Telegram Web Link
የግእዝ ቋንቋ ክፍል 15
ሥርዓተ ንባብ
የግእዝ ቋንቋ የራሱ የሆነ የንባብ ሥርዓት አለው እኒህም ተነሽ፥ተጣይ፥ወዳቂ፥ሰያፍ ተብለው ይጠራሉ።ተነሹን በወዳቂ ያለ አገባቡ ከተነበበ የትርጉም ለውጥ ያመጣል።ምሳሌ "አእመራ" ተነስቶ ሲነበብ እና በወዳቂ ሲነበብ የተለያየ ትርጉም አለው።ሲነሳ አወቁ ተብሎ ሲተረጎም በወዳቂ ሲነበብ ደግሞ አወቃት ይላል።ስለዚህ የንባብ ሥርዓቱ ከተበላሸ ምስጢርም ስለሚያፈርስ ይህንን ጠንቅቀን መለየት አለብን። አንድን ቃል ተነሽ ይሁን ሰያፍ ወይም ወዳቂ ወይም ተጣይ መሆኑን በምን እንለያለን ስንል 3 መለያ መንገዶች አሉ።እነዚህም የቃሉ መድረሻ ፊደል፥የቃሉ የንግግር ክፍል እና የፊደላት ተጽእኖ ናቸው።እያንዳንዱን እንመልከት
1ኛ ተጣይ ንባብ፦ተጥለው የሚነበቡ ቃላት የመጨረሻ ፊደላቸው ሳድስ የሆነ እና የቃል ክፍላቸው ስም የሆኑ ናቸው።ለምሳሌ ቅድሳት፥ስብከት፥ቀትል፥መድኃኒት፥ማርያም ይላል።
2ኛ ሰያፍ ንባብ፦ይህም የቃሉ መጨረሻ ሳድስ የሆነ እና የቃል ክፍሉ ስምም ግሥም የሆነ ነው።ምሳሌ ዳንኤል፥ቀደሰት፥ይትባረክ ይላል።
3ኛ ተነሽ ንባብ፦ከሳድስ እና ከኃምስ ውጭ ባለው ይጨርሳል።የቃል ክፍሉ ብዙ ጊዜ ግስ ነው።
በግእዝ=አእመረ
በካእብ=አእመሩ
በሣልስ=አእምሪ
በራብእ=አእመራ
በሳብእ=አእምሮ
ይላል።በሳድስ እና በኃምስ የሚጨርስ ተነሽ ቃል የለም።
4ኛ ወዳቂ ንባብ፦ይህም በሰባቱም ሆሄያት ሊጨርስ ይችላል።ብዙ ጊዜ የቃል ክፍሉ ስሞች ናቸው።
በግእዝ=ህየ
በካዕብ=ሥጋሁ
በሣልስ=ቀታሊ
በራብእ=ሥጋሃ
በኀምስ=ቅዳሴ
በሳድስ=በሳድስ የሚጨርስ ወዳቂ "ዝ" ብቻ ነው።
በሳብእ=መሰንቆ
ይላል።

የፊደላት ተጽእኖ
"ሰ" በወዳቂ ላይ ሲወድቅ ተነስቶ እንዲነበብ ያደርገዋል።ምሳሌ እንበሌሁ ወዳቂ ነው።ሰ ሲወድቅበት እንበሌሁሰ ሲል ግን ተነሽ ይሆናል። "ሰ" በተነሽ በወዳቂ እና በተጣይ ሲወድቅ ወዳቂ ያደርገዋል።
"ሂ" በ4ቱም ሥርዓተ ንባቦች ሲወድቅ ወዳቂ ያደርጋል።

ሁለት ፊደል ያለው ግሥ ሆኖ በሳድስ ከጨረሰ ሁሌም ተጣይ ነው።ምሳሌ ኖኅ፥ካም።
በኃምስ የሚጨርስ ማንኛውም ቃክ ሁሌም ወዳቂ ነው።ምሳሌ ሙሴ፥አውሴ
ሁሉም ሳድስ የሆነ ስም ሁሌም ተጣይ ነው።ምሳሌ እስክንድር፥ግብጽ

ጥያቄ
የሚከተሉትን ቃላት ሥርዓተ ንባብ ለይ
1 ኢሳይያስ
2 ሚካኤል
3 ምናሴ
4 አጽደልደለ
5 ኪዳነ ምሕረት
መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
የግእዝ ቋንቋ ክፍል 16
የግስ እርባታ በ10ሩ መራሕያን
1 ይእቲ=ቀተለት=ገደለች
ትቀትል=ትገድላለች
ትቅትል=ትገድል ዘንድ
ትቅትል=ትግደል
2 ውእቶሙ=ቀተሉ=ገደሉ
ይቀትሉ=ይገድላሉ
ይቅትሉ=ይገድሉ ዘንድ
ይቅትሉ=ይግደሉ
3 ውእቶን=ቀተላ=ገደሉ
ይቀትላ=ይገድላሉ
ይቅትላ=ይገድሉ ዘንድ
ይቅትላ=ይግደሉ
4 ውእቱ=ቀተለ=ገደለ
ይቀትል=ይገድላል
ይቅትል=ይገድል ዘንድ
ይቅትል=ይግደል
5 አንተ=ቀተልከ=ገደልክ
ትቀትል=ትገድላለህ
ትቅትል=ትገድል ዘንድ
ቅትል=ግደል
6 አንትሙ=ቀተልክሙ=ገደላችሁ
ትቀትሉ=ትገድላላችሁ
ትቅትሉ=ትገድሉ ዘንድ
ቅትሉ=ግደሉ
7 አንቲ=ቀተልኪ=ገደልሽ
ትቀትሊ=ትገድያለሽ
ትቅትሊ=ትገድይ ዘንድ
ቅትሊ=ግደይ
8 አንትን=ቀተልክን=ገደላችሁ
ትቀትላ=ትገድላላችሁ
ትቅትላ=ትገድሉ ዘንድ
ቅትላ=ግደሉ
9 አነ=ቀተልኩ=ገደልኩ
እቀትል=እገድላለሁ
እቅትል=እገድል ዘንድ
እቅትል=ልግደል
10 ንሕነ=ቀተልነ=ገደልን
ንቀትል=እንገድላላን
ንቅትል=እንገድል ዘንድ
ንቅትል=እንግደል
በአሥሩ መራሕያንን ይህንን እየመሰለ ሌላው ግሥም ይረባል

