Telegram Web Link
ማኅበረ ቅዱሳን በደቡብ ወሎ ገራዶና ጃሪ መጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረገ
+++

በሀገራችን ኢትዮጵያ እያጋጠመ ባለው ልዩ ልዩ ማኅበራዊ ቀውስ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንና ኦርቶዶክሳዊያን ጨምሮ የሀገራችን ሕዝቦችን ለከፍተኛ ማኅበራዊ ቀውስ ተጋላጭ መሆናቸው ይታወቃል።

ማኅበረ ቅዱሳን እነዚህን ችግሮች በስፋት በማጥናት ላለፉት 5 ዓመታት በሙያና ማኅበራዊ አገልግሎት ማስተባበሪያው በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች እያጋጠሙ ያሉ ማኅበራዊ ቀውስና ሃይማኖት ተኮር ጥቃቶችን መረጃ በማደራጀት ፕሮጀክቶችን በመንደፍ ድጋፍ አድራጊ ምእመናንና ተቋማትን እያስተባበረ የአልባሳት፣የምግብ እና መሠል አስቸኳይ ድጋፎችን በስፋት ሲያደርግ ቆይቷል። አሁንም አጠናክሮ ቀጥሏል።

በአሁኑ ወቅትም ባለፉት ዓመታት ከወለጋ ተፈናቅለው የተሰደዱ በደቡብ ወሎ ገራዶ፣ ሐይቅ እስጢፋኖስና አካባቢው በጠቅላላው 5,913 ተፈናቃዮች ይገኛሉ። ማኅበረ ቅዱሳን ከእነዚህ መጠለያ ጣቢያዎች መካከል በሦስቱ ለሚገኙ ተፈናቃዮች በቦታው በመገኘት 362,000 ብር በላይ የፈጀ አስቸኳይ ማኅበራዊ ድጋፍ አድርጓል። ድጋፉ ከሜሪላንድ ኆኅተ ምሥራቅ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የተከናወነ ነው።

በተመሳሳይ መረጃ በቅርብ ጊዜያት ብቻ በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅና ጃን አሞራ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች፣ በሰቆጣና አካባቢው ለሚገኙ ተፈናቃዮች፣ በደቡብ ኦሞ በናጸማይ ወረዳ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች፣ በሃይማኖት ተኮር ጥቃት ለተጎዱ የቅበት ኦርቶዶክሳዊያን፣ በደብረ ብርሃን ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ተመሳሳይ ድጋፎች ተደርገዋል።
ማኅበረ ቅዱሳን በቀጣይ ጊዜያትም በድርቅ ለተጎዱ እንዲሁም በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች ተጨማሪ ድጋፎችን ለማድረስ “አለሁ ለወገኔ” በሚል ሰፊ የድጋፍ ማሰባሰብ ዘመቻ እያደረገ ይገኛል። ስለሆነም የከበረችን ሕይዎት ለማዳን በሚደረገው የሰብአዊነት ሥራ ምእመናን፣ማኅበራት፣ ልዩ ልዩ ተቋማትና በጎ አድራጊ ድርጅቶች የተለመደ ድጋፍ እንድታደርጉልን ሲል ጥሪውን ያቀርባል።

ድጋፍ ለማድረግም፡- በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡-

1. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000309803648
2. በአሐዱ ባንክ - 0025393810901
4. በወጋገን ባንክ - 0837331610101
5. በአቢሲንያ ባንክ - 37235458
6. በአዋሽ ባንክ 01329817420400 መጠቀም የምትሉ መሆኑን እንገልጻለን። 7. በወገን ፈንድ፡- https://www.wegenfund.com/causes/nu-badereqe-yatagodu-waganocaacenene-hheyete-eneta/

ለበለጠ መረጃ
• 09 43 00 04 03
• 09 1 1 38 27 53
ማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ 1ኛ ወለል
የማኅበረ ቅዱሳን ሙያና ማኅበራዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ
#የመጽሔት ዳሰሳ

