Telegram Web Link
ማኅበረ ቅዱሳን ዱራሜ ማእከል የደም  ልገሳ መርሐ ግብሩን አከናውኗል።
በማኅበረ ቅዱሳን የሚሠሩ የማኅበራዊ አገልግሎት ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተገለጸ፡፡

ግንቦት ፳፱/፳፻፲፯ ዓ.ም

በማኅበረ ቅዱሳን የሕዝብ ግንኙነት እና ትብብር አገልግሎት ከብሔራዊ የደም ባንክ አገልግሎት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የደም ልገሳ መርሐ ግብር በዋናው ማእከል እና በሌሎች ማእከላቶች ተከናውኗል፡፡

አቶ ሰይፉ ዓለማየሁ በማኅበሩ የሕዝብ ግንኙነት እና ትብብር አገልግሎት ዋና ሥራ አስኪያጅ እንደገለጹት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳስተማረን እና ክርስትና የመስጠት ሕይወት እንደመሆኑ መጠን የዛሬው የደም ልገሳ መርሐ ግብር ለተከታታይ 10 ዓመታት እየተካሄደ እንደቆየ ተናግረዋል፡፡

አክለውም በርካታ ሰዎችን ካሉበት የሥጋዊ ሕመም በመታደግ የነፍስ አድን ተግባራትን ማከናወን በሚል መሠረታዊ ዓላማ እና መርሕ ይህን ሰብአዊ ሥራ በማኅበሩ መጀመሩን  አስታውሰዋል።

እንደየ ማእከላቱ ወቅታዊ ሁኔታ መርሐ ግበሩ በየዓመቱ እየተከናወነ ሲሆን አባላቱም ተሳትፎውን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እና የመረዳዳት ባህሉም  እያደረገው ይገኛል ብለዋል፡፡

ዋና ሥራ አስኪያጁ አያይዘው እንዳነሱት የደም ልገሳ መርሐ ግብሩን በተሻለ ሁኔታ ለማጎልበት ዕቅድ ታቅዷል ያሉ ሲሆን የቅድስት ቤተ ክርስቲያን መዋቅር ሰፊ በመሆኑ በማኅበረ ቅዱሳን እየተሠሩ የሚገኙ የተለያዩ የማኅበራዊ አገልግሎት ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን በደባርቅ፣ በወሊሶ፣ በአርባ ምንጭ፣በሰቆጣ እና በሌሎች ማእከላቶች የደም ልገሳ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት ግንቦት 29 ቀን 2017 ዓ.ም ሲያከናውን መዋሉ ተጠቁሟል።
2025/07/08 04:53:18
Back to Top
HTML Embed Code: