Telegram Web Link
በሳንሆዜ የሚገኙ  የማኀበሩ አባላት የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል ፣ የማኅበረ ቅዱሳን ፴፫ኛ ዓመት የምስረታ በዓል እና ግብረ ሰላም   በደመቀ ሁኔታ አክብረዋል።
👍51🙏1
ለተመራቂ ጋዜጠኛ ተማሪዎች ሥልጠና መሰጠቱ ተገለጸ።

ግንቦት ፲፩/፳፻፲፯ ዓ.ም

ማኅበረ ቅዱሳን በደብረ ማርቆስ ማእከል ሚዲያ አገልግሎት ዋና ክፍል አዘጋጅነት ለደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ እና 3ኛ ዓመት የጋዜጠኝነት ተማሪዎች ስለሚዲያ አጠቃቀምና አገልግሎትና መንፈሳዊነት በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ግንቦት 09 ቀን 2017 ዓ.ም  ሥልጠና መሰጠቱ ተገልጿል ።

ዶ/ር ሃይማኖት ጌታቸው የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ኃላፊና የጋዜጠኝነት መምህር የሚዲያ አጠቃቀም እስከምን ድረስ የሚል ሰፊ ገለጻ ያቀረቡ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ዓለምን 1ኛ መንግስት ሆኖ እየመራ የሚገኘው ማኅበራዊ ሚዲያ በመሆኑ ቤተክርስቲያን ላይ የሚነሱትን የሐሰት ትርክቶች ፣ የቤተክርስቲያንን ትምህርት በመማርና በማወቅ በሙያችሁ ለእውነት በመቆም የቤተክርስቲያን ድምጽ መሆን እንደሚገባቸው ለተማሪዎች አስገንዝበዋል።

የማኅበራዊ ሚዲያው በደንብ ከተሠራበት የገቢ ምንጭም እንደመሆኑ ቋሚ ሥራ ሆኖ ሊሠራ የሚችል በመሆኑ ከሥራ ፈላጊነት ሐሳብ ወጥተው በሙያቸው ለቤተክርስቲያን ዘብ በመቆም ከተቀጣሪ የበለጠ የገቢ ምንጭ ማግኘት የሚቻልበት የሙያ መስክ መሆኑን አስረድተዋል።

የደብረ ማርቆስ ማእከል ጽ/ቤት ኃላፊ ግዛቸው ባወቀ የአገልግሎትን ምንነትና መንፈሳዊነት በሰፊው ገለጻ አድርገው "የምናውቀውን እንናገራለን፣ ያየነውን እንመሰክራለን።" እንደተባለው ሥልጠናውን የወሰዳችሁት የቤተክርስቲያኗ ዓይንና ጆሮ ሆናችሁ "የምታውቁትን እንድትናገሩ ያያችሁን እንድትመሰክሩ።" ነው በማለት አስገንዝበዋል።
👍3🙏3
"ሥነ ልቦናዊ ዝግጅት ለአገር አቀፍ ፈተና" በሚል ርእስ ሥልጠና መሰጠቱን  ደብረ ብርሃን ወረዳ ማእከል አስታወቀ

ግንቦት ፲፩/፳፻፲፯ ዓ.ም

ማኅበረ ቅዱሳን ደብረ ብርሃን ወረዳ ማእከል አገር አቀፍ ፈተና ለሚፈተኑ የ12ተኛ ክፍል ተማሪዎች"ሥነ ልቦናዊ ዝግጅት ለአገር አቀፍ ፈተና" በሚል ርእስ ግንቦት 10 ቀን 2017 ዓ.ም  በአጼ ዘርዓ ያዕቆብ ሕንፃ 5ተኛ ወለል ላይ ሥልጠና እንደተሰጠ አስታውቋል።

ሥልጠናዉን የሰጡት የደ/ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የሳይኮሎጂ መምህር የሆኑት ዘነበ ደምሴ  በሥልጠናዉ  ስለ ሰዓት አጠቃቀም ፣ ስለ ፈተናዉ አዕምሮአዊ ዝግጅት ፣ የፈተና ጭንቀት መንስዔዎች ፣ ለነገሮች የምንሰጠዉ በጎ እሳቤ ፣ ስለምናጠናባቸዉ ቦታዎች ምርጫ ፣ ልምምድ ፣ ራስን ማክበር ፣ በራስ መተማመን ፣ ለማይችሉት ነገር ዕርዳታ መጠየቅ፣ አዕምሮ ላይ መሥራት እና የመሳሰሉ ርዕሰ ጉዳዮች እንደተነሱበት ተጠቁሟል።

መምህር ዘነበ ደምሴ አያይዘውም ከተማሪዎች የተነሱ ጥያቄዎች እና ስጋቶች ስለ ቅድመ ፈተና ዝግጅትን እና ጥሩ ውጤት ለማምጣት መደረግ ያለባቸዉን  የመፍትሔ ሐሳቦች ላይም  አካባቢን መቃኘት ፣ እገዛን መጠየቅ፣ ጠንካራ ልምድን ማዳበር
በጊዜ ዕቅድ መመራት ፣ ካለፈ ስህተት መማር ፣አዎንታዊ አስተሳሰብን ልምድ ማድረግ፣ እችላለሁ የሚል መንፈስን ማዳበር ፣ ጥሩ ጓደኛን መምረጥ፣ የሚሰጡ ሥልጠናዎችን መሳተፍ  እና የመሳሰሉትን እንደ ምሳሌ አንስተው ምላሽ ሰጥተዋል።

በመጨረሻም "በጠንካራ መንፈስ፣ በልበ ሙሉነት፣ በይሳካል መንፈስ   ተነስተን በመሥራት ዉጤታማ እንሆናለን" !!
በማለት ተፈታኞችን አነቃቅተዋል።
👍5🙏41
የማኅበረ ቅዱሳን ደ/ብርሃን  ማእከል ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አካሉ ማስረሻ በበኩላቸው ይህ ሥልጠና ቀጣይነት እንደሚኖረው እና በማንኛውም አጋጣሚ ተማሪዎችን ዉጤታማ ለማድረግ ማእከሉ ከሚመለከተው አካል ጋር በጋራ  እንደሚሠራ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።

በመርሐ ግብሩ  የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር  ትምህርት መምሪያ፣ የደ/ብርሃን አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ጉድኝት ሱፐር ቫይዘር የሆኑት መምህርት መዝገበ ወርቅ ቢችል ማኅበረ ቅዱሳን ደ/ብርሃን ወረዳ ማእከል በዘንድሮዉ ዓመት በተለየ ሁኔታ ለ12ኛ ክፍል ሲያደርግ የቆየውን የሥልጠና እና የቀለም ትምህርት እገዛ በማንሳት ማእከሉ ስላደረገው ድጋፍ ምሥጋና አቅርበዋል።

አያይዘውም ስለ ፈተናው አሰጣጥ ሂደት እና ስለ online ፈተና ሰፋ ያለ ማብራሪያ ለተማሪዎቹ ሰጥተዋል።

በመጨረሻም በሥልጠናው ላይ የተገኙ የ12ተኛ ክፍል ተማሪዎች ማኅበሩ እያደረገላቸው ያለውን ድጋፍ በማንሳት ብዙ ለውጥ እንዳመጡ እና እንደተጠቀሙ አንስተው ማኅበሩ እስከ ፈተና ሰዓታቸው ድረስ እገዛው እንዳይለያቸው አሳስበዋል።


ሐሳባቸውን የሰጡት ተማሪዎችም አያይዘውም ማኅበሩ ስላደረገላቸው ድጋፍ ሁሉ አመስግነዋል።
👍16🕊5
2025/07/09 01:39:24
Back to Top
HTML Embed Code: