ሁመራ ማእከል በሁመራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግቢ ጉባኤ ሲያስተምራቸው የቆዩትን የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ለመጀመሪያ ግዜ ማስመረቁ ተገለጸ
ሰኔ ፳፬/፳፻፲፯ ዓ.ም
ማኅበረ ቅዱሳን ሁመራ ማእከል በሁመራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግቢ ጉባኤ ሲያስተምራቸው የቆዩትን የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ለመጀመሪያ ግዜ ማስመረቁ ተገልጿል።
በምርቃት መርሐ ግብሩ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መጋቢ ሐዲስ መ/ር ዜናዊ አሸተ፣ የሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ መጋቢ ሰላም መ/ር ኃይሌ አምዴ እንዲሁም የሀገረ ስብከቱ ዋና ኦዲትና ኢንስፔክሽን ገንዘብ ቁጥጥር እና የደብረ ፀሐይ ቅ/ጊዮርጊስ ሰ/ት/ቤት ሰብሳቢ የሆኑት ዲ/ን ዳኛቸው ሰው ዓለም እና የተመራቂ ወላጆች ተገኝተዋል።
ኮሌጁ ለመጀመሪያ ጊዜ በዲፕሎማ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም ካስመረቃቸው ምሩቃን መካከል 23 የሚሆኑት በግቢ ጉባኤ አገልግሎት ውስጥ ሲከታተሉ ቆይተዋል።
ከተመራቂ ተማሪዎች ውስጥ የግቢ ጉባኤው ሰብሳቢ የነበረችው ተማሪ ሕይወት ደመወዝ በኮሌጁ አጠቃላይ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ የዋንጫ እና የብር ተሸላሚ መሆኗ ተገልጿል።
በመርሐ ግብሩ ያሬዳዊ ዝማሬ በተመራቂዎችና በማእከሉ መዘምራን የቀረበ ሲሆን ለተመራቂ ተማሪዎች የአደራ መስቀል ተበርክቶላቸዋል፡፡

❤18👍7