Telegram Web Link
የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ያዘጋጀው የግእዝ እና የአማርኛ የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍ ቅዱስ የድምጽ ቅጂ ተመረቀ።

የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጋር በመተባበር ለዓይነ ስውራን፣ መጻፍ እና ማንበብ ለማይችሉ ምእመናን እንዲሁም ለአብነት ተማሪዎች የሚያገለግል የአማርኛ እና የግእዝ የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍ ቅዱስ በዘመናዊ መሣሪያ በድምጽ ቅጂ ተዘጋጅቶ በዛሬው ዕለት በቦሌ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ካቴድራል ተመርቋል።

በምርቃት ሥነ ሥርዓቱ ላይ ብፁእ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባሕር ዳር እና ሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁእ አቡነ ማርቆስ የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ አገልግሎት መምሪያ የበላይ ኃላፊ ፣ ብፁእ አቡነ ቀሌምንጦስ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ  የበላይ ኃላፊ እንዲሁም የጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያ ኃላፊዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ዋና ጸሐፊ የሆኑት ሊቀ ኅሩያን ይልማ ጌታሁን በመርሐ ግብሩ ላይ እንደገለጹት የመጽሐፍ ቅዱስ የድምጽ ቅጂ መሣሪያው አገልግሎት ላይ እንዲውል ከ11 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ሲሆን ከ26 በላይ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት እና ባለሙያዎች በሥራው ላይ ተሳትፈዋል ብለዋል።

ዋና ጸሐፊው ጨምረው እንደገለጹት የድምጽ መሣሪያውን አዘጋጅቶ ለማጠናቀቅ ሁለት ዓመታትን የወሰደ ሲሆን አጠቃላይ ወጪው "Faith comes by hearing" በተሰኘ ዓለም አቀፍ ተቋም እንደተሸፈነ ተናግረዋል።
ብፁእ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባሕርዳር እና ሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመርሐ ግብሩ ላይ እንደተናገሩት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ዛሬ የተመረቀው የድምጽ መሣሪያ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ገልጸው በሥራው ላይ ተሳታፊ ለነበሩት አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ብፁእነታቸው ጨምረው እንደተናገሩት የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ቤተክርስቲያን በቅርበት እየተከታተለች እንደምትደግፍ ገልጸው በተለይ ማኅበሩ  የጀመረውን መጽሐፍ ቅዱስን በኦሮምኛ ቋንቋ የመተርጎም ሂደት በባለቤትነት እንደምትከታተለው ገልጸዋል።

በመጨረሻም በድምጽ ቅጂ ሥራው ላይ ለተሳተፉ አካላት የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።
የሳርዶ ቅድስት ማርያም አዳሪ አብነት ትምህርት ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ 9 ደቀ መዛሙርትን አስመረቀ።

በኢሉ ባቡር ሀገረ ስብከት በኖኖ ሰሌ ወረዳ ቤተ ክህነት በ2013 ዓ.ም የተመረቀው ዘመናዊ አዳሪ አብነት ትምህርት ቤት የመጀመሪያ ዙር በንባብና ቅዳሴ 9 የሚሆኑ ደቀ መዛሙረትን ግንቦት 11 ቀን 2016 ዓ.ም በደማቅ ሥነ ሥርዓት አስመርቋል።

በምረቃው መርሐ ግብር ላይ ተመራቂ ደቀመዛሙርቱ ወርብ ያቀረቡ ሲሆን በሁለት ዓመት የትምህርት ቆይታቸው ከአብነት ትምህርቱ ጎን ለጎን የትምህርተ ሃይማኖት የኮርስ ሥልጠና ሲሰጣቸው እንደነበር ተገልጿል ።

በማኀበረ ቅዱሳን የገዳማትና አብነት ት/ቤቶች ዋና ክፍል ም/ኃላፊ ዲ/ን ደረጀ ጋረደው ፣ የኢሉ ባቡር ሀገረ ስብከት ተወካይ ቀሲስ ጌቱ ሠይድ፣ የኖኖ ሰሌ ወረዳ ሊቀ ካህናት ቄስ ደረጀ ፈጠነ ፣ እንዲሁም የአካባቢው ህዝበ ክርስቲያን በመረሐ ግብሩ ላይ ተገኝተዋል።

ዲ/ን ደረጀ ጋረደው እንደተናገሩት ሀገረ ስብከቱ የአገልጋይ ካህናት እጥረት ያለበት መሆኑና በርካታ አብያተ ክርስቲያናት ቀዳሽ አጥተው ተዘግተው ያሉበት በመሆኑ የእነዚህ ደቀመዛሙርት መመረቅ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው ያሉ ሲሆን አብነት ትምህርት ቤቱ ለሌሎች ክልሎች አጎራባች ስለሆነ የተለያየ ቋንቋ ተናጋሪዎችን ማፍራት እንደሚችል ጠቁመዋል።

የተማሪዎችን ሙሉ የቀለብ ወጭ የሸፈነው ማኅበረ ቅዱሳን ሲሆን ለዚህም ከ 700 ሽህ ብር በላይ ማድረጉም ተገልጿል።
ቅዱስነታቸው የደቡብ አፍሪካ ሐዋርያዊ አገልግሎታቸውን አጠናቀው አዲስ አበባ ገቡ።
**

ብፁ
ዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ
ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዮንቨርሲቲ ፕሬዝዳንት፣የደቡብ ኦሞና
አሪ ዞኖች ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ የዳውሮ-ኮንታ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የጠቅላይ ቤተክህነት የመምሪያ ኃላፊዎች በደቡብ አፍሪካ ሲያካሒዱት የቆዩትን ሐዋርያዊ አገልግሎት አጠናቀው ዛሬ ከቀትር በኋላ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ቅዱስነታቸውና ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር ወደ ደቡብ አፍሪካ የተጓዙት የልዑካን ቡድን አባላት ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የባህርዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ክቡር መልአከ ሕይወት ቆሞስ አባ ኃይለ ገብርኤል ነጋሽ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፣የጠቅላይ ቤተክህነት መምሪያ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገው
ላቸዋል።

በመቀጠልም በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም የእንኳን ደህና መጡ አቀባበል መርሐ ግብር የሚካሔድ ሲሆን በዚሁ መርሐ ግብር ላይም ቅዱስ ፓትርያርኩ ትምህርተ ወንጌል፣ቃለ ምዕዳንና ቃለ ቡራኬ ሰጥተው የአቀባበል መርሐ ግብሩ የሚጠናቀቅ ይሆናል።

ምንጭ: የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
2024/09/29 12:26:56
Back to Top
HTML Embed Code: