እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቃል የተሞሸረባት ሐዲስ አዳራሽ እርሷ ናት፡፡
ሚያዝያ ፳፬/፳፻፲፯ ዓ.ም
ከቅድስት ቤተ ክርስቲያናን የነገረ ማርያም አስተምህሮ ውጭ የሆነ ማርያም ቤዛዊተ ዓለም አትባልም የሚል የስሕተት ትምህርት በዕለተ ስቅለት በፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር ማኅበራዊ ሚዲያ ገጽ የተላለፈው የቤተ ክርስቲያናንን አባቶች፣ሊቃውንትን እንዲሁም መላው ሕዝበ ክርስቲያኑን አሳዝኗል፡፡
ከዚህም ጋር በተያያዘ የቤተ ክርስቲያን አባቶች በማኅበረ ቅዱሳን የቴሌቪዥን ጣቢያ በወቅታዊ መርሐ ግብር ላይ በመገኘት ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
አባቶች በማብራርያቸው የማይታየውን እና የሚታየውን የፈጠረው የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የአዳምን ኃጢአት ተሸክሞ መከራን ተቀብሎ ቤዛ ሆኖ እንዳዳነ ጠቁመዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቤዛነትን ለአምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለድንግል ማርያም እና ለሌሎች ቅዱሳን ሰጥታ ስትናገር ጠንቅቃ ታውቃለች ብለዋል፡፡
የፍጥረታትን ኃይል ሁሉ የያዘ አካላዊ ቃል ያለ ዘር ተጸንሶ ከሴት መወለድን አላፈረም ሲሉም ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ የጻፈውን በማጣቀስ ወንድሞቼ ስለ ድንግል ማርያም ልንናገር፣ልንመሰክርና ልንተረጉም ይገባል ሲሉ አስረድተዋል፡፡
ታላቁ ሊቅ የሆነው ቅዱስ ኄራቅሊስ በተረፈ ቄርሎስ በምዕራፍ ፫ ፥ ፲፮ የጸፈውን በማንሳት መለወጥ የሌለባት፣ድንግልና ያላት፣ንባበ አእምሮ ያላት፣የዳግማዊ አዳም ክርስቶስ ወላጅ የምትሆን፣ሁለቱን አንድ ያደረገች፣ከፍዳ የዳንባት የድኅነት ባለቤት፣የክርስቶስ እናት ቃል የተሞሸረባት ሐዲስ አዳራሽ እርሷ ናት ብለዋል፡፡

👍15
አባቶች በነበራቸው ቆይታ ስለ እመቤታችን ቤዛ አትባልም የሚል ጥያቄ የሚያነሱ ሰዎች የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነት፣መድኃኒትነት፣ቤዛነት የተቀማ የሚመስላቸው ምሥጢሩን ካለማወቅ እና ካለመረዳት ነው ያሉ ሲሆን በተጨማሪም ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤዛነት የሚያነሱ ሰዎች የመጠራጠር ስሜትን መፍጠር እንጂ መመርመር አይፈልጉም ብለዋል፡፡
በዚህም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ድንግል ማርያምን ቤዛ ስትል የኢየሱስ ክርስቶስን ቤዛነት ቀምታ እና እመቤታችንን ተገዳዳሪ አድርጋ አታውቅም በማለት አባቶች በአጽንዖት ተናግረዋል፡፡
አክለውም ስለ እመቤታችን ቤዛነት የሚጠራጠሩ የማያምኑ ሰዎች ከመመርመር እና ከመጠየቅ ይልቅ መንቀፍ፣መቃረን፣ታቃራኒ የሆነ ቃል መናገር፣ሰዎችን ማጠራጠር ነው የሚፈልጉት ሲሉ ገልጸዋል።
አክለውም በመጽሐፍ ቅዱስ እንደተጻፈው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "እኔ የዓለም ብርሃን እንደሆንኩ ሐዋርያትን እናንተም የዓለም ብርሃን ናችሁ" ሲል መናገሩን ስለ እመቤታችን ቤዛነት ለየማያምኑ ሰዎች በምሳሌነት በነበራቸው ቆይታ ላይ የጠየቁ ሲሆን በዚህም የዓለም ብርሃን ማነው? የሚለውን መልሱ ቢባሉ አይመልሱም ይልቁንስ ሌሎች ሐሳቦችን ይጠቅሳሉ ብለዋል፡፡
አይይዘውም በኦሪት ዘጸ ፯ ላይ "እግዚአብሔር ሙሴን ለፈርዖን አምላክ አድርጌሀለሁ" ብሎአል በመሆኑም የእግዚአብሔር አምላክነት ለሙሴ ተቀንሷል ወይ? ሲሉም አያይዘው ጠይቀዋል፡፡
አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሥዋዕት ሆኖ ደሙን አፍስሶ፣ሞቶ እና አዳም መቀበል የሚገባውን መከራ ተቀብሎ የዓለም ቤዛ እንደሆነን ሁሉ እመቤታችንም እርሱን የዓለም መድኃኒት ክርቶስን በመጽነሷ፣በመውለዷ፣በማሳደጓ፣ለመስቀል ሞት በማብቃቷ እና በአማላጅነቷ ቤዛዊተ ዓለም እንደሆነች አስገንዝበዋል፡፡
እያንዳንዱን በመጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈውን ቃል አገባቡን እና ትርጓሜውን ተከትሎ መጠየቅ እንደሚገባም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
እመቤታችን ዓለሙ እንዲድን ክርስቶስን ፀንሳለች፣ወልዳለች፣እያጠባች በጀርቧ አዝላው ወደ ግብጽ ወርዳለች ይህም አምላክ ዓለሙን ማዳን አቅቶት አግዛዋለች ማለት አይደለም ይህን ባለመረዳት በነገረ ድኅነት ያላትን ድርሻ ማሳጣት እንደማይገባ አንሥተዋል።
ለተጨማሪ መረጃ ሊኩን በመጫን ይመልከቱ፡-
https://youtu.be/GP_fvk0267s?si=4AYyxY3dgOGRG4ze

YouTube
MK TV || ወቅታዊ || ድንግል ማርያም የዓለም ቤዛ መድኃኒት ትባላለች
Subscribe and share https://www.youtube.com/user/EOTCMK?s......
https://www.youtube.com/user/EOTCMK?s......
#MKTV #MahibereKidusan #EOTCMK
https://www.facebook.com/eotcmkidusan

❤22👍13🙏4
በሲያትል የሚገኙ በሀገረ አሜሪካ ተወልደው ያደጉ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ለወቅቱ የሚመጥን በሊቃውንት ታግዘው ያዘጋጁት ልዩ ዝማሜ ተጋበዙልን፤ ለሌሎችም አጋሩ። መልካም ሰንበት
https://youtu.be/PqlK4dhiUuw
https://youtu.be/PqlK4dhiUuw
YouTube
MK TV ll ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን l Christ is risen from the dead l Seattle Campus Ministry, WA
👍18❤8
"ሥርዐተ መነኮሳት ለግብረ ትሩፋት" በሚል መሪ ቃል የምክክር መርሐ ግብር እየተካሄደ እንደሚገኝ ተገለጸ
ሚያዝያ ፳፯/፳፻፲፯ ዓ.ም
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የገዳማት መምሪያ አዘጋጅነት ለ3 ተከታታተይ ቀናት የሚቆይና ከመላው ኢትዮጵያ የመጡ ገዳማውያን የሚሳተፉበት የምክክር መርሐ ግብር በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽርሐ ተዋሕዶ በዛሬው ዕለት መጀመሩ ተገልጿል ።
በመርሐ ግብሩ ብፁዕ አቡነ አብርሃም
የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣
የባሕርዳር እና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ካህናት ጸሎተ ወንጌል የጀመረ ሲሆን ብፁዕ አቡነ አብርሃም እንኳን ደኅና መጣችሁ በማለት ጉባኤው ለሁለተኛ ጊዜ መደረጉን አውስተው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ገዳማት ወደ ቀደመ ክብራቸው ለመመለስ የገዳማውያኑ እና ሁላችን ኃላፊነት አለብን በማለት ከዛሬ ጀምሮ በቀጣይ ቀናት ቤተ ክርስቲያናችንን የሚጠቅሙ ሐሳቦች በገዳማውያኑ እንደሚነሳ እንደሚጠብቁ ተናግረዋል።
በቀናቱም የተለያዩ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው የሚጠበቅ ሲሆን የመጀመሪያውን ጽሑፍ "ምንኩስና ከአኃት አብያተ ክርስቲያናት አንጻር" የሚለውን በርዕሰ ሊቃውንት በአባ ገ/ኪዳን በመቅረብ ላይ ይገኛል።
ጉባኤው ዛሬን ጨምሮ ለ3 ተከታታይ ቀናት የሚቀጥል ይሆናል።

👍45🙏5❤4
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል የሚያስገነባው ባለ 14 ወለል የልህቀት ማእከልን አስመልክቶ ከአጋር አካላት ጋር የውይይት መርሐ ግብር መካሄዱ ተገለጸ
ሚያዝያ ፳፰/፳፻፲፯ ዓ.ም
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል የሚያስገነባው ባለ 14 ወለል የልህቀት ማእከልን አስመልክቶ በትናትናው ዕለት ሚያዝያ 27 ቀን 2017 ዓ.ም በዮድ አቢሲኒያ ሆቴል ከአጋር አካላት ጋር ውይይት ማድረጉ ተገልጿል።
በመርሐ ግብሩ የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ሥራ አስፈጻሚ መምህር ዋሲሁን በላይ፣ የማኅበሩ የሕዝብ ግንኙነት ም/ሥራ አስኪያጅ ዲያቆን ሲሳይ ብርሃኑ፣ የማኅበሩ ጽሕፈት ቤት ግንባታ ዐቢይ ኮሚቴ፣ የአራቱ ጉባኤያት የምስክር መምህር መምህረ መምህራን በጽሐ ዓለሙ፣ የማኅበሩ አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ሥራ አስፈጻሚ መምህር ዋሲሁን በላይ እንደገለጹት ማኅበሩ በርካታ ሥራዎችን እየሠራ የሚገኝ ሲሆን ይህም የሚሠራው የአገልግሎት ቦታው የተሻለ እንዲሆንና የሚቀጥለው ትውልድ የተሻለ የአገልግሎት ስፍራ ስለሚገባው እንዲሁም አገልግሎትም እያደገ በመምጣቱ የሚከናወኑ ተግባሮችን በስፋት ለማከናወን የልህቀት ማእከሉን ከፍጻሜ ማድረስ አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።
ዋና ሥራ አስፈጻሚው አክለውም መርሐ ግብሩን ለመካፈል የማኅበሩን ጥሪ አክብረው ለተገኙና ለተሳተፉ በሙሉ በማኅበረ ቅዱሳን ስም አመስግነዋል።
የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ማእከል የሕዝብ ግንኙነት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ዲያቆን ሲሳይ ብርሃኑ የልህቀት ማእከሉ የደረሰበትን ሁኔታ አስመልክቶ ሪፖርት አቅርበዋል።
በመርሐ ግብሩ የሥዕል ዐውደ ርእይን ጨምሮ ሌሎች ዝግጅቶች የቀረቡ ሲሆን የልህቀት ማእከል ግንባታውን ለማከናወን አባላት እና አጋር አካላት የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።

👍29❤11🙏6
የመሠረታዊ የርቀት ትምህርት መርሐ ግብር የመጀመሪያ ክፍል (ሦስት ኮርሶችን የያዘ) ሲሆን የክፍያ መጠን እና አማራጮች እንደሚከተለው ነው:-
1. ለአገር ውስጥ ተማሪዎች የትምህርት ክፍያ ከነ መመዝገቢያው 590 ብር ነው።
2. መካከለኛው ምስራቅ አካባቢ እና ከኢትዮጵያ ውጪ ያሉ አፍሪካ አገራት ለሚኖሩ የርቀት ት/ት ተማሪዎች =10usd
3. አውሮፓ ፣ ሩቅ ምስራቅ እና ላቲን አሜሪካ አካባቢ ለሚኖሩ የርቀት ት/ት ተማሪዎች = 15 usd
4. አሜሪካ ፣ ካናዳ እና አውስትራሊያ አካባቢ ለሚኖሩ የርቀት ት/ት ተማሪዎች = 20 usd
- በብር መክፈል ለምትፈልጉ ተማሪዎች የየአካባቢያችሁን ተመን በዕለቱ የዶላር ምንዛሬ በመጠቀም ቀይሮ መክፈል ይቻላል!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000195489541(*889#)
ይህ ፎርም የርቀት ትምህርትን በኦንላይን (በኢለርኒንግ አማራጭ) ብቻ ለመማር በሚመዘገቡ ተማሪዎች የሚሞላ ነው። ፎርሙን ለመሙላት መዘጋጀት ያለባቸው ነገሮች :-
1, ፎቶ (ስካን የተደረገ፣ ፖስፖርት ሳይዝ)
2, መታወቂያ (ማንኛውም አይነት፣ ስካን የተደረገ)
3, የትምህርት ክፍያ የከፈሉበት ደረሰኝ (ስካን የተደረገ) ወይም በሞቫይል አፕ የከፈሉበት ስናፕሾት

👍11❤4