የማኅበረ ቅዱሳን ሙያ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት ባለፉት 7 ወራት ብቻ በመጠለያዎች ጣቢያዎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች፣ በድርቅና መሰል ማኅበራዊ ቀውስ ለተጎዱ ወገኖች፣ ለገዳማትና አብነት ት/ቤቶች ከ10 በላይ የሚሆኑ ተመሳሳይ ማኅበራዊ ድጋፎችን አድርጓል። በቀጣይ ጊዜም መሰል የነፍስ አድን ድጋፎችን ለማድረስ በሚደረገው የሰብአዊነት ሥራ ምእመናን የተለመደ ድጋፍ እንድታደርጉልን ማኅበሩ ጥሪውን ያቀርባል።
ድጋፍ ለማድረግ፡-
#በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡-
1. በአሐዱ ባንክ - 0025393810901
2. በአቢሲንያ ባንክ - 37235458
3. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000309803648
4. በወጋገን ባንክ - 0837331610101
5. በአዋሽ ባንክ 01329817420400
6. በጎ ፈንድ ሚ፡- https://gofund.me/f4c1b82e
6. በወገን ፈንድ፡- https://Www.wegenfund.com/mknu መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

gofundme.com
Donate to ኑ! የክቡራን ወገኖቻችንን ሕይወት እናትርፍ !!!, organized by Mahibere Kidusan
ኑ! የክቡራን ወገኖቻችንን ሕይወት እናትርፍ !!!
+++
ማኅበረ ቅዱሳን ባለፉት 6 ዓመታት በሀገራችን ኢትዮጵያ እያጋጠመ ባለው ማኅ… Mahibere Kidusan needs your support for ኑ! የክቡራን ወገኖቻችንን ሕይወት እናትርፍ !!!

❤3
የማኅበረ ቅዱሳን ላሊበላ ወረዳ ማእከል የጤና ቡድን ለተከዜ ኃይላ ለጥበብ ወምእራፈ ቅዱሳን አቡነ ሐዋርያ ክርስቶስ አንድነት ገዳም ገዳማውያን ነጻ የሕክምና አገልግሎት ሰጠ
ሰኔ ፲፱/፳፻፲፯ ዓ.ም
የማኅበረ ቅዱሳን ሙያ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት ኦርቶዶክሳዊያን ሙያተኞች በሙያቸው ተገቢውን አገልግሎት ለቤተ ክርስቲያን መስጠት ይችሉ ዘንድ በሁሉም ማእከላት ተገቢውን ድጋፍና ክትትል የማድረግ ሥራዎችን እየሠራ እንዳለ ይታወቃል።
በዚሁ መሠረት በማኅበረ ቅዱሳን ላሊበላ ወረዳ ማእከል ሙያ ገዳማትና አብነት ት/ቤቶች አገልግሎት ክፍል የጤና ባለሙያዎች ኅብረት በላስታ ወረዳ ቤተ ክህነት ስር ለሚገኘው ለተከዜ ኃይላ ለጥበብ ወምእራፈ ቅዱሳን አቡነ ሐዋርያ ክርስቶስ አንድነት ገዳም 46 መናንያን ነጻ የሕክምና አገልግሎት መስጠቱን የጤና ባለሙያዎች ኅብረት አስተባባሪው ዲ/ን ዶ/ር ፈንታ ሲሳይ ገልጸዋል።
ወቅቱ ወረሽኝ የሚበዛበት በመሆኑ የሕክምና አገልግሎቱን መስጠት አስፈልጓል ያሉት ዲ/ን ዶ/ር ፈንታ በሙያችን ገዳማውያንን በማገልገላችን የእኛም ነፍስ ታክማለች፤ በቀጣይም አገሎግሎቱን ለማስፋት የዳሰሳ ጥናት በመሥራት ወደ ሌሎች ገዳማት ለመድረስ እንሠራለን ብለዋል።
ዲ/ን ዶ/ር ፈንታ አክለውም ለሥራቸው መሳካት ከፍተኛ ድጋፍ ያደረጉትን አካላት አመስግነው ለቀጣይ መሰል ተግባራትም በጎ አድራጊዎች፣ አጋርና ባለድርሻ አካላት መድኃኒትና መሰል ድጋፎችን እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
የገዳሙ መጋቢ አባ ገብረ ጻድቅ ከፍያለ በበኩላቸው "የገዳሙን ሕግና ሥርዓት በጠበቀ እንዲሁም የመናንያኑን መንፈሳዊ ሕይወት ባከበረ መልኩ ይህ አገልግሎት መሰጠቱ እንዳስደሰታቸው ገልጸው የሕክምና አገልግሎቱ በተጠናከረ መንገድ ቀጣይነት እንዲኖረው" አባታዊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

❤18🙏3
ለሕክምናው የወጣው ወጭ በገንዘብ ሲተመን 51,050.90 ብር እንደሚሆንና የላስታ ወረዳ ጤና ጽ/ቤትና ሌሎች በጎ አድራጊዎች ባደረጉት ድጋፍ የተሸፈነ መሆኑ ተገልጿል።
በሕክምና አገልግሎቱ 3 ሐኪሞች፣ 3 ነርሶች፣ 2 የላብራቶሪ ባለሙያዎች እንዲሁም 1 ፋርማሲ በአጠቃላይ 9 የጤና ባለሙያዎች ተሳታፊ መሆናቸውን የተገኘው መረጃ ያመልክታል።

🙏9❤3👍1
በሽሬ ከተማ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች 1.5 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የሆነባቸው የምግብ ግብዓቶች ድጋፍ መደረጉ ተገለጸ፡፡
ሰኔ ፳፫/፳፻፲፯ ዓ.ም
የማኅበረ ቅዱሳን ሙያ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት በሀገራችን እያጋጠሙ ያሉ ሰፊ ማኅበራዊ ቀውሶች በማኅበረሰብ ክፍሎች፣ በገዳማትና አብነት ት/ቤቶች ላይ እያስከተሉት ያለውን ችግር ለማቅለል ፣ ባለፉት 7 ተከታታይ ዓመታት ሁለገብ ማኅበራዊ ድጋፎችን በመላ ሀገራችን እያደረገ እንደሆነ ተገልጿል።
በዚህ መሠረት በሰሜን ኢትዮጵያ ባጋጠመው ማኅበራዊ ቀውስ፣ ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በትግራይ ሽሬ እንደ ሥላሴ ከተማና ዙሪያው በሚገኙ 18 ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች ከ35,000 በላይ ተፈናቃዮች በከፍተኛ ማኅበራዊ ቀውስ ውስጥ እንደሚገኙ ተጠቁሟል።
ማኅበሩም በመላ ሀገሪቱ እንደሚያደርገው ሁሉ ሰኔ 19 እስከ 20 ቀን 2017 ዓ.ም በመጠለያ ጣቢያዎች በመገኘት 1.5 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የሆነበት 100 ኩንታል የምግብ ግብዓቶች ድጋፍ አድርጓል።
በድጋፉም ከ500 የሚልቁ ወገኖች ተጠቃሚ የሆኑ ሲሆን በዚህ የድጋፍ ርክክብ ወቅትም የማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል ልዑካን፣ የማኅበረ ቅዱሳን ሰሜን ምሥራቅና ሽረ ማእከል ተወካዮች እንዲሁም የመንግሥት አካላት በመገኘት ድጋፉን ለተጎጅዎች አስረክበዋል።
በተጨማሪም በችግሩ ለተጎዱ በአካባቢው ለሚገኙ ከ10 ለሚልቁ ገዳማት ድጋፎች የተደረጉ ሲሆን በተመሳሳይ ከወራት በፊት በአክሱም ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፎች መደረጋቸው ይታወሳል።

❤11
ድጋፎቹ የተደረጉት ማኅበራዊ ቀውሶችን ለማቃለል ከፍተኛ ሚናውን እየተወጣ ከሚገኘው ከማኅበረ በዓለ ወልድ ዘሰሜን አሜሪካ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ሲሆን ማኅበረ ቅዱሳንም በዚህ ዘመን ለወገን ደራሽነቱን በገቢር እያስመሰከረ፣ ሕያው የአገልግሎት ታሪክ እያስቀመጠ ለሚገኘው ማኅበረ በዓለወልድ ዘሰሜን አሜሪካ ልባዊ ምሥጋናውን ያቀርባል።
የማኅበረ ቅዱሳን ሙያ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት ባለፉት 9 ወራት ብቻ በማኅበራዊ ቀውስና ድርቅ ለተጎዱ የተለያዩ አካባቢዎች ከ12 በላይ ማኅበራዊ ድጋፍ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ አድርጓል።
መሰል የነፍስ አድን ድጋፎችን ለማድረስ በሚደረገው የሰብአዊነት ሥራ ምእመናን የተለመደ ድጋፍ እንድታደርጉልን ሲል ማኅበሩ ጥሪውን ያቀርባል።
ድጋፍ ለማድረግ፡-
በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡-
1. በአሐዱ ባንክ - 0025393810901
2. በአቢሲንያ ባንክ - 37235458
3. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000309803648
4. በወጋገን ባንክ - 0837331610101
5. በአዋሽ ባንክ 01329817420400
6. በወገን ፈንድ ፡- https://Www.wegenfund.com/mknu መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የማኅበረ ቅዱሳን ሙያ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት

የአዲስ አበባ ማእከል 650 የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን በትናንትናው ዕለት ማስመረቁ ተገለጸ
ሰኔ ፳፫/፳፻፲፯ ዓ.ም
ማእከሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአራት ፣ የአምስት እና የስድስት ኪሎ ግቢ ጉባኤያት ፣ የሲፒዩ ኮሌጅ ፣የሂልኮ ኮሌጅ ፣ ለደግ ሚድዋይፈሪ ኮሌጅ ፣ ኪዊንስ የማታ እና የካ ኢንዱስቱሪያል ኮሌጅ ግቢ ሲያስተምራቸው የነበሩ ስድስት መቶ ሃምሳ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን በጠቅላይ ቤተክህነት አዳራሽ በትናንትናው ዕለት ማስመረቁ ተገልጿል፡፡
በዕለቱ ወረብ በተመራቂ ተማሪዎች ፣ የበገና ዝማሬ ፣ የክብር እንግዳ መልእክት የቀረበ ሲሆን በከፍተኛ ማዕረግ ለተመረቁ ተማሪዎች እውቅናና ለተመራቂዎቹ የአደራ መስቀል ተበርክቷል።
ተመራቂ ተማሪዎች በበኩላቸው በግቢ ጉባኤ ሕይወት ውስጥ ማለፋችን ከዓለማዊ ፈተናዎች ተጠብቀን ከመጣንበት ሳንወጣ እንድንኖር አስችሎናል በማለት በቀጣይም በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ ሁሉ ቅድስት ቤተክርስቲያንን በማገልገል ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።

❤20