ርእሰ፦ሐመር መጽሔት ፴፩ኛ ዓመት ቁጥር ፩
 የኅትመት ዘመን ፦ ጥር ፳፻፲፮ ዓ.ም
አዘጋጅ ፦በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኀበረ ቅዱሳን በልማት ተቋማት አስተዳደር በመጽሔት ዝግጅት ክፍል የሚዘጋጅ ትምህርታዊ መጽሔት
• ገጽ ብዛት፦፳፰
ዋጋ ፦፵ ብር
ሐመር መጽሔት በማኀበረ ቅዱሳን በ1985 ዓ.ም በወርኃ ጥር የተጀመረች ታሪካዊ መጽሔት ናት፡፡ሐመር መጽሔት ለብዙዎች በተለይም ገጠር ተኮር የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ለሚሰጡ ሰባክያነ ወንጌል መምህራቸው ናት፡፡
• ሐመር መጽሔት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት ሥርዓትና ትወፊት ጠብቃ በልማት ተቋማት አስተዳደር በመጽሔት ዝግጅት ክፍል በየወሩ የምትወጣ መንፈሳዊ መጽሔት ናት፡፡
• ሐመር መጽሔት ፴፩ኛ ዓመት ቁጥር ፩ ጥር ፳፻፲፮ ዓ.ም በመልዕክት ዐምድ" #የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዓላት የድኅነት #መንገዶች ናቸው !. በማለት የጥምቀተ ባሕር ቦታዎችን በግዴለሽነት አሳልፎ ለሌላ ጉዳይ ማዋለም ከሃይማኖታዊ ግዴለሽነቱ ይልቅ ብሔራዊ ቅርስና ታሪክ ማጥፋት ይሆናል፡፡ ይህን የሚያደርጉትን አካላት ከሾማቸው መንግሥትም ሆነ ከሚገለገለው ሕዝብ ተጠያቂነት እንዳላባቸው አውቀው ከጥፋታቸው ሊታረሙ እንደሚገባ ያሳያል፡፡
*.ዐውደ ስብከት ሥር” #ኢያድለወ ሞተ ክርስቶስ ለሥጋ አባሉ” በሚል ርእስ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ ጥር ፳፩ አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለከበረች ለድንግል ማርያም #የዕረፍቷ በዓል መታሰቢያ ታላቅ በዓልን እንደምታከብር ይዳስሳል፡፡
• በትምህርተ ሃይማኖት ዐምድ ሥር “#ቅዱሱ አቡነ ሰላማ የማያውቁት “#የሰላማ መንበር “ክፍል ፪ በሚል ዐቢይ ርእስ“መንበረ ሰላማ” የሚለው ሕገ ወጥ ስያሜ በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ትውፊትም ሆነ በቀደምት አብያተ ክርስቲያናት ትውፊት የማይታወቅ፣ ሃይማኖታዊ መሠረት የሌለው፣ ከቀኖና የወጣ፣ አስተዳደራዊ መዋቅርን የሚያዛባ በመሆኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አትቀበለውም፤በተጨማሪም ከአንዲት፣ ቅድስት፣ ሐዋርያዊትና ዓለም አቀፋዊት የሆነች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ መንበር መሠረተ እምነት፣ታሪክና ቀኖና፣ ከአስተዳደር እና ሕግ ባፈነገጠ ሁኔታ ትውፊትን በመዳፈር ጎሣን መሠረት አድርጎ የተፈጠረ ሕገ ወጥ አደረጃጀት በመሆኑ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አ እንዳወገዘው በማስረጃ ይሞግታል፡፡
• ዐቢይ ጉዳይ ዐምድ ሥር ደግሞ “#የቤተ ክርስቲያናችን #ወቅታዊ ፈተናዎች “ በሚል ርእስ ለሕገ ወጦች ከለላ እየሆኑ ያሉትንና በሁለት ቢላዋ የሚበሉትን ለሰውም ለእግዚአብሔርም የማይታመኑትን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን በቊስሏ ላይ እንጨት የሚሰዱትን በሰው ኃይል አስተደዳር መመረያው መሠረት አስተዳደራዊ ርምጃ መወሰድ እንዳለበት ይጠቁማል፡፡
• ክርስትና በማኀበራዊ ዐምድ ሥር ደግሞ “#መረዳዳት አብሮ ለማደግ “በማለትእንደ ሀገርም ሆነ እንደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዛሬ ዛሬ ያለው ማኅበራዊ፣ ምጣኔ ሀብታዊ፣ ሥነ ልቡናዊ፣ ባህላዊ ወዘተ. ቀውስ አሁን እየተተገበረ ባለው ጊዜያዊ እና ደራሽ ተግባር ዘላቂ የሆነ መፍትሔ ማምጣት አይቻልም። ስለዚህ ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት ነገን ተረካቢ የሆኑ ሕፃናት ላይ መሥራት፣ በምጣኔ ሀብት ዕድገት ማምጣት የሚቻልባቸው ተግባራት ላይ መረዳዳት፣ እንደሚገባ ይሳያል፡፡
• በእናስተዋውቃችሁ ዐምድ ሥር “ #ገድለ ቅዱስ ዞሲማስ ብሔረ ብፁዓንን የሚያስጎበኝ መጽሐፍ (ክፍል ፫) የቅዱሱን ተጋድሎ በዐይነ ሕሊና እንጎበኛለን፡፡ብሔረ ብፁዓን በአባ ዞሲማስ ትምህርትና መረጃዎች እናገኛለን፡፡
• በነገዋ ቤተ ክርስቲያን ዐምድ ሥር “#ለነገዋ ቤተ ክርስቲያን ተረካቢ እናዘጋጅላት “ በሚል ለልጆች ሁለንተናዊ ዕድገት ባለድርሻ አካላት የሚሆኑት ወላጆች፣ ጎረቤት፣ ማኅበረሰብ፣ ትምህርት ቤት ወዘተ. የሚኖራቸውን ሚና ያስነብባል፡፡
• በኪነ ጥበብ ዐምድ “ #ሕይወት “ ክፍል ፫ በሚል ርእስ ሃይማኖትን መቀየር እንዲሁ ቀላል እንዳልሆነ ይዳስሳል፡፡(ገጽ _፳፫)
• የጥያቄዎቻችሁ መልስ ዐምድ “#ምሥጢረ ሥጋዌ”ክፍል ፪ በምሥጢረ ሥጋዊና ተያያዥ ጉዳች የመጻሕፍተ ሐዲሳት መምህር ከሆኑት መምህር ኃይለ ማርያም ዘውዱ ዘቦሩሜዳ የወሎ ዪኒቨርስቲ የልሳነ ግእዝ መምህር እና በባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ የሁለተኛ ድግሪ ተማሪ ጋር መሠረታዊ ትምህርት ይሰጣል፡፡
ስለዚህ ማዕከላት፣የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት ሐመር መጽሔት ፴፩ኛ ዓመት ቁጥር ፩
ዕትም ለአንባቢያን እንድትደርስ የድርሻችሁን እንደትወጡ ምክንያቱም ሐመር መጽሔት ትምህርተ ወንጌል ለመላው ዓለም ለማዳረስ አንዱ መሣረያ ናት፡፡
አስተያየት ለመስጠት
magazine @eotcmk.org ወይም በ0111540484/0944259014 ያግኙን

 ሐመር መጽሔት ፴፩ኛ ዓመት ቁጥር ፩ ታትማ ሥርጭት ላይ ስለምትገኝ በማሰራጨት ፡በማንበብና በማስነበብ ዘመኑነም በመዋጀት የድርሻችን እንወጣ ይላል #ማኀበረ ቅዱሳን!
የዳውሮ ሀ/ስብከት አዳሪ የአብነት ት/ቤት ተመረቀ።

በማኅበረ ቅዱሳን አስተባባሪነት በዳውሮ ሀ/ስብከት በምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም የተገነባው አዳሪ የአብነት ት/ቤት ጥር 23 ቀን 2016 ዓ.ም የዳውሮና ኮንታ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ፣ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የአካባቢው ምእመናን በተገኙበት ተመርቋል።

ማኅበረ ቅዱሳን የአብነት ት/ቤት ባልተስፋፋባቸውና የአገልጋይ ካህናትና ዲያቆናት እጥረት ባለባቸው  በደቡብ፣በምእራብና በምሥራቅ በሚገኙ አህጉረ ስብከት አብነት ትምህርትን ለማስፋፋት እየሠራ የሚገኝ ሲሆን ይህ የአብነት ት/ቤት ኘሮጀክት አንዱ ነው።

  በማኅበረ ቅዱሳን አውሮፓ ማእከል አስተባባሪነት በአውሮፓ በተለያዩ ሀገራት በሚገኙ ምእመናን የገንዘብ ድጋፍ የተገነባው የአዳሪ አብነት ት/ቤት  40 ተማሪዎችን በአዳሪነት ፣ 100 ተማሪዎችን በተመላላሽነት ተቀብሎ ማስተማር የሚችል ሲሆን ለት/ቤቱ የሚያስፈልጉ የተለያዩ ቁሳቁሶች የተሟሉለት መሆኑንና ለግንባታውም ከ 3.8 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ መደረጉ ተገልጿል።

በምርቃቱ መርሐግብር ላይ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ መልእክታቸውን ያስተላለፉ ሲሆን የአብነት ት/ቤቱ  መገንባት በአገልጋይ እጥረት ምክንያት በሀ/ስብከቱ የተዘጉ አብያተ ክርስቲያትን ለማስከፈትና የሚታየውን የአገልጋዮች እጥረት በዘላቂነት ለመፍታት አስተዋጽኦው ከፍተኛ መሆኑን በመግለጽ  ከሁሉም ወረዳዎች  ተማሪዎች ተመርጠው እንደሚገቡ በመግለጽ ለኘሮጀክቱ መሳካት ድጋፍ ላደረጉ ምእመናን ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በተያያዘ ዜና ለሀ/ስብከቱ መንበረ ጵጵስና በታርጫ ከተማ አስተዳደር በተሰጠው ቦታ ላይ ብፁዕነታቸው የመንበረ ጵጵስና ግንባታ የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ አገር እንዳይገቡ ተከለከሉ

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በአሜሪካ የነበራቸውን ሐዋርያዊ አገልግሎት ጨርሰው ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ እንዳይገቡ መከልከላቸው ተሰምቷል።

ብፁዕነታቸው ከሳምንታት በፊት በቋሚ ሲኖዶስ እውቅና ወደ ሀገረ ስብከታቸው በመሄድ የአጋእዝተ ዓለም ሥላሴ ዓመታዊ በዓል፣ የከተራና የጥምቀት በዓላትን ከመንፈስ ልጆቻቸው ጋር ያከበሩ ሲሆን ለአዳጊ ሕጻናትም ማዕረገ ዲቁና መስጠታቸው ይታወቃል።

ብፁዕነታቸው በአሁኑ ሰዓት ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያው እንደሚገኙ ታውቋል።
ማኅበረ ቅዱሳን ( Mahibere Kidusan)
Photo
ብፁዕነታቸው ወደ አሜሪካ እንደተመለሱ ተሰምቷል።

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ወደ ሀገር እንዳይገቡ በመከልከላቸው ወደ አሜሪካ ለመመለስ መገደዳቸውን አሳውቀዋል።

ብፁዕነታቸው ከደቂቃዎች በፊት ለማሕበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት ቃል ፤ " አሁን አሳፍረውኝ ተመለስኩ፤ ወደ አሜሪካ ወደመጣሁበት መለሱኝ ፤ ወደ ስራዬ እንዳልመለስ ከለከሉኝ። " ብለዋል።

ለቴሌቪዥን ጣቢያው ቃላቸውን በሰጡበት ወቅት አውሮፕላኑ ሊነሳ እንደነበር ለማወቅ የተቻለ ሲሆን ወደ አሜሪካ እንዲመለሱ የሚደረግበት ምክንያት ምንድነው ? ተብለው ተጠይቀው ፤ ብፅዕነታቸው ፤ " በቃ ግሪን ካርዱን ብቻ ነው የምንፈልገው እኛ ያንተን ፓስፖርት አንፈልግም ግሪንካርድ ብቻ ነው የምንፈልገው ብለው ወሰዱ በሩን ዘጉ !! " ሲሉ ተናግረዋል።

ይህን ያደረጉት የደህንነት ሰዎች ናቸው ብለዋል።

ብፅዕነታቸው ወደ አውሮፕላን እንዲገቡ ከመደረጋቸው በፊት ውጭ ላይ ሲጉላሉ እንደነበር ተናግረው አንድ የኢሚግሬሽን ሰው " የማውቀው ነገር የለም ግሪንካርዱ ትክክል አይደለም " እንዳላቸውና እሳቸውን ግሪንካርዱ ገና 3 ዓመት እንደሚቀረው እንደነገሩት አስረድተዋል።

ይህን ሲያስረዱ ከግለሰቡ መልስ እንዳልተሰጣቸውና " ሌሎች ሰዎችንም #ዲፖርት እያደረግን ነው " በማለት እንደነገራቸው ገልጸዋል።

ብፅዕነታቸው የአሜሪካ ፓስፖርት እንዳላቸው ገልጸው ፤ " እሱን ምንም ለማድረግ ስላልቻሉ ግሪንካርድ እንወስዳለን በማለት ወስደዋል " ሲሉ ተናግረዋል።

ከሳምንታት በፊት ለአገልግሎት ከሀገር ሲወጡ ብፁዕ አቡነ አብርሃምን ጨምሮ ሌሎችም " ሊያስቀሩህ ይችላሉ " የሚል ነገር ሰምተው እንደነገሯቸው ነገር ግን በአሜሪካ የያዙትን አገልግሎት መተው ስላልፈለጉ ወደ አሜሪካ መሄዳቸውን ገልጸዋል።

ብፅዕነታቸው ወደ አሜሪካ በሄዱበት ወቅት " ኮበለሉ " የሚሉ መረጃዎች ተሰራጭተው እንደነበር ይታወሳል። በኃላም ቤተክርስቲያኗ በሰጠችው መግለጫ ፤ በህጋዊ መንገድ በቤተክርስቲያን እውቅና ከሀገር እንደወጡ ፤ የሚደበቁም ሆነ የሚኮበልሉ የወንጀል ሰው እንዳልሆኑ አሳውቃ ነበር።
2024/09/29 22:19:23
Back to Top
HTML Embed Code: