Telegram Web Link
#Update

የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ  ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) ዛሬ አሜሪካ ገብተዋል።

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) አሜሪካ ሲደርሱ አቀባበል ተደርጎላቸው።

ማክሰኞ ጥር 28 / 2016 ዓ/ም በአሜሪካ የነበራቸውን አገልግሎት አጠናቀው ወደ ኢትዮጵያ ቢመለሱም በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ከደረሱ በኃላ ወደ #ኢትዮጵያ መግባት እንደማይችሉ ተነግሯቸው ዛሬ ወደ አሜሪካ ለመመለስ ተገደዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፤ ብፁዕነታቸው ወደ አሜሪካ ከመመለሳቸው በፊት የሚመለከተው የመንግስት አካል የቤተክርስቲያኗ ከፍተኛ  የሥራ ኃላፊና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ  መሆናቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ወደ አገር እንዲገቡ  እንዲፈቀድላቸው እንዲያደርግ ብትጠይቅም የመፍትሄ ምላሽ ባለመገኘቱ ወደ መጡበት አሜሪካ ተመልሰዋል።

መንግሥት እስካሁን ስለጉዳዩ የሰጠው ማብራሪያ የሌለ ሲሆን በቀጣይ የሚሰጠው ማብራሪያ ካለ ተከታትለን እናቀርባለን።
በተጠቀሱት ጉዳዮች ላይ በትብብርና በአጋርነት ለመስራት የሚያስችል ሕጋዊ የስምምነት ማዕቀፍ መኖሩ መልካም ቢሆንም የስምምነቱ ዝርዝር ጉዳዮችና ነጥቦች ሲፈተሹ ግን ከየሃይማኖታችን ሕግጋትና አስተምህሮ ጋር በእጅጉ የሚቃረኑ ሀሳቦችና አቅጣጫዎች የያዘ ሰነድ በመሆኑና በዚህም ምክንያት በህዝባችን ውስጥ ከፍተኛ ድንጋጤን፣ መረበሽንና ስጋትን እንደፈጠረ በማጤን እና ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመስጠት የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አስፈላጊውን ማጣራት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

በዚህም መሠረት የትብብርና የአጋርነት ስምምነቱ በውስጡ ከኢትዮጵያ ሕዝብ የሃይማኖትና የባህል እሴቶች ጋር የሚፃረሩ ጽንስ ሀሳቦችና ትርጉሞች ያላቸውን ይዘቶች ያካተተ ስለመሆኑና ይህም በዓለም አቀፍ ድርጅቶችና መድረኮችም ጭምር የሚታወቁ ሐረጎችንና አንቀፆችን እንደያዘ ጉባኤው ካገኘው መረጃ ማረጋገጥ ተችሏል:: ለአብነት ያህል፡-

ሀ) በስምምነቱ አንቀፅ 36.2 ላይ የተጠቀሰው “የወሲብና የተዋልዶ ጤናና መብቶች” (“Sexual and Reproductive Health and Rights”) የሚለው ሐረግ በቀጥታ ከግብረሰዶም መብቶች፣ ከፆታ መቀየር፣ ከውርጃ፣ ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርትና ግልሙትናን ሕጋዊ ከማድረግ ጋራ በቀጥታ የተያያዘ መሆኑ በአውሮፓ ፓርላማና በዓለም የጤና ድርጅት የመረጃ ምንጮች ላይ በግልፅ መቀመጡ ፣

ለ) በስምምነቱ የአፍሪካ ፕሮቶኮል አንቀፅ 40.6 ላይ በአህጉሪቱ ለሚገኙ ልጆችና ታዳጊዎች ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርት (Comprehensive Sexuality Education) የተባለ እጅግ አደገኛ ኢግብረገባዊና ልቅ የወሲብ ትምህርት እንዲማሩ አስገዳጅ መሆኑ ለዚህም በዩኔስኮ የተዘጋጀውና እጅግ አደገኛ ይዘት እንዳለው የተረጋገጠው መተግበርያ “International Technical Guidance on Sexuality Education” በስም ተጠቅሶ መቀመጡ ፣

