Telegram Web Link
ያሬዳዊ ዜማ ተጠብቆ ከትውልድ ወደ ትውልድ መተላለፍ እንዲችል ሥራዎች እየተሠሩ እንደሚገኝ የዜማና የኪነ ጥበብ  ማእከል  አስታወቀ

ሰኔ ፳፮/፳፻፲፯ ዓ.ም

በማኅበረ ቅዱሳን የዜማና የኪነ ጥበብ ማእከል ያሬዳዊ ዜማ ተጠብቆ ከትውልድ ወደ ትውልድ መተላለፍ እንዲችል ሥራዎች እየተሠሩ እንደሚገኝ አስታውቋል።

በማኅበረ ቅዱሳን የዜማና የኪነ ጥበብ ማእከል  ምክትል ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ምሕረቴ እንደገለጹት ማኅበረ ቅዱሳን  ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ያሬዳዊ ዜማ ተጠብቆ መልኩን፣ ጸባዩን ሳይቀይር እንዲቀጥል ለማድረግ የኅትመት ሥራዎችን እያዘጋጀ ለምእመናን ተደራሽ ለማድረግ እየሠራ እንደቆየ ገልጸው አሁንም የበኩሉን ሚና እየተወጣ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ምክትል ኃላፊው አክለው በተለይ ምእመናን፣ ሰንበት ትምህርት ቤቶች፣ ማኅበራት ጋር ግቢ ጉባኤያትን በተመለከተ አመለካከት ላይ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናዎችን በተለያየ ጊዜ በመስጠት፣ ማእከላት ራሳቸውን እንዲችሉ ተተኪ መምህራንን ከማፍራት አንጻር ላለፉት ሦስት ወራት የአሠልጣኞች ሥልጠና እየተሰጠ እንደሚገኝ   ገልጸዋል።

በተጨማሪም በሥልታዊ ዕቅዱ መሠረት በአገልግሎት ዘርፍ ያሉ ተግዳሮቶችንና መፍትሔዎችን የሚያሳይ ጥናቶችን በማጥናት በተለይ ሽብሻባን፣እንቅስቃሴን፣የመሣሪያ አጠቃቀምን በተመለከተ 25 ሰ/ት/ቤቶች በተገኙበት ጥናቱን ማቅረብ ተችሏል።

ተግዳሮቱንና መፍትሔውን በተመለከተ የተጠናው ጥናት  በዋናነት ለውይይትና ለውሳኔ የሚሆኑ 12 አጀንዳዎችን በመለየት ከዋናው መዋቅር ከቤተ ክህነት ታይተው ውሳኔ እንዲሰጥባቸው ለማድረግ እንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝም ተጠቁሟል።
14🙏3
ከሰ/ት/ቤቶች ጋርም የመግባባትና አብሮ የመሥራት ለውጥ እየመጣ ሲሆን በተለይ የተወሰኑት  በተግባር በሚታይ መንገድ ከሕትመት ጀምሮ መሳሪያ አጠቃቀምን ጭምር ለውጥ የታየባቸው ቢሆንም በቂ ነው ማለት ግን አይቻልም  ስለዚህ ከዚህ በላይ አስቦ፣ ተናቦ፣ ተቀናጅቶ እንደ ቤተ ክርስቲያን በዚህ ዘርፍ የሚያገለግል የትኛውም አወቃቀር ጋር በጋራ መወያየት  ያስፈልጋል በማለት የማእከሉ ም/ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ምሕረቴ አመላክተዋል።

በመጨረሻም አቶ ፍቃዱ ከሰ/ት/ቤቶችና ከሚመለከተው አካላት ጋር በጋራ በመሥራት፣ በመተጋገዝ፣ በመረዳዳት ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ያለውን አገልግሎት ሰፊ ተደራሽነት እንዲኖረው ለማድረግ ሁሉም አካል የበኩሉን መወጣት ቢችል ለውጥ ማምጣት ይቻላል በማለት መልእክት አስተላልፈዋል።
19🙏4
በማኅበረ ቅዱሳን አሜሪካ ማእከል የምእራብ ማስተባበሪያ ጠቅላላ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ።

"በጎውን ማን ያሳየናል? የሚሉ ብዙ ናቸው" መዝ ፬፥፮  በሚል መሪ ቃል በሳንፍራንሲስኮ ከተማ የተጀመረው ጉባኤ ለ፫ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የባለፈው ዓመት ክንውን የሚመጣው ዓመት እቅድ ጨምሮ በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች እንደሚመክር ከአዘጋጅ ኮሚቴው ለዝግጅት ክፍላችን ያደረሰው መረጃ ያሳያል። አሜሪካ ማእከል በተቋማዊ ለውጡ  በሦስት ማስተባበሪያዎች የተደራጀ ሲሆን የምእራብ ማስተባባሪያም አንዱ  ነው። በሥሩም
አምስት ንዑሳን ማእከላት እና ሁለት ግንኙነት ጣቢያዎች የሚገኙ ሲሆኑ የጠቅላላ ጉባኤው ተሳታፊዎች ናቸው እነርሱም ሳን ሆዜ ን/ማእከል ፥ ላስ ቬጋስ  ን/ማእከል ፥ ሎስ አንጀለስ  ን/ማእከል ፥ ሲያትል  ን/ማእከል ፥ ዴንቨር  ን/ማእከል ፥ ፖርትላንድና አሪዞና ግጣቢያዎች ናቸው።

የምእራብ ማስተባበሪያ ማእከል ጠቅላላ ጉባኤ ለ፪ተኛ ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን በአካል ግን የመጀመሪያ ነው:: የሳንሆዜ ንዑስ ማእከል ተረኛው አዘጋጅ ነው ።

ጉባኤው በተሳታፊዎች የእድሜ ደረጃ መሠረት በ፬ ደረጃዎች የተከፈለ ሲሆን ከዋናው ጉባኤ በተጨማሪ  ለሕጻናትና ወጣቶች እንደ እድሜያቸው ዝግጅቶች መሰናዳታቸውን ለማወቅ ችለናል።

ዘገባው የአሜሪካ ማዕከል ሚዲያ ክፍል ነው።
13
አሜሪካ ማእከል ምእራብ ማስተባበሪያ ጠቅላላ ጉባኤ በፎቶ
3
2025/10/04 03:12:07
Back to Top
HTML Embed Code: