ማኅበረ ቅዱሳን ከስልጤ ዞን ቅበት ከተማ ተፈናቅለው በቡታጅራ ለሚገኙ ተጎጅዎች አስቸኳይ ድጋፍ አደረገ
+++
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በኦርቶዶክሳዊያን ላይ እየተካሄዱ ያሉ ሃይማኖት ተኮር ጥቃቶች አድማሳቸውን እያሰፉ በመላ ሀገሪቱ ቦታና ጊዜ እየቀያሩ ይፈጸማሉ። ከእነዚህ ውስጥ አንዱ ስልጤ ዞን ነው። በዚህ ዞን ከዓመት በፊት 5 አብያተ ክርስቲያናት ልዩ ልዩ ዓይነት ቃጠሎ፣ ውድመትና ምዝበራ ደርሶባቸዋል። በዚህ ያላበቃው ጥቃት ባለፈው ነሐሴ 29 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በስልጤ ዞን ቅበት ከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚገኙ ኦርቶዶክሳዊያን ላይ የከፋ ውድመት እንዲያደርስ ሁኖ ተመልክተናል።
በዚህ ችግር ንብረታቸው የወደመ፣ ቤትና የሥራ ቦታቸው የተቃጠለባቸው ከ1520 በላይ የሚሆኑ ኦርቶዶክሳዊያን ነፍሳቸው ለማትረፍ ተሰደው በቡታጅራ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያ አጸድ ከተጠለሉ ከአንድ ወር በላይ አስቆጥረዋል።
ማኅበረ ቅዱሳን እነዚህንና ሌሎች መሰል ማኅበራዊ ቀውስና ሃይማኖት ተኮር ጥቃት ወለድ ችግሮች በስፋት በማጥናት ላለፉት 4 በኩል በአርሲ፣ በሐረር ፣ በባሌ፣ በወሊሶ፣ በሻሸመኔ፣ በመተከል፣ በቤንሻጉል ጉምዝ፣ በቦረና፣ በትግራይ እና በአማራ ክልል እንዲሁም በሌሎች የሀገራችን ክፍል ያጋጠሙ ማኅበራዊ ቀውስና ሃይማኖታዊ ጥቃቶችን መረጃ በማደራጀት ፕሮጀክቶችን በመንደፍ ድጋፍ አድራጊ ምእመናንና በጎ አድራጊ ተቋማትን እያስተባበረ የአልባሳት፣የምግብ እና መሠል አስቸኳይ ድጋፎችን በስፋት ሲያደርግ ቆይቷል። አሁንም አጠናክሮ ቀጥሏል።
ለእነዚህ ከስልጤ ዞን ቅበት ከተማ አስተዳደር ተፈናቅለው በቡታጅራ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ጊዜያዊ መጠለያ ለሚገኙ ተፈናቃዮችም ጥቅምት 03 ቀን 2016 ዓ.ም በቦታው በመገኘት የአስቸኳይ ምግብ ግብዓቶችና አልባሳት ድጋፍ አድርጓል።

👍22
ለድጋፉም 519,000 (አምስት መቶ አሰራ ዘጠኝ ሺህ) ብር ወጭ ተደርጓል።
በድጋፉም ርክክብ ወቅትም የማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል ልዑካን፣ የቡታጅራ ወረዳ ማእከል ተወካዮችና ተፈናቃዮች ያረፉበት የቡታጅራ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም አስተዳዳሪ ቆሞስ አባ ገብረ ኢየሱስ በቦታው ተገኝተው የእጅ በእጅ ርክክብ ፈጽመዋል። ይህ ድጋፍም ለቦታው 2ኛው ዙር ሲሆን ችግሩ በተፈጠረበት ጊዜም የተቻለውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ፈጥኖ በመድረስ ተገቢ የሚዲያ ሽፋን እንዲያገኝ አድርጓል።
ድጋፉ በሀገረ እስራኤል ከሚገኙ የቤተ አብርሃም በጎ አድራጎት ማኅበርና ሌሎች በጎ አድራጊ ምእመናን ባደረጉት የገንዘብ ድጋፍ የተከናወነ ነው። በተመሳሳይ ባለፉት ጊዜያት ብቻ በሻሸመኔና በወለቴ ጉዳት ለደረሰባቸው የሰማዕታት ቤተሰቦች፣ በትግራይ ክልል ለሚገኙ 10 ገዳማትና አገልጋዮች፣ በቦረና ያቤሎ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች፣በጦርነቱ ተፈናቅለው በጎንደር አዘዞ ለሚገኙ ተፈናቃዮችና በዋግኸምራ ለሚገኙ ተጎጅዎች ተመሳሳይ ድጋፎች ተደርገዋል።
በድጋፉ ወቅት ያነጋገርናቸው ተጎጅዎችም “የደረሰብን ጉዳት ቀላል እንደሆነና ችግሩ እንደተፈታ አስመስለው፣ ባልተገባ መንገድ የሐሰት ዜና በሚያሰራጩ አካላት ማዘናቸውን ገልጸው፣ አሁንም የሚመለከተው አካል የወደመብንን ንብረት እንዲተካ አድርጎ ወደ ቦታችን ይመልሰን” ሲሉ አጽኖት ሰጠው ተናግረዋል።
ማኅበረ ቅዱሳን በቀጣይ ጊዜም በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በማኅበራዊ ቀውስ ጉዳት ለደረሰባቸው አካባቢዎች ተጨማሪ ድጋፎችን ለማደረስ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን መሰል የነፍስ አድን የአስቸኳይ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሥራዎችን አጠናክሮ ለመቀጠል በሚደረገው የሰብአዊ ድጋፍ ሥራ ምእመናን፣ማኅበራት፣ልዩ ልዩ ተቋማትና በጎ አድራጊ ድርጅቶች የተለመደ ትብብራችሁን አድርጉልኝ ሲል ጥሪውን ያቀርባል።
ለዚህ የማኅበራዊ ሰብአዊ ድጋፍ ለማድረግም፡- በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡-
1. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000309803648
2. በአሐዱ ባንክ - 0025393810901
3. በወጋገን ባንክ - 0837331610101
4. በአቢሲንያ ባንክ - 37235458
5. በአዋሽ ባንክ - 01329817420400 መጠቀም የምትሉ መሆኑን እንገልጻለን።
ለበለጠ መረጃ
• 09 84 18 15 44
• 09 43 00 04 03
• ማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ 1ኛ ወለል
የማኅበረ ቅዱሳን ሙያና ማኅበራዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ

👍21
" ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ያጋጠመው የሥርዓተ ቀኖና ጥሰት ከፈተናቸው አካባቢዎች መካከል አንዱ የምዕራብ ሐረርጌ ሀ/ስብከት ሲሆን ለ6 ወራት ያህል ምንም ዓይነት አገልግሎት ሳይሰጥ ቆይቷል።
በወቅቱም የቅዱስ ሲኖዶስን ክብር ለማስጠበቅ የሀ/ስብከቱ እና የምእመናን ድርሻ ከፍተኛ ነበር። ሕገ ወጡ ቡድን በጉልበት የሀ/ስብከቱን ሕንጻ በመውረር የተለያዩ ጉዳቶችን ያደረሰ ሲሆን ከፍተኛ ገንዘብም በስርቆት ወስዷል።
ይህንን ሕገ ወጥ ተግባር በመቃወም ብዙ ምእመናን ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን የከተማው ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶችም ለ20 ቀናት ለእስር ተዳርገው ነበር።
ቅዱስ ሲኖዶስ ችግሩን ለመቅረፍ ባደረገው ጥረት መሠረት ሐምሌ 18 ቀን 2015 ዓ.ም የሀገረ ስብከቱ ሥራ በአዲስ መልክ እንዲጀምር ተደርጓል።" ምዕራብ ሐረርጌ ሀ/ስብከት

👍17👎1
"በሀገራችን የተለያዩ ግጭቶች ከሚታዩባቸው አካባቢዎች መካከል አንዱ የመተከል ሀገረ ስብከት ነው። አካባቢው የኢትዮጵያ የድንበር አካባቢ እንደመሆኑ ከፍተኛ የእርስ በእርስ ግጭቶችን ሲያስተናግድ ነበር አሁንም በማስተናገድ ላይ ይገኛል።
በእነዚህ ችግሮች ምክንያት ምእመናን እጅግ ተፈትነው የነበረ ሲሆን የስብከተ ወንጌል አገልግሎትን ለማዳረስም ከፍተኛ ችግር ውስጥ ነበር።
ምንም እንኳን ፈተናው ቢበዛም በሀገረ ስብከቱ ስር ባሉ ጠንካራ አገልጋዮች አማካኝነት 1017 ኢ አማንያንን ወደ ቤተክርስቲያን ልጅነት መመለስ ተችሏል።" መተከል ሀገረ ስብከት

👍42
የ፵፪ ኛው አጠቃላይ ዓለም አቀፍ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የሁለተኛው ቀን ውሎ የጠዋት ክፍለ ጊዜ ጊዜ ተጠናቋል።
ሁለተኛውን ቀን በያዘው የ፵፪ ኛው አጠቃላይ ዓለም አቀፍ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አህጉረ ስብከቶች የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቶቻቸውን በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።
በጠዋቱ የሪፖርት ማቅረብ መርሐ ግብር የደቡብ ጎንደር ሀ/ስብከት፣ የከፋ ሀ/ስብከት፣ የአሶሳ ሀ/ስብከት፣ የምዕራብ ሐረርጌ ሀ/ስብከት፣ የምዕራብ ሸዋ ሀ/ስብከት፣ የአፋር ሀ/ስብከት፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀ/ስብከት፣ የዋግ ኸምራ ሀ/ስብከት፣ የመተከል ሀ/ስብከት፣ የሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀ/ስብከት፣ የወላይታ ሀ/ስብከት እና የጉራጌ ሀ/ስብከት ሪፖርታቸውን አቅርበዋል።

👍2