ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብን ማጠናከርና ማብቃትን መሠረት ያደረጉ የአመካካሪዎች ሥልጠና በተለያዩ ቦታዎች መሠጠታቸው ተገለጸ ።
የማኅበረ ቅዱሳን ሙያ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት በሥልታዊ ዕቅዱ ትኩረት አድርጎ ከሚሠራባቸው አገልግሎቶች አንዱ በመንፈሳዊ የምክክር አገልግሎት የሚሰማሩ ካህናትና ባለሙያዎችን በማሠልጠንና በበቂ ሁኔታ በማዘጋጀት ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ የሚያጠናክሩ አካላትን ማፍራት አንዱ ነው።
በዚሁ መሠረት ከኅዳር 14 እስከ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በወልቂጤ ማእከል አስተባባሪነት በጉራጌ ሀገረ ስብከት መንበረ ጵጵስና አዳራሽ በተሰጠው ሥልጠና ከጉራጌና ምሥራቅ ጉራጌ አህጉረ ስብከት የተውጣጡ 31 ካህናት፣ ዲያቆንት፣ መምህራን፣ የሥነ-ልቦናና ሌሎች ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል፡፡
በዚህ ሥልጠና ክብረ ክህነትና አበ ነፍስ፣ መንፈሳዊ የምክክር አገልግሎት አሰጣጥ፣ ኦርቶዶክሳዊ ጋብቻና የልጆች አስተዳደግ፣ የሱስ ችግሮችን ለማቃለል በኦርቶቶዶክሳዊ አስተምህሮ ዕይታ እንዲሁም ምጣኔ ሐብትና ማኅበራዊ ዕድገት ጉዳዮች ተዳሰውበታል፡፡
በወልቂጤ ከተማ በተሠጠው ሥልጠና ብፁዕ አቡነ መልከጸዴቅ የጉራጌ ሀገረ ስብከት እና የቅዱስ አቡነ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ መሥራችና የበላይ ጠባቂ ሊቀ ጳጳስ በቦታው በመገኘት ሥልጠናውን በጸሎት በመክፈት የሥራ መመሪያ የሰጡ ሲሆን፣ ሠልጣኞች ባገኙት ሥልጠና በመታገዝ ዘመኑን የዋጀ የቅድስት ቤተክርስቲያን ሁለንተናዊ አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

👍11❤9
በተመሳሳይ ጊዜና ርእሰ ጉዳይ በሰቆጣ ማእከል በተሰጠው ሥልጠናም 43 ያህል ካህናት፣ መምህራንና ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ በእነዚህ ሥልጠናዎች የተሳተፉ ሠልጣኞች በሥልጠናው ጥሩ ግንዛቤና ልምድ እንዳገኙበት ገልጸው ወደ መጡበት አካባቢ ሲመለሱ ምእመናን ያለባቸውን ዘርፈ ብዙ ማኅበራዊ ቀውስ እንዲቋቋሙ የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት እንደሚያስችላቸው ተናግረዋል፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን ለሥልጠናው መሳካት ቦታ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ጭምር ለተባበሩት የጉራጌ ሀገረ ስብከትና ማእከላትን እያመሰገነ ቀጣይ በሌሎች አካባቢዎች ለሚሰጠው ሥልጠናም በገንዘብና ቁሳቁስ ጭምር በመደገፍ የቤተ ክርስቲያን አካላት በቅንጅት አብረው እንዲሠሩ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
ይህን የሥልጠና መርሐ ግብር በገንዘብ መደገፍ ለምትፈልጉም፡-
#በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡-
1. በአሐዱ ባንክ - 0025393810901
2. በአቢሲንያ ባንክ - 37235458
3. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000309803648
4. በወጋገን ባንክ - 0837331610101
5. በአዋሽ ባንክ 01329817420400 መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

❤5👍2
"ወደ ቀደመው ነገር እንመለስ"
ልዩ የአባላት የቃል ኪዳን ማጽኛ መርሐ ግብር
በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት በሙሉ የተዘጋጀ ልዩ የአገልግሎት ቃል ኪዳን ማጽኛ መርሐ ግብር
እርስዎም በማኅበሩ ምሥረታ ጀምሮ በየትኛውም ወቅት በአባልነት ሲሳተፉ ከነበሩ በዚህ መርሐ ግብር ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል።
ቀን፡ ኅዳር 22/2017 ዓ.ም
ሰዓት፡ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ
ቦታ፡ በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም እና መጥምቁ ዮሐንስ ካቴድራል አዳራሽ
ለተጨማሪ መረጃ፡- 0911898990
"ወደ ሁሉም አቅጣጫ መመለሻ ትራስፖርት ተዘጋጅቷል"

👍20❤8
“ወደ ቀደመው ነገር እንመለስ” በሚል መሪ ቃል የአባላት የቃል ኪዳን ማጽኛ መርሐ ግብር ተካሄደ፡፡
በኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን በሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ወደ ቀደመ ነገር እንመለስ በሚል መሪ ቃል የአባላት የቃል ኪዳን ማደሻ መርሐ ግብር በደብረ ሰላም ቦሌ መድኃኔዓለም እና መጥምቀ መለኮት ቤተ ክርስቲያን በትላንትናው ዕለት አከናውኗል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስን ጨምሮ የማኅበሩ የሥራ አመራር አባላት እና ከ2000 በላይ የአዲስ አበባ ማእከል አባላት ታድመዋል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ማእከል ሰብሳቢ ዲ/ን ኃ/ማርያም መድኅን የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ሲያስተላልፉ “ አዲስ አበባ ማእከል በተቋማዊ ለውጡ ትግበራ መሠረት የጀመረውን አዲሱን መዋቅራዊ አደረጃጀት ውጤታማ ለማድረግ ቀዳሚው ተግባር የአባላትን አገልግሎት ማጠናከር ነው” ብለዋል፡፡ ቀጥለውም “ አባላት ቃል ኪዳናቸውን አድሰው የአገልግሎት ተሳትፏቸውን እንዲያጠናክሩ እና ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ወደ ማኅበሩ ሲቀላቀሉ የገቡትን ቃል ሊፈጽሙ ይገባል “ ሲሉ የአጽንዖት መልዕክታቸውን አስተላለፍዋል፡፡
የአባላት ተቋማዊ ለውጥ ትግበራ ዐቢይ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዲ/ን ሲሳይ ብርሃኑ በዕለቱ ለተገኙ ታዳሚዎች ስለ ጉባኤው ዓላማ እና የአባላት ድርሻን በተመለከተ “የአባላት የአገልግሎት በር” በሚል ርዕስ ጽሑፍ ያቀረቡ ሲሆን አባላት በተቋማዊ ለውጥ ትግበራ ተሳትፏቸው የጎላ እንዲሆን የሚሳተፉባቸው የአገልግሎት አማራጭ በሮች ክፍት ሁነው እንደሚጠብቋቸውና ገብተው እንዲያገለግሉ አማራጭ የአገልግሎት በሮችን በዝርዝር አስረድተዋል፡፡

❤12👍3
በዚሁ የአባላት ልዩ መርሐ ግብር ላይ በመ/ር ብርሃኑ አድማስ " እግዚአብሔርን ማየት" በሚል ትምህርተ ወንጌል፣ በቀ/ዶ/ር ይቻለዋል ጎሽሜ የማኅበረ ቅዱሳን የአገልግሎት ፈተናዎችና ጉዞን በተመለከተ ልምድ የማካፈል እና በቀሲስ ዘማሪ ምንዳዬ ብርሃኑ እና በዘማሪት ብዙዓየሁ ተክሉ የመዝሙር መርሐ ግብራት ተከናውነዋል፡፡
በመጨረሻም በብፁዕ አቡነ መቃርዮስ የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አማካኝነት “እርፍ ይዞ ወደ ኋላ የለም፣ ማኅበራችሁን ጠብቁ ፣በገባችሁት ቃል መሠረት ቤተ ክርስቲያናችሁን አገልግሉ፡፡” በሚል አባታዊ ቡራኬ እና ቃለ ምዕዳን መርሐ ግብሩ ተጠናቋል፡፡

👍19❤10🙏5
https://youtu.be/48VpDrn7n2Y?si=CoSaBR5by0LYPrN6
ገባሬ መንክራት ሰማዕት ሰማዕት መርቆሬዎስ
ተራድአነ በገሃድ ተራድአነ በገሃድ
አዝ......
ለአረማዊ ወጣት መድኃኒት የሆንከው
ከአራዊት ጠብቀህ ከሞት የታደግከው
ካለመኖር ወደመኖር የመለስከው
ተራዳን በሃይማኖት ሆነን ለደከምነው
አዝ....
ዛሬም በእኛ ዘመን እንደ ዑልያኖስ
ጣኦት የሚያመልኩ የወጡ ከመንፈስ
ከርስት እንዳይለዩን እደር በእኛ መሐል
ጥበብ ኃይል ሁነን መርቆሬዎስ ኃያል
አዝ....
የሮማዊ ሰማዕት የጳጳሳት ደስታ
የእግዚአብሔር አገልጋይ የኢትዮጵያ አለኝታ
ከእስር ቤት ወጥቶ ሥዕልህ በተአምር
ዑልያኖስን ገድሎ ተመለሰ በክብር
አዝማች....
የአብ ወዳጁ የእግዚአብሔር አገልጋይ
ልመናችንን አድርስ ወደአምላክ አዶናይ
በሞት እንዳንጠፋ በሕይወት ጠብቀን
በአንተ ተማጽነናል ኪዳንህን አምነን
አዝ.....
ገባሬ መንክራት ሰማዕት ሰማዕት መርቆሬዎስ
ተራድአነ በገሃድ ተራድአነ በገሃድ
አዝ......
ለአረማዊ ወጣት መድኃኒት የሆንከው
ከአራዊት ጠብቀህ ከሞት የታደግከው
ካለመኖር ወደመኖር የመለስከው
ተራዳን በሃይማኖት ሆነን ለደከምነው
አዝ....
ዛሬም በእኛ ዘመን እንደ ዑልያኖስ
ጣኦት የሚያመልኩ የወጡ ከመንፈስ
ከርስት እንዳይለዩን እደር በእኛ መሐል
ጥበብ ኃይል ሁነን መርቆሬዎስ ኃያል
አዝ....
የሮማዊ ሰማዕት የጳጳሳት ደስታ
የእግዚአብሔር አገልጋይ የኢትዮጵያ አለኝታ
ከእስር ቤት ወጥቶ ሥዕልህ በተአምር
ዑልያኖስን ገድሎ ተመለሰ በክብር
አዝማች....
የአብ ወዳጁ የእግዚአብሔር አገልጋይ
ልመናችንን አድርስ ወደአምላክ አዶናይ
በሞት እንዳንጠፋ በሕይወት ጠብቀን
በአንተ ተማጽነናል ኪዳንህን አምነን
አዝ.....
YouTube
"ገባሬ መንክራት መርቆሬዎስ "ZwT||ዜማ ወጥበብ ዘማኅበረ ቅዱሳን (Official Video)

#MKZwT#ዜማወጥበብዘማኅበረቅዱሳን#Mahiberekidusan
Subscribe: https://www.youtube.com/channel/UC2U27bED0bj7ONXPNmBEKmA
Telegram: https://www.tg-me.com/+5e0PniMWKnsyMWFh
ገባሬ መንክራት ሰማዕት ሰማዕት መርቆሬዎስ
ተራድአነ በገሃድ…

👍16❤8