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
የግእዝ ቋንቋ ክፍል 17
ዝርዝር እርባታ ክፍል 1
ይህ ባለቤቱንና ተሳቢውን በአንድ ጊዜ የሚያሳውቀን ነው።
1ኛ ውእቱ=ቀተሎ=ገደለው
ቀተላ=ገደላት
ቀተሎሙ=ገደላቸው
ቀተሎን=ገደላቸው(ሴቶችን)
ቀተለከ=ገደለህ
ቀተለኪ=ገደለሽ
ቀተለክሙ=ገደላችሁ
ቀተለክን=ገደላችሁ(ሴቶችን)
ቀተለኒ=ገደለኝ
ቀተለነ=ገደለን
2ኛ ውእቶሙ=ቀተልዎ=ገደሉት
ቀተልዋ=ገደሏት
ቀተልዎሙ=ገደሏቸው
ቀተልዎን=ገደሏቸው(ሴቶችን)
ቀተሉከ=ገደሉህ
ቀተሉኪ=ገደሉሽ
ቀተሉክሙ=ገደሏችሁ
ቀተሉክን=ገደሏችሁ(ሴቶችን)
ቀተሉኒ=ገደሉኝ
ቀተሉነ=ገደሉን
3ኛ ይእቲ=ቀተለቶ=ገደለችው
ቀተለታ=ገደለቻት
ቀተለቶሙ=ገደለቻቸው
ቀተለቶን=ገደለቻቸው(ሴቶችን)
ቀተለተከ=ገደለችህ
ቀተለተኪ=ገደለችሽ
ቀተለተክሙ=ገደለቻችሁ
ቀተለተክን=ገደለቻችሁ (ሴቶችን)
ቀተለተኒ=ገደለችኝ
ቀተለተነ=ገደለችን
4 ውእቶን=ቀተላሁ=ገደሉት
ቀተላሃ=ገደሏት
ቀተላሆሙ=ገደሏቸው
ቀተላሆን=ገደሏቸው(ሴቶችን)
ቀተላከ=ገደሉህ
ቀተላኪ=ገደሉሽ
ቀተላክሙ=ገደሏችሁ
ቀተላክን=ገደሏችሁ(ሴቶችን)
ቀተላኒ=ገደሉኝ
ቀተላነ=ገደሉን
5 አነ=ቀተልክዎ=ገደልኩት
ቀተልክዋ=ገደልኳት
ቀተልክዎሙ=ገደልኳቸው
ቀተልክዎን=ገደልኳቸው
ቀተልኩከ=ገደልኩህ
ቀተልኩኪ=ገደልኩሽ
ቀተልኩክሙ=ገደልኳችሁ
ቀተልኩክን=ገደልኳችሁ
6 ንሕነ=ቀተልናሁ=ገደልነው
ቀተልናሃ=ገደልናት
ቀተልናሆሙ=ገደልናቸው
ቀተልናሆን=ገደልናቸው(ሴቶች)
ቀተልናከ=ገደልንህ
ቀተልናኪ=ገደልንሽ
ቀተልናክሙ=ገደልናችሁ
ቀተልናክን=ገደልናችሁ
7 አንተ=ቀተልኮ=ገደልከው
ቀተልኮሙ=ገደልካቸው
ቀተልካ=ገደልካት
ቀተልኮን=ገደልካቸው
ቀተልከኒ=ገደልከኝ
ቀተልከነ=ገደልከን
8 አንቲ=ቀተልኪዮ=ገደልሺው
ቀተልኪያ=ገደልሻት
ቀተልኪዮሙ=ገደልሻቸው
ቀተልኪዮን=ገደልሻቸው(ሴቶች)
ቀተልክኒ=ገደልሽኝ
ቀተልክነ=ገደልሽን
9 አንትሙ=ቀተልክምዎ=ገደላችሁት
ቀተልክምዋ=ገደላችኋት
ቀተልክምዎሙ=ገደላችኋቸው
ቀተልክምዎን=ገደላችኋቸው
ቀተልክሙኒ=ገደላችሁኝ
ቀተልክሙነ=ገደላችሁን
10 ውእቶን=ቀተልክናሁ=ገደላችሁት
ቀተልክናሃ=ገደላችኋት
ቀተልክናሆሙ=ገደላችኋቸው
ቀተልክናሆን=ገደላችኋቸው(ሴቶችን)
ቀተልክናኒ=ገደላችሁኝ
ቀተልክናነ=ገደላችሁን
ሌላውም ግስ ይህን እየመሰለ ይረባል።

