Telegram Web Link
የገዳማት አባቶች የተሰጣቸውን ኃላፊነት መወጣት እንዳለባቸው ተጠቆመ ፡፡

ሚያዝያ ፴/፳፻፲፯ ዓ.ም

ሥርዐተ መነኮሳት ለግብረ ትሩፋት በሚል መሪ ቃል በጠቅላይ ቤተ ክህነት በገዳማት መምሪያ አዘጋጅነት ሲካሄድ የነበረው የምክክር ጉባኤ የጋራ አቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል፡፡

አባ አትናቴዎስ የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል አስተዳዳሪ የጋራ አቋም መግለጫውን ባቀረቡበት ወቅት እንዳሉት የገዳማት አባቶች የተሰጣቸውን ኃላፊነት እና የሚጠበቅባቸውን ድረሻ መወጣት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በመግለጫውም በገዳማት ያሉትን በርካታ ችግሮችን በመለየት መፍታት እንደሚጠበቅ ገልጸው በገዳማት የአብነት ትምህርት ቤቶችን በመክፈት ማጠናከር  ይገባል ብለዋል፡፡

አክለውም መነኮሳት በትምህርት ራሳቸውን ማሳደግ እንዲችሉ ገዳማቶች ላይ የመኮሳት ኮሌጅ መክፈት እንዳለበት አባ አትናቴዎስ በመግለጫው ላይ ገልጸዋል፡፡

ለገዳም አባቶች  አድራሻ ያለው  እና መረጃዎችን የያዘ አንድ ወጥ መታወቂያ በዚጋጅ እንዲሁም የመነኮሳት ፍሰትን ማስቀረት የሚቻልበት መንገዶችን በመፍጠር ሥራዎችን መሥራት እንደሚስፈልግ  በመግለጫቸው ላይ አንስሥተዋል፡

በተካሄደው የምክክር ጉባኤ ላይ የተነሡ በርካታ ሐሳቦችን ቅዱስ ሲኖዶስ ተነጋግሮ እንዲያጸድቅ ጠይቀዋል፡፡

እንዲሁም በተነበበው መግለጫ ላይ የጉባኤው ተሳታፊዎች ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ  ቀዳማዊ  ፓትርያርክ  ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ  ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት እና ከብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የባሕርዳር እና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የተሰጠውን  መመሪያ ለመፈጸም ቃል ገብተዋል፡፡
👍6🕊1
‹‹በማርያም ልደት ምክንያት ዛሬ ደስታ ሆነ!›› ቅዱስ ያሬድ
በከበረች በግንቦት አንድ ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደች። እርሷም ለሰው ሁሉ ወገን ድኅነት የሆነባት ናት፡፡ ከወንዶች ወገን የከበረ አባቷም ስሙ ኢያቄም ከሴቶች ወገን የከበረች ሚስቱ ሐና ይባላሉ፡፡ ሁለቱም ልጅ በማጣት ሲያዝኑ ኖሩ። በዚያ ወራት የመካኖች መብዓ ካህናቱ አይቀበሉም ነበርና፡፡ እነርሱም ከሰው የሚደርስባቸውን ሽሙጥና ኅዘናቸውን ያርቅላቸው ዘንድ በቀንና በሌሊት ወደ እግዚአብሔር ፈጽሞ ይማልዱ ነበር፡፡ ሰውን የሚወድ እግዚአብሔርም ከዘራቸው ለዓለሙ ሁሉ መድኃኒት ይሆን ዘንድ መልካም የሆነ ሐሳባቸውን ተመለከተ፡፡ ክቡር ኢያቄምም አርባ ቀን እስኪፈጸም በተራራ ውስጥ ቁሞ ሲጸልይ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገለጸለትና ለዓለሙ ሁሉ ድኅነት የሚደረግባት ዘር እንደሚሰጠው አበሠረው፡፡
በፍጹም ልብ አምኖ ከተራራው ወረደ፤ ለተመሰገነች ሚስቱ ለሐናም ከእግዚአብሔር መልአክ የሰማውን ያንን ራእይ ነገራት። ቃሉ እውነት እንደሆነ እርሷም አመነች። ልዑል እግዚአብሔርንም አመሰገነች። የተመሰገነች ቅድስት ሐናም ከእርሷ የሚወለደውን በዘመኑ ሁሉ ለቤተ እግዚአብሔር አገልጋይ ታደርገው ዘንድ ለእግዚአብሔር ስለትን ተሳለች፡፡
ከዚህም በኋላ ይህችን የከበረች ሕፃን ፀንሳ ወለደች። ከአይሁድ ለማምለጥ የተሰደዱት ቅድስት ሐና እና ቅዱስ ኢያቄም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን በአድባረ ሊባኖስ ሥር ግንቦት አንድ ቀን ወለዷት፡፡ ስሟንም ‹ማርያም› ብላ ሰየመቻት። ትርጓሜውም ‹እመቤት› ነው። ‹ደግሞም ሀብታና ስጦታ› ማለት ነው፡፡ በእውነት የዓለሙ ሁሉ እመቤት ሁላችን በእርሷ ሰማያዊ ሀብት ልጅነትን ያገኘንባት ናትና።
22👍10
በንጽሕናዋ እና በቅድስናዋ ተደንቀው ሰማያውያን ቅዱሳን መላእክትም ያመሰግኗታል፡፡ ቤተ ክርስቲያን የቅድስት ድንግል ማርያምን ልደት በታላቅ ድምቀት የምታከብረው ከዚህ ታላቅ በዓል በረከት ረድኤትን እንድናገኝበት ነው፡፡ የሕይወት ክርስቶስ እናት ዛሬ ተወልዳለችና፡፡ በሥርዓት ቤተ ክርስቲያን መሠረት በቀናች በተዋሕዶ እምነት ሆነን፤ የድኅነታችን ምክንያት የሆነችውን ድንግል ማርያምንም እያመሰገንን ልናከብረው ይገባል፡፡

አምላካችን እግዚአብሔር ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በዓል በረከት ረድኤት ይክፈለን፤ አሜን!
36👍4
እንኳን ለማኅበረ ቅዱሳን ፴፫ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
🙏3011
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል በዓለ ልደት እና የማኅበረ ቅዱሳን የምስረታ ፴፫ኛ ዓመት በዓል በአትላንታ ንዑስ ማእከል አስተባባሪነት በአትላንታ መካነ  ሕይወት አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ  ካቴድራል ግቢ ውስጥ በድምቀት ተከብሯል። ንዑስ ማእከሉ በአዘጋጀው በዚህ መርሐ ግብር ላይ በከተማው የሚገኙ በርካታ ምእመናን ተሳታትፈዋል
11🕊2
2025/07/14 22:35:25
Back to Top
HTML Embed Code: