Telegram Web Link
የማኅበረ ቅዱሳን ኬንያ ማእከል ያዘጋጀው ዐውደ ርእይ በኬንያ ናይሮቢ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ተከናወነ።

የማኅበረ ቅዱሳን ኬንያ ማእከል "“ቤተክርስቲያንን እንያት፣ እንወቃት፣ እንውደዳት፤ ድርሻችንን እንወጣ" በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው ዐውደ ርእይ ናይሮቢ በሚገኘው በደብረ መድኃኒት መድኃኔ ዓለም ቤተክርስቲያን ለዕይታ ቀርቧል።

ምእመናን የቤተክርስቲያንን መሠረተ እምነትና ዓለማቀፋዊነት ተረድተው ሃይማኖታቸውን ጠብቀው የቤተክርስቲያን ትውፊት እና ተቋማዊ አንድነት ለማስጠበቅ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ማስገንዘብን ዓላማ ያደረገው ዐውደ ርእይ የደብሩ አስተዳዳሪ ሊቀ ብርሃናት ሄኖክ ይገዙን ጨምሮ ጥሪ ተደረገላቸው እንግዶች እና ምእመናን ተገኝተው እንደጎበኙት ለማወቅ ተችሏል።
የማኅበረ ቅዱሳን መደበኛ አገልጋዮች " ንጹሕ ምንጭ ኢትዮጵያ " የተሰኘውን ዐውደ ርእይ ጎበኙ

በሐመረ ብርሃን የብራና ሥራ ድርጅት  አማካኝነት " ንጹሕ ምንጭ ኢትዮጵያ " በሚል መሪ ቃል ግዮን ሆቴል እየተዘጋጀ የሚገኘውን ዐውደ ርእይ የማኅበረ ቅዱሳን መደበኛ አገልጋዮች በዛሬው ዕለት ጎብኝተውታል። አገልጋዮቹ የብራና ሥራ ድርጅቱ እያከናወነ ያለው ተግባር እጅግ ሊበረታታ የሚገባው እንደሆነ ገልጸዋል።

ዐውደ ርእዩ የቤተ ክርስቲያንን ቀደምት ታሪክ ፣ አስተምህሮ እና ሥርዓት ከማሳየት አንጻር ከፍተኛ ሚና ያለው ሲሆን በተለይም የብራና ሥራን አሁን ላለው ትውልድ ለማስተዋወቅ ትልቅ ዕድል የሚፈጥር ነው።

ድርጅቱ  በዘርፉ ከፍተኛ ሥራ እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን ምእመናን በቀሩት ሁለት ቀናት በቦታው በመገኘት ዐውደ ርእዩን እንደከታተሉ ጥሪ ቀርቧል።
ሐመር መጽሔት ፴፪  ኛ ዓመት   ቁጥር ፬

የኅትመት ዘመን ፦ ሚያዝያ   ፳፻፲፮ ዓ.ም
አዘጋጅ ፦በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ  ቤተ ክርስቲያን ማኀበረ ቅዱሳን በልማት ተቋማት አስተዳደር  በመጽሔት ዝግጅት ክፍል የሚዘጋጅ ትምህርታዊ መጽሔት
•  ገጽ ብዛት፦፳፰
   ዋጋ ፦፵ ብር 
•  ሐመር  መጽሔት  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት  ሥርዓትና ትወፊት ጠብቃ በልማት ተቋማት አስተዳደር  በመጽሔት ዝግጅት ክፍል  በየወሩ የምትወጣ መንፈሳዊ መጽሔት ናት፡፡
•  ሐመር መጽሔት ፴፪ ኛ ዓመት  ቁጥር ፬  ሚያዝያ ፳፻፲፮ ዓ.ም በመልዕክት ዐምድ "# የመንግሥት  እና የሃይማኖት ግንኙነት በአግባቡ ይሁን" በማለት በቤተ ክህነቱም በኩል  ምንም እንኳን   ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንደተቋም አስተዳደራዊ  ወሰኗን ጠብቃ የምትመራ ብትሆንም  አንዳንድ ግለሰቦች ቅድስት   ቤተ ክርስቲያንን በማይወክሉ ግለሰቦች የሚደረገው እሰጣ ገባ መርሕን የለቀቀ በመሆኑ ሊታረምና ሊስተካከል ይገበዋል  ያሳያል፡፡

በሀገር ልማትና በመልካም ዜጋ ግንባታ ውስጥ ሊተባበሩ  በሃይማኖትና በፓለቲካዊ ጉዳዩች  ግን የየራሳቸውን መስመር ጠብቀው ሊጓዙ  እንደሚገባ  በግልጽ  መታወቅና ተግባራዊ መሆን እንዳለበት ይጠቁማል። ቤተ መንግሥትና ቤተ ክህነት አንዱ ሌላውን ሳይገፋ ፣አንዱ የሌላውን አስተዳዳራዊ ሥርዓት  ሳያደናቅፍ በየራሳቸው ምሕዋር ሊጓዙና በጋራ ለሚመሯቸው ሕዝቦች መብትና ደኅንነት በጋራ ሊቆሙላቸው  እንዲሁም ሥጋዊና መንፈሳዊ ተጠቃሚነታቸውን ሊያረጋግጡ እንደሚገባ ይጠቁማል።
ዐውደ ስብከት  ሥር” #አንድነታችን አንተው "  በሚል ርእስ    በአንድነት ጸንቶ ፣ በሥራ ተግቶ መኖር የተፈጠርንበት ዓላማ መሆኑን መረዳት እንደሚያስፈልግ   ይዳስሳል፡ከዘረኝነት ሐሳብ ወጥተን መንፈሳዊ አንድነታችንን ልናጠነክር  እንደሚገባ ያሳያል ። የማይመካከርና የማይተባበር ማኅበረሰብ ለችግር ራሱን አሳልፎ ይሰጣል ። ስለዚህ እኛም ከዘረኝነት ከልዩነት ሐሳብ  ወጥተን ወደ አንድነቱ መምጣት  አማራጭ ሳይሆን መንፈሳዊ ግዴታችን ነው።

በትምህርተ ሃይማኖት ዐምድ ሥር “#ትንሣኤ ክርሰቶስ "በሚል ዐቢይ ርእስ  መልአከ ሰላም ቀሲስ #ደጀኔ ሺፈራው   ከሰሜን አሜሪካ ሀገረ ስብከት ዴንቨር  ደብረ ሰላም   መድኃኔዓለም  ቤተ ክርስቲያን  አስተዳዳሪ ሦስት መዓልት እና ሥስት ሌሊት የሞላው እንዴት እንደሆነ ፣  እንዴት ተነሣ?፣ ለምን በአዲስ መቃበር እንደተቀበረ፣ በኩረ ትንሣኤ እንደተባለ ፣ እንዴት በዝግ መቃበር ተነሣ?  ሙታን እንዴት ይነሣሉ? በበቂ  ማስረጃ የተደገፈ  ትምህርት ይዛለች።

• ዐቢይ ጉዳይ  ዐምድ  ሥር  ደግሞ “ #በቅድስት ቤተ ክርስቲያንና በሀገር ችግሮች ላይ በጋራ መሥራት ዘላቂ መፍትሔ ያመጣል “ በሚል ርእስ በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት "መንግሥትና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸው። (አንቀጽ  11) ይህም ማለት መንግሥታዊ ሃይማኖት አይኖርም ። መንግሥትና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸው የሚባለው ፅንሰ ሐሳብ እስከ ምን ድረስ ነው?

በመንግሥት ብቻ የተሠራ ሀገር የለም ፤።በሃይማኖት ተከታዮች ብቻም የተሠራ ሀገር የለም። ዛሬ ዛሬ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሀገር ግንባታ የነበራት ሚና  እየተረሳ ብቻ ሳይሆን እንዲጠፋ የሚፈለግ በሚመስል  መልኩ  ከምንም ነገር ገጽታዋ  እንዲጠፋ እየተደረገ ነው።  ስለዚህ  ከማኅበራትና ከሰንበት ትምህርት ፣ከአባቶች ምን እንደሚጠበቅ ይዳስሳል።

•  ክርስትና በማኀበራዊ ዐምድ ሥር  ደግሞ  " ከሚያለቅሱ ጋር አልቅሱ  ክፍል _፪  “በማለት  ወላጆች ልጆቻቸውን አጥተው ፣ የሚያግዛቸውንና የሚንከባከባቸውን  ቤተሰቦቻቸውን አጥተው ከበሰዝተው እያለቀሱባቸው ላሉት ችግሮች  መፍትሔው ምንድን ነው? ይጠቁማል ።

•  በእናስተዋውቃችሁ ዐምድ ሥር “#በእንተ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርዊ  ክፍል_፪"  በሚል ርእስ ቅዱስ ኤፍሬም ያየው ራእይ ፣የቅዱስ ኤፍሬም ተጋድሎና ያደረጋቸውን ተአምራት ፣ስለ ቅዱስ ኤፍሬም ድርሳናት   በስፋት ይዳስሳል ።

•  በነገዋ  ቤተ ክርስቲያን ዐምድ  ሥር “ነገን ዛሬ እንሥራ _ክፍል ፩  “ በሚል  ሕዝብ  ግንኙነት እና ትብብር አገልግሎት ማስተባበሪያ   ቤተ ክርስቲያንን እንዴት  እንደተቀበልናት ?  አባቶቻችን ቤተ ክርስቲያንን ከእኛ ለማድረስ  ብዙ  መከራን እንደተቀበሉና አሁን ላይ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተግዳሮት በጣም ብዙ  መሆኑን ለማንም የተደበቀ እንዳልሆነ  በጥቅሉ ቤተ ክርስቲያን በስደት ላይ ያለችበት  ወቅት እንደሆነ ፣የነገዋ ቤተ ክርስቲያንና ክብረ ክህነት  አደጋ ላይ እንደወደቀ ያሳያል ፡፡

#በኪነ ጥበብ ዐምድ "# አጋዥቷ  ክፍል _፪ " በሚል ያስነብባል።
•  የጥያቄዎቻችሁ መልስ ዐምድ “#የተመሳሳይ  ጾታ ግንኙነትና    ክፍል ፪- "  በሚል ርእስ ከመምህር ግርማ ባቱ የቅድስት ሥላሴ ዪኒቨርስቲ መምህር ጋር የተደረገ  ወቅታዊ ምላሽ ይዛለች  ።

#መ/ር ግርማ ባቱ "ተመሳሳይ ነጾታ ግንኙነት  ሕይወት የሚኖር ሰው ዘር አይተካም ፤ዘርን መተካት ግን  ለሰው ልጅ በጸጋ የተረጠው ትልቁ ሀብቱ ነው ። እንደ ኦርቶዶክስ  ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ብቻ ሳይሆን እንደ ሰውነት ፣ሀገራዊ እሴትን  በመጠበቅ ለኖረ  ሰውም  እጅግ ጎጂ እንደሆነ መረዳት ያሰፈልጋል "ይላሉ። የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ አቋሟ ግልጽ ነው። ይህ ነገር ኃጢአት ነው።ያልተገባ አካሄድ ነው። መጨረሻው ጥፋት ነው።
       
ሐመር መጽሔት ፴፪ኛ ዓመት  ቁጥር ፬ በማሰራጨት ፡በማንበብና በማስነበብ የድርሻችን እንወጣ !
[email protected]  ሐመር መጽሔት  ዝግጅት  ክፍል
2024/09/28 18:16:23
Back to Top
HTML Embed Code: