Telegram Web Link
በማኅበረ ቅዱሳን ካናዳ ማእከል የቫንኮቨር ንዑስ ማእከል በገዳመ ቅዱሳን (All saints orthodox Monastery) ሐዊረ ሕይወት አካሄደ፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰ/ማ/መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ካናዳ ማእከል የቫንኮቨር ንዑስ ማእከል  በገዳመ ቅዱሳን (All saints orthodox Monastery) ምእመናን በማስተባበር የሐዊረ ሕይወት/የሕይወት ጉዞ/  መርሐ ግብር አካሄደ ፡፡ በዕለቱ ከ180 ምዕመናን በላይ በጉዞው የተሳተፉ ሲሆን በመርሐ ግብሩ ዝማሬ፣ ትምህርተ ወንጌል፣ምክረ አበው፣ እንዲሁም ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ተዳስሰውበታል። እንዲሁም የጉዞው ተሳታፊዎች በመንፈሳዊ ሕይወት ዙሪያ ውይይት አከናውነዋል።

ጉዞውን፣ መርሐ ግብራቱ እና ዝግጅቱን በተመለከተ ምእመናን ሐሳብ የሰጡ ሲሆን የሕይወት ጉዞው  በመንፈሳዊነት ለማደግና በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ለመትጋት ስንቅ እንደሚሆናቸው ተናግረዋል፤መርሐ ግብሩን ለአዘጋጁት አስተባባሪዎችም ምስጋና አቅርበው ይኸ ዓይነት ጉዞ ከሌሎች ንዑሳን ማእከላትም ጋር በመሆን ቢቀጥል የሚሉና ሌሎችም ገንቢ አስተያየት ተሰጥቶ የጉባኤው ፍጻሜ ሆኗል፡፡ 
መምህር ሆይ!

መሆንህን አውቆ እውነተኛ
ገሰገሰ ወዳንተ በሌሊት ሳይተኛ
ቅዱስ ቃልህንም ሲሰማ ፈወሰው
የታወረ ኅሊናውን አብርቶ አቀናው
ጥያቄውን እንዲያቀርብ አበረታታኸው
ስለ ዳግም ውልደትም አስተማርከው

‹‹እውነት እውነት እልሀለሁ›› ስትለው
ዳግመኛ ያልተወለደ ሰው…
የእግዚአብሔርን መንግሥት ለማየት አይቻለው››
ምሥጢሩ ባይገባው

‹‹ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፡፡
ከመንፈስ የተወለደ መንፈስ ነው››
ብለህ አስረዳኸው፡፡

‹‹ይህ ሊሆን እንዴት ይቻላል?›› ብሎ ኒቆዲሞስ ቢጠይቅህ
‹‹አንተ የእስራኤል መምህራቸው ነህ፤
ነገር ግን እንዴት ይህን አታውቅም?....
ከሰማይ ከወረደው የሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም፤…
የሰው ልጅ እንዲሁ ይሰቀል ዘንድ አለው፡፡››
ብለህ አስተማርከው፡፡

አሁንስ ገባው፤ እውነቱንም አውቆ ጌታውን
ዘመናት አልፈው ሲደርስ ጠብቆ ተራውን
ቢኖርም ተብሎ መምህር፣ በሌላ ሕግ ተደብቆ
ያለ አንተ ሲኖር ከአይሁድ ተደባልቆ

አሁን ግን ሰጠኸው የእውነት ሕይወት
በመስቀል ላይ ገልጸህ ፍጹም አፍቅሮት
ክብርንም አገኘ በአንተ ስቅለት
ገንዞ እንዲቀብርህ በዓርብ ዕለት!
የተተኪ መምህራን ሥልጠና ሲከታተሉ የነበሩ ሠልጣኞች ተመረቁ

ከጌዲኦ፣ ቡርጂ እና አማሮ ዞን ሀገረ ስብከት ተውጣጥተው በቤቴል ደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ለተከታታይ 15 ቀናት ሥልጠና ሲከታተሉ የነበሩ 35 ሠልጣኞች ዛሬ ሚያዝያ 13 ቀን 2016 ዓ.ም ተመርቀዋል።

ማኅበረ ቅዱሳን ከደብሩ ሰበካ ጉባኤ እና ሰ/ት/ቤት ጋር በመተባበር በተዘጋጀው በዚህ ሥልጠና ላይ የትምህርተ ሃይማኖት እና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ርእሰ ጉዳዮች የተዳሠሡ ሲሆን ሠልጣኞች ወደ አካባቢዎቻቸው ሲመለሱ  ማገልገል የሚችሉባቸውን እውቀቶች እንዲጨብጡ ተደርጓል።

በምርቃት ሥነ ሥርዓቱ ላይ መልእክት ያስተላለፉት የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ የሆኑት ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ሥዩም እንደገለጹት ማኅበረ ቅዱሳን በ2016 ዓ.ም 6 ወራት ውስጥ ከ 28,000 በላይ ኢ አማንያንን አስጠምቆ ወደ ቤተ ክርስቲያን ልጅነት የመለሰ ሲሆን ዛሬ የተመረቁት ሠልጣኞች ስብከተ ወንጌልን በማስፋፋት ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸው ተናግረዋል።

የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ሃይማኖት መምህር ኢሳይያስ ቸርነት እንደገለጹት የደብሩ ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር በመተባበር የስብከተ ወንጌል አገልግሎትን ለማስፋፋት በርካታ ሥራዎችን እየሠራ ሲሆን ለዚህ አንዱ ማሳያ የዛሬ ተመራቂዎች ናቸው ብለዋል።

አስተዳዳሪው ጨምረው እንደገለጹት የደብሩ ሰ/ት/ቤትን በማስተባበር በቀጣይ ሌሎች 36 ሠልጣኞችን ከተለያዩ አካባቢዎች በማምጣት ሥልጠናዎችን ለመስጠት በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
#ኒቆዲሞስ
(የዐቢይ ጾም ሰባተኛ ሳምንት)

ከፈሪሳውያን ወገን የአይሁድ አለቃ በነበረው በኒቆዲሞስ የተሰየመ ሰንበት ነው፡፡ የአይሁድ አለቆች አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን “ምልክት አሳየን” እያሉ ይፈታተኑት ነበር፡፡ ስለሞቱና ትንሣኤው በምሳሌ ቢነግራቸው አልገባቸውም፡፡ ሲያስተምር ብዙዎች ያምኑ ነበር፡፡ ለአይሁድ አለቆች ግን ጭንቅ ነበር፤ የታመሙ ሲፈወሱ ሕጋችን ተሻረ ይሉ ነበር፡፡ በዚህ ሁሉ ተአምራትና ትምህርት የአይሁድ አለቆች ክርስቶስን ለመክሰስ በሚፈልጉበት ወቅት ከአይሁድ አለቆች አንዱ ኒቆዲሞስ በቀን እንዳያደርገው አይሁድን ፈርቶ አንድም ጊዜ አላደርሰው ብሎ እንደ አይሁድ አለቆች ኢየሱስን መቃወሙን ትቶ በሌሊት ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ሄደ፡፡ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በነፍስ የታመሙትን በቃሉ በሥጋ የታመሙትን በተአምራቱ ሲፈውስ፤ ኒቆዲሞስ ሰምቶና ተመልክቶ “መምህር ነኝ” ብሎ በመምህርነቱ ሳይኮራ አለቅነቱን መመኪያ ሳያደርግ፡፡ በልቦናው የተሳለውን እውነትን የመፈለግ ስሜት አንግቦ ጌታው መምህሩ ዘንድ በሌሊት ገሠገሠ ዮሐ.3÷1ደርሶም ምስክርነቱን እንዲህ ሲል መስጠት ጀመረ “መምህር ልታስተምር ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደመጣህ እናውቃለን፡፡ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርገውን ተአምራት ሊያደርግ የሚችል የለምና” ዮሐ.9÷24፣ የሐዋ.ሥራ 10÷38 በማለት መመስከር ሲጀምር ጎዶሎን የሚሞላ፡፡ አላዋቂነት በአዋቂነት የሚለውጥ፡፡ ከምድራዊ እውቀት ወደ ሰማያዊ ምስጢር የሚያሸጋግር አምላክ፡፡ “ዳግመኛ ያልተወለደ የእግዚአብሔርን መንግሥት ለማየት አይችልም” ዮሐ.3÷6 ,1ጴጥ.1÷23 በማለት የአይሁድ መምህር ለሆነው ኒቆዲሞስ ቢያስተምረው ስለዳግመኛ መወለድ ከመጽሐፍ ቢያገኘውም ምስጢሩ አልተገለጠለትምና “ሰው ከሸመገለ በኋላ ዳግመኛ መወለድ እንደምን ይቻላል? ዳግመኛ ይወለድ ዘንድ ወደ እናቱ ማኅፀን ተመልሶ መግባት ይችላልን?” በማለት ጥያቄ አቅርቧል፡፡

“እውነት እውነት እልሃለሁ ዳግመኛ ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ ያልተወለደ ወደ እግዝአበሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም፡፡ ኤፌ.5÷26 ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፡፡ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነውና፡፡ በማለት አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቢያስረዳው ምስጢሩ ከአቅሙ በላይ የሆነበት ኒቆዲሞስ እንደምን ይቻላል? በማለት ጠይቋል፡፡ አበ ብዙኀን አብርሃም ከአምላኩ ሞገስን አግኝቶ፤ የሰዶምና ገሞራ ጥፋት እንዳይደርስ እያማለደ ከእግዚአብሔር ጋር ሲነጋገር እንደ ነበረ፤ ኒቆዲሞስም አላዋቂነቱን አምኖ ያልገባውን ምስጢር አምላኩን የመጠየቅ ዕድል በማግኘቱ ሲጠይቅ፣ ኢየሱስ ክርስቶስም “አንተ የእስራኤል መምህራቸው ነህ ግን ይህን ነገር አታውቅምን? በምድር ያለውን ስንነግራቸው ካላመናችሁ በሰማይ ያለውን ብንነግራችሁ እንደምን ታምናላችሁ? ከሰማይ ከወረደው ከሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም፡፡ ሙሴ ምድረ በዳ እባቡን እንደ ሰቀለ የሰው ልጅ እንዲሁ ይሰቀላል፡፡

ያመኑበት ሁሉ ለዘለዓለም ሕያው ሆኖ እንዲኖር እንጂ እንዲጠፉ አይደለም…..” ዮሐ.3÷14፡፡ እያለ ለድኅነተ ዓለም እንደ መጣ ሰው በመብል፣ አምላኩን ከድቶ ልጅነቱን ትቶ ከእግዚአብሔር ቢለይም የሰው ልጅ ያጣውን ልጅነት ለመመለስ ስመ ግብርና ሀብተ ወልድን ለመስጠት መምጣቱን አስረዳው። “ሐወጽከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብየ፡፡ አመከርከኒ ወኢተረከ በዓመፃ በላዕሌየ፡፡ ከመ ኢይንብብ አፉየ ግብረ እጓለ እመሕያው፡፡ ልቤን ፈተንከው በሌሊትም ጎበኘኸኝ ፈተንከኝም ምንም አላገኘህብኝም፡፡ የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው” መዝ.16÷3 እንዳለ ቅዱስ ዳዊት ምስጢረ ሥጋዌን የድኅነት ምስጢር ገልጾለታል፡፡

በሌሊት ከአምላኩ ተምሮ ምስጢሩ የተገለጸለት ኒቆዲሞስ ፍርሃት ርቆለት ቀድሞ በአደባባይ ሄዶ መማርን የፈራ ምስጢሩ ሲገለጽለት አይሁድ በሰቀሉት ዕለት ሳይፈራ ከአርማትያሱ ዮሴፍ ጋር ቅዱስ ሥጋውን ገንዞ ለመቅበር በቃ “ወአልቦ ፍርሃት ውስተ ተፋቅሮትነ፡፡ ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል ማቴ.27÷58፣ 1ዮሐ.4÷18 እንዲል፡፡ ያመነ የተጠመቀ ይድናል፡፡ ያላመነ ያልተጠመቀ ይፈረድበታል ማር.16÷16፡፡ ባለው አማናዊ ቃል ኪዳን መሠረት አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ አምላክነቱ አምነን ለመንግሥቱ ዜጋ እንድንሆን ለኒቆዲሞስ ምስጢሩን ጥበቡን የገለጸ አምላክ ለኛም ይግለጽልን፡፡

#የዕለቱ_የሰንበት_መዝሙር_እና_ግጻዌ

#መዝሙር
ሖረ ኀቤሁ ዘስሙ ኒቆዲሞስ ወይቤሎ ለኢየሱስ ረቢ ሊቅ ንሕነ ነአምን ብከ ከመ እምኃበ አብ መጻእከ ከመ ትኩን መምህረ፤ ዕጓለ አንበሳ ሰከብከ ወኖምከ አንሥአኒ በትንሣኤከ፡፡ (ስሙ ኒቆዲሞስ የተባለው ሰው ወደ ጌታችን ኢየሱስ ሄደ፤ መምህር ሆይ ልታስተምር ከእግዚአብሔር አብ ዘንድ እንደመጣህ እናምንብሃለን አለው። የአንበሳ ደቦል ተኛህ፣ አንቀላፋህም፤ በትንሣኤህ አንሣኝ።)

#መልዕክታት
ሮሜ 7÷1-12
"ወንድሞች ሆይ፥ ሕግን ለሚያውቁ እናገራለሁና ሰው ባለበት ዘመን ሁሉ ሕግ እንዲገዛው አታውቁምን? ያገባች ሴት ባልዋ በሕይወት ሲኖር ከእርሱ ጋር በሕግ ታስራለችና፤ ባልዋ ቢሞት ግን ስለ ባል ከሆነው ሕግ ተፈትታለች።...

1ኛ ዮሐ. 4 ÷18 - ፍጻሜ
ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም። .....

የሐዋ.ሥራ 5÷34 - ፍጻሜ
በሕዝብ ሁሉ ዘንድ የከበረ የሕግ መምህር ገማልያል የሚሉት አንድ ፈሪሳዊ በሸንጎ ተነሥቶ ሐዋርያትን ጥቂት ፈቀቅ እንዲያደርጉአቸው አዘዘ......

#ምስባክ
መዝ.16፥3
ሐወጽከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብየ፡፡
አመከርከኒ ወኢተረክበ ዓመፃ በላዕሌየ፡፡
ከመ ኢይንብብ አፉየ ግብረ እጓለ እመ ሕያው፡፡
ትርጉም፦
በሌሊትም ጐበኘኸኝ፤ ልቤንም ፈተንኸው÷
ፈተንኸኝ÷ ዐመፅም አልተገኘብኝም፡፡
የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር

#ወንጌል
ዮሐንስ 3፥1-12
"ከፈሪሳውያንም ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ። መምህር ሆይ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህን ምልክቶች ሊያደርግ
የሚችል የለምና መምህር ሆነህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን አለው።....

#ቅዳሴ - ዘእግዝእትነ ማርያም [ጎሥዐ]

(#ማኅበረ_ቅዱሳን_ድረ_ገጽ እና
#ግጻዌ)

https://youtu.be/asRsJ2nU0K0?si=44_JSEaIBlgy-9QF
የተተኪ መምህራን ሥልጠና ሲከታተሉ የነበሩ ሠልጣኞች ተመረቁ

ከጌዲኦ፣ ቡርጂ እና አማሮ ዞን ሀገረ ስብከት ተውጣጥተው በቤቴል ደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ለተከታታይ 15 ቀናት ሥልጠና ሲከታተሉ የነበሩ 35 ሠልጣኞች ዛሬ ሚያዝያ 13 ቀን 2016 ዓ.ም ተመርቀዋል።

ማኅበረ ቅዱሳን ከደብሩ ሰበካ ጉባኤ እና ሰ/ት/ቤት ጋር በመተባበር በተዘጋጀው በዚህ ሥልጠና ላይ የትምህርተ ሃይማኖት እና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ርእሰ ጉዳዮች የተዳሠሡ ሲሆን ሠልጣኞች ወደ አካባቢዎቻቸው ሲመለሱ  ማገልገል የሚችሉባቸውን እውቀቶች እንዲጨብጡ ተደርጓል።

በምርቃት ሥነ ሥርዓቱ ላይ መልእክት ያስተላለፉት የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ የሆኑት ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ሥዩም እንደገለጹት ማኅበረ ቅዱሳን በ2016 ዓ.ም 6 ወራት ውስጥ ከ 28,000 በላይ ኢ አማንያንን አስጠምቆ ወደ ቤተ ክርስቲያን ልጅነት የመለሰ ሲሆን ዛሬ የተመረቁት ሠልጣኞች ስብከተ ወንጌልን በማስፋፋት ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸው ተናግረዋል።

የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ሃይማኖት መምህር ኢሳይያስ ቸርነት እንደገለጹት የደብሩ ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር በመተባበር የስብከተ ወንጌል አገልግሎትን ለማስፋፋት በርካታ ሥራዎችን እየሠራ ሲሆን ለዚህ አንዱ ማሳያ የዛሬ ተመራቂዎች ናቸው ብለዋል።

አስተዳዳሪው ጨምረው እንደገለጹት የደብሩ ሰ/ት/ቤትን በማስተባበር በቀጣይ ሌሎች 36 ሠልጣኞችን ከተለያዩ አካባቢዎች በማምጣት ሥልጠናዎችን ለመስጠት በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
2024/09/28 16:23:05
Back to Top
HTML Embed Code: