የሲጋራ) ተጠቂ ሁነዋል ተብሏል። በተመሳሳይ የንጥረ ነገርም ይሁን የባሕሪ ሱስ የተጋላጮች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ስለመሆኑ ተነግሯል።
በዳሰሳ ጥናቱ ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች በንጥረ ነገር ሱስ ከመጠቃታቸው ባሻገር ሲሶ የሚሆኑት የኢንተርኔት ሱስ ተጠቂ ናቸው ተብሏል። ይህም ብቻ ያይደለ በጥናቱ የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎቹም ማኅበራዊ የመገናኛ አውታር መጠቀም የማይችሉበት አጋጣሚ ከተፈጠረ ጭንቀት እንደሚፈጥርባቸው አምነዋል ተብሏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በጥናቱ 52 ከመቶ ገደማ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በተለያዩ የሱስ አምጭ ንጥረ ነገሮች አማካኝነት የሱስ ተጠቂ ሁነው መገኘታቸው የተገለጸ ሲሆን ከቤተክርስቲያናችን ምእመናን ውስጥ 50 ከመቶ ገደማ የሚሆኑትም ለተለያዩ ሱሶች ተገዢ መሆናቸው ተጠቅሷል።
በማያያዝም ምእመናን በሱስ ምክንያት የቤተክርስቲያንን ሥርዓት ለመፈጸም እንደሚቸገሩ ነው የተነሳ ሲሆን ቁጥር ልክ የሱሰኛ ወገኖቻችን ቁጥር መጨመሩ ለአገራችን እና ለቤተክርስቲያናችን እጅግ አሳሳቢ ነው ተብሏል።

የንጥረ ነገርም ይሁን የባሕሪ ሱስ ተጠቂ የሆኑ ግለሰቦች የአካልና የአእምሮ ጤናቸው ከመታወኩ ባለፈ ሱሰኝነት በማኅበራዊ ሕይወት ፤ በሰላም እና ደህንነት ብሎም በኢኮኖሚው ላይ የሚያሳርፈው ጠባሳም ቀላል የሚባል እንዳልሆነ ተመላክቷል።
ታዲያ ለቤተክርስቲያናችን ብሎም በአገር ደረጃ አሳሳቢ ለሆነው ሱሰኝነት በጊዜ መፍትሔ ማስቀመጡ አግባብነት ያለው ተግባር መሆኑ ነው በምክክር መርሐ ግብሩ የተነገረው።
ማኅበረ ቅዱሳንም በሙያ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት በኩል ለችግሩ መፍትሔ ብሎ ያስቀመጠው ቤተክርስቲያናችን ባሏት ገዳማትና አድባራት "የሱስ ማገገሚያ ማእከል" ማቋቋምን ሲሆን ለምክረ ሐሳቡ ተግባራዊነት ደግሞ ለእያንዳንዱ ሱስ የሚያስፈልገው የማገገሚያ ዓይነትና ተቋም የሚለያይ በመሆኑ ለሁሉም የሱስ ዓይነቶች ማገገሚያ ተቋም በአንድ ላይ እንዲሁም በተናጠል ማቋቋም በርከት ያለ ገንዘብ፣ ጊዜ፣ የሰው ኃይል ማሰናዳት ያስፈልጋል ተብሏል።
በቀጣይ ጊዜም ይህን ሥራ ወደ ተግባራዊ መፍትሔ ለመቀየር የሚቻልበት ዝርዝር መፍትሔዎችን ወደ ተግባር የሚቀየር ግብረ ኃይል በማቋቋም ጉባኤው ፍጻሜውን አግኝቷል ተብሏል።

ማኅበረ ቅዱሳን ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሥነ ልቡና ዝግጅት ሥልጠና እየሰጠ እንደሚገኝ ተጠቆመ
ሰኔ ፪/፳፻፲፯ ዓ.ም
ማኅበረ ቅዱሳን ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሥነ ልቡና ዝግጅት ሥልጠና እስካሁን በማእከላት ሲሰጡ የነበረ ሲሆን ከእነዚህም መካከል በጅግጅጋ፣ በመቱ፣ በነቀምቴ፣ በጂንካ ማእከላትና በስማዳ ወረዳ ማእከል እንደሚገኙበት ተመላክቷል።
በአገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ሰኔ 8 ቀን 2017 ዓ.ም በቴሌግራም (@MKFOR12TH) የስነ ልቦና ሥልጠና እንደሚሰጥ የተጠቆመ ሲሆን በዚህም ማኅበረ ቅዱሳን ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሥልጠናው እንዲሳተፉ ጥሪውን ያቀርባል።

ለግቢ ጉባኤያት ዕጩ ምሩቃን ተማሪዎች የቢዝነስ ፕላን (ፕሮጀክት) አዘገጃጀት ሥልጠና መሰጠቱን ደብረ ታቦር ማእከል ገለጸ
ሰኔ ፪/፳፻፲፯ ዓ.ም
በማኅበረ ቅዱሳን ደብረ ታቦር ማእከል ለግቢ ጉባኤያት ዕጩ ምሩቃን ተማሪዎች የቢዝነስ ፕላን (ፕሮጀክት) አዘገጃጀት ሥልጠና መሰጠቱ ተገልጿል፡፡
የማእከሉ ሙያና ማኅበራዊ አገልግሎት ዋና ክፍል ባዘጋጀው በዚህ መርሐ ግብር 82 የጉና ታቦር ጤና ሳይንስና ቢዝነስ ኮሌጅ ዕጩ ምሩቃን ተማሪዎች ተሳትፈዋል፡፡
ሥልጠናው በደብረ ታቦር ማእከል የትብብርና ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ በሆኑት አቶ ደግሰው ምስጋናው በሰኔ 1 ቀን 2017 ዓ.ም በማእከሉ አዳራሽ ተሰጥቷል፡፡
የመርሐ ግብሩ ዋና ዓላማ በማኅበረ ቅዱሳን ተቋማዊ ለውጥ መነሻነት በተዘጋጀው 5ኛ ዙር ሥልታዊ ዕቅድ መሠረት “ለግቢ ጉባኤያት ተመራቂዎች የሥራ እና ክህሎት ማበልጸጊያ ሥልጠናዎችን በመስጠት ተወዳዳሪ እንዲሆኑ መደገፍ” እንደሆነ ተገልጿል።
ስለሆነም ዕጩ የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎች ስለ ቢዝነስ ፕላን አዘገጃጀት መሠረታዊ መነሻ ሐሳቦችን እንዲጨብጡ በማድረግ የተለያዩ ስፖንሰር አድራጊ ተቋማት በሚሰጧቸው የቢዝነስ ፕላን ውድድሮች ተወዳዳሪ ሁነው ውጤታማ መሆን የሚችሉበትን ዕድል ይፈጥርላቸዋል ተብሏል።