ሁመራ ማእከል በሁመራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግቢ ጉባኤ ሲያስተምራቸው የቆዩትን የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ለመጀመሪያ ግዜ ማስመረቁ ተገለጸ
ሰኔ ፳፬/፳፻፲፯ ዓ.ም
ማኅበረ ቅዱሳን ሁመራ ማእከል በሁመራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግቢ ጉባኤ ሲያስተምራቸው የቆዩትን የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ለመጀመሪያ ግዜ ማስመረቁ ተገልጿል።
በምርቃት መርሐ ግብሩ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መጋቢ ሐዲስ መ/ር ዜናዊ አሸተ፣ የሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ መጋቢ ሰላም መ/ር ኃይሌ አምዴ እንዲሁም የሀገረ ስብከቱ ዋና ኦዲትና ኢንስፔክሽን ገንዘብ ቁጥጥር እና የደብረ ፀሐይ ቅ/ጊዮርጊስ ሰ/ት/ቤት ሰብሳቢ የሆኑት ዲ/ን ዳኛቸው ሰው ዓለም እና የተመራቂ ወላጆች ተገኝተዋል።
ኮሌጁ ለመጀመሪያ ጊዜ በዲፕሎማ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም ካስመረቃቸው ምሩቃን መካከል 23 የሚሆኑት በግቢ ጉባኤ አገልግሎት ውስጥ ሲከታተሉ ቆይተዋል።
ከተመራቂ ተማሪዎች ውስጥ የግቢ ጉባኤው ሰብሳቢ የነበረችው ተማሪ ሕይወት ደመወዝ በኮሌጁ አጠቃላይ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ የዋንጫ እና የብር ተሸላሚ መሆኗ ተገልጿል።
በመርሐ ግብሩ ያሬዳዊ ዝማሬ በተመራቂዎችና በማእከሉ መዘምራን የቀረበ ሲሆን ለተመራቂ ተማሪዎች የአደራ መስቀል ተበርክቶላቸዋል፡፡

❤19👍7
ጎንደር ማእከል ለግቢ ጉባኤያት ተተኪ ሥራ አስፈጻሚዎች ሥልጠና መሰጠቱ ተገለጸ
ሰኔ ፳፭/፳፻፲፯ ዓ.ም
በማኅበረ ቅዱሳን ጎንደር ማእከል ለግቢ ጉባኤያት ተተኪ ሥራ አስፈጻሚ ሥልጠና መሰጠቱ ተገልጿል።
በሥልጠና መርሐ ግብሩ የኔታ መዝገበ ቃል ገብረ ሕይወት የሰቆጣ ወለህ ነቅዐ ሕይወት የ4ቱ መጽሐፍተ ጉባኤያት ምሥክር መምህር "የዓላማ ሰው በአብሮነት" በሚል መነሻ ርእስ የግቢ ጉባኤ ሥራ አስፈጻሚዎችን መንፈሳዊ ሕይወትና የአገልግሎት አፈጻጸም የሚያሳድግ ሥልጠና ሰጥተዋል።
በዕለቱም የማእከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ሥልጣናት ቆሞስ አባ ዮሴፍ ደስታ የተገኙ ሲሆን ለተተኪ ሥራ አስፈጻሚዎች ምክርና መልእክት አስተላለፈዋል።

❤15👍6