የ፵፪ ኛው አጠቃላይ ዓለም አቀፍ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ይጀምራል።
፵፪ ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዛሬጥቅምት ፭ ቀን ፳፻ ፲ወ ፮ ዓ.ም ይጀመራል።
ጉባኤው ከመላው ዓለም የሚመጡ ተሳታፊዎች የሚታደሙበት ሲሆን ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤትን የ፳፻ ፲ ወ ፭ ዓ.ም እቅድ አፈጻጸምን የሚያቀርቡ ሲሆን የሁሉም አህጉረ ስብከት ሪፖርት በንባብ ይሰማል ጉባኤውም በተመረጡ የመወያያ ርዕሶችና በምልዓት በሚነሱ ሀሳቦች ዙሪያ ውይይት በማድረግ ለአምስት ቀናት ይካሔዳል።
በጉባኤው በሪፖርትና በውይይት የሚነሱ ሐሳቦችን መሠረት ያደረገ የአቋም መግለጫ የሚቀርብ ሲሆን ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኘኤ ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ሲጸድቅ የ፳፻ ፲ወ ፮ ዓ.ም የሥራ መመሪያ ሆኖ ለማዕከልና ለአህጉረ ስብከት ይተላለፋል።
በዛሬ ዕለት የሚጀምረውን ዓለም አቀፍ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤን ለማካሔድ የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ሁሉ በሚገባ የተጠናቀቁ ሲሆን ጉባኤተኞችም አስቀድመው በመግባት የጉባኤውን መጀመር እየተጠባበቁ ይገኛሉ።ጉባኤው ስኬታማና ውጤታማ እንደሚሆን ይጠበቃል።

👍16
የ፵፪ ኛው አጠቃላይ ዓለም አቀፍ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በተገኙበት በጸሎተ ወንጌል እየተጀመረ ይገኛል።
👍5
"የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ንዋይ አሰባሰብ ላይ ብቻ ሳይሆን የምእመናን መዳን እና አጠቃላይ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ላይ በጥልቀት ሊመክር ይገባል"
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት
የ፵፪ ኛው አጠቃላይ ዓለም አቀፍ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ቅዱስ ፓትርያርኩ በተገኙበት በጸሎተ ወንጌል ተጀምሯል።
ከጸሎተ ወንጌሉ በመቀጠል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ለጉባኤው ከተለያዩ በሀገር ውስጥ እና በውጭ አገራት ከሚገኙ አህጉረ ስብከቶች ለመጡ ተሳታፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።
የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ለማከናወን እና ምእመናንን ለማገልገል የሀገር ሰላም ወሳኝ መሆኑን ያነሱት ቅዱስ ፓትርያርኩ መንግሥት እና የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ለሀገር ሰላም ተባብረው በመሥራት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
በተጨማሪም በሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ ስለሚነሱ ጉዳዮች ባስተላለፉት መልእክት ላይ ጉባኤው የምእመናን መዳን እና የቤተ ክርስቲያ አገልግሎት መጠናከር ላይ በትኩረት መወያየት እንደሚገባው አንስተዋል።

👍25
"በ2012 ዓ.ም እና በ2013 ዓ.ም በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በተከሰተው ጦርነት ሀ/ስብከታችን እጅግ የተፈተነ ሲሆን አሁንም ከዚህ መከራ መውጣት አልቻልንም። በእነዚህ ጦርነቶች እየሞተ ያለው ኦርቶዶክሳዊ ወጣት መሆኑን ደጋግመን ስንናገር ነበር።
ይህ ጉዳይ አሁንም ልጆቻችንን እየነጠቀን በመሆኑ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በጥልቀት ተወያይቶበት በመንግሥት እና በጦርነቱ ላይ ተሳታፊ በሆኑ አካላት ላይ ጫና በማሳደር ለሀገራችን ሰላምን እንዲያመጣልን በጽኑ እንጠይቃለን" ደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት

👍45👎2
የ፵፪ ኛው አጠቃላይ ዓለም አቀፍ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የመጀመሪያ ቀን ውሎ ተጠናቀቀ።
በዛሬው ዕለት የተጀመረው ፵፪ኛው አጠቃላይ ዓለም አቀፍ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ቅዱስ ፓትርያርኩ እና ብፁአን አባቶች በተገኙበት የአህጉረ ስበከቶችን የ2015 ዓ.ም የሥራ አፈጻጻም ሲያዳምጥ ውሏል።
በዚህም መሠረት የማእከላዊ ጎንደር ሀ/ስብከት፣የጅማ ሀ/ስብከት፣የኢሉ አባቦራ ሀ/ስብከት፣ የሲዳማ ሀ/ስብከት፣የደቡብ ወሎ ሀ/ስብከት፣የምሥራቅ ሐረርጌ ሀ/ስብከት፣የምሥራቅ አርሲ ሀ/ስብከት፣ ባሌ ሀ/ስብከት፣የጋሞ ጎፋ ሀገረ ስብከት፣ የምሥራቅ ወለጋ ሀ/ስብከት፣ የባሕርዳር ሀ/ስብከት፣የምሥራቅ ሸዋ ሀ/ስብከት፣ ድሬዳዋ ሀ/ስብከት እና የሰሜን ወሎ ሀ/ስብከት የሥራ አፈጻጸማቸውን በዛሬው ዕለት አቅርበዋል።
በመጨረሻም በቅዱስ ፓትርያርኩ የመዝጊያ ጸሎት የዛሬው መርሐ ግብር ተጠናቋል

👍18