ሐ) ይህም “ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርት” በሚል የሚታወቀውና በዚህ ስምምነት ውስጥ “Comprehensive Sexual and Reproductive Health Information and Education” የሚል ስያሜን ይዞ የሚገኘው ዕድሜንና ባህልና ያማከለ እንደሆነ የሚነገርለት ኢግብረገባዊ የትምህርት ዓይነት በዓለማችን በበርካታ ሃገራት ተተግብሮ በታዳጊዎችና በወጣቶች ላይ በከፍተኛ ደረጃ የሞራል ውድቀትንና ወሲባዊ ልቅነትን ማስከተሉ በብዙ ሳይንሳዊ ምርምሮች የተረጋገጠና በተለይም በአፍሪካ ካሁን በፊት በተተገበረባቸው ሃገራት 84% ጊዜ ውድቀት ያስከተለ መሆኑ መረጋገጡ

መ) በዚህ ደረጃ ያለ ዓለም አቀፋዊ ስምምነትን የያዘው ዶኩመንት በውስጡ የቃላት መፍቻ (Glossary) አለመካተቱ, እንዲሁም ሃገራት ያለተስማሙባቸውን አንቀፆች የሚቃወሙባቸው ዕድሎች (reservation clause or interpretive declaration) ሆን ተብለው እንዲወጡ ወይም እንዳይኖሩ መደረጋቸው፤

ሠ) በስምምነቱ አንቀፅ 40. 6 ውስጥ እንደተመለከተው ሀገራችንን ካሁን በፊት ተካሂደው በነበሩና ገና ወደፊት በሚካሄዱ ውጤታቸውም በማይታወቅ ዓለም አቀፍ ሰብሰባዎች የሚወጡ አደገኛ ይዘት ያላቸው የጋራ መግለጫዎችን እንዲህ በሚሉ አንቀጾች (“The Parties shall commit to the full and effective implementation of the Beijing Declaration and Platform for Action and the Programme of Action of the International Conference on Population and Development and the outcome documents of their review conferences.”) ተግባራዊ የማድረግ ግዴታ ውስጥ የሚያስገባት መሆኑ እየታወቀ መፈረሙ፣

ረ) እንዲሁም ኢትዮጵያ ፈራሚ ባልሆነችባቸው አካባቢያዊና አህጉራዊ ስምምነቶች አካል የሚያደርጋት መሆኑና የሀገር ሉዓላዊነትን በግልፅ ተቀምጦ እያለ የተፈረመ መሆኑ፣

ሰ) የፆታ ትንኮሳን (gender based violence) ማስቀረት በሚል በጣም አሻሚ የሆኑ ግብረሰዶማዊ አስተሳሰቦችን ለማስረፅ እንዲረዳው በሰነዱ በበርካታ ክፍሎች ውስጥ “አካታች” (“inclusive”) በሚሉ ቃላት ተሸፍኖ እንዲገባ የተደረገ መሆኑ፣

ሸ) በተጨማሪም በበርካታ ሥፍራዎች የተጠቀሰው “Gender” የሚለው ቃል ወንድና ሴት ተብሎ እንደሚተረጎም በስምምነቱ በግልጽ ባለመቀመጡ ይልቁንም በርካታ ጾታዎች እንዳሉ በማስመሰል ሀገራትን የሚያደናግሩባቸው እንደ (sexual orientation አና gender identity)ን የመሳስሉ ግብረሰዶማዊ አስተሳሰቦችን የያዙ ዶክመንቶች በስም ተጠቅሰው በስምምነቱ ውስጥ መካተታቸው፣

ቀ) ስምምነቱ የወላጆችን መብት የሚጥስና የኢትዮጵያዊ ቤተሰብ እሴቶችን አደጋ ላይ የሚጥሉ አንቀፆችን የያዘ ስለመሆኑ በሰነዱ ላይ ከተደረገ የኤክስፐርቶች ጥልቅ ጥናት ተረድተናል፡፡

በአጠቃላይ ይህ አዲስ የአጋርነት ስምምነት ልዩ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡና ትውልድንና ብሎም ሀገርን እጅግ የሚጎዱ በርካታ አንቀጾች የተካተቱበት በመሆኑ ለሀገራችን ህዝብ ዕድገትን ሳይሆን ውድቀትንና ከፍተኛ የሞራል ዝቅጠትን የሚያስከትል የሀገራችንንም ሉዓላዊነት አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን በሚገባ ተረድተናል፡፡ ስለሆነም እኛ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች የአጋርነት ስምምነቱ አስገዳጅና አሳሪ እንዲሆን ተደርጎ የተዘጋጀ ከመሆኑ አንፃር መንግስት ከዚህ በታች ያቀረብናቸውን ምክሮችና ተግሳፆችን በመቀበል የሀገርን ሉዓላዊነትና ትውልድን የመጠበቅ ሕጋዊ፣ ሞራላዊና ታሪካዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ከታላቅ አባታዊ አደራ ጋር በአጽንኦት እናሳስባለን፡፡

1. መንግስት የአዲሱን የሳሞአ የንግድና የኢኮኖሚ የአጋርነት ስምምነትን በርካታ ጎጂ ጎኖች እንዳሉት በማመን ከዚህ ስምምነት ኢትዮጵያ ራሷን እንድታገልል በማድረግ መንግስታዊ ኃላፊነቱንና አደራውን በተግባር እንዲወጣ በአጽንኦት እንጠይቃለን፡፡

2. የሀገሪቱ ከፍተኛው የሥልጣን አካል የሆነው የተከበረው የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና በሥሩ ያሉ የሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች የስምምነት ሰነዱ ውስጥ በዝርዝር የቀረቡትን በተለይም ከሰብኣዊ መብቶች፣ ከወሲባዊና የተዋልዶ ጤናና መብቶች፣ ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርት፣ አካታችነት እና መሰል በሰነዱ የተካተቱ አንቀጾች ወይም ይዘቶች ከግብረሰዶማዊነትና ጾታን ከመቀየር እንዲሁም ከልቅ ወሲብና ከውርጃ ጋራ በቀጥታ ተያያዥነት ያላቸው ጽንሰ ሃሳቦች መሆናቸውን በመረዳት ይህንን እጅግ አደገኛ ስምምነት ባለማጽደቅ ህዝባዊና ታሪካዊ አደራውን እንዲወጣ በአጽንኦት እንጠይቃለን፡፡

3. መንግስታችን ከህዝብ አደራን ተቀብሎ ሀገርን የሚያስተዳድር እንደመሆኑ ከዚህ በኋላ በሚያደርጋቸው ተመሳሳይ የትብብር ስምምነቶች ከላይ የዘረዘርናቸውን ዓይነት የሀገራችንን ኃይማኖት፣ባሕልና ነባር እሴቶችን የሚንዱ ጽንሰሃሳቦችን ያዘሉ አሳሳች ሀረጎች ያሉባቸውን ስምምነቶች ፈጽሞ እንዳይፈርም እያሳሰብን፣ ስምምነቶችንም ለመፈራረም በሚደረጉ ድርድሮች ወቅትም የሚፈርማቸው ዶክመንቶች ውስጥ የምንወዳት ሀገራችን ኢትዮጵያ እንደሀገር የማትስማማባቸውን ወይም የማትቀበላቸውን አንቀጾች የምትቃወምበት (reservation clause or interpretive declaration) ዕድልና መብት እንዲኖራት ሊሠራ እንደሚገባ በአጽንኦት እንመክራለን፡፡
በመጨረሻም የአጋርነት ስምምነቱ ማዕቀፍ ውስጥ በሰብኣዊ መብት፣ በንግድና የኢኮኖሚ ትብብር ሽፋን ከሃይማኖታችን መሠረታዊ አስተምህሮ የወጡና የሀገራችንን ባሕልና ነባር እሴቶችን የሚንዱ ጸያፍ ልምምዶች ቀጥተኛ ባልሆነ አግባብ በሰነዱ ውስጥ የተካተቱ መሆናቸውን ተገንዝበናል፡፡ ስለሆነም በየትኛውም ሁኔታና አግባብ የሰነዱ ዋናና ዝርዝር አንቀጾች ወይም ይዘቶች ትርጓሜ ከሃይማኖቶቻችን መሠረታዊ አስተምህሮ፣ ከዶግማዊና ቀኖናዊ ጉዳዮች ጋር የሚቃረኑና የማይስማሙ ወይም ተቀባይነት የሌላቸው አንቀጾች ወይም ይዘቶች/ሀሳቦች በሀገራችን ኢትዮጵያ በየትኛውም ሁኔታና ደረጃ በምንም መልኩ ፍፁም ተፈፃሚ ሊሆኑ እንደማይችሉ ከወዲሁ በአጽንኦት እያስገነዘብን 98% የሚሆነውን ህዝባችንን እንደመወከላችን ይህን ቁርጠኝነታችንን የአውሮፓ ኅብረት፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ ምዕራባውያኑ ሀገራት እና የአፍሪካ ኅብረት ከወዲሁ እንዲገነዘቡ በአጽንኦት እናሳስባለን፡፡

ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ!
ማኅበረ ቅዱሳን ( Mahibere Kidusan)
Photo
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች በአውሮፓ ኅብረት እና በአፍሪካ፣ በካሪቢያንና በፓስፊክ ሀገራት መካከል የተፈረመውንና የሳሞአ ስምምነት በመባል የሚታወቀውን የንግድና የኢኮኖሚ አጋርነት ስምምነት አስመልክቶ የተሠጠ መግለጫ

የተወደዳችሁ በሀገር ውስጥና በውጪው ዓለም የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ኢትዮጵያዊያት ልጆቻችን ከሁሉ በማስቀደም መንፈሳዊ ሰላምታችንን እናቀርባለን፡፡

ባሳለፍነው የህዳር ወር በ5ኛው ቀን 2016 ዓም የተወሰኑ የአፍሪካ የካሪቢያንና የፓሲፊክ ሀገራት ለሚቀጥሉት 20 ዓመታት ጸንቶ የሚቆይ የንግድና ኢኮኖሚ አሳሪ የአጋርነት ስምምነትን ከአውሮፓ ኅብረት ጋራ ሳሞአ በምትባል ሀገር በተከናወነው የስምምነት የፊርማ ሥነ ሥርዓት ወቅት ሀገራችን ኢትዮጵያም ይህንኑ ስምምነት መፈረሟን በብራሰልስ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

ይህ በአውሮፓ ኅብረት እና በአፍሪካ፣ በካሪቢያንና በፓስፊክ ሀገራት መካከል ለ20 ዓመታት እንዲዘልቅ ታሳቢ ተደርጎ የተከናወነው የንግድና የኢኮኖሚ ትብብር የአጋርነት ስምምነት በዋናነት የሰብኣዊ መብቶች፣ የዲሞክራሲና የአስተዳደር፣ የሰላምና ደኅንነት፣ የሰብኣዊና ማኅበራዊ ልማት፣ አካታች የሆነ ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገትና ልማት፣ የአካባቢና የአየር ንብረት ለውጥ፣ እና የሰዎች ፍልሠትና የመዘዋወር ጉዳዮች ላይ በጋራ መርኅና የየሀገራቱን ፍላጎት መሠረት በማድረግ ተፈፃሚ እንደሚሆን የሰምምነት ሰነዱ ያትታል፡፡
የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻና ግብረ ሰዶማዊነትን አስመልከቶ እየተደረጉ ያሉ ሁለገብ ተጽእኖዎችንና መመሪያ የማስለወጥ ማግባባቶችን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፤

“ወለእመቦ ዘሰከበ ምስለ ተባዕት ከመ አንስት ርኵሰ ገብሩ ክልኤሆሙ … ወጊጉያን እሙንቱ..ማንኛውም ሰው ከሴት ጋር እንደሚተኛ ከወንድ ጋር ቢተኛ ሁለቱ ጸያፍ ነገር አድርገዋል። ደማቸውም በላያቸው ነው" (ዘሌ.፳ ፥፲፫) ግብረ ሰዶማዊነት በሕገ ተፈጥሮም ሆነ በሰው ልጅ ሰብአዊ አኗኗር ፈጽሞ ተቀባይነትየሌለው፣ ዓለምን በልዩ ጥበብ በፈጠረ አምላክ ፈቃድ፣ መለኮታዊ ሥርዓቱ በተገለጠባቸው ቅዱሳት መጻሕፍት ፈጽሞ የተከለከለ፣ በቀኖናተ ቤተክርስቲያን፣ በፍትሕ መንፈሳዊና በፍትሐ ብሔር ድንጋጌዎች፣ በሥነ ልቦና ደንቦች የተወገዘ፣ ሥነ አእምሮዊ ሚዛንን የሚያዛባ፣ግለሰባዊ ማንነትንና ማኅበራዊ ትሥሥርን የሚያናጋ የረከሰ ተግባር ነው፡፡

ግብረ ሰዶማዊነት በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተገለጸው ለአንድ ሀገርና ሕዝብ ከነጎረቤቶቹ መጥፋት ምክንያት የሆነ ተግባር ሲሆን የሰዶምና ገሞራ በመቅሰፍተ እሳት መቃጠል ከእነርሱ መቀጣትም አልፎ ላለውና ለመጪው ትውልድ አስተማሪ የሆነ ምልክት እንዲሆን ነው።

መጽሐፍ ቅዱስም ግብረ ሰዶማውያን የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም በማለት የግብሩን አስከፊነት፣ በማኅበረ ሰብእ ላይም የሚያመጣውን ጥፋት በአጽንዖት ይነግረናል። (ሮሜ ፩፳፮ ፩ቆሮንቶስ ፮፱፣I፣)
ይህንንም ግብረ ርኩሰት ቅዱሳት መጻሕፍት በተለያየ ሥያሜ ጠርተውታል፤ ከእነዚህም ርኩሰት፣ ጸያፍ፣ ትልቅ ኃጢአት፣ በደልና አመጻ የሚሉት ቃላት ይገኙበታል፡፡ (ዘሌ ፲፰-፳)

የኃጢአተኛውን ሞት የማይሻው እግዚአብሔር ሌሎች ሕዝቦች በሚበድሉበት ጊዜ በዕዶምና በገሞራ የደረሰውን ጥፋት እየጠቀሰ ከጥፋታቸው እንዲመለሱ ማስጠንቀቁን በቅዱሳት መጻሕፍት በሰፊው ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ (ኢሳ፫÷፱፣ኤር፶÷፵፣ ሰቆ ኤር ፬÷፮፣ ሕዝ ፲÷፵፱፣ አሞ ፬÷፲፩፣ ማቴ ፲÷፲፭፣ ፪ ጴጥ ፪÷፮) በመሆኑም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ማንኛውም በጾታ ተፈጥሯዊ ስጦታ ላይ የሚሠራ ኃጢአት ሕገ ተፈጥሮን የሚጻረር ጽኑዕ በደል እንደሆነ ታስተምራለች። የያዕቆብ ወንድም ይሁዳም “እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ የተከተሉ ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩ ከተማዎች በዘላለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል” በማለት ይህ ተግባር የተወገዘና በዘላለም እሳት የሚያስቀጣ መሆኑን አስረግጦ ይናገራል።

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ግብረ ሰዶማዊነትን የምትቃወመው ተፈጥሮዋዊ ስላልሆነ ብቻ ሳይሆን በብሉይ ኪዳንም ሆነ በሐዲስ ኪዳን ትምህርት በእግዚአብሔር ዘንድ የረከሰ፣ ተቀባይነት የሌለው፣ ኃጢአት በመሆኑ ነው፡

ጌታችንም ሲያሰተምር “ፈጣሪ በመጀመሪያ ወንድና ሴት አደረጋቸው" በማለት ጾታ የፈጣሪ ሥጦታ መሆኑን እና ይህንም መጠበቅ ግዴታ እንደሆነ ያስረዳል። (ማቴ፲፱÷፲፭) ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ግብረ ሰዶማዊነት አጸያፊ ድርጊት መሆኑን “እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባው ለወጡ እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ ወንዶችም በወንዶች ነውር አድርገው በስሕተታቸው የሚገባውን ብድራት በራሳቸው ተቀበሉ የሚገባውን እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው"በማለት ገልጾታል፡፡

ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ጾታዊ ግንኙነት ወይም የተቀደሰ ጋብቻ በተቃራኒ ጾታዎች ብቻ የሚፈጾም እንዲሆን የምታስተምረው ከዚህ የተነሣ ነው። (፩ ቆሮ ፯፡፪፣ ፩ ጢሞ ፩፡፱)ግብረ ሰዶማዊነት የሰውን ልጅ ተፈጥሯዊ ማንነት የሚንድ፣ መሠረተ እምነትንና ቀኖናን የሚሽር፣ ማኅበራዊ ዕሴት የሚያጠፋ፣ ከሥነ ምግባር መገለጫዎች በአሉታዊ ገጽ የቆመ፣ ሕሊናን የሚያውክ ለትውልድ ጥፋት፣ ለሀገር መውደም ምክንያት የሆነ አጸያፊ ተግባር ነው፡፡

በመሆኑም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይህን ተግባር የሚፈጽሙ ሰዎች ወደ ንሥሓና ድኅነት እንዲመጡ፣ ከሥጋና ከመንፈስ ስብራት እንዲፈወሱ ዘወትር ጥሪ ታደርጋለች እንጅ ማንም ሰው የኃጢአቱ ወይም የርኩሰቱ ተባባሪ እንዲሆን አትፈቅድም።

በ፲፱፻፺፮ በወጣው የሀገራችን የወንጀል ሕግ ክፍል፪ አንቀጽ ፮፻፳፱ ጠቅላላ ድንጋጌ “ግብረ ሰዶምና ለንጽሕና ክብር ተቃራኒ የሆኑ ሌሎች ድርጊቶች፤ በሚለው ንዑስ አንቀጽ ርእስ ሥር ይህ ድርጊት ወንጀል ስለሆነ በትክክል የሚያስቀጣ መሆኑን አስቀምጧል። በተለይ አንቀጽ ፮፻፴፩ ዕድሜያቸው ፲፰ ዓመት ያልሞላቸው ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች ላይ ለሚፈጸም ግብረ ሰዶማዊነት ከ፭ እስከ ፳፭ ዓመታት የሚያስቀጣ መሆኑ በግልጽ ተጽፏል።በተሻሻለውም የሀገራችን የቤተሰብ ሕግ በአንቀጽ 13 መሠረት የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ በሕግ የተከለከለ መሆኑ ተደንግጓል፡፡

ይሁን እንጅ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይህን ተግባር በግልጥ በሕገ መንግሥታቸውና በልዩ ልዩ ማኅበራዊ ድንጋጌዎቻቸው እንደ ጥሩ ነገርእንደ ፍትሐዊነትና አካታችነት በመቁጠር በይፋ የደነገጉ የምዕራቡ ዓለም ሀገራት መኖራቸው ግልጽነው።

እነዚሁ ሀገራት ያላቸውን የፖለቲካና የኢኮኖሚ አቅም መከታ በማድረግ በእምነታቸው፣ በባሕላቸው በማኀበራዊ መገለጫቸው ይህን አጸያፊ ድርጊት ፈጽመው በማይቀበሉ የአፍሪካና የምሥራቁ ዓለም ሀገራት ላይ ቢቻል በማግባባት፣ ካልሆነም የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጫና በማሳደር እንዲቀበሉ የጥፋት ልማዳቸውን እንዲጋሩ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉትን ድብቅና ግልጽ እንቅስቃሴዎች ቋሚ ሲኖዶስ በጽኑ ይቃወማል፡፡

ይህ ግብረ ርኩሰት በዘመናችን ተቀባይነት እንዲኖረው፣ የሚደረጉ ሁለገብ ማግባባቶች፣ ተጽዕኖዎችና ተያያዥነት ያላቸው ስምምነቶች በሀገራችን መንግሥት ተቀባይነት አግኝተው እንዳይፈጸሙ ቋሚ ሲኖዶስ በጥብቅ ያሳስባል።

ከመገናኛ ብዙኃንና ከሌሎችም የመረጃ ምንጮች ለማወቅ እንደተቻለው ግብረ ሰዶማዊነትንና ተያያዥነት ያላቸውን ተግባራት የንግድ፣ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የፍትሕና የሰብዓዊነት ግንኙነቶች አካል በማድረግ በቃላትና በዓረፍተ ነገሮች ውስጥ አስርጎ በማስገባት አሣሪ ስምምነቶች እንዲፈጸሙ ለማድረግ ያለው ሃደት በአፋጣኝ እንዲፈተሽ የሀገራችን መንግሥት ብሎም የአፍሪካ መንግሥታት የአህጉራችንን ሃይማኖታዊ ማኅበራዊና ሥነ ልቦናዊ ዕሴቶች አስጠብቀው እንዲቀጥሉ ቋሚ ሲኖዶስ ጥብቅ የሆነ የአደራ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

በስምምነቱ ሰነድ ጤናማ መስለው የሠረፁ ዐረፍተ ነገሮች ውስጥ እንደታየው በጾታና ሥርዓተ ጾታ መብት፣ የሥርዓተ ጾታ ትምህርት ጋር በማያያዝ ጾታን በቀዶ ጥገና የመቀየር ውርጃ፣ልቅ የሆነ የተመሳሳይና ተቃራኒ ጾታ ግንኙነትን መፍቀድ፣ ግለሰቦችን እና ማኅበረሰብን መረን በማድረግ ውስብስብ ለሆኑ ሃይማኖታዊ፣ ማኅበራዊና ባህላዊ ችግሮች የሚዳርጉ መሆናቸውን ቅዱስ ሲኖዶስያምናል።

በመሆኑም በብዙ መስዋዕትነት ተጠብቆ የቆየው እምነት፣የባህልና የሥነ ምግባር ማኅበራዊ ዕሴት የክብር ስፍራውን ይዞ እንዲቀጥልና በእጅ አዙር ቅኝ ግዛት
ኃጢአትንና ርኩሰትን አባብሎ በማስረጽ፣ለዚህ አጸያፊ ድርጊት ትውልዱ እንዳይጋለጥ የሚመለከተው ሁሉ በልዩ ጥንቃቄ እንዲመለከተው ቋሚ ሲኖዶስ ጥሪውን ያስተላልፋል።

ግብረ ሰዶማዊነት በማንኛውም የቃላት አግባብ ተገልጦ በጾታ መብት መካተት የማይችል የመደበኛ ተፈጥሯዋዊ ክስተት ጋር በጭራሽ አቻ የማይሆን በመሆኑና ተግባሩንም
መቃወም ቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ ተልእኮዋ ስለሆነ ይህን አስመልክተው የሚደረጉ ስምምነቶች የሀገራችንን ሃይማኖታዊ፣ ማኅበራዊና ሥነ ልቦናዊ ዕሴት የሚጥሱ መሆኑ ታውቆ ሁሉም ዜጎች እንዲቃወሙት፣ የፈዴራል መንግሥትም ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እንዲከታተለው ቋሚ ሲኖዶስ በጥብቅ ያሳስባል፡፡

ግብረ ሰዶምን እና ተያያዥ የጾታ ሥርዓትን የሚበርዙ፣ ጾታን መቀየር፣ ሁለት ዓይነት ጾታን መጠቀምና የመሳሰሉት ተግባራት በሙሉ ሀገራችን በሃይማኖት፣ በሕግ፣ በማኅበራዊ ዕሴቶቿ፣ በሥነ ምግባር መመሪያዎቿ የማትቀበላቸው ጉዳዮችና ልምምዶች ስለሆኑ በማናቸውም ይፋዊ ግንኙነቶች እንደማንቀበላቸው በግልጽ እንዲቀመጡ ቋሚ ሲኖዶስ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

ግልጽ የሆኑ ግብረ ሰዶማዊነትን የሚያበረታቱ፣
የሚያዛምቱ፣ ድብቅና እንቅስቃሴዎች የሚያደርጉ አካላት ከድርጊቸው እንዲቆጠቡ፣ በንሥሓ እንዲመለሱ ቅድስት ቤተክርስቲያን በጥብቅ ታሳስባለች።

ለወደፊቱም ማናቸውም የሥርዓተ ትምህርት መማሪያ ሲዘጋጅ፣ ሀገር በቀል ደንቦችና መመሪያዎች ሲወጡ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ስምምነቶች ሲፈጸሙ በሀገሪቱ ያሉ የእምነትና የባህል፣ ዕሴቶችን፣ የሕግ ማዕቀፎችንና የሥነ ምግባር መርሆችን ተጠብቀው እንዲፈጸሙ፣ መላው ሕዝባችንም የእምነት መሠረቱን፣የቀኖና ሥርዓቱን፣ ማኅበራዊ ዕሴቱን ጠብቆ እንዲኖር፣ ሀገራችን ሰላም እንድትሆን ሁላችንም ከወትሮው በተለየ ሁኔታ በጸሎት እንድንተጋ ቋሚ ሲኖዶስ መንፈሳዊ ጥሪውን ያስተላልፋል።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ
የካቲት ፬ ቀን ፳፻፲ወ፮ ዓ/ም
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮችን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።
++++++++++++++++++++++++++++++

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዛሬ የካቲት 5/2016 ዓ.ም ከማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች ጋር በወቅታዊ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሁኔታና ቀጣይ የቤት ሥራዎች ላይ ተወያይተዋል።

በውይይቱ የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉኀን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ሥዩም፣ የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ መምህር ዋሲሁን በላይን ጨምሮ የሥራ አመራር ጉባኤ አባላት ተገኝተዋል።
አደራ አለብኝ!

የ 2016 ዓ.ም 2ኛ ዙር ጉባኤ

ዓለም ዓቀፍ የግቢ ጉባኤ ምሩቃን ኅብረት ጉባኤ

• ቀን፡ መጋቢት 08/2016 ዓ.ም
• ሰዓት፡ ከ 7፡00 ጀምሮ
• ቦታ፡ በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ
2024/09/29 20:31:46
Back to Top
HTML Embed Code: