Telegram Web Link
ግእዝ ክፍል 35
የይቤ ዝርዝር (Reported speech)
ይቤ ኢየሱስ አፈቅረክሙ
Jesus said,I love you
እያለ ይሄዳል።ይቤ በ10ሩ መራሕያን ይረባል
ይቤ=አለ=he said
ትቤ=አለች=she said
ትቤ=አልክ=you said
ትቤሊ=አልሽ=you said
እቤ=አልኩ=I said
ንቤ=አልን=We said
ይቤሉ=አሉ=they said
ይቤላ=አሉ=they said (ሴቶች)
ትቤሉ=አላችሁ=you said
ትቤላ=አላችሁ=you said (ሴቶች)
እያለ በ10ሩ መራሕያን ይዘረዘራል።ይቤ መጻእኩ ወደ አማርኛ ሲተረጎም መጣሁ አለ ማለት ነው።ይህ በቅኔ ቤት መጻእኩ የይቤ ተሳቢ ይባላል።አንዳንድ ቅኔ ቤቶች ደግሞ መጻእኩ የይቤ ተለዋጭ ይባላል።ምስጢሩ አንድ ነው።

ይህ 10ሩ ደግሞ በካልዓይ በዘንድ በትእዛዝ እንደሚከተለው ይገለጻል።
ውእቱ ይቤ=አለ
ይብል=ይላል
ይበል=ይል ዘንድ
ይበል=ይበል
ውእቶሙ ይቤሉ=አሉ
ይብሉ=ይላሉ
ይበሉ=ይሉ ዘንድ
ይበሉ=ይበሉ
ውእቶን=ይቤላ=አሉ
ይብላ=ይላሉ
ይበላ=ይሉ ዘንድ
ይበላ=ይበሉ
ይእቲ=ትቤ=አለች
ትብል=ትላለች
ትበል=ትል ዘንድ
ትበል=ትበል
አንተ=ትቤ=አልክ
ትብል=ትላለህ
ትበል=ትል ዘንድ
በል=በል
አንቲ=ትቤሊ=አልች
ትብሊ=ትያለሽ
ትበሊ=ትይ ዘንድ
በሊ=በይ
አንትሙ=ትቤሉ=አላችሁ
ትብሉ=ትላላችሁ
ትበሉ=ትሉ ዘንድ
በሉ=በሉ
አንትን=ትቤላ=አላችሁ
ትብላ=ትላላችሁ
ትበላ=ትሉ ዘንድ
በላ=በሉ
አነ=እቤ=አልኩ
እብል=እላለሁ
እበል=እል ዘንድ
እበል=ልበል
ንሕነ=ንቤ=አልን
ንብል=እንላለን
ንበል=እንል ዘንድ
ንበል=እንበል።

ጥያቄ
ግእዙን ወደ አማርኛ አማርኛውን ወደ ግእዝ ተርጉም።

1 ይቤ ኢየሱስ እመኑ ብየ
2 ትቤ ማርያም ትኩነኒ
3 ኩሉ ሰራዊተ ሰማያት ይብሉ
4 አንተ አልክ
5 አይሁድ ስቀለው ስቀለው አሉ።

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግእዝ ክፍል 36
©ንኡስ አንቀጽ~~Gerund©
ክፍል 1
በልአ=በላ (ግስ)።በሊዕ/በሊዖት=መብላት(ስም)
Eat=በላ(verb)።eating=መብላት (noun)
ከግስ ላይ ንኡስ አንቀጽ ለማውጣት ሁለት መንገድ አለ።1ኛው መንገድ ቅድመ መድረሻውን ሣልስ አድርጎ መጨረሻውን ሳድስ ማድረግ ወይም ቅድመ መድረሻውን ሣልስ አድርጎ መጨረሻውን ሳብእ አድርጎ ትን መጨመር ነው።
የቀተለ፥ክህለ፥ቆመ፥ሤመ እና ገብረ ቤቶች ናቸው።
ቀቲል/ቀቲሎት=መግደል=killing
ክሂል/ክሂሎት=መቻል
ቀዊም/ቀዊሞት=መቆም
ሠይም/ሠይሞት=መሾም
ገቢር/ገቢሮት=መስራት=working ነው። በእንግሊዘኛ verb+ing ነው።

2ኛው አካሄድ ቅድመ መድረሻውን ሳድስ አድርጎ መጨረሻውን ሳብእ ማድረግ ወይም ቅድመ መድረሻውን ሳድስ አድርጎ መድረሻውን ሳብእ አድርጎ ትን መጨመር ነው።የቀደሰ የተንበለ የጦመረ የባረከ የሴሰየ ቤቶች በዚህ መልኩ ይሄዳሉ።
ቀድሶ/ቀድሶት=ማመስገን
ባርኮ/ባርኮት=ማመስገን/መባረክ
ተንብሎ/ተንብሎት=መለመን=begging
ጦምሮ/ጦምሮት=መጻፍ=Writing
ዴግኖ/ዴግኖት=መከተል ይላል።

ጥያቄ
1ኛ ለሚከተሉት ቃላት ንኡስ አንቀጽ አውጡ
ወደሰ=አመሰገነ
ሞተ=ሞተ
ሰምረ=ወደደ
2ኛ የሚከተሉትን አማርኛዎች ወደ ግእዝ ቀይር
መጮህ (hint ጸርሐ=ጮኽ)
ደስ መሰኘት (hint ተፈግዐ=ደስ ተሰኘ)
ዝም ማለት (hint አርመመ=ዝም አለ)


መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግእዝ ክፍል 37
©ንኡስ አንቀጽ~~Gerund©
ክፍል 2
ይህ ንኡስ በ5ቱ አእማድ ይሄዳል
ቀቲል/ቀቲሎት=መግደል
አቅትሎ/አቅትሎት=ማስገደል
ተቃትሎ/ተቃትሎት=መገዳደል
አስተቃትሎ/አስተቃትሎት=ማገዳደል
ተቀትሎ/ተቀትሎት=መገደል።
እያለ በ5ቱ አእማድ ማለት በአድራጊ በተደራጊ በአደራራጊ በተደራራጊ በአስደራጊ ይሄዳል።በአድራጊ እንዴት እንደሚሄድ ሙሉ ዝርዝሩን ክፍል 36 ላይ ገልጸናል።በቀሪዎቹ በ4ቱ እንዴት እንደሚሄድ እንመልከት።
በ4ቱም ቅድመ መድረሻውን ሳድስ እያደረገ ወይም እንዲህ አድርጎ በተጨማሪ ትን በመጨመር ይወጣል።ይኽውም
አቅትሎ/አቅትሎት
ተቀትሎ/ተቀትሎት
ተቃትሎ/ተቃትሎት
አስተቃትሎ/አስተቃትሎት
እያለ ይሄዳል።በቀደሰ ቤት
አቀድሶ/አቀድሶት=ማስመስገን
ተቀድሶ/ተቀድሶት=መመስገን
አስተቃድሶ/አስተቃድሶት=ማመሰጋገን
ተቃድሶ/ታቃድሶት=መመሰጋገን
እያለ ይሄዳል።ሌሎችንም አርእስት እንዲህ እንዲህ እያልን ማርባት እንችላለን።
ግልጽ እንዲሆንልን ግን የ8ቱን አርእስት አእማድ እንይ
1 ቀተለ=ገደለ
አቅተለ=አስገደለ
ተቃተለ=ተገዳደለ
ተቀትለ=ተገደለ
አስተቃተለ=ተጋደለ
2 ቀደሰ=አመሰገነ
ተቀደሰ=ተመሰገነ
ተቃደሰ=ተመሰጋገነ
አስተቃደሰ=አመሰጋገነ
አቀደሰ=አስመሰገነ
3 ባረከ=ባረከ/አመሰገነ
አባረከ=አስባረከ/አመሰገነ
ተባረከ=ተባረከ/ተመሰገነ
ተባረከ=ተማሰጋገነ
አስተባረከ=አመሰጋገነ
3 ተንበለ=ለመነ
አተንበለ=አስለመነ
ተተንበለ=ተለመነ
ተተናበለ=ተለማመነ
አስተተናበለ=አለማመነ
4 ጦመረ=ጻፈ
ተጦመረ=ተጻፈ
አጦመረ=አጻፈ
ተጥዋመረ/ተጡዋመረ/ተጠዋመረ=ተጻጻፈ
አስተጥ/ጠ/ጡዋመረ=አጻጻፈ
5 ሴሰየ=መገበ
ተሴሰየ=ተመገበ
አሴሰየ=አስመገበ
ተሲ/ሰ/ስያሰየ=ተመጋገበ
አስተሲ/ሰ/ስያሰየ=አመጋገበ
6 ክህለ=ቻለ
አክሀለ=አስቻለ
ተክህለ=ተቻለ
ተካሀለ=ተቻቻለ
አስተካሀለ=አቻቻለ
እያለ እያለ ይሄዳል።ይህም የግእዝን ቋንቋ ጥልቀት ያሳያል።

ጥያቄ
የሚከተሉትን ተርጉም
1 እምተናግሮ ይሄይስ አርምሞ
2 እፎ ይክል ብእሲ ዳግመ ተወልዶ
3 ከመራብ መሞት ይሻላል (ርኅበ=ተራበ)
4 መጠመቅ ይገባናል (ይገባናል=ይደልወነ፥ተጠምቀ=ተጠመቀ)

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግእዝ ክፍል 38
አሉታዎች~~Negatives
በግእዝ ቋንቋ አሉታ የሚሆኑ 3 ናቸው እነዚህም ©ኢ፣አኮ እና ሐሰ© ናቸው።አኮ የውእቱ ወይም የነባር አንቀጾች (auxiliary verbs) አሉታ ነው።ይህም ማለት እርሱ አይደለም ለማለት አኮ ውእቱ he is not/he isn't ይላል።ኢ አሉታ የሚሆነው ለማሰሪያ አንቀጽ ነው።ይህም ማለት መጣ ለማለት መጽአ እንላለን።አልመጣም ለማለት ደግሞ ኢመጽአ እንላለን።ሐሰ ደግሞ መጨረሻ ላይ እየመጣ አሉታ ይሆናል።ይህም ማለት ክርስቶስን ሁለት አካል ሁለት ባህርይ እንላለንን ብሎ ይጠይቅና ሐሰ አንልም ይላል።
በተለየ መንገድ የቦ ዝርዝር አሉታ "አል" ነው።
ቦ=አለ
ብየ=አለኝ=have
ብነ=አለን=have
ባቲ=አላት=has
ቦቱ=አለው=has
ቦሙ ቦን ብክሙ ብክን እያለ በ10ሩ መራሕያን ይዘልቃል።የዚህ የቦ ዝርዝር ብቻ አሉታው "አል" ነው።ይህም ማለት ለምሳሌ ቦ=አለ ለሚለው አሉታው አልቦ=የለም ይላል ማለት ነው።

ኃይል አለን.....................አማርኛ
ብነ ኃይል.......................ግእዝ
We have a power......English
የዚህ አሉታ እንደሚከተለው ቀርቧል
ኃይል የለንም...................አማርኛ
We haven't a power.....English
አልብነ ኃይል......................ግእዝ
በአጭሩ የቦ ዝርዝሮች አሉታ ፊት ለፊታቸው "አል"ን በመጨመር ይገኛል።አል አሉታ የሚሆነው ለቦ ዝርዝሮች ብቻ ነው።

©© አሉታ የሚሆነው ለማሰሪያ አንቀጾች (verbs) ነው።ይህም ማለት ቀተለ ገደለ ለሚለው ቃል አሉታው ኢቀተለ አልገደለም ይላል ማለት ነው።በዓረፍተ ነገር ለማየት ያህል።

ይሁዳ ገንዘብ ይወዳል................. አማርኛ
Judah loves a mony.............. English
ይሁዳ ያፈቅር ንዋየ....................... ግእዝ

የዚህ አሉታ እንደሚከተለው ቀርቧል።

ይሁዳ ገንዘብ አይወድም...............አማርኛ
Judah doesn't love a money....English
ይሁዳ ኢያፈቅር ንዋየ.....................ግእዝ

©አኮ© አሉታ የሚሆነው ለ10ሩ መራሕያን ነባር ሆነው ሲያገለግሉ ነው።ይህም አኮ ማለት አይደለም ማለት ነው።የነው አሉታ ነው። ናቡከደነጾር ሰው ነው ለሚለው አሉታ ናቡከደነጾር ሰው አይደለም ነው።በምሳሌ እንየው።

አርጌንስ ቅዱስ ነው...................አማርኛ
Origen is a saint..................English
አርጌንስ ቅዱስ ውእቱ.................ግእዝ
የዚህ አሉታ እንደሚከተለው ቀርቧል።

አርጌንስ ቅዱስ አይደለም.............አማርኛ
Origen isn't a saint...............English
አኮ ቅዱስ አርጌንስ.....................ግእዝ
በአጭሩ ሲጠቃለል የቦ (have,has) አሉታ "አል/not" ሲሆን የመራሕያን (be,is,was,were) አሉታ "አኮ/not" ነው። የግሶች (verbs,do,does,did) አሉታ "ኢ/not" ነው።በእንግሊዘኛ ሁሉም not ነው በግእዝ ግን ከላይ እንዳየነው 3 ነው።

ጥያቄ
ለሚከተሉት ቃላት አሉታ አውጣ
1 ብኪ ነውር
2 ኄራን ውእቶሙ
3 ሐነጸ ቤተ
4 ተወልደ ዮም
5 ጎሐ ጽባሕ

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግእዝ ክፍል 39
ጥያቄ መፍጠር~~Forming Questions
በግእዝ ቋንቋ ጥያቄ ለመጠየቅ ጥያቄ ምልክት የለም።በጥያቄ ምልክት ፈንታ "ኑ" የምትለዋን ፊደል እንጠቀማለን።በአማርኛ ጸገየ መጣ? ብለን ጥያቄ ምልክት ካደረግን መምጣት አለመምጣቱን እየጠየቅን መሆኑ ግልጽ ነው።ጸገየ መጣ። ብለን አራት ነጥብ ካደረግን ግን መምጣቱ የተረጋገጠ ነው።በግእዝ ጸገየ መጣ? ብለን ስንጠይቅ መጽአኑ ጸገየ ይላል። በጥያቄ ምልክቱ ፈንታ ©© ፊደልን እንደተጠቀምን አስተውል።

ግልጽ እንዲሆንልን በምሳሌ እንመልከት።

አቤሜለክ ተኝቷል?.................አማርኛ
Is Abemelek sleeping.......English
ሰከበኑ አቤሜሌክ....................ግእዝ

እንዲህ እንዲህ እያለ ይሄዳል።

ጥያቄ
ግእዙን ወደ አማርኛ አማርኛውን ወደ ግእዝ ተርጉም።
1 ሀሎኑ በዝ ሰማይ አምላከ እስራኤል
2 ቅዱስ ሚካኤል ረዳችሁ?
3 ቦኑ ለከንቱ ኪዳንኪ ኮነ


መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ልሳነ ግእዝ ክፍል 40
የመጨረሻ ክፍል
ይህ የመጨረሻ ክፍል ስለሆነ እስካሁን የተማርነውን መሰረት አድርጋችው 20 የምርጫ ጥያቄዎች አሉ።እስካሁን በድብቅም በገሀድም ስትከታተሉ የነበራችሁ ጥያቄውን መልሱ። በዚህ አድራሻችን ላኩልን @learnGeezbot
1ኛ ተስዓ ወተሰዓቱ በግእዝ ሲጻፍ እንዴት ነው?
ሀ.፱፱
ለ.፺፺
ሐ.፺፱
2ኛ ማርያም ወማርታ.......ይትቀበልዎ ለክርስቶስ።
ሀ.ሮጹ
ለ.ሮጻ
ሐ.ሮጽክሙ
መ.ሮጸት
3ኛ ፀሐይ በምሥራቅ ወጣች ለማለት በግእዝ ትክክለኛው የቱ ነው።
ሀ.ፀሐይ ሠረቀት በምስራቅ
ለ.ፀሐይ ሠረቀት በምሥራቅ
ሐ.ጸሐይ ሰረቀት በምስራቅ
መ.ፀሐይ ሰረቀት በምሥራቅ
4ኛ 982 በግእዝ ሲጻፍ እንዴት ነው?
ሀ.፱፻፹፪
ለ.፱፻፰፪
ሐ.፺፻፰፪
መ.፱፼፹፪
5ኛ ውእቱ ብሎ ሀገሩ ካለ አነ ብሎ......ይላል
ሀ.ሀገርከ
ለ.ሀገርየ
ሐ.ሀገራ
መ.ሀገርኪ
6ኛ ማርያም.........እምኩሉ ፍጥረት
ሀ.የዐቢ
ለ.ተዐቢ
ሐ.አዐቢ
መ.ነዐቢ
7ኛ መጽአት ማርያም ምስለ ገብርኤል ለሚለው የአማርኛ ትርጉሙ......ነው
ሀ.ማርያምና ገብርኤል መጡ
ለ.ማርያም ወደ ገብርኤል መጣች
ሐ.ማርያም ከገብርኤል ጋር መጣች
8ኛ መሰረተ ዜማ.....ያሬድ ካህን
ሀ.ወጠነ (ነ ጠብቆ)
ለ.ወጠኑ
ሐ.ወጠነ (ነ ላልቶ)
መ.ወጠንክሙ
9ኛ አእመረ ብሎ አእመርኩ ካለ ሰበከ ብሎ ምን ይላል?
ሀ.ሰበክኩ
ለ.ሰበኩ (ኩ ጠብቆ)
ሐ.ሰበኩ (ኩ ላልቶ)
10ኛ መድኃኒ እና ዓለም ሲናበቡ....ይሆናሉ
ሀ.መድኃኒዓለም
ለ.መድኃኔዓለም
ሐ.መድኃኒዓለመ
መ.መድኃኔዓለመ
11ኛ ወደ እኔ መቼ ትመጣለህ በግእዝ.....ነው።
ሀ.ማእዜ ትመጽኢ ኀቤየ
ለ.ማእዜ ይመጽእ ኀቤየ
ሐ.ማእዜ ትመጽእ ኀቤሁ
መ.ማእዜ ትመጽእ ኀቤየ
12ኛ ኢይፈርሆ ለሞት ወደ አማርኛ ሲተረጎም..... ይላል።
ሀ.ሞትን አልፈራውም
ለ.ሞትን አልፈራትም
ሐ.ሞትን አላስፈራውም
መ.ሞትን አላስፈራትም
13ኛ ተሰቅለ ክርስቶስ....... መስቀል
ሀ.ላእለ
ለ.ዲበ
ሐ.መልእልተ
መ.ሁሉም
14ኛ ክርስቶስ ሞተ ሞተ ዚአነ የሚለው ሲተረጎም...... ይሆናል።
ሀ.ክርስቶስ የእኛን ሞት ሞተ
ለ.የእኛ ሞት በክርስቶስ ሞተ
ሐ.የእኛ ሞት ክርስቶስ ሞተ
መ.መልሱ የለም
15ኛ እኛስ የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን የሚለው ወደ አማርኛ ሲተረጎም?
ሀ.ንሐነ ንሰብክ ክርስቶስ ዘተሰቅለ
ለ.ንሕነሰ ንሰብክ ክርስቶስሀ ዘተሰቅለ
ሐ.ንሕነሰ ንሰብክ ክርስቶስሃ ዘተሰቅለ
መ.ንሕነ ንሰብክ ክርስቶስሃ ዘተሰቅለ
16ኛ ደብረ መድኃኒት ከሚለው ቃል ዘርፉ ማን ነው?
ሀ.ደብር
ለ.ደብረ
ሐ.መድኃኒተ
መ.መድኃኒት
17ኛ ......ተሰቅለ ክርስቶስ ፀሐይ ጸልመ።
ሀ.ሶበ
ለ.አመ
ሐ.ጊዜ
መ.ሁሉም
18ኛ እናንተን አያሳየኝ የሚለው ቃል ወደ ግእዝ ሲተረጎም.....ይሆናል።
ሀ.ኪያክሙ ኢያርእየኒ
ለ.ኪያክን ኢያርእየኒ
ሐ.ለሊክሙ ኢያርእየኒ
መ.ሀ እና ለ
19ኛ ንሕነ ብለን ለሊነ ካልን አንትን ብለን ምን እንላለን?
ሀ.ለሊክሙ
ለ.ለሊክን
ሐ.ለልየ
20ኛ የ "መርሐ" አሉታ.....ነው
ሀ.ኢይመርሕ
ለ.አኮ መርሐ
ሐ.ኢመርሐ
መ.አልመርሐ
አነሳስቶ ላስጀመረን
አስጀምሮ ላስፈጸመን
እግዚአብሔር ክብር
ምስጋና ይግባው

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግእዝ ቋንቋ ክፍል 41
አገባቦች
1
ትርጉሙ እና ወይም በእንግሊዘኛ and ማለት ነው።ሚካኤልና ገብርኤል ለማለት ብንፈልግ በግእዝ ሚካኤል ወገብርኤል እንላለን ማለት ነው።
2 ባሕቱ/ዳእሙ
በአማርኛ ግን ነገር ግን ማለት ነው።በእንግሊዘኛ but/though/although የሚለው ነው።ለምሳሌ ሰማእት መሆን እፈልጋለሁ ነገር ግን እፈራለሁ የሚለውን ወደ ግእዝ ስንቀይረው እፈቅድ እኩን ሰማእቱ ዳእሙ እፈርህ ወይም ባሕቱ እፈርህ ይላል።
3 አመ/ሶበ/ጊዜ
እኒህ በአማርኛ በ....ጊዜ ተብለው ይተረጎማሉ በእንግሊዘኛ when የሚለው ይተካቸዋል።
ለምሳሌ ሕጻን በነበርኩ ጊዜ /when i was a child/አመ ነበርኩ ሕጻነ ይላል ማለት ነው።

ይቆየን

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግእዝ ክፍል 42
©ጥሬ ዘርና ዘመድ ዘር©
እኒህ ከማሰሪያ አንቀጽ (verb) የሚወጡ ስሞች (nouns) ናቸው።ናማ ልንገርህ/ነይማ ልንገርሽ በጣም ቀላል ነው።ለምሳሌ ተሰፈወ ተስፋ አደረገ ከሚለው ተስፋ የሚል ጥሬ ዘር ይወጣል።ደምፀ=ተሰማ ከሚለው ግስ ደግሞ ድምፅ የሚል ዘመድ ዘር ይወጣል።ስለዚህ አወጣጡ እንደሚከተለው ይቀርባል።
ዘመድ ዘር
ዘመድ ዘር የሚባለው ከግሱ/ማሰሪያ አንቀጹ ላይ ምንም ዓይነት ሌላ ባእድ ቀለም ሳይጨምር የመጨረሻው ፊደል ሳድስ ሆኖ ከወጣ ነው።ለምሳሌ ደምፀ=ተሰማ ማለት ነው።ከዚህ የወጣው ዘመድ ዘር ድምፅ ይላል።አስተውል የወጣው ዘመድ ዘር የመጨረሻ ፊደል "ፅ" ሳድስ ናት።ይህን የመሰለ ሌላ
አገረ=ተራመደ ብሎ=እግር
ፈትሐ=ፈረደ ብሎ=ፍትሕ
ሀለበ=አለበ ብሎ=ሐሊብ
ይህን ይህን የመሰለው ዘመድ ዘር ይባላል። አስተውል ዘመድ ዘር ከግሱ ላይ ምንም የሚጨምረው ሌላ ፊደል የለም።የፊደላት ቅርጽ ሊለያይ ይችላል መጨረሻው ግን ሳድስ ነው።ከግሱ ላይ የሚቀንሰው ፊደል ግን ሊኖር ይችላል ለምሳሌ
አንቀልቀለ=ተነዋወጠ ብሎ=ቃል ይወጣል። አስተውል ቃል ዘመድ ዘር ነው ግን "አ" እና "ን"ን ከግሱ እንደቀነሰ ተመልከት ሌላም ምሳሌ
አፍቀረ=ወደደ ብሎ ፍቅር
አማእበለ=ማእበል አደረግል ብሎ ማእበል
አመዐርዐረ=አጣፈጠ ብሎ=መዓር
ዘመድ ዘር በአጭሩ ይህን ይመስላል።
ጥሬ ዘር
ጥሬ ዘርም እንደ ዘመድ ዘር ከግስ የሚወጣ ስም ሲሆን ከዘመድ ዘር የሚለየው ሲወጣ የመጨረሻ ፊደሉ ሳድስ ሳይሆን ራብእ ኀምስ እና ሳብእ በመሆኑ ነው።ለምሳሌ ከተሰፈወ ተስፋ የሚል ጥሬ ዘር ይወጣል።አስተውል የመጨረሻ ፊደሉ "ፋ" ራብእ ነው።በሳብእ ከብረ ከበረ ብሎ ከበሮ ይወጣል።በሃምስ መነነ ናቀ ብሎ ምናኔ ይወጣል።በጥሬ ዘርም የሚጨመር ምንም ዓይነት ባእድ ፊደል የለም።ምናልባት ግን ከነበረው ግስ ቀንሶ ሊወጣ ይችላል ምሳሌ ተሠገወ=ሰው ሆነ ብሎ ሥጋ የሚል ጥሬ ዘር ይወጣል።አስተውል "ተ" እና "ወ" ተጎርዳዋል።

ተጨማሪ ምሳሌ
ቀደሰ=አመሰገነ ብሎ=ቅዳሴ
አንዘረ=መሰንቆ መታ ብሎ=እንዚራ
ሰበከ=ጣዖት ሰራ ብሎ=ስብኮ
እያለ እያለ ይሄዳል።

የእለቱ ጥያቄዎች
የትኛው ጥሬ ዘር የትኛው ዘመድ ዘር እንደሆነ ግለጽ።

1 ፍካሬ
2 ሰብል
3 አእምሮ
4 ፈጠራ
5 ነጎድጓድ

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግእዝ ክፍል 43
®® ባእድ ዘር እና ምእላድ®®
እኒህም ከግስ (verb) የሚወጡ ስሞች ናቸው ለምሳሌ ቀደሰ=አመሰገነ ከሚለው ቃል "መቅደስ" የሚል ባእድ ዘር ይወጣል።ቆረበ ከሚለው ደግሞ ቁርባን የሚል ምእላድ ይወጣል።እያንዳንዳቸውን በደንብ እንመልከታቸው።
ባእድ ዘር
ከግሱ ከመነሻው ላይ ሌላ ባእድ ፊደል ጨምሮ የሚወጣ ሲሆን መጨረሻውም ሳድስ ነው።ለምሳሌ ቀደሰ=አመሰገነ ከሚለው ግን መቅደስ የሚል ባእድ ዘር ወጥቷል።ከመጀመሪያው ላይ"መ" ፊደልን ባእድ እንደጨመረ አስተውል።ባእድ የሚሆኑ ቃላት "ተ፥መ፥አ" ናቸው ከለለ=ጋረደ ብሎ ተክሊል ይወጣል።ሰከለ=አፈራ ብሎ አስካል ይወጣል።
ገብረ=ሰራ ብሎ ምግባር
ገብረ=ሰራ ብሎ ተግባር
ቀተለ=ገደለ ብሎ ምቅታል፥እቅታል፥ትቅታል
ወረደ=ወረደ ብሎ ሙራድ
ቆመ=ቆመ ብሎ ተቅዋም፥ምቅዋም
እያለ ይሄዳል።
ምእላድ
ምእላድ ደግሞ ከመጨረሻ ፊደሉ ላይ ባእድ ጨምሮ የሚወጣ ዘር ነው።ለምሳሌ ቆረበ=ቆረበ ከሚለው ግስ "ቁርባን" የሚል ምእላድ ይወጣል አስተውል ባእድ "ን"ን ከመጨረሻ እንደጨመረ። ምእላድ የሚሆኑ ቀለማት እኒህ ናቸው "ይ፥ት፥ን፥ው፥ል"
ኀበሰ=ጋገረ ብሎ=ኅብስት
ቀደሰ=አመሰገነ ብሎ=ቅዱሳን
እደው፥ለያልይ፥ኪሩቤል ሌሎች ምሳሌዎች ናቸው።

የእለቱ ጥያቄዎች
ምእላዱንና ባእድ ዘሩን ለይ

1 ቅድሳት
2 አድባር
3 መብረቅ
4 ተግሣፅ

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግእዝ ክፍል 44
©ሳቢ ዘር©
ይህ ደግሞ የግሱን መድረሻ ፊደል ብቻ ግእዝ አድርጎ ሌላው ሳድስ ያደርግና "ት" ፊደልን የሚጨምር ነው።ለምሳሌ ሠርዐ ሰራ ብሎ ሥርዐት ይወጣል።አስተውል "ዐ" የመጨረሻዋ ፊደል ብቻ ግእዝ ሆና ሌላው ሳድስ ሆኖ "ት" ፊደልን መጨመር ነው።ሌላ ምሳሌ
ሰበከ=አስተማረ ብሎ ስብከት
መሐረ=ማረ ብሎ ምሕረት
ሐይወ=ኖረ ብሎ ሕይወት
እያለ ይሄዳል።
የቆመ ቤት ማለትም 2 ፊደል ሆኖ በሳብእ የጀመረ የተለየ አካሄድ አለው ይሄውም መነሻውን ካእብ አድርጎ መድረሻውን ግእዝ አድርጎ "ት"ን መጨመር ነው።ቆመ ብሎ ቁመት ይላል።
የሤመ ቤቶች ማለት ሁለት ፊደል ሆነው በኃምስ የሚጀምሩት ደግሞ መነሻቸውን ሣልስ መድረሻውን ግእዝ አድርገው "ት"ን ይጨምራሉ ሤመ ሾመ ብሎ ሢመት ይላል።

ሌላው በ"ወ" የሚጀምሩ ግሶች ሳቢዘራቸው "ወ"ን ጎርዶ ይወጣል።ይህም ማለት ለምሳሌ ወረደ=ወረደ ብሎ ውርደት ሳይሆን ርደት ይላል።ወለደ=ወለደ ብሎ ልደት ይላል እንጂ ውልደት አይልም።

ደጊመ ቃል ያላቸው ቃላት ሳቢዘራቸው ከተደገመው አንዱን ፊደል ጎርደው ይወጣል ለምሳሌ ሰደደ=ሰደደ ብሎ ስደት ይላል እንጂ ስድደት አይልም።ደ ስለተደገመ አንዱን ደ ጥለን አንዱን ብቻ ይዞ ይወጣል።

ወስብሀት ለእግዚአብሔር

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግእዝ ክፍል 45
© ባዕድ ከምእላድ ©
ባእድ ከምእላድ የሚባለው ከመነሻው እና ከመድረሻው ላይ ባእድ ሲጨምር ነው። ለምሳሌ "መሀረ=አስተማረ ብሎ=ትምህርት" ይወጣል።አስተውል ትምህርት ባእድ ከምእላድ ነው ምክንያቱን ከመነሻው እና ከመድረሻው ላይ "ት" ፊደልን ጨምሯል።ሌላ ምሳሌ
ቀሰፈ=ቀሰፈ ብሎ=መቅሰፍት
ሰፈረ=ለካ ብሎ=መስፈርት
አወፈየ=ሰጠ ብሎ=ትውፊት
ድኅነ=ዳነ ብሎ=መድኃኒት
እያለ እያለ ይወጣል።
©ባዕድ ጥሬ ዘር©
ይህ ደግሞ ከመነሻው ባእድ ጨምሮ የመጨረሻው ፊደል ራብእ ወይም ኃምስ ወይም ሳብእ ሲሆን ነው።ለምሳሌ ሰፈነ=ገዛ ብሎ ምስፍና ባዕድ ጥሬ ዘር ይወጣል።ባዕድ ያስባለው "ም"ን መጨመሩ ሲሆን ጥሬ ያስባለው ደግሞ የመጨረሻው ፊደል "ና" ራብእ ስለሆነ ነው።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግእዝ ክፍል 46
©©ጥሬ ምእላድ©©
ጥሬ ምእላድ የሚባለው ከግሱ መጨረሻ ባእድ የሚጨምር ሆኖ በተጨማሪም ያው የተጨመረው ፊደል ራብእ ወይም ኃምስ ወይም ሳብእ ከሆነ ነው።ለምሳሌ ነፅሐ=ንፁሕ ሆነ ብሎ ንፅሕና ይወጣል።ይህ ንጽሕና ጥሬ ምእላድ ይባላል።ምእላድ ያስባለው ባእድ "ና"ን መጨረሻ ላይ ስለጨመረ ሲሆን ጥሬ ያስባለው ደግሞ ይህችው የተጨመረችዋ "ና" ራብእ ስለሆነች ነው።ተጨማሪ ምሳሌ
ተትህተ=ትሁት ሆነ ብሎ=ትህትና
ሀለወ=ኖረ ብሎ=ሕልውና
ተደንገለ=ድንግል ሆነ ብሎ=ድንግልና
ኀለየ=አሰበ ብሎ=ኅሊና
እያለ እያለ ይወጣል።

ዘመድ ዘር፥ጥሬ ዘር፥ባእድ ዘር፥ምእላድ፥ባእድ ከምእላድ፥ጥሬ ምእላድ፥ባእድ ጥሬ፥ሳቢዘር ሆነው በዘርነታቸው ከግሱ የሚቀራረብ ስምን ያወጣሉ።ለምሳሌ አንድ እንመልከት።ቀተለ=ገደለ ከሚለው ቀትል የሚል ዘመድ ዘር ይወጣል።ስለዝህ ቀትል የሚተረጎም ገደለ ከሚለው ግስ ጋር የተቀራረበ ስም ይወጣል ምሳሌ ግድያ ጦርነት ብለን ልንተረጉመው እንችላለን።ሳቢ ዘር ቅትለት ብሎ አገዳደል መግደል መገደል ይላል።ባእድ ዘር ምቅታል ብሎ መግደያ መገደያ ማስገደያ መገዳደያ ማገዳደያ ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።
መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግእዝ ክፍል 47
©ውስጠዘነት ያላቸው ዘሮች©©
እኒህ ዘሮች ቃላቸው ሲመረመር የቅጽልነት (Adjective) ሚና ያላቸው ወይም የሰው መጠሪያ ስም ከሆኑ ውስጠዘነት አላቸው ይባላል።ግልፅ እንዲሆንልን አንድ በአንድ እንይ
© ዘመድ ዘር ውስጠዘ©
ይህ ልክ ዘመድ ዘር ሆኖ ግን የሰው ስም ወይም ቅጽል ከወጣበት ነው።ምሳሌ ባረከ ብሎ ባሮክ ቢወጣ ይህ የሰው ስም ስለሆነ ዘመድ ዘር ውስጠዘ ይባላል።ተዘምደ=ዘመድ ሆነ ብሎ ዘመድ ቢወጣ ይህ ዘመድ ዘር ውስጠ ዘ ይባላል ምክንያቱም ውስጡ ሰውነት አለበት።
©ባእድ ዘር ውስጠዘ©
ይህም ባእድ ዘር ሆኖ የሰው ስም ከሆነ ነው።ምሳሌ ሬመ=ከፍ ከፍ አለ ብሎ ማርያም ትወጣለች።ለአከ ብሎ መልአክ ይወጣል።
©ጥሬ ውስጠዘ©
ይህ ደግሞ ጥሬ ሆኖ የሰው ስም ከወጣበት ነው።ምሳሌ ኀመሰ=ዋኘ ብሎ ሙሴ ይወጣል ሖረ ሄደ ብሎ ሐራ/ወታደር ይወጣል።
©ምእላድ ውስጠዘ©
ምእላድ ሆኖ የሰው ስም ከወጣበት ነው።ምሳሌ ሐይወ ዳነ ብሎ ሔዋን ይወጣል
©ጥሬ ምእላድ ውስጠዘ©
ጥሬ ምእላድ ሆኖ ውስጠዘነት ያለው ነው ምሳሌ ኖተወ=ዋኘ ብሎ ኖትያ/ዋናተኛ ይወጣል።
ጉልት
ጉልት የሚባለው በካእብ ጨርሶ የሚወጣ ነው። ምሳሌ ተልእለ ከፍከፍ አለ ብሎ ላእሉ ጉልት ይወጣል።ቀደመ ቀደመ ብሎ ቀዲሙ ይወጣል።
©ጉልት ውስጠ ዘ©
ውስጠዘነት ያለው ጉልት ነው።ምሳሌ አከለ በቃ ብሎ ኩሉ ይወጣል።አሐደ አንድ አደረገ ብሎ አሐዱ ይወጣል።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግእዝ ክፍል 48
©©የውስጠ ዘ ትርጉም©©
ውስጠ ዘ በ15 ይተረጎማል/በመራሕያን ከገባነው በ45 ይተረጎማል።ምሳሌ ቅዱስ
ያመሰገነ፥የተመሰገነ፥ያስመሰገነ፥ያመሰጋገነ፥የተመሰጋገነ፥የሚያመሰግን፥የሚመሰገን፥የሚያስመሰግን፥የሚያመሰጋግን፥የሚመሰጋገን፥አመስጋኝ፥ተመስጋኝ፥አመሰጋጋኝ፥ተመሰጋጋኝ፥አስመስጋኝ።ያመሰገንኩ፥የማመሰግን፥የምመሰገን፥የማስመሰግን፥የማመሰጋግን፥የተመሰገንኩ፥ያስመሰገንኩ፥የተመሰጋገንኩ፥ያመሰገንክ፥ያስመሰገንክ፥ያመሰጋገንክ፥የተመሰገንክ፥የተመሰጋገንክ፥የምታመሰግን፥የምታመሰጋግን፥የምታስመሰግን.......... ወዘተ እያለ ይተረጎማል።
መድበል
መድበል ማለት ለብዙ ወንዶችና ለብዙ ሴቶች ቅፅል የሚሆን ሲሆን።አወጣጡም የመጨረሻ ፊደሉ ሳድስ አድርጎ ሌላውን ግእዝ አድርጎ "ት"ን የሚጨምር ነው።ለምሳሌ ቀተለ ገደለ ብሎ ቀተልት ይወጣል።አስተውል "ቀ" እና "ተ" ግእዝ ሆነው "ል" ሳድስ ሆኖ "ት"ን ጨምሯል።ትርጉሙ ቅቱላን ወይም ቅቱላት ካለው ጋር ተመሳሳይ ነው።ሌላ ምሳሌ
ጸሐፈ=ጻፈ ብሎ=ጸሐፍት ይወጣል
ገብረ=ሰራ ብሎ=ገበርት ይወጣል።

በ "ሀ" እና "አ" የሚጨርሱ ግሶች ግን የተለየ አካሄድ አላቸው ይኽውም ቅድመ መድረሻቸውን ራብእ አድርገው መነሻቸውን ግእዝ አድርገው መድረሻውን ሳድስ አድርገው "ት"ን ይጨምራሉ ምሳሌ መርሐ ብሎ መራሕት ይላል።ገዝአ ብሎ ገዛእት ይላል።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግእዝ ክፍል 49
ጥያቄዎች
1 ከሚከተሉት ውስጥ ሳቢዘር የሆነው የቱ ነው?
ሀ ፍርሀት
ለ እምነት
ሐ ሕብረት
መ ሁሉም መልስ ናቸው
2 ዘመድ ዘር የሆነው የቱ ነው?
ሀ ሁከት
ለ ጥበብ
ሐ ዕርገት
መ ፍጥረት
3 ዘር ውስጠዘ የሆነው የትኛው ነው?
ሀ ኤዶም
ለ ኀዘን
ሐ ሰቆቃው
መ ነፀብራቅ
4 ባዕድ ዘር የሆነው የቱ ነው?
ሀ ፍጥነት
ለ ሠርክ
ሐ ምዕራፍ
መ ክርስቲያን
5 ባዕድ ውስጠዘ የሆነው የቱ ነው?
ሀ አክሊል
ለ ማርያም
ሐ መስቀል
መ ተአምር
6 ጥሬ ዘር የሆነው የትኛው ነው?
ሀ ይባቤ
ለ ስብሐት
ሐ ግርማ
መ ሀ እና ሐ
7 ጥሬ ውስጠ ዘ የሆነው የትኛው ነው?
ሀ እድሜ
ለ ጥያቄ
ሐ ሥላሴ
መ ደብተራ
8 ባዕድ ጥሬ ዘር የሆነው የትኛው ነው?
ሀ ንባብ
ለ መሰንቆ
ሐ ፍሬ
መ ከርቤ
9 ምእላድ የሆነው የቱ ነው?
ሀ ስልጣን
ለ ትርሲት
ሐ ብርሃን
መ ሁሉም
10 ምእላድ ውስጠዘ የሆነው የትኛው ነው?
ሀ ተውኔት
ለ መለኮት
ሐ ሐሴት
መ ሃይማኖት
11 ጥሬ ምእላድ የሆነው የቱ ነው?
ሀ ብህትውና
ለ ማዕዶት
ሐ አሜን
መ ቅንዋት
12 ጥሬ ምእላድ ውስጠዘ የሆነው የትኛው ነው?
ሀ ልቡና
ለ ሐዋርያ
ሐ ግርማ
መ ሐመልማል
13 ባእድ ከምእላድ የሆነው የቱ ነው?
ሀ ምንኩስና
ለ አኮቴት
ሐ መዓልት
መ ማዕከል
14 ጉልት የሆነው የቱ ነው?
ሀ ሠለስት
ለ ስድሳ
ሐ ታሕቱ
መ ረድኤት
15 መድበል የሆነው የቱ ነው?
ሀ እረፍት
ለ እፍረት
ሐ ኀለፍት
መ ኅልፈት

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ክፍል 50 ! መሠረተ ግእዝን ሼር ያድርጉ! የአባላቱን/የሚማሩትን/ ቁጥር ከፍ እናድርግ🙏

ይህንን ሊንክ ይጫኑት&Share
👇👇👇
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1

https://www.tg-me.com/learnGeez1
https://www.tg-me.com/learnGeez1

👆 Join ያድርጉና የግእዝ ቋንቋን ይማሩ!!!!

@learnGeezbot
👆👆👆
ለአስተያየት ይጠቀሙ
ግእዝ ክፍል 51
የቀለም ዓይነቶች በግእዝ
ፀዐዳ=ነጭ=white
ጸሊም=ጥቁር=black
ቀይሕ=ቀይ=red
ሐመልሚል=አረንጓዴ=green
የአካል ክፍሎች በግእዝ
እድ=እጅ
አንፍ=አፍንጫ
አፍ=አፍ
ሥእርት=ጸጉር
ክሳድ=አንገት
ርእስ=ራስ
ዓይን=ዓይን
እራኅ=መዳፍ
ጽፍር=ጥፍር
ደም=ደም
አካል=አካል
እንግድዓ=ደረት
ሐቌ=ወገብ
ብርክ=ጉልበት
ልብ=ልብ
እዝን=ጆሮ
እስትንፋስ=ትንፋሽ
ጉርኤ=ጉረሮ
መትከፍ=ትከሻ
ዘባን=ጀርባ
ኅንብርት=እምብርት

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግእዝ ክፍል 52
© Engineering words በግእዝ ©
መሠረት=መሠረት=foundation
ጠፈር=ጣራ=Roof
አረፍት=ግድግዳ=wall
ሕንጻ=ሕንጻ=building
ኬንያ=መሐንዲስ=engineer
ፍኖት=መንገድ=road
ማይ=ውሃ=water
ጽኑዕ=የጸና=consistent
ኮኲሕ=አለት=rock
ጠያር=አውሮፕላን=aeroplane
ሐመር=መርከብ=ships
ሰማይ=ሰማይ=sky
አዘቅት=የውሃ ጉድጓድ=well
ዋካ=ብርሃን=light
ታዕካ/ጽርሕ=አዳራሽ=hall
ሐነፀ=ሰራ=build/built
መንገኒቅ=ጥይት/ነፍጥ=Gun

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግእዝ ክፍል 53
©ቅኔ ፩©
እነ ተዋነይ እነ እማሆይ ገላነሽ ሐዲስ እነ አለቃ ዶሪ የኢትዮጵያ ሊቃውንት መኳንንት የተፈላሰፉበት መንፈሳዊ ፍልስፍና ነው ቅኔ።ፈጣሪ የሚመሰገንበት ልዩ ቋንቋ ነው ቅኔ። ቋንቋ ፍሬ ነገሩ ፈጣሪን ለማመስገን ስለሆነ የቅኔ ሊቃውንት ሰብሕዎ ለእግዚአብሔር ስብሐተ ሐዲሰ ስለሚል መጽሐፉ ፈጣሪን በአዳዲስ ምስጢር ሲያመሰግኑት ኖረዋል።ሊቃውንቱም ማእበል፥ገሞራው፥ነበልባል እየተባሉ የተጠሩበት ነው ቅኔ።በቅኔ በምስጢር ሠረገላ ጽርሐ አርያም ትደርሳለህ።ከአጽናፍ እስከ አጽናፍ ትበራለህ። ቅኔ ለፈጣሪ ምስጋና የሚውሉ የተጣሩ የግእዝ ቃላትን በመጠቀም የሚደረስ ልዩ ድርሰት ነው። ቅኔ ሁል ጊዜ አዲስ ነው።መምህሩ ቅኔ ለተማሪዎቻቸው ሲያቀርቡ "ዘረፉ" ይባላል። ዘረፋ ማለት መምህሩ ከአእምሯቸው አፍልቀው በቅጽበት ለተማሪዎች ሲያቀርቡ የሚሰጥ ስያሜ ነው።ሌላው "ቆጠራ" ይባላል ጀማሪ ተማሪ ቅኔ ሲማር አስቦ አውጥቶ አውርዶ ቅኔ እያዘጋጀ ካለ "እየቆጠረ" ነው ይባላል። ቅኔ ቀነየ ገዛ ከሚል ቃል የመጣ ጥሬ ዘር ሲሆን ትርጉሙ መገዛት ማለት ነው።ይህም ለፈጣሪ መገዛታችንን የምንገልጽበት ምስጋና ነው።

ስለዚህ ከአሁን ቀጥሎ ባሉት ክፍሎች ቅኔ እንማማራለን ማለት ነው።በዚህ አጋጣሚ ቅኔ መሰዳደቢያ አሽሙር አይደለም።ቅኔ እግዚአብሔር የሚመሰገንበት ልዩ ድርሰት ነው።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግእዝ ክፍል 54
©ቅኔ 2©
ለስለላ (intelligence) የሚያገለግል ቅኔ አለ። ስለላም ለመልካም ከተጠቀሙበት መጽሐፋዊ ነው።ምሳሌ ካሌብ እና ሰልሞን ሰላዮች እንደነበሩ ኦሪት ትናገራለች።አንድ ቅኔ እንይ
"አቅረበ ምጽአተክርስቶስ ልቃሔ ጥዑም"
ለምሳሌ ይህንን ቅኔ አበባ ለቀማ በሚባለው የቅኔ መንገድ ብናየው "አምልጥ" ማለት ነው። ይኽውም አቅረበ ከሚለው የመጀመሪያ ፊደሏን "አ"ን ምጽዐተ ክርስቶስ ከሚለው "ም"ን ልቃሔ ከሚለው "ል"ን ጥዑም ከሚለው "ጥ"ን ወስደን ስናጋጥመው "አምልጥ" ይላል።
ቅኔ በአንድ አረፍተ ነገር ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ሀሳቦችን ማስተላለፍ ነው።እኒህ ሀሳቦችም በዋናነት @ሰም እና ወርቅ@ ይባላሉ።ሰሙ ብዙ ጊዜ ለብዙዎች ከላይ ከላይ የሚታየው ሲሆን ወርቁ ግን ለተመራማሪዎች እና በአእምሮ ለመጠቁ ብቻ የሚታይ ነገር ነው።ስለዚህ ማንኛውም ቅኔ ሰምና ወርቅን አንድ ላይ የያዘ ነው።
ምሳሌ
ማርያም ምሥራቅ ዘአሥቀት ፀሐየዓለም ክርስቶስ።ቢል 2 ሀሳብ ይዟል።አንደኛው ማርያም ክርስቶስን የወለደች ተብሎ ይተረጎማል።ሌላው ፀሐይ የሚወጣበት ምሥራቅ የሚል አለው።ግን በአንድ አረፍተ ነገር ተገልጿል።ይህንን በሰፊው እንመለከታለን። ቅኔ መማር የፈለገ ሰው
1 የግእዝ ቃላትን ማወቅ አለበት
2 ዜማ ልኩን (formula of kine) ማወቅ አለበት።
3 የሰምና የወርቅን መንገድ ማወቅ አለበት
4 የሰዋሰውን አገባብ (Grammar) ማወቅ አለበት።
5 የቅኔ ዓይነቶችን መለየት አለበት።

የቅኔ ዓይነቶች በቤት
ግእዝ ጉባኤ ቃና
እዝል ጉባኤ ቃና
ዘአምላኪየ
ሚበዝኁ
ዋዜማ
አጭር ዋዜማ
ዘይእዜ
አጭር ዘይእዜ
ሥላሴ
ሣህልከ
መወድስ
ኩልክሙ
ክብር ይእቲ ግእዝ
ክብር ይእቲ እዝል
እጣነ ሞገር ግእዝ
እጣነ ሞገር እዝል
አሠረ ንጉሥ ግእዝ
አሠረ ንጉሥ እዝል
ሕንጼሃ
ሐዋርያቲሁ ከበበ
እየተባሉ ይጠራሉ።የእኒህ የራሳቸው የሆነ መንገድ አላቸው።እያንዳንዱን በጥልቀት በቀጣይ ክፍል እናያለን

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
2024/10/02 00:33:21
Back to Top
HTML Embed Code: