Telegram Web Link
“አሁን ባለን የአስተዳደር ክፍተቶችና በውስጣችን ያሉ ግልጽነት የጎደላቸው አሠራሮች ለአገልግሎታችን እንቅፋት እየሆኑብን ነው”ሲሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ገለጹ፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት 43ኛው ዓለም አቀፍ መደበኛ ጉባኤ መክፈቻ ላይ ለተገኙ ተሳታፊዎች መልእክት አስተላልፈዋል።

ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው አሁን ባለን የአስተዳደር ክፍተቶችና በውስጣችን ያሉ ግልጽነት የጎደላቸው አሠራሮች ለአገልግሎታችን እንቅፋት እየሆኑብን ነው። በዚህ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያናችን የሚታየውን  ችግር ለመፍታት በጥናት ላይ የተመሠረተ መፍትሔ ማምጣት ይገባል ሲሉ አፅዕኖት ሰጥተዋል፡፡

ቅዱስነታቸው ጨምረው እንደገለጹት ቅዱስ ሲኖዶስ ተግባራዊ እንዲሆን የወሰነውን የቤተ ክርስቲያን የ10 ዓመት መሪ ዕቅድ ውጤታማ ለማድረግ ሁላችንም በትብብር መሥራት ይገባናል ብለዋል።

በዛሬው ዕለት የተጀመረው 43ኛው አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ ከሀገር ውስጥ እና ውጪ ከሚገኙ አህጉረ ስብከቶች፣ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አድባራት እና ገዳማት እንዲሁም ከተለያዩ መንፈሳዊ ማኅበራት የተወከሉ ተሳታፊዎች በተገኙበት እየተከናወነ ይገኛል።
በ43ኛው አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ዋና ሥራዎች ሪፖርት ቀረበ

በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት እየተከናወነ በሚገኘው አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ የማኅበረ ቅዱሳንን ሥራዎች ሪፖርት የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የመንፈሳዊ ዘርፍ ዋና ምክትል ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ንቡረ እድ ኤልያስ አብርሃ አቅርበዋል።

በቀረበው ሪፖርትም ማኅበሩ 310 የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን በማስተማር ክህነትን እንዲቀበሉ ማድረጉ፣ ለዐይነ ስውራን የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ማስተማሪያ ዐምስት የኮርስ መጻሕፍት የድምጽ ትረካ አዘጋጅቶ ማሰራጨቱ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም በሀገር ቤት ዐርባ ሺሕ ፣በውጭ ሀገር ደግሞ አንድ መቶ ዐስራ ሁለት አዳዲስ አማንያን የሥላሴ ልጅነት እንዲያገኙ ማድረጉ ተጠቅሷል፡፡

በከንባታ ጠንባሮ ሀላባ፣ በደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች፣ በወላይታ ሶዶ፣ በካፋ፣ በጋሞና አካባቢው ዞኖች፣ በቤንች ሸኮ፣ ሸካና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች እንዲሆም በዳውሮ አህጉረ ስብከት በካህናት እጥረት ተዘግተው የነበሩ 34 አብያተ ክርስቲያናት ካህናት ተቀጥሮላቸው አገልግሎት እንዲጀምሩ ተደርጓል ተብሏል፡፡

በደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች፣በወላይታ ሶዶ፣ በቤንች ሸኮ፣ ሸካና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች አህጉረ ስብከት ለአዳዲስ አማንያን መገልገያ የሚውሉ ዐምስት ሕንጻ አብያተ ክርስቲያናትና ዐራት መካነ ስብከት አዳራሾችን አሠርቶ ለአገልግሎት ማዋሉ በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡

በ169 የአብነት ትምህርት ቤቶች ለሚገኙ 224 መምህራንና 2018 ደቀ መዛሙርት የገንዘብ ድጋፍ የተደረገ ሲሆን 73 ተማሪዎችን የአባ ጊዮርጊስ ነጻ የትምህርት እድል ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ተብሏል፡፡
በትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት በተለያዩ  ቋንቋዎች አገልግሎት እንዲሰጡ ለ1226 አገልጋዮች፣ ለ3650 የደረጃ 1 እና 2 ተተኪ አመራሮች ሥልጠና መስጠቱና ለ213 አገልጋዮች ወርሐዊ ደሞዝ በመክፈል ድጋፍና ክትትል ማድረጉ በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡

ስብከተ ወንጌልን ተደራሽ ለማድረግ በአማርኛና ኦሮምኛ ቋንቋዎች በርቀት ትምህርት 111 በሞጁልና 68 በኢለርኒንግ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን መሠረተ እምነት ማስተማር መቻሉና ለዐይነ ሥውራን ወገኖች የውዳሴ ማርምና ሰኔ ጎለጎታ የጸሎት መጽሐፍ በብሬል ተዘጋጅቶ ተሰራጭቷል፡፡

ማኅበሩ በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት የደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ አንድነት ገዳም፣ በቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት የበደሌ ሁለገብ የገቢ ማስገኛ ፕሮጀክት ግንባታ ማከናወኑ ተገልጿል፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን በተጨማሪም በምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት የምስካበ ቅዱሳን ቅዱስ ዑራኤል ወሳሙኤል ዘዋልድባ ገዳም አብነት ትምህርት ቤት ግንባታ አከናውኗል፡፡

በሦስት አህጉረ ስብከት በድርቅ ለተጎዱና በሃይማኖት ተኮር ጥቃት ከስልጤ ዞን ቅበት ከተማ ተሰደው ለነበሩ ኦርቶዶክሳውያን የምግብና የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉም በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡

በተለያዩ 7 ቋንቋዎች የተዘጋጁ 261 መዙሙራትንና በ10 ቋንቋዎች 328 መዝሙራትን የያዘ ጥራዝ ለምእመናን ተደራሽ ማድረጉ በሪፖርቱ የተገለጸ ሲሆን በማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን የተለያዩ ይዘቶችን በመጨመር የተመልካቾችን ፍላጎት ለማሳደግ የሚየስችሉ ሥራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡
43ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የመጀመሪያ ቀን የከሰዓት በኋላ ውሎ ተጀመሯል።

በአሁኑ ሰዓት የተለያዩ አህጉረ ስብከቶች የ2016 ዓ.ም የአገልግሎት አፈጻጸም ሪፖርቶችን በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።
በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ተሸለሙ።

ማኅበረ ቅዱሳን ከሰ/ት/ቤቶች ጋር በመተባበር በተለያዩ ቦታዎች ሲያስተምራቸው የነበሩ እና በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተናን ለተፈተኑ ተማሪዎች ጥቅምት 3 ቀን 2016 ዓ.ም የሽኝት መርሐ ግብር ተከናውኗል።

በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አዳራሽ በተከናወነው የሽኝት መርሐ ግብር ላይ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት እና የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን የወሰዱ ተማሪዎች ተገኝተዋል።

ብፁዕነታቸው በተሰጠው ሀገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላመጡት ተማሪ ዮናስ ንጉሠ እና ተማሪ ሄለን በርሀ የተዘጋጀውን የላፕቶፕ ኮምፒዩተር ሥጦታ ያበረከቱ ሲሆን በመርሐ ግብሩ ላይ ለተገኙት ተማሪዎችም አባታዊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ተማሪ ዮናስ ንጉሠ ከ700 ጥያቄዎች 675 በመመለስ ከወንድ ተፈታኞች መካከል አንደኛ እንዲሁም ተማሪ ሄለን በርሀ ከ700 ጥያቄዎች 662 በመመለስ ከሴት ተፈታኞች መካከል አንደኛ መውጣታቸው ያታወቃል።
የማኅበረ ቅዱሳን አዳማ ማእከል ከሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጋር በመተባበር የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ወደ ዩኒቨርስቲ ለሚገቡ ተማሪዎች የሽኝት መርሐ ግብር አከናወነ፡፡

በመርሐ ግብሩ ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ሲገቡ ስለሚጠበቅባቸው አካላዊ እና መንፈሳዊ ዝግጅት ሰፋ ያለ ምክር የተሰጣቸው ሲሆን 500 እና ከዚያ በላይ ውጤት ላስመዘገቡ ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎችም ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

በመጨረሻም በከፍተኛ ት/ት ተቋም በሚኖራቸው ቆይታ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንዳለባቸው እና ጎን ለጎን በግቢ ጉባኤ የሚሰጠውን መንፈሳዊ ትምህርት በመከታተል በሁለት መልኩ የተሳለ ሰይፍ መሆን እንዲችሉ የአዳራ መልዕክት ተሰጥቷቸዋል፡፡
2024/11/06 03:01:54
Back to Top
HTML Embed Code: