ሐመር መጽሔት ፴፩ ኛ ዓመት ቁጥር -፲ ጥቅምት ፳፻፲ ፯ ዓ.ም በመልዕክት ዐምድ "#የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ነባራዊ ሁኔታ የሚረዳ፣ ከሥጋትም የሚታደግ ትውልድ እናፍራ "በሚለል ዐቢይ ርእስ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በየዘመናቱ የደረሰባትን ፈተና ሁሉ እያለፈች ዛሬ ላይ የደረሰችው ከእግዚአብሔር ጥበቃ ጋር የዘመኑን ፍልስፍና ተረድተውና ዘመኑን ዋጅተው ሃይማኖትን ከሥነ ምግባር ጋር አዋሕደው ይዘው ጠላት ዲያብሎስ የሚዋጉ ጠንካራ አባቶች ስለነበሯት ነው፡፡ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተልእኮ መሳካትና ለህልውናዋ የሚተጋ፣ ሁለንተናዊ ዕድገትን የተላበሰ ትውልድ ለማፍራት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሁሉ መሥራትም ጊዜ የማይሰጠው ተግባር መሆኑን መረዳት ይገባል። በማኅበረ ቅዱሳን ፲፮ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተስተዋለውን የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያ ኃላፊዎች ተሳትፎ በማጠንከር እና የየማዕከላቱ ተወካዮች በተለያየ ችግር ውስጥ ሁነው ሳላ ስለ አገልግሎት ለመመካከር ብዙ ነገሮችን ተቋቁመው መምጣታቸው፣ለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በመናበብ ማገልገል ከማኅበረ ቅዱሳን የሚጠበቅ ተግባር ነው ። ማኅበረ ቅዱሳን እንደ ቤተ ክርስቲያን ልጅነቱ ከአባቶቹ መመሪያ እየተቀበለ ለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት መጠናከርና ተደራሽነት እያደረገ ያለውን ጥረት ከአሁኑ በተጠናከረና ዘመኑን በዋጀ መልኩ ማከናወን ይጠበቅበታል።"በማለት ታስነብባለች።
.#ዐውደ ስብከት ሥር” #ምሉዕ ኦርቶዶክሳዊት ” በሚል ርእስ ምሉዕ ኦርቶዶክሳዊነት ማለት ሰፊ ጽንሰ ሐሳብ ያለው ከመሆኑ የተነሣ በአጭር ዐረፍተ ነገር ለመግለጽ አስቸጋሪ እንደሆነ ያሳያል ። ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን አንዲት፣ ጋራ ተራራ፣ ድንበር ወሰን፣ ቋንቋ፣ ዘርና ቀለም የማይገድባት ዓለም ዐቀፋዊት፣ ሐዋርያዊት፣ ጥንታዊት፣ ሰላማዊት፣ እና ርትዕት ናት፡፡ “ኦርቶዶክሳዊ ተዋሕዶ” ነት ከዓለም ፈጣሪና መጋቢ ከልዑል እግዚአብሔር እና ካከበራቸው ቅዱሳን ጋር አሁን በረድኤት ኋላም በመንግሥተ ሰማያት በክብር መንግሥቱ አብሮ መኖር ማለት መሆኑን ያሳያል።
#በትምህርተ ሃይማኖት ዐምድ ሥር “# "ዘመነ ጽጌ " በሚል ዐቢይ ርእስ በመልአከ ሰላም ቀሲስ #ደጀኔ ሺፈራው #የደንቨር ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ይህን ወቅት(ዘመነ ጽጌን) ቤተ ክርስቲያን:-እመቤታችንን በምድር አንድም በአበባ፥ተወዳጅ ልጇን ኢየሱስ ክርስቶስንም በአበባ አንድም በፍሬ እየመሰለች ዘመነ ስደታቸውን በየዓመቱ በማኅሌት፥ በቅዳሴ በመዝሙርና በትምህርት በልዩ ኹኔታ ታስበዋለች።የሚፈጸመውም አገልግሎት ለጊዜው ዘመነ ጽጌ ምነው ባላለቀ የሚያሰኝ፥ ለፍጻሜው ደግሞ የከርሞው መቼ በደረሰ የሚያስብል አገልግሎት እንዳላት ያስተምራሉ ።
#ዐቢይ ጉዳይ ዐምድ ሥር ደግሞ “#ለመማከር ተሰበሰቡ "በሚል ዐቢይ ርእስ ብፁዓን አባቶችም ከሰበካ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ የሚቀርበው ሪፖርት ምን ያህል በአደራ የተቀበሏቸውን የክርስቶስን ግልገሎች ጠቦቶችንና፣ በጎችን የማገልገል ጉዳይ ሆኖ ቀርቧል የሚለውን ነጥብ ይፈትሻሉ፡፡ ከዚህ ያፈነገጠ ሪፖርት፣ ዕቅድ፣ ውሳኔና አቋም ሁሉ ብፁዓን አባቶች የሚመሯትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን እንደማይመለከት በግልጽ ያሳያሉ፡፡ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ሪፖርትም ለዚህ በአደራ የተሰጣቸውን ከባድ ኃላፊነት መወጣት የሚያስችል ምላሽ የሚሰጥ መሆን ይገባዋል፡፡ በዚህ ጉባኤ ከሚገኙት የሪፖርት ምላሽ ተነስተው አባቶቻችን የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤን አጀንዳ ይቀርጻሉ፡፡
አገልጋዮች ለአገልግሎታቸው ምን ዓይነት ማነቆዎች አጋጠሟቸው? የትኞቹስ ቀኖናዊ መፍትሔ የሚፈልጉ ናቸው? የትኞቹ በጸሎት የሚፈቱ ናቸው? የትኞቹ በምክርና ተግሣጽ የሚፈቱ ናቸው? …ወዘተ ብሎ በዓይነትና በመልክ አቅጣጫ ይሰጣል፡፡
• #ክርስትና በማኀበራዊ ዐምድ ሥር ደግሞ "#ጭንቀት ክፍል_ ፩ "በሚል ርእስ መጋቤ ሐዲስ #አእምሮ ደምሴ #የኳታር ጸርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የብሉያትና የሐዲሳት ትርጓሜ መ/ር ደግሞ ሥጋዊ ጭንቀት፦ከልብ የሚመነጭ በሕሊና የሚወጣና የሚወርድ ፣በረቂቁ አእምሯችን የሚመላለስ ፣ በሐሳብ መሥመር የሚንቀሳቀስ፣ በሕሊና ቦይ የሚፈስ፣ ለጉዳት የሚያጋልጥ ነው። ጭንቀት፦ ክብደቱና ቅለቱ ይለያያል እንጂ በሁሉም ሰው ላይ የሚታይና የሚገለጽ ነው።ጭነቀትት ፦ መጠኑ ከሚገባው በላይ እየጨመረ ከሄደ ሰውነትን የሚያዛባ፣ አእምሮን የሚያቀውስ፣ ሕሊናን የሚያዘነጋ፣ ራስን እስከመጣል የሚያደርስ፣ ከቤተሰብ፣ ከትዳር፣ ከጓደኛ፣ ከጎረቤት፣ ከማኀበራዊ ኑሮ የሚለይ ፣ በብቸኝነት መኖርን እንዲመርጡ የሚያደርግ፣ ከፍ ሲልም ተስፋ እስከ መቁረጥ የሚያደርስ አደገኛ እንደሆነ በጹሑፋቸው ይጠቁማሉ። ስማችን፣ አለባበሳችን፣ ኦርቶዶክሳዊ ሆኖ ነገር ግን ከኦርቶዶክሳዊነት ውጭ በሆነ እሳቤ ብዙ ጉድለቶች እንዳሉብን ያሳያሉ ።
• #በእናስተዋውቃችሁ ዐምድ ሥር “#የምሥራቅ አፍሪካ ፈርጥ #ናይሮቢ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን " በሚል ርእስ በኬንያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለመመሥረቱ ምክንያቶችና የአመሠራረት ሁኔታውን ፣የናይሮቢ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የስብከተ ወንጌል እንቅስቃሴ ፣ በአብነት ትምህርት ፣ የደብሯን የሰበካ ጉባኤ የልማት እንቅስቃሴ ፤በሰንበት ትምህርት ቤት እና በየዘመናቱ የነበሩ ተግዳሮቶች ፣ወቅታዊጉዳዩች፣ የናይሮቢ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያንን ልዩ የሚያደርጉት ጉዳዮችን ፣-በደብሩ የሚገኙት የሰበካ ጉባኤ አባላት ፣የሰንበት ት/ቤት አባላትና በማኀበረ ቅዱሳን የኬንያ ማእከል አባላት በፍጹም አንድነት ያለ ምንም ልዩነት አገልግሎት የሚሰጥበት ቤተ ክርስቲያን ነው፡፣ የናይሮቢ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን መልካም አጋጣሚዎችን ታስቃኛለች ።
• #በነገዋ ቤተ ክርስቲያን #ዐምድ ሥር "ለነገዋ ቤተ ክርስቲያን የስብከተ ወንጌል ሚና _ክፍል ፪ " በሚል ስብከተ ወንጌላችን ተደራሽ እንዲሆን ምን መደረግ እንዳለበት የተወሰኑ ነጥቦችን ያነሳል ።ተልዕኮ ተኮር የስብከት ዘዴን መከተል ፤የቋንቋ እንቅፋትን ማስወገድ፣ በቦታ ያልተገደደበ አገልግሎት መስጠት ይገባናል ።
#በኪነ ጥበብ ዐምድ "# ትንሣኤ_፪ "በሚል ታስነብባለች ።
• # በጥያቄዎቻችሁ መልስ ዐምዳችን “ወርኃ ጽጌን ክፍል -፩ ” በተመለከተ የሚነሡ ጥያቄዎችን መሠረት አድርገን ምላሽ ይሰጡን ዘንድ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተ ክርስቲያን ሰባኬ ወንጌል የሆኑትን መጋቤ ሐዲስ #ተስፋ ሚካኤል ታከለ ጋር የተደረገውን ምልልስ ይዛለች ።
ሐመር መጽሔት #፴፩ ኛ ዓመት ቁጥር ፲ በማሰራጨት ፡በማንበብና በማስነበብ የድርሻችን እንወጣ !
magazine @eotcmk.org #ሐመር #መጽሔት ዝግጅት ክፍል

👍33❤10
የማኀበረ ቅዱሳን ላልይበላ ወረዳ ማእከል በላልይበላ ገዳም ለሚገኙ ከስምንት ጉባኤ ቤቶች ለተውጣጡ 108 የአብነት ተማሪዎች ነጻ የሕክምና አገልግሎት ሰጠ፡፡
የወረዳ ማእከሉ ሙያ፤ ገዳማትና አብነት ትምህርት ቤቶች አገልግሎት ክፍል ኀላፊ አቶ ብርሃን ሀብታሙ እንደገለጹት ክፍሉ በላልይበላ ገዳም የሚገኙ የአብነት ተማሪዎች ያሉበትን ሁኔታ ለመረዳት የዳሰሳ ጥናት በማድረግና የጤና ባለሙያዎች ቡድን በማደራጀት ነጻ የሕክምና አገልግሎት እንዲያገኙ አድርገናል ብለዋል፡፡
በተላላፊ በሽታ ምክንያት ሕክምና የሚያስፈልጋቸው አብነት ተማሪዎችን ለማስተናገድ የመድኀኒት እጥረት በመኖሩ ማስተናገድ አልተቻለም ሲሉም ኀላፊው አክለዋል፡፡
ነጻ የሕክምና አገልግሎቱን ለመስጠት የላልይበላ ሆስፒታል ድጋፍ ከፍተኛ ነበር ያሉት አቶ ብርሃን ሌሎች በጎ አድራጊዎችም ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የጉባኤ ቤቶቹ መምህራን በበኩላቸው ማኀበረ ቅዱሳን ለአብነት ተማሪዎቹ ነጻ ሕክምና መስጠቱ ለቤተ ክርስቲያን አለኝታ መሆኑን የሚያመላክት ነው ብለዋል፡፡
ነጻ ሕክምናው ከሀያ ሰባት ሺህ ስምንት መቶ ብር በላይ ወጭ እንደተደረገበት ለማወቅ ተችሏል

👍35❤10
የጌዴኦ፣ ኮሬና ቡርጅ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገሪማ የማኅበረ ቅዱሳን ሚዲያ አገልግሎት ተቋምን ጎበኙ፡፡
ብፁዕነታቸው በጉብኝቱ መደሰታቸውን ገልጸው ማኅበሩ ከሌሎች አገልግሎቶች በተጨማሪ ለሚዲያ ትኩርት በመስጠት እየሠራ ያለውን ሥራ አድንቀዋል፡፡
ብፁዕነታቸው አክለውም የማኅበሩ ሚዲያ አሁን ላይ ያለው የቋንቋ ተደራሽነት የሚበረታታ መሆኑን አንስተው በቀጣይም በሌሎች ቋንቋዎች አገልግሎቱን እንዲያሰፋ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን ከሚዲያ አገልግሎቱ ባሻገር ከጌዴኦ፣ ኮሬና ቡርጅ ሀገረ ስብከት ጋር በመነጋገር ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን እየሰጠ ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም ተገፋፍተን የምናመጣው ለውጥ የለም ያሉት ብፁዕ አቡነ ገሪማ በመተባበርና በመደማመጥ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ማሳደግ ይኖርብናል ብለዋል፡፡

👍33❤10🙏6
የቅድመ ግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ሽኝት እየተከናወነ ይገኛል
ማኅበረ ቅዱሳን ከሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጋር በመተባበር በየዓመቱ የሚያዘጋጀው የቅድመ ግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ሽኝት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አዳራሽ በመከናወን ላይ ይገኛል።
በመርሐ ግብሩ ላይ በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን የተፈተኑ ለ700 በላይ ተማሪዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
ማኅበረ ቅዱሳን ከሰ/ት/ቤቶች ጋር በመተባበር ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎችን በቅድመ ግቢ ጉባኤ አማካኝነት በዓለማዊ እና መንፈሳዊ ሕይወት የሚጠነክሩበትን መንገድ በማመቻቸት ላይ እንደሚገኝ ያታወቃል።

❤26👍9🕊1
በ17 ሀገረ ስብከቶች በተገነቡ አዳሪ አብነት ትምህርት ቤቶች ዙሪያ ከአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች ጋራ ውይይት ተካሄደ።
ማኅበረ ቅዱሳን በተለያዩ ሀገረ ስብከቶች በተገበራቸው አዳሪ አብነት ትምህርት ቤቶች ኘሮጀክቶች ዙሪያ በነበሩ ስኬቶች እና ተግዳሮቶች ላይ ከአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች ጋራ ነው ውይይት የተደረገው።
ውይይቱ በምእራብ ፣በምሥራቅ እና በደቡብ በሚገኙ አህጉረ ስብከት በተገነቡ አዳሪ አብነት ትምህርት ቤቶች ማለትም በተመረጡ በ17 አዳሪ አብነት ትምህርት ቤቶች ላይ ሲሆን በርካታ ተተኪ አገልጋዮችን በማፍራት ስኬታማ ጉባኤ ቤቶች መኖራቸውን እንዲሁም በተለያየ ምክንያት አገልግሎት ያልጀመሩ ጉባኤ ቤቶች እንዳሉም በውይይቱ ላይ ተገልጿል።
ውይይቱም የተገነቡት አዳሪ አብነት ትምህርት ቤቶች በሙሉ አቅማቸው አገልግሎት በመስጠት ውጤታማ እንዲሆኑ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን መለየትና ችግሮቹን ለመቅረፍ ከማን ምን ይጠበቃል የሚሉት ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።
አገልግሎት ያልጀመሩት አብነት ትምህርት ቤቶች የበጀት እጥረት ዋነኛ ምክንያት መሆኖ የተገለጸ ሲሆን ሥራ እንዴት መጀመር እንዳለባቸው እና አገልግሎት ጀምረው ስኬታማ የሆኑ ጉባኤ ቤቶች ደግሞ እንዴት ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው የመፍትሔ አቅጣጫ ተጠቁሟል።
ስኬታማ አብነት ትምህርት ቤቶች ልምዳቸውን በውይይቱ መርሐ ግብር ላይ የገለጹ ሲሆን ስኬታማ ስራዎቻቸው ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ሁሉም ምእመናን ድጋፍ እንዳደርጉ አሳስበዋል።
የውይይቱ ዋና ዓላማ በአዳሪ አብነት ትምህርት ቤቶች ትግበራ ላይ የጋራ ግንዛቤ መፍጠር ፣ ከሀገረ ስብከቶች ጋር የአገልግሎት ቅንጅት ማጠናከር እና ጉባኤ ቤቶች የታለመላቸውን አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ እንደሆነ ተገልጿል።

👍10❤2
የተገነቡት አዳሪ አብነት ትምህርት ቤቶች የአገልጋይ እጥረት ባለባቸው አካባቢዎች በመሆናቸው ዘመኑን የዋጀ አገልጋዮችን በማፍራትና የተዘጉ አብያተ ቤተ ክርስቲያናትን በማስከፈት የተተገበሩት አብነት ትምህርት ቤቶች ሚና የጎላ ነው ተብሏል።
፵፫ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ተጀመረ።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በየዓመቱ ከሚደረጉት ጉባኤያት መካከል አንዱ የሆነው እና ከሁሉም አህጉረ ስብከቶች የተወጣጡ ተወካዮች የሚሳተፉበት የአጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዘንድሮ ለ፵፫ኛ ጊዜ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ይከናወናል።
ጉባኤው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በተገኙበት በዛሬው ዕለት መካሄድ ጀምሯል።
አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤው ከጥቅምት ፬እስከ፲ ቀን ፳፻ ፲፯ ዓ.ም ድረስ የሚከናወን ይሆናል።

👍5