Telegram Web Link
በማኅበረ ቅዱሳን የሰሜን ምዕራብ ማእከላት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ተቋማዊ ምክክር እየተካሄደ ይገኛል።

ተቋማዊ ምክክሩ በማኅበረ ቅዱሳን ሰሜን ምዕራብ ማእከላት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሥር የሚገኙ ማእከላት በዋናው ማእከል የሀገር ውስጥ ማእከላት ማስተባበሪያ አዘጋጅነት እየተካሄደ መሆኑ ተገልጿል።

የባሕር ዳር ማእከል፣ የግልገል በለስ፣ ፍኖተ ሰላም፣ እንጅባራና ደብረ ታቦርን ያካተተው ይህ መርሐ ግብር ከማኅበረ ቅዱሳን አዲሱ መዋቅራዊ ለውጥ አኳያ የማእከላትን የአፈጻጸም አቅም ለማሳደግ ታሳቢ ያደረገ መሆኑ ተጠቅሷል።

የማእከላቱን ሥራ አስፈጻሚዎች የሥልጠና መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት ኅዳር 28 ቀን 2017 ዓ.ም የጀመረ ሲሆን በማኅበረ ቅዱሳን ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመ/ር ዋስይሁን በላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ተላልፏል።

መ/ር ዋስይሁን በላይ በመልእክታቸው ከዓለም ተለዋዋጭ ባሕርይ እና ቤተ ክርስቲያን ካለባት ጫና አንጻር ማኅበሩ ዘመኑን የሚዋጅ መዋቅራዊ ለውጥ ማድረግ እንደነበረበትና በዚህም በማኅበረ ቅዱሳን አባላትና መዋቅር፣ በግቢ ጉባኤያት፣ በሰ/ት/ቤቶች እና በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚጠበቁ የለውጥ ታሳቢዎችን ጠቁመዋል።

መርሐ ግብሩ በልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ለሁለት ቀናት የሚቆይ ይሆናል።
👍3221🙏1
✍️✍️ሐመር መጽሔት በታኅሣሥ ወር እትሟ!

✍️".. ጉዳዩን ከአንዱ ወደ ሌላው መግፋት ሳይሆን ሁሉም የየድርሻውን ወስዶ፣ ሁሉም የሚጠበቅበትን ተግባር በአግባቡ አከናውኖ ሁሉም ሰላምን ተከትሏት..) #ሐመር #መጽሔት ታኀሣሥ በ፳፻፲፯ ዓ.ም መልእክት ዐምድ  ✍️      
                      ༺ ༻ 
  #የኅትመት ዘመን ፦# # ታኀሣሥ ፳፻፲፯  ዓ.ም
#አዘጋጅ ፦በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ  ቤተ ክርስቲያን ማኀበረ ቅዱሳን በልማት ተቋማት አስተዳደር  በመጽሔት ዝግጅት ክፍል የሚዘጋጅ ትምህርታዊ መጽሔት
•  ገጽ ብዛት፦፳፰
   ዋጋ ፦፵ ብር 
👍111
•  ሐመር  መጽሔት  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት  ሥርዓትና ትወፊት ጠብቃ በልማት ተቋማት አስተዳደር  በመጽሔት ዝግጅት ክፍል  በየወሩ የምትወጣ መንፈሳዊ መጽሔት ናት፡፡
•  ሐመር መጽሔት ፴፩ ኛ ዓመት  ቁጥር ፲፪  # ታኀሣሥ ፳፻፲፯  ዓ.ም መልእክት ዘማኅበረ ቅዱሳን " #ይእዜኒ ለሰላም ንትልዋ መድኃኒነ ተወልደ ነዋ” (ቅዱስ.ያሬድ)  "በሚል ዐቢይ መልእክት   ያለንበት ዘመን ግን “የዓባይን ልጅ ውኃ ጠማው” እንደሚባለው የሰላም አምላክ ደሙን ያፈሰሰላት፣ሥጋውን የቆረሰላት፣ የሕይወት ዋጋ የከፈለላት፣ሁል ጊዜ “ጸልዩ በእንተ ሰላም፤ ስለ ሰላም ጸልዩ”እያለች የምትጽልይ፣ስለ ሀገር፣ ስለ ሠራዊት፣ ስለ ሕዝብ የምትለምን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በውስጥም በውጭም ሰላም አጥታ እየታወከች ፤ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከአባቶች በኩል “መምህር ወመገሥጽ ዘኢያደሉ ለገጽ” በመሆን ለማንም ሳይወግኑ ማንንም  ሳይፈሩና ሳያፍሩ የሚመከረውን መምከር የሚገሠጸውን መገሠጽ የውስጥ መለያየትንም በመፍታት በአንድነት  ለሰላም እንዲቆሙላት  እንደምትጠበቅ ፣በዓለ ልደት የተጣሉት የታረቁበት፣ የተለያዩት አንድ የሆኑበት፣ ሰላም የተሰበከበት   እንደሆነ ሐመር በመልእክት ዐምድ ታስነብባለች።
   
  .#ዐውደ ስብከት  ሥር” # “ናሁ ድንግል ትፀንስ ወትወልድ ወልደ”  በሚል ርእስ  ይህ ትንቢት በብሉይ ኪዳን ስለ እመቤታችንና ስለክርስቶስ በአንድነት
ከተነገሩ ደረቅ (ቀጥተኛ) ትንቢቶች መካከል አንዱ መሆኑን ፣የእመቤታችን ሕይወት ሰለእኛ ምን እንደሚያስተምረን  ታስነብባለች።
  #በትምህርተ ሃይማኖት ዐምድ ሥር “# “ቃል ሥጋ ሆነ” (ዮሐ.፩፥፲፬)  ክፍል አንድ " በሚል ዐቢይ ርእስ በመልአከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ ሺፈራው  ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ "በመጀመሪያ ቃል ነበረ "በማለት  ወንጌሉን የመጻፉን ምክንያት በጥልቀት  ቀርቦበታል።ቃል ሥጋ የሆነው እንደሆነ በዝርዝር ተዳሶበታል፤ድንግል ማርያም እንዴት ኢየሱስን ክርስቶስን እንደወለደችው የሊቃውንት መጽሐፍ በማጣቀስ ትምህርት ይሰጣል ።

    #ዐቢይ ጉዳይ  ዐምድ  ሥር  ደግሞ “# የቅዳሴ አገልግሎትና ምሥጢሩ" በሚል ርእስ  በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ የተሠራ  ጥናታዊ ጽሑፍ (Investigative Reporting) ላይ ትኩረት ያደረገ  ስለ ቅዳሴ በዝርዝር ያሳያል
   •  #ክርስትና በማኀበራዊ ዐምድ ሥር  ደግሞ  "#ኦርቶዶክሳዊ የልጆች አስተዳደግ "በሚል ርእስ  አንድ ነገር መፍትሔ መነሻው በተከሰተው ችግር ላይ ያለን ግንዛቤ እና ከዚያ ችግር ለመውጣት የሚነሣ የልቡና ቁጭት  እንደሆነ ያሳያል ።የልጆች ማንነት ፤የልጆች እና የወላጅ /አሳዳጊ/ ግንኙነት ምን መምሰል እንዳለበት ፤ ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብን በመገንባት አርአያ መሆን እንደሚገባ  በአጠቃላይ ልጅን በመንፈሳዊ ዕውቀት፣በሥነ ምግባርና በኢትዮጵያዊ ባሕል ቀርጾ ማሳደግን የመሰለ ወላጅ ለልጁ የሚመኘው ተግባር ያለ አይመስለኝም።"በማለት ትኩረት ለልጆች መስጠት እንደሚገባ በአጽንዖት ታሰተምራለች።
   • #በእናስተዋውቃችሁ ዐምድ ሥር “#የስደተኞች መጠጊያ ጁባ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን " በሚል ርእስ  የአመሠራረት  ሁኔታውን ፣ ያሉን መልካም  ዕድሎችና ተሞክሮዎች ታስቃኛለች ።
   •  #በነገዋ  ቤተ ክርስቲያን #ዐምድ  ሥር “ መንፈሳውያን ማኅበራት ለነገዋ ቤተ ክርስቲያን" በመ/ር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል ክፍል አንድ  በሚል ርእስ ስለ መንፈሳዊ ማኅበራት ምንነትና አመሠራረት ጥናት ተኮር ጹሑፍ ይዛለች ።ስፍር ቁጥር የሌላቸው፣ ህልውናቸው በምንና እንዴት እንደሆነ ለመረዳት አሰቸጋሪ የሆነ፣ የሚሠሩት ሥራም ሆነ የሚፈጽሙት
ተልእኮ ተለይቶ የማይታወቅ በርካታ ማኅበራት ያሳያል ።
  #በኪነ ጥበብ ዐምድ "# በፍላጻ የተወጋ ልብ  ክፍል _፪ "በሚል  ታስነብባለች ።ዲያቆን ጴጥሮስ በሚል የአንድ ቅን ወንድማችን ታሪክ ታስነብባለች። የሚገርም እጅግ የሚመስጥ ታሪክ ይዛለች።በተለይም የሐረማያ ግቢ ጉባኤ ተማሪዎች እና ደቡብ ኢትዮጵያ ያላችሁ ከገጸ ባሕርይው ተነስታችሁ ዲ/ን ጴጥሮስ ማን እንደሆነ ትረዳለች ።በእርግጠኝነት በዕንባ ይኽን ኪነ ጥበብ ታነቡታላችሁ ።(ገጽ_፳፫)
•  #የጥያቄዎቻችሁ መልስ ዐምድ “በዐልና አከባበሩ- # ክፍል ፩ " በሚል ርእስ #“በዓልንና የበዓል  አከባበርን” በተመለከተ የሚነሡ ጥያቄዎችን መሠረት በማድረግ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ  ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የትምህርትና ማሠልጠኛ መምሪያ ዋና ኃላፊ የሆኑትን መጋቤ ሐዲስ ኀይለ እግዚእ አሰፋ ጋር የተደረገ  ጥያቄና መልስ ይዛለች  ።
  
   ሐመር መጽሔት #፴፩ ኛ ዓመት   ቁጥር ፲፪ በማሰራጨት ፡በማንበብና በማስነበብ የድርሻችን እንወጣ !

magazine @eotcmk.org  #ሐመር #መጽሔት  ዝግጅት  ክፍል
11👍7
በዓታ ለማርያም
ታኅሣሥ በባተ በሦስተኛው ቀን የሚታሰበውና የሚከበረው በዓል ‹‹በዓታ ለማርያም›› በመባል ይታወቃል፡፡ ከእናቷ ከቅድስት ሐና እና ከአባቷ ቅዱስ ኢያቄም በስዕለት የተወለደችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ዕለት የከበረ እንደመሆኑ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ታከብረዋለች፡፡
በዓት ቃሉ የግእዝ ሲሆን ቤት ማለት ነው፡፡ ደጋጎቹ የእግዚአብሔር ሰዎች ቅዱስ ኢያቄምና ቅድስት ሐና ልጅ አጥተው ለብዙ ዘመናት ከመኖራቸው የተነሣ በኀዘን ፈጣሪያቸውን ሲማጸኑ ቃል በመግባት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሦስት ዓመት ሲሆናት በእግዚአብሔር ቤት ትኖርና ታገለገል ዘንድ በቤተ ክርስቲያን እንድትኖር ስለሰጧት በዓሉም ስያሜውን በዚያ መሠረት አግቷል፡፡
በዚያን ጊዜም በቤተ ክርስቲያን ያገለግል የነበረው ካህኑ ዘካርያስ ስዕለታቸውን አስተውሶ ቅድስት ድንግል ማርያምን ሊቀበላት ሲቀርብ እንደ ፀሐይ የምታበራ ሕፃን ሆና አገኛት፤ በመገረምና በመጨነቅም ከወላጆቿ ጋር ምን ሊመግቧት እንደሚችሉ በመጨነቅ ላይ ሳሉ ሕዝቡ በተሰበሰበበት መካከል መልአኩ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ይዞ ከሰማይ ወረደ፡፡ ካህኑ ዘካርያስም ለእርሱ የመጣ መና መስሎት ሲቀረብ ወደ ላይ ተመለሰበት፡፡ በዚያ የተሰበሰቡት ሰዎችም እያንዳንዳቸው ቢሞክሩ በተመሳሳይ መልኩ ተመልሶ ወደ ላይ ራቀባቸው፡፡ ‹‹ምን አልባት ለእንግዶች የመጣ ሀብት እንደሆነ›› ብለው ቅድስት ሐና እና ቅዱስ ኢያቄም እንዲቀርቡ ቢደረግም ለእነርሱም ራቀባቸው፡፡ ካህኑ ዘካርያስም ቅድስት ሐናን ‹‹እግዚአብሔር የሚያደርገውን የሚያውቅ የለምና ልጅቷን ትተሸ ወደዚህ ነይ›› አላት፤ ሆኖም ግን ቅድስት ማርያም እናቷ ትታት ስትሄድ መከተል ጀመረች፤ ምርርም ብላ አለቀሰች፡፡
👍2615
በዚህም ጊዜ መልአኩ ፋኑኤል ወደ እርሷ ቀርቦ አንድ ክንፉን አንጥፎ አንድ ክንፉን ጋርዶ መገባት፤ ከዚያም በክብር ዐረገ፤ ሊቀ ካህናቱና ሕዝቡም ‹‹የምግቧ ነገር ከተያዘልን በቤት እግዚአብሔር ትኑር›› ብለው ወደ ቤተ መቅደስ አስገቧት፡፡
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ሰማያዊ ኅብስትና መጠጥ እየተመገበች  በቤተ መቅደስ  ለ፲፪ ዓመታትም ኖራለች፡፡
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትና ተራዳኢነት አይለየን፤ በረከቷ ይደርብን፤አሜን! 
ምንጭ፡- ነገረ ማርያም
👍3815🙏9
በቤንሻንጉል ክልል አሶሳ አህጉረ ስብከት ኦርቶዶክሳዊ ቤተ ሰብን በማጠናከርና በማብቃት ዙሪያ የአሠልጣኞች ሥልጠና ተሰጠ፡፡

የማኅበረ ቅዱሳን አሶሳ ማእከል ከአሶሳ ሀገረ ስብከት ጋር በመተባበር ከታኅሣሥ አራት እስከ ስድስት ፳፻፲፯ ዓ.ም ድረስ በቤንሻንጉል ክልል አሶሳ ሀገረ ስብከት መንበረ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ሰበካ ጉባኤ አዳራሽ በተሰጠው ሥልጠና በሀገረ ስብከት ሥር ባሉ ከሁሉም አጥቢያ ቤተ ክርስቲያንና ወረዳ ቤተ ክህነት ለተውጣጡ 47 ካህናት፣ ዲያቆናት፣ መምህራን፣ የሥነ ልቦናና ባለሙያዎች እና አገልጋዮች የአሠልጣኞች ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን ከ ፳፻፲፮ ዓ.ም ጀምሮ በአምስት ዓመት ሥልታዊ ዕቅዱ ውስጥ በማካተት መንፈሳዊ ምክክር በመስጠት ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብን የሚያጠናክሩ ካህናትና ባለ ሙያዎችን በማሠልጠን በልዩ ልዩ ማእከላት ሥልጠና ሲሠጥ የቆየ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በመሆኑም በዚህ ሥልጠና ክብረ ክህነትና አበ ነፍስ፣ መንፈሳዊ ምክክር፣ ኦርቶዶክሳዊ ጋብቻና የልጆች አስተዳደግ፣ ሱስ በኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ እይታ እንዲሁም ምጣኔ ሀብትና ማኅበራዊ እድገት ጉዳዮች ተዳሰውበታል፡፡

በዕለቱም መልአከ ፀሐይ ቆሞስ አባ ዘካሪያስ በጸጋው የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ በመገኘት ሥልጠናውን በጸሎት በመክፈት የሥራ መመሪያ የሰጡ ሲሆን ሠልጣኞች ባገኙት ሥልጠና በመታገዝ ዘመኑን የዋጀ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
👍122
ሠልጣኞች በሥልጠናው ጥሩ ግንዛቤና ልምድ እንዳገኙበት ገልጸው ወደ መጡበት አካባቢ ሲመለሱ ምእመናን ያለባቸውን ዘርፈ ብዙ ቀውስ እንዲቋቋሙ የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት እንደሚያስችላቸው ተናግረዋል፡፡

የአሶሳ ማእከልም ለሥልጠናው መሳካት ቦታ በማመቻቸትና አሠልጣኝ መምህራንን ከመመደብ ጀምሮ ለተባበሩት የአሶሳ ሀገረ ስብከትንና ዋናው ማእከልን እያመሰገነ ቀጣይ በሌሎች አካባቢዎች ለሚሰጠው ሥልጠናም በገንዘብና ቁሳቁስ ጭምር በመደገፍ የቤተ ክርስቲያን አካላት በቅንጅት አብረው እንዲያገለግሉ ጥሪውን አቅርቧል፡፡
🙏9👍2
በደብረ ብርሃን ከተማ “ወደ ቀድሞ ነገር እንመለስ” በሚል መሪ ቃል የአባላት የቃል ኪዳን ማደሻ መርሐ ግብር ተካሄደ።

በደብረ ብርሃን በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ አዳራሽ “ወደ ቀድሞው ነገር እንመለስ” በሚል መሪ ቃል የአባላት የቃል ኪዳን ማደሻ መርሐ ግብር በማእከሉ አዘጋጅነት ተካሄዷል።

መርሐ ግብሩ በዋናነት ከቀደሙ አባቶች የአገልግሎት ልምድና መንፈሳዊ ሕይወት ለመማር እንዲሁም የማኅበሩ አባላት ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል የገቡትን ቃል እንዲያጸኑ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

በተካሄደው ጉባኤ ከአንድ ሺህ በላይ አባላት የተሳተፉ ሲሆን በመጋቤ ሀብታት ታደሰ አሰፋ “ወደ ቀደመ ነገር እንመለስ” በሚል መሪ ቃል የማኅበረ ቅዱሳንን የአገልግሎት ሂደት የሚያሳይ ጽሑፍ ቀርቧል።

በተጨማሪም ከማእከሉ ምሥረታ ጀምሮ በማእከሉ አገልግሎት ላይ የነበሩ አባላት የአገልግሎት ልምዳቸውን አካፍለዋል።

የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑት መጋቤ ሐዲስ ነቅዐ ጥበብ አባቡ በበኩላቸው “ልጄ ሆይ አደራህን ጠብቅ!” በሚል መሪ ቃል በአገልግሎት መትጋት እንደሚገባ መልእክታቸውን ያስተላለፉ ሲሆን ቤተ ክርስቲያን ካለችበት ከውስጣዊም ሆነ ከውጫዊ ፈተና እንድትላቀቅ የአባላት መጠናከር አስፈላጊ በመሆኑ “አባላትን ማስተማር ያስፈልጋል” በማለት ጥሪ አቅርበዋል።
🙏7👍51
“የገና ስጦታ ለየኔታ”

እግዚአብሔር በሥጋ ተገልጦ ራሱን ለዓለም በሰጠበት በዓለ ልደት (ገና)


✝️ ሰብአ ሰገል ወርቅ ዕጣን ከርቤን አቀረቡለት (ማቴ 2፡11)
✝️ መላእክት እና እረኞች ምስጋናን አቅርበዋል (ሉቃ 2፡14-20)
✝️ እንስሳት በበረት ትንፋሻቸውን ገብረዋል (ሉቃ 2፡7)

እርስዎስ ነቢያት የጌታን መወለድ እያሰቡ በጾሙት ጾመ ነቢያት ለቤተ ክርስቲያን ራሳቸውን ለሰጡ ገዳማትና አብነት ት/ቤቶች ምን ለመስጠት አስበዋል?
👍10
የማኅበረ ቅዱሳን አሜሪካ ማእከል ግቢ ጉባኤያት የማኅበራዊ ሚድያ ገጾችን ይጎብኙ፣ ይከተሉ፣ ለሌሎችም ያጋሩ!
Our campus Ministry Social media serves the youth in the Ethiopian Orthodox Tewahido faith through spreading the word of God (amplifying the teachings of the Church) and sharing spiritual guidance, building a spiritual community, empowering and inspiring them (through testimonials, devotionals, and stories), and promoting events (inform students about campus gatherings, conferences, retreats, and online events).
Please follow and subscribe to our Facebook, YouTube, Instagram, TikTok, and X (Twitter) accounts, and share our posts with your friends.
1. TikTok:
https://www.tiktok.com/@usa_campus_ministry

2. Instagram:
https://www.instagram.com/usa_campus_ministry/

3. YouTube:
https://www.youtube.com/@campus_ministry_usa

4. Facebook:
https://www.facebook.com/campusministryusa

5. X(Twitter):
https://twitter.com/gibigubae_usa
👍7
2025/07/13 14:23:01
Back to Top
HTML Embed Code: