የውጭ ሀገራት ዜጎችን የተመለከት ልዩ ጉባኤ በዳላስ ተካሄደ!!!
ከመላው አሜሪካ እና ከካሪብያን የተለያዩ ግዛቶች ከተለያዬ ኅይማኖት ወደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የተጨመሩ አዳዲስ ተጠማቂያንና ተጠምቀው የቆዩ ነገር ግን በእምነት ውስጥ ለመጽናት እና ለመቆየት በተለያየ ምክንያት ያልቻሉ የሌሎች ሀገራት ተወላጆችን የተመለከተ ጉባኤ በዳላስ ቴክሳስ ደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ቅዳሜ ሰኔ 21 ቀን 2017 ዓ/ም ተካሄደ፡፡ በጉባኤው 42 በአካል 15 ደግሞ በዙም በድምሩ 57 ተሳታፊዎች ታዳመውበታል፡፡ የጉባኤው ተሳታፊዎች የተለያዬ ሀገር ተወላጆች ሲሆኑ በያሉበት ግዛት በሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት በኩል ሀይማኖታዊ ትምህርቶችን ተከታትለው : ጥያቂያቸው ተመልሶላቸው እና አምነው የተጠመቁ መሆናቸውን ለዝግጅት ክፍላችን ገልጸዋል:: ከያሉበት ተሰባስበው በጋራ እንዲህ መሰሉ ጉባኤ ማድረጋቸውም በቋንቋ ተግዳሮት እየበዛበት ያለውን የአዳዲስ ተጠማቂዎች መንፈሳዊ ሕይዎት ለማሻሻል እና እርስ በእርስ በመንፈሳዊ ሕይዎት ለመደጋገፍ እንደሚረዳቸው አስተያየታቸውን የሰጡ ሲሆን በአገልግሎት ያለመጽናታቸው ዋነኛ ችግሮች የቋንቋ እጥረት እና የባህል ልዩነት እንደዋነኛነት የቀረቡ ናቸው። ጉባኤውን ያዘጋጀው በማኅበረ ቅዱሳን አሜሪካ ማእከል የስብከተ ወንጌልና ሐዋሪያዊ ተልእኮ ዋና ክፍል ነው፡፡

❤7