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
የግእዝ ቋንቋ ክፍል 18
ዝርዝር እርባታ ክፍል 2
1ኛ ውእቱ
1 ቀተሎ=ገደለው
ይቀትሎ=ይገድለዋል
ይቅትሎ=ይገድለው ዘንድ
ይቅትሎ=ይግደለው
2 ቀተላ=ገደላት
ይቀትላ=ይገድላታል
ይቅትላ=ይገድላት ዘንድ
ይቅትላ=ይግደላት
3 ቀተሎሙ=ገደላቸው
ይቀትሎሙ=ይገድላቸዋል
ይቅትሎሙ=ይገድላቸው ዘንድ
ይቅትሎሙ ይግደላቸው
4 ቀተሎን=ገደላቸው
ይቀትሎን=ይገድላቸዋል
ይቅትሎን=ይገድላቸው ዘንድ
ይቅትሎን=ይግደላቸው
5 ቀተለከ=ገደለህ
ይቀትለከ=ይገድልሀል
ይቅትለከ=ይገድልህ ዘንድ
ይቅትልከ=ይግደልህ
6 ቀተለኪ=ገደለሽ
ይቀትለኪ=ይገድልሻል
ይቅትልኪ=ይገድልሽ ዘንድ
ይቅትልኪ=ይግደልሽ
7 ቀተለክሙ=ገደላችሁ
ይቀትለክሙ=ይገድላችኋል
ይቅትልክሙ=ይገድላችሁ ዘንድ
ይቅትልክሙ=ይግደላችሁ
8 ቀተለክን=ገደላችሁ
ይቀትለክን=ይገድላችኋል
ይቅትልክን=ይገድላችሁ ዘንድ
ይቅትልክን=ይግደላችሁ
9 ቀተለኒ=ገደለኝ
ይቀትለኒ=ይገድለኛል
ይቅትለኒ=ይገድለኝ ዘንድ
ይቅትለኒ=ይግደለኝ
10 ቀተለነ=ገደለን
ይቀትለነ=ይገድለናል
ይቅትለነ=ይገድለን ዘንድ
ይቅትለነ=ይግደለን
2ኛ ውእቶሙ
1 ቀተልዎ=ገደሉት
ይቀትልዎ=ይገድሉታል
ይቅትልዎ=ይገድሉት ዘንድ
ይቅትልዎ=ይግደሉት
2 ቀተልዋ=ገደሏት
ይቀትልዋ=ይገድሏታል
ይቅትልዋ=ይገድሏት ዘንድ
ይቅትልዋ=ይግደሏት
እንዲህ እንዲህ እያለ ክፍል 17 ላይ ያየነው እያንዳንዱ በካልዓይን አንቀጽ በዘንድ አንቀጽና በትእዛዝ አንቀጽ እየረባ ይሄዳል።ሰፊ ስለሆነ ማሰልቸት ይሆንብኛል ብየ ትቼዋለሁ።ይህ ብቻ አይደለም።ይህ በ5ቱ እእማድ ይረባል።በዚህ አካሄድ እስከመጨረሻው ብንሄድ አንዱ ቀተለ ገደለ የሚለው ግስ ብቻ ከ4700 በላይ ይረባል።ይህም የግእዝ ቋንቋ ምን ያህል ጥልቅ እንደሆነ ያሳየናል።የግእዝ ቋንቋ መማርያ በሚለው መጽሐፌ ሙሉውን ጽፌዋለሁ።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
የግእዝ ቋንቋ ክፍል 19
ዘመድ ዘር፥ጥሬ ዘር፥ምዕላድ፥ባዕድ ዘር፥ሳቢ ዘር
እነዚህ ከግስ የሚገኙ ስሞች ናቸው።እንዴት እንደሚገኙ እና እንዴት እንደሚተረጎሙ ከዚህ ቀጥለን እንመለከታለን።
ሳቢዘር
ሳቢዘር የሚባለው የግሱን መጨረሻ ብቻ ግእዝ አድርጎ "ት"ን የሚጨምር ነው።ምሳሌ ዐርገ ብሎ ዕርገት ይወጣል።ትርጉሙ ማረግ ነው።
ጥሬ ዘር
ከግሡ ላይ መጨረሻውን ራብእ ወይም ኃምስ ወይም ሳብእ አድርጎ የሚወጣ ነው።ምሳሌ ቀደሰ አመሰገነ ብሎ ቅዳሴ=ምስጋና ይወጣ
ባዕድ ዘር
ከግሡ ውጭ ያለ ፊደል መጀመሪያ ላይ ጨምሮ የሚወጣ ስም ነው።ምሳሌ ቀደሰ ከሚለው መቅደስ ይወጣል።መ መጀመርያ ላይ እንደወጣ አስተውል።ትርጉሙ መቀደሻ ማስቀደሻ መቀደሻ እያለ በ5ቱ አእማድ ይረባል።
ምእላድ
ከግሡ መጨረሻ ላይ ባዕድ በመጨመር የሚወጣ ስም ነው።ምሳሌ=ቀረበ ቆረበ ከሚለው ቁርባን ይወጣል።ን መጨረሻ ላይ እንደተጨመረ አስተውል።
ባዕድ ከምእላድ
ከመነሻው ባዕድ ጨምሮ ከመድረሻው ላይም ምእላድ የሚጨምር ነው።ምሳሌ ቀሰፈ=ቀሰፈ ከሚለው መቅሰፍት ይወጣል።አስብ ከመነሻው መን ከመድረሻው ትን እንደጨመረ አስተውል።
ዘመድ ዘር
ከግሡ ላይ ምንም ምን ሳይጨመር መጨረሻው ሳድስ የሆነ ቃል ሲወጣ ዘመድ ዘር ይባላል።ለምሳሌ አገረ ተራመደ ብሎ እግር ይወጣል።አንቀልቀለ=ተነዋወጠ ብሎ ቃል ይወጣል።
ጥሬ ምእላድ
ከመድረሻው ባዕድ ጨምሮ ያውም ኃምስ ሳብእ ወይም ራብዕ ከሆነ ነው።ምሳሌ ቀደሰ አመሰገነ ከሚለው ግስ ቅድስና የሚል ጥሬ ምእላድ ይወጣል።አስተውል "ና" ምእላድ ሆኖ ራብዕ ስለሆነ ጥሬ ምእላድ ተብሏል።

NB፦ከግሥ የሚወጡ ዘሮች ግሡን የመሰለ እና ከግሡ የተቀራረበ ስምን ያስገኙልናል።

ወስብሀት ለእግዚአብሔር።
መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
የግእዝ ቋንቋ ክፍል 20
ስንብት እና ሰላምታ
ዳህና ኩን እኁየ=ወንድሜ ደህና ሁን
ዳህና ኩኒ እህትየ=እህቴ ደህና ሁኝ
እያልን የምንሰነባበትበት ስንብት ይባላል።
አንድን ሰው ሰላም ስንል
በሐ=ጤና ይስጥልኝ፥ሰላም
ሰላም=ሰላም
ሰላም ለከ=ሰላም ለአንተ ይሁን
ሰላም ለኪ=ሰላም ለአንቺ ይሁን
ይላል።
ለመመለስ ደግሞ
እግዚአብሔር ይሰባሕ=እግዚአብሔር ይመስገን ይላል።

አነሳስቶ ያስጀመረን
አስጀምሮ ያስፈጸመን
ልዑል እግዚአብሔር
የተመሰገነ ይሁን አሜን

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግእዝ ክፍል 21
በግእዝ ቋንቋ አብዥ ቀለማት 7 ናቸው።እኒህም ል፥ሙ፥ት፥ን፥አ፥ው፥ይ ናቸው።ይህም ማለት ነጠላ ቃልን ወደ ብዙ (plurals) ለመቀየር ይጠቅማሉ
ነጠላ/singular.................. ብዙ/plural
ኪሩብ..................................ኪሩቤል
ሱራፊ..................................ሱራፌል
ኩሉ.....................................ኲሎሙ
ሕጻን...................................ሕጻናት
ካህን...................................ካህናት
ቅዱስ..................................ቅዱሳን
ጻድቅ...................................ጻድቃን
ደብር...................................አድባር
ሕዝብ..................................አሕዛብ
አብ.....................................አበው
ሌሊት..................................ለያልይ
አስተውል።አ ሲያበዛ መጀመሪያ ይመጣል ሕዝብ ብሎ ለማብዛት አሕዛብ ብሎ "አ"ን አስቀድሞ እንዳመጣ አስተውል።ሌሎቹ ግን በመጨረሻ እየመጡ ሲያበዙ እንመለከታለን። ነጠላው ወደ ብዙ ሲላወጥ ምን ዓይነት የፊደላት ለውጥ እንዳመጣ በደንብ አስተውለህ/ሽ ሌላውን ሁሉ ይህን እያስመሰሉ ማውጣት ነው።ሌላው ግን የብዙ ብዙ የሚባል አለ። ይህ ብዙን እንደገና በማብዛት ይነገራል።ለምሳሌ
ደብር........አድባር.......አድባራት
ጾም.........አጽዋም.......አጽዋማት
እያለ የሚሄድም አለ።

ጥያቄ የሚከተሉትን ቃላት ወደ ብዙ/plural ቀይር።
1 ጳጳስ
2 ኄር
3 ዲያቆን
4 ሀገር
5 ዕፅ

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግእዝ ክፍል 22
ተናባቢ ቀለማት
ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ ቃላት በአንድ ድምጽ ከተነበቡ ተናባቢ ቀለማት ይባላሉ።በእንግሊዘኛ of የሚል ትርጓሜን ያመጣሉ።በአማርኛ "የ"ን ያመጣሉ።ለምሳሌ ሕዝበ ኢትዮጵያ ስንል የኢትዮጵያ ሕዝብ ማለት ሲሆን people of Ethiopia ብሎ በእንግሊዘኛ ይተረጎማል።ይህ በግእዝ የራሱ ሕግ አለው።ሕጉም ይህ ነው።
1 የሚናበበው ቃል የመጨረሻ ቃሉ ሳድስ ከሆነ ወደ ግእዝ ተቀይሮ ይናበባል።ምሳሌ ቤት የሚለውን ቃል መንግሥት ከሚል ጋር ስናናብበው ቤተ መንግሥት ይላል።"ት" ወደ ግእዝ "ተ" እንደተቀየረ አሳተውል።
2 የሚናበበው ቃል መጨረሻ ሣልስ ከሆነ ሲናበብ ወደ ኃምስ ይለወጣል።ለምሳሌ መጋቢ የሚለው ቃል ብሉይ ከሚለው ጋር ሲናበብ መጋቤ ብሉይ ይላል።አስተውል "ቢ" ወደ "ቤ" ተለውጧል።
3 የሚናበበው ቃል የመጨረሻ ፊደል ራብእ ኃምስ እና ሳብእ ከሆነ እንዳለ ይሆናል አይለወጥም።ይህም ማለት እንዚራ የሚለው ከስብሀት ጋር ሲናበብ እንዚራ ስብሀት ይላል። አስተውል "ራ" ባለበት እደሆነ።ሳብእም ያው ሳብእ ኃምስም ያው ኃምስ ይሆናል።
ተናባቢ ቃላት ሲናበቡ የመጨረሻው የተናበበው ቃል "ዘርፍ" ይባላል።ይህም ማለት ለምሳሌ።ቤተ መንግሥት ከሚለው ቃል።መንግሥት የቤት ዘርፍ ይባላል።

ማንኛውንም ቃል በዚህ መልኩ ማዛረፍ ወይም ማናበብ ይቻላል።ሌላ የሚያናብቡ ቃላት አሉ እኒህም።ዘ እና ለ ናቸው። ዘ እና ለ ሲያዛርፉ ምንም ዓይነት የፊደል ለውጥ አይመጣም። ይህም ማለት ቤተ መንግሥት የሚለውን ቃል በሌላ መልኩ ቤት ዘመንግሥት ቤቱ ለመንግሥት ብለን መግለጽ እንችላለን። ዘ እና ለ እንዲህ ሲሆኑ ዘርፍ አያያዥ ይባላሉ።ትርጉሙ ግን ቤተ መንግሥት፥ቤት ዘመንግሥት ቢል ያው የመንግሥት ቤት ማለት ነው።

የእለቱ ጥያቄዎች
የሚከተሉትን ቃላት በ ዘ እና ለ እንዲሁም ያለ ዘ እና ለ አናብብ

1 መንበር እና ጸባኦት
2 ቅዳሴ እና መላእክት
3 መጋቢ እና ሐዲስ
4 መድኃኒ እና ዓለም
5 ፅላት እና ሙሴ
6 መዝሙር እና ዳዊት
7 መልአክ እና ብርሃን
8 ሊቅ እና ሊቃውንት
9 ታዕካ እና ነገሥት
10 ደብር እና መድኃኒት

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግእዝ ክፍል 23
ተሳቢ ቃላት (objects)
በግእዝ ቋንቋ አንድ ቃል ባለቤት (subject) ሲሆንና ተሳቢ (object) ሲሆን የተለያየ የፊደል ቅርጽ አለው ለምሳሌ ኅብስት ባለቤት ሲሆን ኅብስት ነው።ተሳቢ ሲሆን ኅብስተ ይላል።ይህ በግእዝ የራሱ ሕጎች አሉት።ያእቆብ ባለቤት ሲሆን ያእቆብ ይላል ተሳቢ ሲሆን ያእቆብሀ ይላል።በአማርኛ አበበ እንጀራ በላ በግእዝ አበበ በልአ ኅብስተ ይላል።በእንግሊዘኛ Abebe eats injera ይላል።

1 ሳድስ ቀለም ሲሳብ ወደ ግእዝ ይቀየራል ኅብስት ወደ ኅብስተ።መንበር ወደ መንበረ ይለወጣል።
2 ካዕብ ወደ ሳብእ ይቀየራል።ቤቱ የሚለው ሲሳብ ቤቶ ይላል
3 ሣልስ ወደ ኃምስ ይቀየራል።ጸሐፊ የሚለው ጸሐፌ ይላል።
4 ራብዕ ኃምስ እና ሳብእ አይለወጡም ባለቤት የሆነው ቃል ምንም የፊደል ቅርጽ ሳይለውጥ ተሳቢ ይሆናል።
5 ተናባቢ ቃላት ተሳቢ ሲሆኑ ምንም ለውጥ ሳያመጡ እንዳሉ ይሆናሉ።ቤተ መንግሥት ሲሳብ ባለበት ቤተ መንግሥት ይላል።
6 አገባብ የወደቀበት ቃል ሲሳብም ምንም ዓይነት ለውጥ አያመጣም።ለኅብስት ይላል እንጂ ለኅብስተ አይልም።
7 የሰው ስም ሲሳብ ወንድ ከሆነ "ሀ"ን ይጨምራል ሴት ከሆነች "ሃ"ን ይጨምራል። ሔዋን ተሳቢ ስትሆን ሔዋንሃ ይላል።አዳም ተሳቢ ሲሆን አዳምሀ ይላል።

በዓረፍተ ነገር እንመልከተው
እኔ ወደ ገዳም ሄድኩ.............አማርኛ
I went to Monastery.......እንግሊዘኛ
አነ ሖርኩ ኀበ ገዳም..............ግእዝ
ቅድስት ማርያምን እንወዳለን.....አማርኛ
We love saint Marry.......እንግሊዘኛ
ናፈቅር ማርያምሃ ቅድስተ........ግእዝ
...
የእለቱ ጥያቄዎች
የሚከተሉትን ቃላት ወደ ተሳቢ ቀይር
1 መፍቀሪ
2 ገነት
3 ሰማያት
4 ምናኔ
5 ዋካ
6 መሰንቆ
7 ጸሐፌ ትእዛዝ
8 ኢሳይያስ
9 ሐና
10 ወልደማርያም


መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግእዝ ክፍል 24
የግእዝ ቃላት እና ፍቻቸው ክፍል አንድ
መርሐ=መራ
ለቅሀ=አበደረ
ሞቅሐ=አሰረ
በርሀ=በራ
በዝኀ=በዛ
በጽሐ=ደረሰ
ተመክሐ=ተመካ
ተራኅርኀ=ቸር ሆነ
ተፈሥሐ=ደስ ተሰኘ
ነስሐ=ተጸጸተ
ነቅሀ=ነቃ
ኖኀ=ረዘመ
ነግሀ=ነጋ
አምኀ=እጅ ነሳ
ከልሐ=ጮኽ
ወክሐ=ደነፋ
የውሀ=አታለለ
ዘግሐ=ዘጋ
ጎሐ=ጠባ፥ነጋ
ጠፍሐ=አጨበጨበ
ጸንሐ=ቆየ
ፈርሀ=ፈራ
ፈልሐ=ፈላ
ፈትሐ=ፈታ፥ፈረደ
ሐዘለ=አዘለ
መሐለ=ማለ
መሰለ=መሰለ
ሰቀለ=ሰቀለ
ሰብለ=ዘረዘረ
ሰከለ=አፈራ
ብህለ=አለ
በሰለ=በሰለ
ብዕለ=ባዕለጸጋ ሆነ
ተለዐለ=ከፍ ከፍ አለ
ተማሕለለ=ምሕላ ያዘ
ተሠሀለ=ይቅር አለ
ተቀበለ=ተቀበለ
ተበቀለ=ቂም ያዘ
ተከለ=ተከለ
ተወከለ=ታመነ
አሕመልመለ=ለመለመ
አንቀልቀለ=ተነዋወጠ
አከለ=በቃ፥ልክ ሆነ
አጽደልደለ=አበራ
ክህለ=ቻለ
ቀተለ=ገደለ
ወዐለ=ዋለ
ፈልፈለ=መነጨ
ፈተለ=ፈተለ
ሐለመ=አለመ
ሐመ=ታመመ
ኀተመ=አተመ
ሰዐመ=ሳመ
ሤመ=ሾመ
ቆመ=ቆመ
ተሳለመ=ተፈቃቀረ
ተርጎመ=ተረጎመ
ተቀየመ=ቂም ያዘ
ተደመ=ተደነቀ
ኖመ=ተኛ
ዐለመ=ፈጠረ
አርመመ=ዝም አለ
አደመ=አማረ
ከርመ=ከረመ
ደክመ=ደከመ
ገረመ=ተፈራ
ጥዕመ=ቀመሰ
ጸልመ=ጠቆረ
ጾመ=ጾመ
ፈጸመ=ጨረሰ
ኀሠሠ=ፈለገ
ሐረሰ=አረሰ
ኄሰ=ተሻለ
ሔሰ=ነቀፈ
ሐደሰ=አዲስ አደረገ
ለብሰ=ለበሰ
መንኮሰ=መነኮሰ
ሰንኮረሰ=አስተማረ
ርሕሰ=ራሰ
ቀደሰ=አመሰገነ
ተዐገሠ=ቻለ፥ታገሠ
ተጸነሰ=ተቸገረ
ነግሠ=ነገሠ
ነፍሰ=ነፈሰ
አክሞሰሰ=ፍግግ ፍግግ አለ
ወረሰ=ወረሰ
ወደሰ=አመሰገነ
የብሰ=ደረቀ
ደቀሰ=ተኛ
ገሰሰ=ዳሰሰ
ጌሠ=ገሰገሰ
ጤሰ=ጤሰ
ፀንሰ=ፀነሰ
ፈለሰ=ተሰደደ
ፈወሰ=አዳነ
ሐብረ=አንድ ሆነ፥ተባበረ
ሖረ=ሄደ
ኀደረ=አደረ
ኀፍረ=አፈረ
መሀረ=አስተማረ
መተረ=ቆረጠ
መከረ=መከረ
ሰክረ=ሰከረ
ሰወረ=ሸሸገ
ቀመረ=ቆጠረ
ቆረ=ቀዘቀዘ
በረ=በረረ
ተዐየረ=ተመጻደቀ
ተዘከረ=አሰበ
ተዝኅረ=ኮራ
ተደረ=በላ ተመገበ (የራት)
ተፃመረ=አንድ ሆነ
ተፃረረ=ተጣላ
ነበረ=ተቀመጠ
ነገረ=ነገረ
ነጸረ=አየ
አመስጠረ=አራቀቀ
አመዐረዐረ=አጣፈጠ
አመዝበረ=አፈረሰ
አብሠረ=የምስራች አለ
አንከረ=አደነቀ
አንጎርጎረ=አጉረመረመ
አንጸረ=አመለከተ
አእመረ=አወቀ
ዖረ=እውር ሆነ
አውተረ=አዘወተረ
አግመረ=ቻለ
አገበረ=ግድ አለ
አፍቀረ=ወደደ
ከብረ=ከበረ
ዘመረ=አመሰገነ
ዘከረ=ስም ጠራ
ደመረ=ጨመረ
ጦመረ=ጻፈ
ጾረ=ተሸከመ
ፈከረ=ተረጎመ
ፈጠረ=ፈጠረ
ኀልቀ=አለቀ
ሐነቀ=አነቀ
ልህቀ=አደገ
ሞቀ=መቀ
መጠቀ=ረዘመ
ሰረቀ=ሰረቀ
ረቀ=ረቀቀ
ረፈቀ=ተቀመጠ
በረቀ=ብልጭ አለ
ናፈቀ=ተጠራጠረ
አልጸቀ=ደረሰ
ዖቀ=አወቀ
አጥመቀ=አጠመቀ
ወድቀ=ወደቀ
ጠየቀ=ተረዳ
ጸድቀ=እውነተኛ ሆነ
ሐለበ=አለበ
ኀፀበ=አጠበ
ሰሐበ=ሳበ
ሰከበ=ተኛ
ርኅበ=ተራበ
ረከበ=አገኘ
ቀረበ=ቆረበ
ቀርበ=ቀረበ
ቀጸበ=ጠቀሰ
ተመገበ=በላ
ነበበ=ተናገረ
ዐቀበ=ጠበቀ
ዐተበ=ባረከ
አንበበ=አነበበ
ወሀበ=ሰጠ
ዘገበ=ሰበሰበ
የበበ=እልል አለ
ጸረበ=ጠረበ
ጸግበ=ጠገበ
ሐመተ=አከሰለ
ሐተተ=መረመረ
ቤተ=አደረ
ተትሕተ=ትሑት ሆነ
አእኮተ=አመሰገነ
ከሠተ=ገለጠ
ከበተ=ሸሸገ
ፈተተ=ቆረሰ
ኀበነ=ጠመጠማ
ሐዘነ=አዘነ
ሐፀነ=አሳደገ
ማሰነ=ጠፋ
መነነ=ናቀ
ሰይጠነ=አጣላ
ረበነ=አስተማረ
ቀጥነ=ቀጠነ
በየነ=ፈረደ
ተመየነ=ተንኮለኛ ሆነ
ተቃረነ=ተጣላ
ተነ=ተነነ
ተጸወነ=ተጠጋ
አምነ=አመነ
ዐጠነ=አጠነ
ኮነነ=ገዛ
ኮነ=ሆነ
ወሰነ=ደነገገ
ድኅነ=ዳነ
ደመነ=ጋረደ
ጸዐነ=ጫነ
ፈተነ=ፈተነ
ፈጠነ=ፈጠነ

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግእዝ ክፍል 25
የግእዝ ቃላት እና ፍቻቸው ክፍል 2
ኀብአ=ሸሸገ
ሀድአ=ጸጥ አለ
ኀጥአ=አጣ
መልአ=መላ
ሞአ=አሸነፈ
መጽአ=መጣ
ሰምዐ=ሰማ
ሦዐ=ሰዋ
ረስአ=ረሳ፥ዘነጋ
ረትዐ=ቀና
ረድአ=ረዳ
ረግዐ=ረጋ
ቀብዐ=ቀባ
ቀንዐ=ቀና
በልዐ=በላ
ቦአ=ገባ
በፅዐ=ተሳለ
ተሰብአ=ሰው ሆነ
ተቆጥዐ=ተቆጣ
ተንሥአ=ተነሳ
ተጋብአ=ተሰበሰበ
ተፈግዐ=ደስ ተሰኘ
ነቅዐ=መነጨ
አስተብፅአ=አደነቀ
አስተጋብአ=ሰበሰበ
አንብዐ=አለቀሰ
አውሥአ=መለሰ
አይድዐ=ነገረ
አጽምዐ=አደመጠ
ከልአ=ከለከለ
ወውዐ=ደነፋ
ወግዐ=ወጋ
ወፅአ=ወጣ
ዘርዐ=ዘራ
ጸምአ=ተጠማ
ጸንዐ=ጸና፥በረታ
ጸውዐ=ጠራ
ለአከ=ላከ
መሐከ=ራራ
ማሕረከ=ማረከ
ሰበከ=አስተማረ
ባረከ=ባረከ
ተዐረከ=ወዳጅ ሆነ
አምለከ=አመለከ
ፈለከ=ፈጠረ
ሀላወ=ኖረ
ሐሰወ=ዋሸ
ሐይወ=ዳነ
ቀነወ=ቸነከረ
ቤዘወ=አዳነ
ተለወ=ተከተለ
ተመርአወ=ተሞሸረ
ተሠገወ=ሰው ሆነ
ተሰፈወ=ተስፋ አደረገ
ተአደወ=ተደፋፈረ
ተባሕትወ=ብቸኛ ሆነ
ተደለወ=ተዘጋጀ
ኖተወ=ዋኘ
አስቆቀወ=አለቀሰ
አርኀወ=ከፈተ
አተወ=ገባ
አንሶሰወ=ተመላለሰ
ዐደወ=ተሻገረ
ወረወ=ወረወረ
ወርዘወ=ጎለመሰ
ዘረወ=በተነ
ዜነወ=ነገረ
ጻዕደወ=ነጭ ሆነ
ጸገወ=ሰጠ
ፈተወ=ወደደ
ፈነወ=ላከ
ኀበዘ=ጋገረ
ሐወዘ=አማረ
ረገዘ=ወጋ
ተከዘ=አዘነ
አኀዘ=ያዘ
አውገዘ=ለየ
አዘዘ=አዘዘ
አግዐዘ=ነጻ አወጣ
ውሕዘ=ፈሰሰ
ሀለየ=አሰበ
ሐለየ=ዘፈነ
ሐመየ=አማ
ሀከየ=ሰነፈ
መስየ=መሸ
ሰመየ=ስም አወጣ
ሴሰየ=መገበ
ሰትየ=ጠጣ
ሠነየ=አማረ
ረሰየ=አደረገ
ርእየ=አየ
ቀነየ=ገዛ
በልየ=አረጀ
ተሐሥየ=ተደሰተ
ተመነየ=ተመኘ
ተረሰየ=ተሸለመ
ተዐበየ=ኮራ
ተዋንየ=ተጫወተ
ነድየ=ተቸገረ
አመክነየ=አመካኘ
አስተርአየ=ታየ
ዐረየ=ተካከለ
አከየ=ከፋ
አወፈየ=ሰጠ
አጥረየ=ገዛ
ከረየ=ቆፈረ
ውዕየ=ተቃጠለ
ወደየ=ጨመረ
ዘርከየ=ሰደበ
ደወየ=ታመመ
ገነየ=ተገዛ
ጎንደየ=ዘገየ
ጎየ=ሸሸ
ጌገየ=በደለ
ጥዕየ=ዳነ
ጸለየ=ለመነ
ጸገየ=አበበ
ፈረየ=አፈራ
መዐደ=መከረ
ሞገደ=ማእበል አደረገ
ሰደደ=አባረረ
ሰገደ=ሰገደ
ርዕደ=ተንቀጠቀጠ
ተዋሐደ=አንድ ሆነ
ተዋረደ=ተዋረደ
ተዘምደ=ዘመድ ሆነ
ንእደ=አማረ
ነደ=ነደደ
ነገደ=ሄደ
ዖደ=ዞረ
ክሕደ=ካደ
ከብደ=ከበደ
ኬደ=ረገጠ
ወለደ=ወለደ
ወረደ=ወረደ
ፈቀደ=ወደደ
ፈድፈደ=በዛ
ኀደገ=ተወ
ሐገገ=ሕግ ሰራ
ነትገ=ጎደለ
ዐርገ=ወጣ
ደግደገ=ከሣ
ፈለገ=መነጨ
ሐብጠ=አበጠ
ሜጠ=መለሰ
አምሰጠ=አመለጠ
ፈለጠ=ለየ
ሐረጸ=ፈጨ
ሐነጸ=ሰራ
ሐወጸ=ጎበኘ
ሐጸ=ጎደለ
ሠረጸ=በቀለ
ቀብጸ=ተስፋ አጣ
ቀነጸ=ዘለለ
ዐመፀ=በደለ
አስተሐየጸ=ተመለከተ፥አመላከተ
አንፈርዐፀ=በደስታ ዘለለ
ደምፀ=ተሰማ
ገሠጸ=ተቆጣ
ኀለፈ=ሄደ
ሰየፈ=ቆረጠ
ቀሠፈ=ገረፈ
ተርፈ=ቀረ
አንገፈ=አዳነ
አዕረፈ=አረፈ
አዝለፈ=አዘወተረ
ከነፈ=በረረ
ዘለፈ=ሰደበ
ጸሐፋ=ጻፈ
ፈልሰፈ=ብልሀተኛ ሆነ

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግእዝ ክፍል 26
የግእዝ ስሞች (nouns) ክፍል 1
ዳሂ=ጓያ
ሱራሕ=ድንች
መናሂ=ነጭ ጤፍ
ወርኅ=ጨረቃ
እም=እናት
ቢሕ=ጉማሬ
ሰላምያሂ=ደጀ ሰላም
አካሂ=ጥገት፥አራስ ላም
ካሂ=ጊደር
መዝያሁ=ሙጃ
ኩሓ=ከያ ዛፍ
መድሔ=መጅ
ትሄ=መስኮት
ኤርጋሄ=አክርማ
ግሔ=እሽኮኮ
መቅድሕ=ወረንጦ
መንቢሕ=መጋኛ
ሰማሕ=ጣፊያ
ስማዝያሁ=ስሚዛ
ቆቅሕ=ቆቅ
ጽርሕ=አዳራሽ
ተፉሕ=ሙዝ
እልታሕ=ያልተሰፋ ቀሚስ
እራኅ=መሐል እጅ
አበጉንባሕ=ርኩም
እዝኅ=ሻፎይ ድንጋይ
ድማኅ=መሐል ራስ
መርኆ=ቁልፍ፥መክፈቻ
ኦሆ=እሽ በጎ በጀ
አፍትሖ=ዳኛ
ዶርሆ=ዶሮ
መምኤሉ=ችፍርግ
ገምሉ=አለቅት
ዔሊ=ድንጋይ ልብሱ
ጠሊ=ፍየል
ሄላ=ምንጭ
ሶልላ=ኮረት፥አሸዋ፥አፈር
ሠረገላ=መኪና
ሰግላ=ሾላ
ተኲላ=ተኩላ
ዔላ=የውሃ ጉድጓድ
አሜከላ=እሾህ
ኳሄላ=ጥንግ፤ኳስ
ጌልጌላ=ሰማይ
ጋላ=ጭፍራ፥ወታደር *ላ ላልቶ ይነበብ*
ስንዳሌ=ስንዴ
ቢረሌ=ብርሌ፥ብርጭቆ
ሐምል=ጎመን
ኀየል=ዋልያ
መሐፒል=ሳሙና
ሙርጡል=አዳራሽ (መርጡለ ማርያም እንዲል)
ቊንጽል=ቀበሮ
ቀይዘል=ሚዳቋ
ቤቴል=ቤተ ክርስቲያን
በድል=ባቄላ
በጸል=ነጭ ሽንኩርት
ቴጌል=የብረት ጉልቻ
ኒል=ሰማያዊ ቀለም
አባል=ሰውነት
አብሪል=የገነት ወፍ
እክል=እህል
አክሊል=ዘውድ፥የራስ ቆብ
አካል=አካል፥ሰውነት
ዕዋል=የአህያ ውርንጭላ
አሳተርሙ=የእሳት ራት
መስቴማ=ሰይጣን
ራማ=ደርብ
ቢጸልቱማ=ቀይ ሽንኩርት
አውቴዝራማ=የነቢያት ሀገር (ኢየሩሳሌም)
አዲማ=ትኋን
ደልጉማ=ገንፎ
ጳኩሲማ=ዳቦ፥አንባሻ
ክጥጥሜ=ቅባኑግ፥ጥጥ
ጊሜ=ጉም
ሐምሐም=ቅል
ላሕም=ላም
ሰሊሖም=ፈሳሽ ውሃ
ቃሕም=ጉንዳን
ቀሥታም=ሽመል
ቢሳም=ምሳና (ብሳና)
ትማልም=ትላንት
ዮም=ዛሬ
ጌሠም=ነገ
ተንከተም=ድልድይ
ዓለም=ዓለም
ኤላም=ደጀ ሰላም
ዓም=ዘመን፥ዓመት
ኤልዳም=ባርያ
ዐምዐም=ረግረግ
እም=እናት
ዖም=ዛፍ
አርያም=ሰማይ
አዲም=ቆርበት
አድያም=አውራጃ
ኤዶም=የገነት ስም
ዐፅም=አጥንት
ገሀነም=የመከራ ቦታ
ገዳም=ዱር በረሐ
ጥቅም=ግንብ
ጼናታም=ጤናዳም
ፀጋም=ግራ
የማን=ቀኝ
ፊካትም=የገነት አበባ፥የውሃ እናት
ፍጽም=ግንባር
ሞ=ብርሌ
መጽአሞ=ዋሻ ገደል
ሳዊሱ=አቅራሪታ
ፋሲልያሱ=እኔ ልሙት
ኮራሲ=የሸክላ አፈር
ከይሲ=እባብ
ብሕንሳ=በረት
ተኬሳ=ትክሻ
ዓሣ=ዓሣ
አንበሳ=አንበሳ
ፒላሳ=ድንኳን፥ደጃፍ
ፒሳ=ሙጫ
ሕዋስ=ሰውነት
ለንጳስ=ግምጃ
ሜሎስ=ሰይፍ
ሊጦስ=ሰሊጥ
መለንስ=ኑግ
መሳውስ=ጅማት
ሱላማጢስ=ቤተክርስቲያን
ሲኖዶስ=ስብሰባ፥ጉባኤ
ሰጳላክስስ=እስስት
ቆሮስ=ላዳን
ቀርጠሉስ=ቅርጫት
ቆንደራጢስ=ዳጉሳ
ቄድሮስ=ዋንዛ
ቄጵርስስ=ጽድ
ባሕሩስ=መቃ፥ሸንበቆ
ናሕስ=የግንብ ቤት
ናብሊስ=አታሞ
ነፋስ=ነፋስ
ነፍስ=ነፍስ
ኤልያስ=ወይራ
አስፈሊጦስ=ሰሊጥ
ዐሪሥ=ጎጆ
ኦርቶዶክስ=የቀና ሃይማኖት
አርዮስፋጎስ=አደባባይ፥መዝናኛ ቦት
አናጉንስጢስ=አንባቢ ዲያቆን
አክሳስ=ሽህ እግር፥የእበት ትል፥ቅምቡርስ
አግሲጦስ=የነቢያት ጉባኤ
ኤጴሞስ=ቀሚስ
ኪስ=ምንጭ
ኬጥሮጋውሎስ=የብረት ጋን
ውቅያኖስ=ውቅያኖስ
ገላሜዎስ=እስስት
ገሙስ=ጎሽ
ጠርቤንቶስ=ዋርካ
ጣዎስ=ዝንጉርጉር ወፍ
ፊላስ=የአልጋ ልብስ
ፎቃንስ=ጉሬዛ
ፊንክስ=ጥንብ አሞራ
ቀሱት=እንስራ

ይቆየን

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግእዝ ክፍል 27
ስሞች (nouns) ክፍል 2
ምድር=ምድር
ፍቅር=ፍቅር
ነባሪ=ቤተሰብ
ኀዳሪ=ቤተሰብ
ሐራ=ወታደር፥ጨዋ
አንበሪ=ታላቅ ዓሣ
ጌልዳቦሩ=ቡሃቃ
ማሪ=ጠንቋይ
ምዕራ=ጉልቻ
ሰይራ=ወገል
ሰጠጢራ=ቡና
ሰጲራ=ወታደር
ቀምጠራ=ሙዳይ
ቶራ=አጋዘን
ንብቲራ=ኩስኩስት
እንዚራ=በገና
አንደበራ=ጋለሞታ
ገንዶራ=የእግር ብረት
ፈጠራ=ልብ ወለድ
ፐፒራ=እንዶድ
ፓፒራ=ክብሪት
ኅንብርብሬ=ዝንጉርጉር
መምሬ=ወይራ
መርመሬ=ኮፌዳ
ኤስከደሬ=እልፍኝ
ኮሬ=የብረት ጋን
ጶደሬ=ግምጃ
ፍሬ=ፍሬ
ፕፕሬ=በርበሬ
ሐመር=ታንኳ፥መርከብ
ሕምር=እንሶስላ
ሐሠር=ገለባ
ሐንዘር=አነር
ሐንዚር=ጅራት
ሀገር=መንደር፥ሀገር፥ከተማ
ማር=አቤቱ፥ሊቅ
መዓር=ማር
ሦር=በሬ
ሶከር=ስኳር
ቄዳር=ዘላን
ባሕር=ባሕር
ብሩር=ብር
በትር=ሽመል
ንስር=አሞራ
እንዶር=ቡዳ
አየር=ነፋስ
ዕጒስታር=ሬት
እግር=እግር
አጽፋር=አደይ አበባ
ከንፈር=ከንፈር
ከፈር=ቅርጫት፥እንቅብ
ኲፋር=ካባ
ወግር=ኮረብታ
ደብር=ተራራ
ጻሕር=ብረት ምጣድ
ፀምር=ግምጃ
ፊቃር=ቀሚስ
ከበሮ=ከበሮ
ውቅሮ=ሕንጻ፥አዳራሽ
እጠቁ=ገበታ
ኬርቃ=ስርጥ መንገድ
ጥቃ=አጠገብ
ጣቃ=ጨለማ
ሐቌ=ወገብ
ሐንቄ=ቅማል
መርቄ=ቆላ
ዝህብ=ጅብ
ቄውንቄ=ጽድ፥ዋንዛ
ዐንቄ=ጭላት
መቀቅ=ሙገጫ
መንገኒቅ=ጠመንጃ
ማዕነቅ=ሽመላ
ረቅ=ብራና
ወርቅ=ወርቅ
ፊላቅ=ጎታ
ብሒእ=እርሾ
ሶርቃቡ=ሊጥ
ትለቤ=ተልባ
ከርቤ=ሽቱ
ሐሊብ=ወተት
መሶብ=መሶብ
መረብ=ሜዳ
መርሕብ=ሜዳ፥መስክ
ምኲራብ=አዳራሽ
መዝገብ=ኮፌዳ፤ሣጥን
መጒረብ=ጅንፎ
ሱጣብ=ወስከንበያ
ርግብ=ርግብ
ንህብ=ንብ
አቅራብ=ጊንጥ
ከልብ=ውሻ
ኮከብ=ኮከብ
ዘነብ=ጅራት
ዝእብ=ጅብ
ግብ=ጉድጓድ
ጻሕብ=ማድጋ
ህቦ=ጤዛ
ውጽቦ=ቀለበት
ኬልቲ=ቀኝ አዝማች
ፌልቲ=ግራ አዝማች
ሣኒታ=ነገ፥ማግስት
ወልታ=ጋሻ
ናቡቴ=የዐረግሬሳ
ኔቡቴ=ሞፈር
ኅለት=ዘንግ
ሕልቀት=ቀለበት
ሔሴሜት=ድመት
ኅብስት=እንጀራ
ሐውልት=ሐውልት
ሐይመት=ድንኳን
ኅጠት=ቅንጣት
ልሕኲት=ገንቦ
ሌሊት=ሌሊት
ሊሊት=የሌሊት ወፍ
ልገት=ጎጆ
ላጽቂት=ፌንጣ
ሜላት=ሐር ግምጃ
መልታሕት=ፊት፥ጉንጭ
መስብክት=ጋን
መሥእርት=ሚዶ
መራናት=መቅረዝ መብራት
መሬት=መሬት፥አፈር
መቅፁት=ድስት፥ምንቸት
መበለት=ባልቴት
ምት=ባል
ምኔት=ገዳም
መክሊት=ሳንቲም
መዝራዕት=ክንድ
ምጽንዐት=ሰማይ
ሣሬት=ሸረሪት
ሥርዐት=ድርጭት
ሥእርት=ጸጉር
ራግናት=ብቅል
ሰኳዕት=ጉንዳን
ቀሡት=እንስራ
ስት=ቄጤማ
ቊናማት=ከረጢት
ብሄሞት=ዘንዶ፥ጉማሬ፥ጎሽ
ብርት=ብረት
ቤት=ቤት
ብእሲት=ሴት
ተረቅት=የሌት ወፍ
ታቦት=ታቦት
ትካት=ዱሮ ቀድሞ
ዓመት=ዓመት
አምትንት=ጅማት
እሳት=እሳት
ዐርