Telegram Web Link
የነቀምቴ ማእከል አባላት ደም እየለገሱ ነው።
የማኅበረ ቅዱሳን ባሌ ሮቤ ማእከል ከብሔራዊ ደም ባንክ አገልግሎት ጎባ ቅርንጫፍ ጋር በመታባበር የደም ልገሳ መርሐ ግብር አከናወነ።

ግንቦት 29/2017 ዓ.ም

የማኅበረ ቅዱሳን ባሌ ሮቤ ማእከል ሕዝብ ግንኙነት እና ትብብር አገልግሎት ዋና ክፍል ከብሔራዊ ደም ባንክ አገልግሎት ጎባ ቅርንጫፍ ጋር በመታባበር የደም ልገሳ መርሐ ግብር ግንቦት 29 ቀን 2017 ዓ.ም በሮቤ ፈለገ ብርሃን ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አካሂዷል።

በመርሐ ግብሩ ቀሲስ ሸዋንግዛው ተክለ ማርያም የብሔራዊ ደም ባንክ አገልግሎት ጎባ ቅርንጫፍ
ኃላፊ፣ ትግስት አለማየው የማኅበረ ቅዱሳን ባሌ ሮቤ ማእከል ምክትል ሰብሳቢ ፣ ፀሃይ ደስታ የማእከሉ ሕዝብ ግንኙነት እና ሚዲያ ክፍል ተጠሪ፣ የማእከሉ አባላት እና ምዕመናን ተገኝተዋል።

ቀሲስ ሸዋንግዛው ተክለ ማርያም የጎባ ደም ባንክ ቅርንጫፍ ኃላፊ እንዳሉት በሆስፒታል የተቸገሩ ብዙ እናቶች እና ወንድሞች ያሉ ሲሆን ከፍተኛ የደም እጥረት እንደ አገራች እና አከባቢያችን ያለ ሲሆን በዛሬው እለት እና ከዚህም በፊት ማኅበረ ቅዱሳን በማስተባበር ላደረገልን የደም ልገሳ እናመሰግናለን ብለዋል።


በመጨረሻም የማኅበረ ቅዱሳን ባሌ ሮቤ ማእከል ሕዝብ ግንኙነት እና ሚዲያ ክፍል ዋና ተጠሪ ፀሃይ ደስታ
በዚህ መርሐ ግብር ላይ ደማቸውን የለገሱ ምእመናን እና የጎባ ደም ባንክ ቅርንጫፍ ባለሞያዎችን አመስግነዋል።
የማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል የደም ልገሳ መርሐ ግብር 5 ኪሎ በሚገኘው የማኅበሩ ሕንጻ ላይ በመከናወን ይገኛል
2025/07/08 00:02:40
Back to Top
HTML Embed Code: