Telegram Web Link
የፍኖተ ትጉሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ለ8ኛ ዙር ያስተማራቸውን 32 ተተኪ ሰባኪያነ ወንጌል ማስመረቁን አስታወቀ

ነሐሴ ፲፭/፳፻፲፯ ዓ.ም

የላፍቶ ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የፍኖተ ትጉሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ከደብሩ ሰበካ ጉባኤና ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር በመተባበር ከደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት የተውጣጡ 32 ተተኪ ሰባኪያነ ወንጌል በማስተማር ነሐሴ13 ቀን 2017 ዓ.ም ማስመረቁን አስታውቋል።

በምርቃት መርሐ ግብሩ መልአከ ፀሐይ ተስፋ ማርያም ነጋሽ የላፍቶ ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ፣ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶክተር ሙሉጌታ ስዩም የማኅበረ ቅዱሳን ሥራ አመራር ጉባኤ አባል፣ ርእሰ ደብር ተስፋ ደጀኔ የደብሩ የስብከተ ወንጌል ኃላፊ፣ አቶ የኋላሸት ሽፈራው የደብሩ የሰበካ ጉባኤ ምክትል ሊቀ መንበር፣ የማኅበረ ቅዱሳን ተወካዮች፣ የሰንበት ትምህርት ቤቱ ተወካዮች፣ ካህናትና ምእመናን ተገኝተዋል።

የፍኖተ ትጉሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ዋና ጸሐፊ ዲያቆን ዳንኤል ደሳለኝ ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ የማኅበረ ቅዱሳንን ጥናት መነሻ በማድረግ አገልግሎቱን ጀምረው እያከናወኑ መሆኑን በመግለጽ አጠቃላይ የተሠሩ ሥራዎችን ሪፖርት አድርገዋል።

ዲያቆን ዳንኤል ደሳለኝ አክለውም በዘንድሮው ዓመትም ለ8ኛ ዙር ያሠለጠኗቸውን ተመራቂ ደቀ መዛሙርት እንኳን ደስ አላችሁ በማለት መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን አያይዘውም ሠልጣኞች ወደ አካባቢያቸው ሲመለሱ በተማሩት ትምህርት ወንጌል ባልተዳረሰባቸው አካባቢዎች በቋንቋቸው እንዲያስተምሩና የእግዚአብሔርን ልጅነት እንዲያገኙ ለማድረግ በኃላፊነት እንዲያገለግሉ አደራ ብለዋል።

አያይዘውም ዋና ጸሐፊው በሥልጠናው ለተሳተፉ ባለድርሻ ፣ አጋር አካላትና ምእመናንን አመስግነዋል።
10
ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶክተር ሙሉጌታ ስዩም የማኅበረ ቅዱሳን ሥራ አመራር ጉባኤ አባል ማኅበሩ ያከናወናቸውን ተግባራት ሪፖርት በማቅረብ በሁለቱ ዞኖች የተወጣጡና በሰባት ማለትም በአራፍ፣ በዳሰነች፣ በበንኛ፣ በማሌኛ፣ በዲሜኛ፣ በኮንሶኛና በሐመርኛ ቋንቋዎች ለሐዋርያዊ ተልእኮ መሠማራት የሚችሉ 32 ተመራቂ ሰባኪያነ ወንጌልን የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

ሊቀ ትጉሃን አክለውም ሠልጣኞች በቋንቋቸው አካባቢያቸውንና ምእመናንን እንዲያገለግሉ ያሳሰቡ ሲሆን ለዚህ ሥልጠና መሳካት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላደረጉም ምስጋናን ችረዋል።

የላፍቶ ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ ፀሐይ ተስፋ ማርያም ነጋሽ በበኩላቸው በጠረፋማውና በገጠራማው አካባቢ የስብከተ ወንጌልን አገልግሎት እንዲስፋፋ ለማድረግና የቤተ ክርስቲያኗን ተልእኮ ከግብ ለማድረስ እየተሠራ ያለው ተግባር የሚበረታታ ነው ያሉ ሲሆን ይህም ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ገልጸዋል።

በመጨረሻም የደብሩ አስተዳዳሪ ደቀ መዛሙርቱ የተማሩትን ትምህርት ወደ ተግባር እንዲቀይሩ ያሳሰቡ ሲሆን ይህን አገልግሎት ለመደገፍ የእምነቱ ተከታይ የሆነ በሙሉ ማኅበራት፣ ገዳማትና አድባራት እንዲሁም ምእመናን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ መወጣት እንዲችሉ አሳስበዋል።
15🙏1
በአሜሪካ ምእከል የቦስተን ንዑስ ማእከል የደብረ ታቦርን በዓል ከምእመናን ጋር አከበረ።

የቦስተን ንዑስ ማእከል በየዓመቱ እንደሚያደረ‍ገው ደብረታቦር በዋለበት ዕለት ማክሰኞ ነሐሴ ፩፫ ቀን ፳፩፯ ከምእመናን ጋር በዳኒ መናፈሻ (ፓርክ) አከበረ። ሕጻናት የሆያ ሆየ መዝሙር ያቀረቡ ሲሆን፣ እናቶች ያዘጋጁትን ሙልሙል ለሕጻናት እንዲሁም ለአዋቂዎች አድለዋል። እለቱን የተመለከተ ሥነ፡ፅሁፍ ፣ወረብ እና ዝማሬም ቀርቧል ።
21👍5
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በማኅበረ ቅዱሳን የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ማስተባበሪያ አገልግሎቱን በማጠናከር በግቢ ጉባኤያት ላይ ውጤታማ ሥራ ለመሥራትና ብቁ አገልጋዮችን ለማፍራት ልዩ ልዩ ፕሮጀክቶችን ቀርጾ በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡
ፕሮጀክቶቹን ለማስፈጸም ይረዳው ዘንድ ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ትኬት ሽያጭ ከሐምሌ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በማሠራጨት ላይ ይገኛል፡፡
እርስዎም ትኬቱን በመግዛት ትውልድን ለመቅረጽ በሚደረገው ጥረት ውስጥ አሻራዎን ያኑሩ፡፡
13
Forwarded from Elohe pictures
🌟 🩸🩸🩸🩸🩸🩸🩸🩸🩸🫵🩸🩸

🤍🤍🤍🤍🤍


መስቀል ሃይላችን ነው ✝️


🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍

🅲🅻🅸🅲🅺 🅷🅴🆁🅴
ይህን ይጫኑት
🔝🔝

🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍
♡ ㅤ  ⎙ㅤ    ⌲        ✉️   
Lᶦᵏᵉ   ˢᵃᵛᵉ  ˢʰᵃʳᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
ቶሎ ቶሎ እንድንለቅ ሪያክሽን እንዳይረሳ 👍
     ⚡️ꌗꃅꍏꋪꍟ ꌩꂦꀎꋪ ꎇꋪꀤꍟꈤꀸ ▶️
🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸
ይቀላቀሉን
https://www.tg-me.com/+Ci5F1FcleWtlZThk
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
8
2025/09/27 01:09:48
Back to Top
HTML Embed Code: