Telegram Web Link
የኢ/ኦ/ተ/ቤ መንበር ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ከየአህጉረ ስበከቱ ለተወጣጡ የሕዝብ ግንኙነት ዋና ክፍል ሓላፊዎች ለሦስት ቀናት የሚቆየው ስልጠና የውይይትና ምክክር መድረክ እያካሄደ ይገኛል።

+++++++++++++++++++++++++++

<< ተደራሽነት ያለው የሕዝብ ግንኙነት ለኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን>> በሚል መሪቃል ከግንቦት 15 እስከ ግንቦት 17 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቆየው ይህ ስልጠና እየተሰጠ የሚገኘው በአዲስ አበባ ጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል ነው።

የስልጠና እና የውይይት መድረኩ የተዘጋጀበት ዓላማ የሕዝብ ግንኙነት ሥራን ለቤተክርስቲያን በሚያግዝ መልኩ እንዲሰሩ ለማነሰሳት ነው።
በተጨማሪም በሥራቸው ወቅት የሚያገጥማቸውን ክፍተት የሚሞሉበትን ግንዛቤ ለመፍጠር መሆኑም ተጠቁሞዋል።

በመድረኩ ላይ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የባህር ዳር እና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ አገልግሎት መምሪያ የበላይ ሓላፊ ፣ ብጹዕ አቡነ ዲዮስቆርዮስ፣ የደቡባዊና ደቡባዊ ምሥራቅ ትግራይ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የጠቅላይ ቤተክህነት የየመምሪያ ሓላፊዎች፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ከየአህጉረ ስበከቱ የተወጣጡ የሕዝብ ግንኙነት ዋና ክፍል ሓላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ተገኝተዋል።
በሥልጣናው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በመንበረ ፓትርያርክ ጽ/ቤት የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ሓላፊ ሊቀ ሥዩማን እስክንድር ገ/ክርስቶስ በዚህ የውይይት መድረክ ለድክመቶቻችን የተለያዪ ምክንያቶችን ከመደርደር ወጥተን ያለንን አቅም አሟጠን ቤተ ክርስቲያንን በጋራ ማገልገል በምንችልበት ጉዳይ ላይ ተቋማዊ ትስስር ለመፍጠር አስበናል ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ሓላፊው እክለውም ሥልጠናው ወሳኝ እና ታማኝ የመረጃ ሥርዓት መዘርጋት በምንችልበት ሁኔታ ዙሪያ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን ብሎም ከሕግ ሥርዓት አንጻር ግንዛቤ የምትጨብጡበት እና ለምትሰጡት አግልግሎት ተጨማሪ ግብዓት እድታገኙ የሚያግዝ በመሆኑ ትኩረት ልትሰጡት ይገባል ሲሉም አመላክተዋል።

ብፁዕ አቡነ አብርሃም በመድረኩ ባስተላለፉት መመሪያ አገልጋዬች ሕዝብን ከሕዝብ ምእመናን ከቤተ ክርስቲያን በማቀራረብ ችግር ፈቺ የሆኑ ሃሳቦችን በማመንጨት ዘምኑን የዋጅ አገልጋዬች መሆን ይጠበቅባችሁዋል ብለዋል።

ብፁዕነታቸው አክለውም ቅድስት ቤተክርስቲያን እያጋጠማት ካለው ፈተና እንድታልፍ የሕዝብ ግንኙነት መዋቅራዊ ሠንሰለቱን ጠብቆ የመረጃ ፍሰቱ በማጠናከር ቤተ ክርስቲያን በመጠበቅ ረገድ ሰፊ ስራ መስራት እንደሚጠበቅበት ተናግረዋል።

ብፁዕ አቡነ ማርቆስ በበኩላቸው የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ አገልጋዬችን በሥልጠና እንዲታገዙ እና የተሻለ አግልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ የሚያከናውነው ተግባር ሊበረታታ እንደሚገባ ገልጸዋል።

በመርሐ ግበሩ ላይ የተሳተፉት ከተለያዩ አሕጉረ ስብከት የተወጣጡ የሕዝብ ግንኙነት ዋና ክፍል ሓላፊዎች ሥልጠናው አስተማሪ በመሆኑ ቀጣይነተ ሊኖረው ይጋበል ብለዋል።
ሰንበት ትምህርት ቤቶች ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ያላቸው አስተዋፅኦ

ክፍል አንድ


በሐዋርያት ትምህርት ላይ የተመሠረተችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዋናው ተልእኮዋ የምሥራች ቃልን ለዓለም ማዳረስ ነው። ይህን የምሥራቹን ቃል ለማዳረስም በተለያየ ዘመን ብዙ ፈተናዎች ገጥሟታል፡፡ ፈተናዋን በጸሎት እና በዘመኑ በነበሩ አበው ምእመናን ጥብዓት ተሻግራ አሁን ካለንበት ዘመን ደርሳለች። ከአባቶቻችን የተረከብናትን ቤተ ክርስቲያን ከእነ ሙሉ ክብሯ ለመጠበቅ ትምህርት ላይ መሥራት ለነገ የማይባል ሥራ መሆኑ የሚያጠራጥር ባይሆንም ነገር ግን አሁን ባለንበት ዘመን ያለውን የትምህርት አሰጣጥ ሁኔታ ስንገመግመው ትኩረት የሚያሻው ጉዳይ ነው።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከሐዋርያት የተቀበለችውን ትምህርት ለማስተማር ከምትጠቀምባቸው መንገዶች አንዱ ልጆቿን በሰንበት ትምህርት ቤት መዋቅር ውስጥ እንዲታቀፉ በማድረግ አስፈላጊውን ትምህርት እንዲያገኙ በማስቻል ነው። በመሆኑም የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች መጠንከርም ሆነ መድከም ቤተ ክርስቲያናችን ላይ ያለው ተጽዕኖ ቀላል ይሆናል ተብሎ አይታሰብም። በዚህ አጭር ጽሑፍ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ያላቸውን አስተዋፅኦ ለማየት እንሞክራለን።

ሰንበት ትምህርት ቤት ማለት ምን ማለት ነው?

ሰንበት ትምህርት ቤት ማለት በቤተ ክርስቲያን መዋቅር ሥር ታቅፈው በበዓላት፣ በዕረፍት ቀናት (በሰንበታት) በመገኘት ትምህርተ ሃይማኖት የሚማሩ ተማሪዎች ስብስብ ማለት ነው።

የአገልግሎት ትርጕም

የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ሲባል ገና ተጋድሎዋን ያልፈጸመችው እና የሚደርስባትን መከራ በጸጋ በመቀበል ክርስቶስን በመከራ ለመምሰል ሥርዓተ አምልኮዋን ዘወትር የምታከናውን ሲሆን ነው፡፡ “እግዚአብሔር የሰማዕትነትን ሥራ ይሰጠን ዘንድ እንማልዳለን” ብላ በዐጸደ ነፍስ ካሉ ቅዱሳን እንዲሁም ዘወትር ያለማቋረጥ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ ከሚያመሰግኑ ቅዱሳን መላእክት ጋር አንድ የሚያደርጋት አገልግሎት ተብሎ ሊገለጽ ይችላል።
ይቆየን!
በአዲስ አበባ የዘነበ ወርቅ ደብረ ከዋክብት አቡነ አረጋዊ እና ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ፈለገ ሰላም ሰንበት ት/ቤት ማኅበረ ቅዱሳን ለሚያከናውነው ሐዋርያዊ አገልግሎት ድጋፍ አደረገ::

ድጋፉም በደቡብ ቤንች ወረዳ ለምትገኘው እና ለአዳዲስ አማንያን መገልገያነት ለታነጸችው ለካቡል ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት ነው::

ሰንበት ትምህር ቤቱ 62ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን ምክንያት በማድረግ መለገሱ የተገለጸ ሲሆን ለ24 ሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች ልብሰ ስብሐት እና 5 መጽሐፍ ቅዱስ አስረክቧል::

የሰንበት ተ/ቤት ተማሪዎች በሃይማኖታቸው እንዲበረቱ፣ ቁጥራቸው እንዲጨምር የማደረግ ጥቅም የሚኖረው ሲሆን ሌሎች ሰንበት ት/ቤቶችም በእንደዚህ አይነት አገልግሎት መሳተፍ እንዳለባቸው የትምህርት እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ ም/ኃላፊ የሆኑት ዲ/ን ኃይሌ አርአያ በርክክቡ ወቅት ገልጸዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ የማኅበረ ቅዱሳን ተወካዮች፣ በአካባቢው በቤንችኛ እና ሸክኛ ቋንቋዎች የሚያገለግሉት መጋቤ ኃይማኖት ቀሲስ ደመላሽ አማኑኤል ጨምሮ የፈለገ ሰላም ሰንበት ት/ቤት አገልጋዮች ተገኝተዋል::

ሰንበት ት/ቤቱ በዚሁ ዓመት በቤንች ወረዳዎች ለሐዋርያዊ ተልእኮ የሚሠማሩ 25 ሰባክያነ ወንጌልን ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር በመሆን አሰልጥኖ መላኩ ይታወሳል፡፡
በማኅበረ ቅዱሳን አስተባባሪነት አገር አቀፍ የደም ልገሳ መርሐ ግብር እየተከናወነ ይገኛል።

ማኅበረ ቅዱሳን ከኢትዮጵያ የደም ባንክ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የደም ልገሳ መርሐ ገብር በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ እየተከናወነ ይገኛል።

አዲስ አበባ በሚገኘው የማኅበሩ ዋና ማእከል ጽ/ቤት በተከናወነው የደም ልገሳ መርሐ ግብር ላይ በርካታ ምእመናን ተገኝተው በመለገስ ላይ ይገኛሉ።
‹‹ነገን ዛሬ እንሥራ››

ክፍል ሰባት


ተወዳጆች! እንዴት ሰነበታችሁ? እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሳችሁ!

በክፍል ስድስት “ክብረ ምንኩስና ትናንት በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የነበረውን ክብርና ሞገስ ያስገኘውን የቅድስና ፍሬና ያሳረፈውን አሻራ” አንስተን ለመዳሰስ ሞክረናል፡፡

በዚህ በክፍል ሰባት ደግሞ ምንኩስና ዛሬ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እያጋጠመው ያለውን ተግዳሮት ለመዳሰስ እንሞክራለን፡፡ ቀደም ብለን እንደ ተመለከትነው ምንኩስና ከምድራዊው ይልቅ ሰማያዊውን፣ ከሰው ይልቅ የመላእክትን ግብር መምረጥ፣ ፍጹም ሆኖ ፍጹም የሆነችውን መንግሥት ለመውረስ ሁሉን ትቶ መመነን፣ ከሰው ከዓለም መለየት፣ በገዳም በአጽንዖ በአት፣ በግብረ ምንኩስና መወሰን መሆኑን ተረድተናል፡፡ ይሁን እንጅ በዘመናችን ምንኩስና በዘርፈ ብዙ ተግዳሮት ውስጥ ይገኛል፤ የተወሰኑ ችግሮችን ለማሳየት ያህል፡-

፩. የምንኩስና ሥርዓትን ተከትሎ አለመመንኮስ፡-

በገዳም ሕግ አንድ መናኝ ሁሉንም ትቶ ወደ ገዳም ሲገባና “እመነኩሳለሁ” ሲል በገዳሙ ያለውን ሥርዓተ መነኮሳት መማርና መጠበቅ፣ የተቀመጠውን የአበው ሥርዓት ማክበር፣ በጉልበቱ እንጨት ሰብሮ፣ ውኃ ቀድቶ፣ ከብት ነድቶ፣ ቡኮ አብኩቶ፣ ዳቤ ጋግሮ በእርድና መነኮሳትን መርዳት ይገባዋል፡፡ ‹‹መነኮሳትን ሳይረዱ “እመነኩሳለሁ” ማለት ሳይበጡ መታገም ነው፡። ምክንያቱም ከሁሉም እርድና ይበልጣልና ከእርድና በኋላ ቢመነኩስ ይጠቅማል›› ይላል መጽሐፈ ምዕዳን፡፡ (ገጽ ፻፶) ይሁን እንጅ በአሁኑ ሰዓት የአመክሮ ጊዜ የሌላቸው ገዳማትን አበው መነኮሳትን በጉልበታቸው በእርድና ያላገለገሉ፣ የኋላ ታሪካቸውና የወደፊት ትልማቸው ያልተገመገመ፣ አንዳዶቹም የትና በማን እንደመነኮሱ የማይታወቁ፣ ተጠየቅ የሌለበት የምንኩስና ሥርዓት ቤተ ክርስቲያንን ፈትኗታል፡፡
2024/09/29 18:22:54
Back to Top
HTML Embed Code: