Telegram Web Link
ሙያን መንከባከብ፣ መጠበቅና ማበጀት እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

ሁሉም ኦርቶዶክሳውያን ባለሙያዎች በሙያቸው ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን እንዲያገለግሉ ዓላማ ያደረገ ጉባኤ ሙያችን ለቤተ ክርስቲያናችን በሚል መሪ ቃል በማኅበረ ቅዱሳን የአዳማ ማእከል አዘጋጅነት በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት አዳራሽ ተካሂዷል፡፡

በጉባኤው የማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል ልዑካን፣ የአዳማና አካባቢው የልዩ ልዩ ዘርፍ ባለሙያ የሆኑ ኦርቶዶክሳውያን ተሳትፈዋል፡፡ በማኅበረ ቅዱሳን ሙያና ማኅበራዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ የቅርስና ቱሪዝም ክፍል ኀላፊ ዶ/ር ታደሰ ዓለሙ ኦርቶዶክሳዊ የሙያ አገልግሎት ምንነት፣ ልምዶችና የቀጣይ ትኩረቶች በሚል የመወያያ ጥናታዊ ጽሑፍ አቅርበዋል፡፡ በዚህም ሙያን ለቤተ ክርስቲያን መስጠት በመንፈሳዊ ይዘት ላይ የተመሠረተ በመሆኑ አሥራት እንደማውጣት የሚወሰድና ፍቅርን በመስጠት ለእግዚአብሔር መታዘዝ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን ባሉት በጎ ፈቃደኛ ባለሙያዎች ከምሥረታው ጀምሮ በፈጸመው አገልግሎት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ያተረፈችባቸውና ባለሙያዎችም በረከት ያገኙባቸው ውጤቶች እንደተመዘገቡ በጥናቱ ተብራርቷል፡፡ ይሁን እንጂ ሙያን በመስጠት ሂደት ከቤተ ክርስቲያን መዋቅር እና ከባለሙያዎች የሚመነጩ ችግሮች እንደሚስተዋሉ ዶ/ር ታደሰ ያነሱ ሲሆን የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎችንም አቅርበዋል፡፡ ተሳታፊዎችም በቀረበው ጥናት እና ባካሄዱት የቡድን ውይይት ጥሩ ልምድና ግንዛቤ እንዳገኙበት ተናግረዋል፡፡

የውይይት ማጠቃለያ ያቀረቡት በማኅበረ ቅዱሳን የሙያና ማኅበራዊ አገ/ት ማስተባበሪያ ኀላፊ ዲ/ን ዶ/ር ቱሉ ቶላ ቅድስት ቤተክርስቲያንን ሊያሻግር የሚችል መዋቅር ለመፍጠር እና የሉላዊነትን ተፅዕኖ ለመቋቋም ሙያን መንከባከብ፣መጠበቅና ማበጀት ይገባል ብለዋል፡፡
በመጨረሻም በማኅበረ ቅዱሳን የአዳማ ማእከል ሰብሳቢ አቶ ከተማ ቢተው ባስተላለፉት መልእክት እየጎዳን ያለው እኛ ያልሠራነው ሥራ ነው፤ ከምክንያት እና ልማዳዊ አሠራር ተላቀን የቤተ ክርስቲያንን ችግር መፍታት አለብን ብለዋል፡፡
• ርእሰ፦ሐመር መጽሔት ፴፩ኛ ዓመት ቁጥር ፪
• የኅትመት ዘመን፦ የካቲት ፳፻፲፮ ዓ.ም
• አዘጋጅ፦በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኀበረ ቅዱሳን በልማት ተቋማት አስተዳደር በመጽሔት ዝግጅት ክፍል የሚዘጋጅ ትምህርታዊ መጽሔት
• ገጽ ብዛት፦፳፰
ዋጋ፦፵ ብር
• ሐመር መጽሔት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት ሥርዓትና ትወፊት ጠብቃ በልማት ተቋማት አስተዳደር በመጽሔት ዝግጅት ክፍል በየወሩ የምትወጣ መንፈሳዊ መጽሔት ናት፡፡

• ሐመር መጽሔት ፴፩ኛ ዓመት ቁጥር ፪ የካቲት ፳፻፲፮ ዓ.ም በመልዕክት ዐምድ "#የገሃነም ደጆች #አይችሏትም "በማለት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በየዘመኑ የገጠሟትን የተለያዩ ፈተናዎችን አልፋ ከዚህ ዘመን መድረሷን ያሳያል፡፡

• ዐውደ ስብከት ሥር #ክፉ ዘመንን እንዴትና #በምን መሻገር #ይቻላል ?” በሚል ርእስ ያለንበትን ክፉ ዘመን እንዴት መሻገር እንደምንችል ይዳስሳል

• በትምህርተ ሃይማኖት ዐምድ ሥር በሊቀ #ሊቃውንት #ስምዐ ኮነ መልአክ “#የሰይጣንን ሥራ ይሽር ዘንድ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ" በሚል ዐቢይ ርእስ ክርስቶስ የሰይጣንን ሥራ ያፈረሰባቸውን አምስቱን መንገዶች በሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ በጥልቀት የተጻፈ ትምህርት ይዛለች።

• ዐቢይ ጉዳይ ዐምድ ሥር ደግሞ “ የሰው ሁሉ ዐይን አንተ ተስፋ ያደርጋል “ በሚል ርእስ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የሃይማኖት ብቻ ሳትሆን ማኅበራዊ ተቋምም እንደሆነች ፣ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ድርቅና ረኅብ ሲከሠት አብራ እየተራበች እንደሆነ ያሳነብባል ፤አብነቱ ያለ አብነት እንዳይቀር በተከሠተው ረኅብ እና ድርቅ የሊቃውንቱ ምንጭም እንዳይደርቅ ከሁሉም ቅድሚያ በመስጠት መረዳዳት እንደሚያስፈልግ ያሳስባል፡፡
• ክርስትና በማኀበራዊ ዐምድ ሥር ደግሞ “#ሦስቱ ፍሬ ቢሶች “በማለት ፍሬ ካላፈራን ደግሞ መርገም እንደሚከተለን ፤ ሦስቱን ፍሬ ብሶች በዝርዝር ይዳስሳል፡፡

• በእናስተዋውቃችሁ ዐምድ ሥር “#ባሕረ ወርቅ መስመስ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካል "ቤተ ክርስቲያን ይዘው ስለመጡ ጠንካራ አባቶች ይተርካል፣ያስተዋውቃል፣ ባሕረ ወርቅ መስመስ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካል ቤተ ክርስቲያን ከመስመስ ሕዝብ ጋር ያለውን ቁርኝት ያሳያል። ባሕረ ወርቅ መስመስ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካል ቤተ ክርስቲያን ለሀድያ ሕዝብ የክርስትና መሠረት ማዔከሉ መሆኑ እሙን እንደሆነ ያስተዋውቃል ።

• በነገዋ ቤተ ክርስቲያን ዐምድ ሥር “ለነገዋ ቤተ ክርስቲያን ተረካቢ እናዘጋጅላት _ክፍል ፪“ በሚል ለልጆች ሁለንተናዊ ዕድገት ባለድርሻ አካላት የሚሆኑት ወላጆች፣ ጎረቤት፣ ማኅበረሰብ፣ ትምህርት ቤት ወዘተ. ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲመላለሱ ምን መሥራት እንዳለባቸው ፣መንፈሳዊ ትምህርት እንዲማሩ ፣ የሚኖራቸውን ሚና ያስነብባል፡፡

• በኪነ ጥበብ ዐምድ “ ምን በጀኝ ? “ በሚል ርእስ ይዳስሳል፡፡(ገጽ _፳፫)

• የጥያቄዎቻችሁ መልስ ዐምድ “#ምሥጢረ ሥጋዌ”ክፍል ፫ በምሥጢረ ሥጋዊና ተያያዥ ጉዳች የመጻሕፍተ ሐዲሳት መምህር ከሆኑት መምህር ኃይለ ማርያም ዘውዱ ዘቦሩሜዳ የወሎ ዪኒቨርስቲ የልሳነ ግእዝ መምህር እና በባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ የሁለተኛ ድግሪ ተማሪ ጋር መሠረታዊ ትምህርት ይሰጣል፡፡

መ/ር ኃይለ ማርያም ".በዘመናችን ሙሉ ብንኖርበትም ምሥጢረ ሥጋዌ ተነግሮ የማያልቅ ትምህርት እንደሆነ ገልጸዋል።

#ማእከላት፣ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት ሐመር መጽሔት ፴፩ኛ ዓመት ቁጥር ፪ ዕትም ለአንባቢያን እንድትደርስ የድርሻችሁን እንደትወጡ ምክንያቱም .ሐመር መጽሔት ትምህርተ ወንጌል ለመላው ዓለም ለማዳረስ አንዱ መሣረያ ናት፡፡

ሐሳብ አስተያየታችሁን ወደ ዝግጅት ክፍላችን በ magazine @eotcmk.org በኩል አድርሱን

ሐመር መጽሔት ከፍተኛ የሆነ የዕቅበተ እምነት ሥራ ሠርታለች ወደፊትም ትሠራለች፡፡

• ሐመር መጽሔት ፴፩ኛ ዓመት ቁጥር ፪ በማሰራጨት ፡በማንበብና በማስነበብ ዘመኑነም በመዋጀት የድርሻችን እንወጣ!

magazine @eotcmk.org ሐመር መጽሔት ዝግጅት ክፍል
ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማዕከል ከጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ ቤት ጋር በመተባበር ያስተማራቸውን ከ120 በላይ የሕክምና ተማሪዎች አስመረቀ።

ዘጠኝ ተመራቂዎች ማዕረገ ዲቁና ተቀብለዋል።

በጥቁር አንበሳ የሕክምና ትምህርታቸውን ተከታትለው በመጨረስ በትናንትናው ዕለት የተመረቁት ተማሪዎቹ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ጎን ለጎን ሲማሩ ቆይተው በማጠናቀቅ ዛሬ የአገልግሎት ተልዕኮ ተሰጥቷቸዋል።

በምርቃት መርሐግብሩ የተገኙት የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ መምህር ዋሲሁን በላይ ዘመናዊውንና መንፈሳዊውን ትምህርት ተምራችሁ በሁለት ሰይፍ የተሳላችሁ በመሆናችሁ እንዲህ ያለው ዕውቀት አገራችሁንና ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችሁን በቅንነት ለማገልገል ያግዛል ብለን እናምናለን ብለዋል።

ማኅበረ ቅዱሳን ዘመኑን የሚመጥን አሠራር ለመከተል ተቋማዊ ለውጥ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አምኖ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል ያሉት ዋና ጸሐፊው ተመራቂዎቹ በማኅበሩ የተለያዩ ማዕከላት በመታቀፍ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት አጠናክረው እንዲያስቀጥሉ የአደራ መልእክት አስተላልፈዋል።

በዕለቱ ለተመራቂዎቹ የአደራ መስቀል የተሰጠ ሲሆን የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ብርሃናት አእምሮ ምስጋና፣ የሰ/ት/ቤቱ አመራር አባላት፣ የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።
የደብረ ከዋክብት ዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም 4 መነኮሳት በታጣቂ ኃይሎች መገደላቸው ተሰምቷል።

ዝርዝሩን እንደደረሰን እናቀርባለን ።
"4 ተገድለው 1 ጠፍተዋል፤ ገዳሙን እና እኛን ለማዳን እነሱ ተሰው፤ የእኛንም በደል እነሱ ከፈሉ"
የደብረ ከዋክብት ዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አባቶች
++++++++++++++++++++++++++++++

የገዳሙን መጋቤ እና ዋና ጸሐፊ ጨምሮ የደብረ ከዋክብት ዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም 4 መነኮሳት በታጣቂ ኃይሎች መገደላቸውን ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን የደረሰው መረጃ ያመላክታል።

ከገዳሙ በስልክ ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው የካቲት 12/2016 ዓ.ም የታጠቁ ሰዎች ወደ ገዳሙ በመግባት ሁለት መነኮሳት መውሰዳቸውን እነሱ ይመለሳሉ ብለው ሲጠብቁ በማግስቱ የካቲት 13/2016 ዓ.ም ታጣቂዎቹ ድጋሚ መጥተው ለውይይት እንፈልጋችኋለን በማለት 3 መነኮሳትን ወደ "ጂዳ ተክለ ሃይማኖት" ወስደዋል ብለዋል።

መነኮሳቱ "ለውይይት" ሲባሉም "ችግር የለውም እናንተ አባቶች እዚህ ቆዩ እኛ አነጋግረናቸው እንመጣለን፤ ተረጋጉ" ብለው ታጣቂዎቹን ተከትለው ከገዳሙ ሂደዋል።

ቀኑን ሙሉ ስልካቸው ክፍት እንደነበረ አመሻሽ ማግኘት ባለመቻላቸው ተጨንቀው የአካባቢውን ምእመናን ሲያጠያይቁ 4ቱ መገደላቸውን እንደነገሯቸው አንደኛው አባት ግን ተለቀዋል ቢባልም እስካሁን ያሉበት እንዳልታወቀ አባቶቹ ለጣቢያችን በእንባ ተናግረዋል።

በታጣቂዎቹ የተገደሉት አባቶች

፩ አባ ተክለ ማርያም አሥራት (የገዳሙ መጋቤ)

፪ አባ ኪዳነ ማርያም ጥላሁን (የገዳሙ ዋና ጸሐፊ)

፫ አባ ገብረ ማርያም አበበ (ቀዳሽ ካህን፣የመጽሐፍ መምህርና የገዳሙ አስተዳደር አባል)

፬ ባህታዊ ኃ/ማርያም ስሜ (የገዳሙ የአስተዳደር አባል)
ሲሆኑ
እስካሁን ያሉበት ያልታወቀው ደግሞ አባ ኪዳነ ማርያም ገ/ሰንበት ናቸው።
ገዳሙ በተደጋጋሚ በታጠቁ ሰዎች ዐይነተ ብዙ ጥቃት እንደሚደርስበት ነገር ግን መፍትሔ እንዳላገኙ በመግለጽ የአሁኑ ጥቃት ግን በቃላት የማይገለጽ ነው ብለዋል።

"ገዳሙን እና እኛን ለማዳን እነሱ ተሰው፤ የእኛንም በደል እነሱ ከፈሉ፤ ጻድቁን አገልግዬ እዚሁ አርፋለሁ ሲሉ ደመ ከልብ ሆነው ዐፈራቸውንም ሳይቀምሱ ቀርተዋል" ሲሉም መረጃ የሰጡን አባቶች በከፍተኛ ሐዘን ገልጸዋል።
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
የተላለፈ ወቅታዊ መልዕክት።


ጥንታዊት፣ ታሪካዊት፣ ብሔራዊትና ዓለም አቀፋዊት በሆነችው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥር ከሚገኙት ጥንታዊያን ገዳማት መካከል ዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አንዱና ዋነኛው መሆኑ ይታወቃል።

ይህ ጥንታዊና ታሪካዊ ገዳም በርካታ ቅርሶችና መናንያን የሚገኙበት ገዳም ሲሆን በተለያዩ ጊዜያት በተከሰተበት ዘረፋና ቃጠሎ ከባድ ጉዳቶችን ያስተናገደ መሆኑም ይታወሳል።

በዛሬው ዕለት ከሀገረ ስብከቱ በደረሰን መረጃ መሰረትም፦
1. የገዳሙ መጋቢ አባተክለማርያም ዐሥራት
2. የገዳሙ ጸሐፊ አባ ኪዳነ ማርያም ጥላሁን
3. የገዳሙ የመጽሐፍ መምህርና ቀዳሽ አባ ገ/ማርያም አበበ
4. በአመክሮ የሚኖሩ መናኝ ኃይለማርያም ወልደሰንበት
የካቲት 12 ቀን "ኦነግ ሸኔ" በተባለው ታጣቂ ቡድን ከተወሰዱ በኋላ አራቱም በትላንትናው አለት የተገደሉ ሲሆን አባ ኪዳነማርያም ገ/ሰንበት የተባሉት አባት ቆስለው በገዳሙ እንደሚገኙ ታውቋል።

በአሁኑ ሰዓትም ታጣቂዎቹ ወደ ገዳሙ ለመግባት እንቅስቃሴ የሚያደርጉበት መንገድ እንዳይኖርና መናንያኑና የገዳሙ ቅርስ አደጋ ላይ እንዳይወድቁ የፌዴራልና የክልሉ የጸጥታ አካላት ገዳማዊያኑንና ገዳሙን የመታደግ ሥራ እንዲሠሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከአደራ ጭምር መልዕክቷን ታስተላልፋለች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት
የካቲት ፲፬ቀኝ ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
ሰሞኑን በማኅበራዊ ሚዲያ እየተዘዋወረ ስለሚገኘው "መነኩሴ"ነኝ ባይ ግለስብ በሀገረ ስብከቱ የማይታወቅ መሆኑን ሀገረ ስብከቱ ገለጸ።

የአርሲ ሀገረ ስብከት ሰሞኑን በማኅበራዊ ድረ ገጾች ራሱን "መነኩሴ"በማስመሰልና በአርሲ ሀገረ ስብከት አገልጋይ እንደሆነ በመግለጽ የሚንቀሳቀሰውን ግለሰብ የማያውቀውና ሐሰተኛ "መነኩሴ" መሆኑን ለጠቅላይ ቤተክህነት በጻፈው ደብዳቤ አስታወቀ።

ከየካቲት 12/20916 ዓ.ም ጀምሮ በማኀበራዊ ሚዲያ እየተዘዋወረ የሚገኘው ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ተችቶ የማስተቸት ድራማዊ ትዕይንት ላይ የቀረበው አስመሳይ "መነኩሴ"ግለሰብ በሀገረ ስብከታችን በተለይ በአሰላ ከተማ በቅዳሴ መምህርነት በስብከተ ወንጌል እንዳገለ በማስመሰል በሰጠው የሀሰት ምስክርነትን በተመለከተ እውነተኛ ምላሽ መስጠት ማስፈለጉን የጠቀሰው ሀገረ ስብከቱ"መንኩሴ "መሳዩ ግለሱብ በሀገረ ስብከቱ በየተኛውም የከተማና የገጠር ገዳማትና አድባራት የማይታወቅና ምንም ዓይነት አገልግሎት ሲሰጥ ያልነበረ መሆኑን ገልጿል።

በተጨማሪ በሀገረ ስብከቱ የሚገኙት ሁሉንም አገልጋዮች የሚታወቁና የተመዘገቡ መሆኑን የጠቀሰው ሀገረ ስብከቱ ግለሰቡ በሀገረ ስብከቱ ካሉት አገልጋች መካከል የማይታወቅና ያልተመዘገበ ከመሆኑም በላይ ሀገረ ስብከቱ በፍጹም የማያውቀው ቀሳጢ ነው በማለት ሐሰተኛ ማንነትን በመላበስ የቤተክርስቲያንን ስም ለማጠልሸተ የተሰማራ መሆኑን ገልጿል።

ስለሆነም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ግለሰቡ የቤተ ክርስቲያናችንን ዓርማ ወይም አልባሳት በመልበስና የሀገረ ስብከታችንን መልካም ገጽታ በማጉደፉ ግለሰቡንና እዩ ጩፋ የተባለውን አጽራረ ቤተ ክርስቲያን በህግ እንዲጠይቅን ስንል በታላቅ አክብሮት እናሳስባለን፤በማለት ለጠቅላይ ጽሕፈት ቤቱ በጻፈው ደብዳቤ ጨምሮ ገልጿል።

ምንጭ: የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
The Queenship of Saint Mary

The Divine Wisdom of God for the salvation of the world is done through His tremendous mercy. The primordial covenants of the Old Testament were without the capability of redeeming mankind. The absolute covenant was done by the seventh covenant for the salvation of human race thru Holy Saint Virgin Mary. 

She is given the covenant of mercy and for this we plead calling her “Covenant of Mercy.”  The promise made for Adam is done thru he; for she gave birth to The Holy Son, Lord and Savior Jesus Christ in virginity.  He suffering and was crucifixion on the cross was by her flesh and soul.

As we find it written in Mariology, after Our Lord and Savior Jesus Christ’s ascension, Saint Virgin Mary went to His grave Golgotha and prayed pleading for the salvation of humans. Then He gave her the covenant of mercy on Yekatit 16.  
This holy day that we are bestowed a mercy of covenant is very great and thus Holy Church celebrates it colorfully.  This Queenship of Saint Mary is the confusion of all the previous six covenants which are Covenant of Adam, Covenant of Noah, Covenant of Melchizedek, Covenant of Abraham, Covenant Moses and Covenant of David. In the commemoration of this eternal covenant, we make celebration in Church by praising in Psalm, Maheleate Song and Divine Liturgy.

Dear Brethren, we shall acknowledge this covenant of the New Testament, which is made for our salvation of soul and plead in the name of Saint Mary’s Queen ship and commemorate her feast day by feeding the hunger, water the thirst and aid the deprived.  
May our Holy Mother’s Saint Mary’s intercession and Mediation be with all of us, Amen
2024/09/29 18:20:54
Back to Top
HTML Embed Code: