በማኅበረ ቅዱሳን የሚሠሩ የማኅበራዊ አገልግሎት ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተገለጸ፡፡
ግንቦት ፳፱/፳፻፲፯ ዓ.ም
በማኅበረ ቅዱሳን የሕዝብ ግንኙነት እና ትብብር አገልግሎት ከብሔራዊ የደም ባንክ አገልግሎት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የደም ልገሳ መርሐ ግብር በዋናው ማእከል እና በሌሎች ማእከላቶች ተከናውኗል፡፡
አቶ ሰይፉ ዓለማየሁ በማኅበሩ የሕዝብ ግንኙነት እና ትብብር አገልግሎት ዋና ሥራ አስኪያጅ እንደገለጹት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳስተማረን እና ክርስትና የመስጠት ሕይወት እንደመሆኑ መጠን የዛሬው የደም ልገሳ መርሐ ግብር ለተከታታይ 10 ዓመታት እየተካሄደ እንደቆየ ተናግረዋል፡፡
አክለውም በርካታ ሰዎችን ካሉበት የሥጋዊ ሕመም በመታደግ የነፍስ አድን ተግባራትን ማከናወን በሚል መሠረታዊ ዓላማ እና መርሕ ይህን ሰብአዊ ሥራ በማኅበሩ መጀመሩን አስታውሰዋል።
እንደየ ማእከላቱ ወቅታዊ ሁኔታ መርሐ ግበሩ በየዓመቱ እየተከናወነ ሲሆን አባላቱም ተሳትፎውን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እና የመረዳዳት ባህሉም እያደረገው ይገኛል ብለዋል፡፡
ዋና ሥራ አስኪያጁ አያይዘው እንዳነሱት የደም ልገሳ መርሐ ግብሩን በተሻለ ሁኔታ ለማጎልበት ዕቅድ ታቅዷል ያሉ ሲሆን የቅድስት ቤተ ክርስቲያን መዋቅር ሰፊ በመሆኑ በማኅበረ ቅዱሳን እየተሠሩ የሚገኙ የተለያዩ የማኅበራዊ አገልግሎት ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን በደባርቅ፣ በወሊሶ፣ በአርባ ምንጭ፣በሰቆጣ እና በሌሎች ማእከላቶች የደም ልገሳ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት ግንቦት 29 ቀን 2017 ዓ.ም ሲያከናውን መዋሉ ተጠቁሟል።
ማኅበረ ቅዱሳን ከሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጋር በመተባበር ለ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ልዩ ሥልጠና አዘጋጅቷል።
ሰኔ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ የሚሰጠውን ሥልጠና ከሥር በተቀመጠው የቴሌግራም አድራሻ ላይ መከታተል ይችላሉ።
@MKFOR12TH

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ባሏት ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶች ላይ አጋር አካላት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
ግንቦት ፴/፳፻፲፯ ዓ.ም
የቅድስተ ቤተ ክርስቲያን በርካታ አገልግሎት በሁለም ዘርፎች እንዲሰፋ፣እንዲጎለብት እና እንዲያድግ አቅም እና ገንዘብ ያላቸው ምእመናን መሳተፍ እንዳለባቸው ተገልጿል፡፡
የተለያዩ ገዳማት እና አብያተ ክርስቲያናት ለሚያስፍልጋቸው ድጋፍ እገዛ በማድረግ እና በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ማስፋፋት ረገድ በግልም ሆነ በኮሚቴ አቅም እና ገንዘብ ካላቸው ባለሀብት ጋር አብረው እየሠሩ መሆናቸውን በግል የሥራ ዘርፍ የተሰማሩት ወ/ሮ ሜሮን ታደለ ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም በግለሰብ ደረጃ ሰዎች ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲመለሱ በማድረግ፣በክረምት ወቅት ለሕጻናት፣ለአዳጊዎች እና ለወላጆች የተለያዩ መንፈሳዊ ሥልጠናዎችን በመስጠት እንዲሁም ከተቋማት ጋር በመተባበር በሴቶች እና በሕጻናት ላይ ሥራችዎን እየሠሩ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡
ወ/ሮ ሜሮን አክለውም ከባለሀብቶች በተጨማሪ ሌሎች ምእመናን ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ያላቸውን ጊዜ እና ገንዘብ እንዲያበረክቱ ከማድረግ በፊት ራሳቸውን እንዲሰጡ ማድረግ እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡
አሁን ያለው የተለያዩ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እንዲሰፋ የምእመናንን ጎዶሏቸውን ማገዝ እንዲሁም መሳተፍ የሚችሉበትን ዕድል እና ሁኔታ መፍጠር እንደሚያስፈልግ ወ/ሮ ሜሮን አያይዘው አንስተዋል፡፡
ትንሽ በመስጠት ብዙ ለማትረፍ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ባሏት ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶች ላይ ባለሀብቶች በመሳተፍ ኀላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባቸው መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