Telegram Web Link
በማኅበረ ቅዱሳን የጎንደር ማእከል “አደራ አለብኝ” በሚል መሪ ቃል መርሐ ግብር አከናወነ።

ጥር ፪ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም

“አደራ አለብኝ” በሚል መሪ ቃል የማኅበረ ቅዱሳን ጎንደር ማእከል ታኅሣሥ 27 ቀን 2017 ዓ.ም በማእከሉ የስብከተ ወንጌል አዳራሽ የድኅረ ግቢ ጉባኤ መርሐ ግብር ማካሄዱ ተገልጿል፡፡

በመርሐ ግብሩ ከ140 በላይ የግቢ ምሩቃን የተሳተፉ ሲሆን "የአገልግሎት በር" በሚል ርዕስ ሥልጠና ተሰጥቷል።

በተለያዩ የአገልግሎት ዘርፎች ለረዥም ጊዜ ያገለገሉ አባላት የልምድ ልውውጥ በማካፈል አባላት ሥራ፣ ሁኔታ፣ ቦታና ጊዜ ሳይገድባቸው ባሉበት ሆነው ሐዊርያዊ አገልግሎታቸውን መፈጸም እንደሚገባቸው መልእክት ተላልፏል።
24👍3
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ 
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት  ወቅታዊ  ጉዳዮችን አስመልክተው  አባታዊ የሰላም ጥሪ አስተላለፉ።
22👍7🕊2
✍️ሐመር መጽሔት በገበያ ላይ !✍️

✍️".. እኛም ጥምቀትን እንፈልጋለን የሚሉ ምእመናን  ብዙ ናቸው ..) #ሐመር #መጽሔት  በጥር  በ፳፻፲፯ ዓ.ም መልእክት ዐምድ  ✍️      
                   ༺ ༻ 
  #የኅትመት ዘመን ፦#ጥር ፳፻፲፯  ዓ.ም
#አዘጋጅ ፦በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ  ቤተ ክርስቲያን ማኀበረ ቅዱሳን በልማት ተቋማት አስተዳደር  በመጽሔት ዝግጅት ክፍል የሚዘጋጅ ትምህርታዊ መጽሔት
•  ገጽ ብዛት፦፳፰
   ዋጋ ፦፵ ብር 
•  ሐመር  መጽሔት  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት  ሥርዓትና ትወፊት ጠብቃ በልማት ተቋማት አስተዳደር  በመጽሔት ዝግጅት ክፍል በየወሩ የምትወጣ መንፈሳዊ መጽሔት ናት፡፡
•  ሐመር መጽሔት ፴፩ ኛ ዓመት  ቁጥር-፩    #ጥር  ፳፻፲፯  ዓ.ም
🙏18👍98
“እንኳን ለከተራ በዓል አደረሳችሁ!”

የከተራ በዓል ምሳሌያት

በበዓለ ጥምቀት ዋዜማ የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድና የባሕረ ጥምቀቱ መዘጋጀት ሃይማኖታዊ ታሪክና ምሳሌ አለው፡፡ የቃል ኪዳኑን ታቦት አክብሮ መጓዝና ወደ ወንዝ መወረድ የተጀመረው በአሮን ልጅ በአልዓዛር ጊዜ ነው፡፡ ኢያሱ በሙሴ እግር ተተክቶ ሕዝበ እስራኤልን እየመራ ከዮርዳኖስ ወንዝ ሲደርስ ባሕሩ ከሁለት ይከፈልና ወራጁም ይቆም/ይከተር/ ነበር፡፡ እስራኤል ዘሥጋ ወደ ምድረ ርስት ለመግባት የዮርዳኖስን ወንዝ ሲሻገሩ፡- ድንኳን ጥለው የቃል ኪዳኑን ታቦት በድንኳን ውስጥ አድርገው ሌዋውያኑ በዙሪያው፣ ካህናቱ ደግሞ በውስጥ ኾነው እግዚአብሔርን እያመሰገኑ አድረው በማለዳ ተሻግረዋል /ኢያሱ 3÷8-9/፡፡ ካህናቱ የቃል ኪዳኑን ታቦት አክብረው የወንዙን ዳርቻ በረገጡት ጊዜ እንደ ክረምት ማዕበል ይወርድ የነበረው ውኃ ግራና ቀኝ ተከፍሎ እንደ ግድግዳ ወደ ላይ ቆሟል፡፡

ሕዝቡ ተሻግሮ እስከሚያበቃ ታቦተ ጽዮንን ያከበሩት ካህናት ከወንዙ መሐል ይቆሙ ነበር፡፡ በዚህ መሠረት ‹‹ወተጠምቃ እገሪሆሙ ለካህናት›› ይህም ‹‹የካህናት እግሮቻቸው የዮርዳኖስን ውኃ በመርገጣቸው እንደ ጥምቀት ሆናቸው›› በሐዲስ ኪዳነ ጌታችን ለመሠረተው ሥርዐተ ጥምቀት ምሳሌ ነበር፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን የጥምቀትን ዋዜማ ከተራ ብላ የጠራችው ከዚህ በመነሣት ነው፡፡

ጌታችን በተጠመቀ ጊዜ የዮርዳኖስ ወንዝ የላይኛው ሸሽቶ ወደ ላይ ተመልሶ ሽቅብ ፈሷል፡፡ የታቹም ወደ ታች ሸሽቷል፡፡ የላይኛው ፈሳሽ ተቋርጦ እንደ ክምር ተቆልሎ ቀርቷል።ቅዱስ ዳዊት የተመለከተውም ይህንኑ ነው። ከአዳም ጀምሮ እስከ ክርስቶስ ድረስ በዘር ይወርድ የነበረው ፍዳ መርገም በክርስቶስ ቤዛነት ተቋርጦ ፤ የታቹም ፈጽሞ መድረቁ ኀጢአተ አዳም የመጥፋቱ ምሳሌ ነው፡፡
5👍5
እስራኤል ፈለገ ዮርዳኖስን ተሻግረው ወደ ኢያሪኮ መሔዳቸው ምእመናን በጥምቀት ከኀጢአት ቍራኝነት ተላቀው እግራቸውን ወደ ልምላሜ ገነት ወደ ዕረፍተ መንግሥተ ሰማያት አቅንተው ለመሔዳቸው ምሳሌ ነው፡፡ ኢያሱ የጌታ፣ እስራኤል የምእመናን፣ ዮርዳኖስ የጥምቀት፣ ምድረ ርስት የገነት መንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ነው፡፡

ታቦቱን አክብሮ የሚሔደው ካህን የቅዱስ ዮሐንስ፣ታቦቱ የጌታችን፣ ባሕረ ጥምቀቱ የዮርዳኖስ ወንዝ፣ ታቦታቱን አጅበው የሚሔዱትና በዓሉን የሚያከብሩት ምእመናን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ እየመጡ የንስሐ ጥምቀት ሲጠመቁ የነበሩት ሰዎች ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ታቦታቱ በጥምቀት ዋዜማ ከመንበራቸው ወደ ጥምቀተ ባሕር መውረዳቸውና በዚያ ማደራቸው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ በፈለገ ዮርዳኖስ ከማታው ጀምሮ መውረዱንና ተሰልፎ ተራውን ሲጠብቅ ማደሩን ያጠይቃል፡፡ ‹‹ጥምቀት የሞቱና የትንሣኤው ምሳሌ ነው፡፡ ከኃጥአን ጋር ተቆጥሮ እንዲጠመቅና እንዲሰቀል የተጻፈውን ቃል ንስሐና ጥምቀት የማያስፈልገው ሲሆን ነገር ግን ፍጹም ኃጥእ መስሎ በዮሐንስ እጅ ጥምቀትን ለመፈጸም በማየ ዮርዳኖስ ተጠመቀ፡፡››
ጌታችን የተጠመቀበት ወርኀ ጥር በእስራኤላውያን ዘንድ የዝናብ፣ የበረዶ ወራት ነው፡፡ ከወንዝ ዳር ያለ መጠለያ መዋልና ማደር አይቻልም፡፡ በመኾኑም ከዮሐንስ ለመጠመቅ የሚሄዱ ሰዎች ሁሉ በዮርዳኖስ ዙሪያ ድንኳናቸውን ተክለው ያርፉ ነበር፡፡ በዚህ አንጻር ዛሬም በባሕረ ጥምቀት ዙሪያ ድንኳኖች ዳሶች ይጣላሉ፡፡

በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች በተለይ በአክሱም የንግሥት ሳባ መዋኛን ‹‹ማይ ሹም›› በጎንደር ዐፄ ፋሲል ያሠሩት  ባሕረ ጥምቀት፣ በላስታ ቅዱስ ላሊበላ ያሠራው ባሕረ ጥምቀት፣ በሸዋ የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ፍርድ መስጫ አደባባይን፣ አርባ አራት ታቦታት የሚያድሩበትን የሸንኮራ ሜዳን “ራቡቴ ወንዝ” በአዲስ አበባ ደግሞ ጃንሆይ ሜዳን /ጃንሜዳን/ ወዘተ ለአብሕርተ ምጥማቃት እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል፡፡ እነዚህ ቦታዎች ዛሬም ድረስ ተከብረው ይገኛሉ፡፡ እኛ በዚህ ወቅት ታቦት ይዘን፣ከወንዝ ወርደን፣ ድንኳን ተክለን በማክበራችን ይፈጸማል፡፡

👇👇👇👇👇👇👇
የማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮች ይቀላቀሉ
ቴሌግራም፡- http://www.tg-me.com/mkpublicrelation
የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት፡- http://www.facebook.com/eotcmkidusan/
ድረገጽ፡- http://www.eotcmk.org
ዩ ቲዩብ፡- http://www.youtube.com/user/EOTCMK
            :- https://www.youtube.com/@-zemawetibebzmk7905
4
በባሕር ዳር ሀገረ ስብከት የደበረ አባይ ቅ/ገብርኤል ታቦት የባሕረ ጥምቀት ጉዞ
5👍2
የ2017 የከተራ በዓል በዋድላ ኮን ከተማ መከበር ጀምሯል።

በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ዋድላ ወረዳ በኮን ከተማ የከተራ በዓል እየተከበረ ይገኛል።

አራት ታቦታት በአንድ ላይ በተዘጋጀላቸው ቦታ የሚያድሩ ሲሆን እነርሱም  ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ታች መካነ  ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣  ላይ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ እና አዳሌ መስክ ቅድስት ልደታ ናቸው።

ታቦታቱ  በወረዳው ቤተ ክህነት ሠራተኞች፣ በአድባራት ካህናት፣ በሊወቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ በሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች፣  በማኅበረ ቅዱሳን ኮን ወረዳ ማእከል  አባላት፣ በበገና ዘማሪያን፣ በበጎ ፈቃድ ወጣቶች እና  ምእመናን በዝማሬና በእልልታ ታጅበው ወደ ተዘጋጀላቸው ቦታ በክብር ገብተዋል።
4👍4
2025/07/14 17:36:36
Back to Top
HTML Embed Code: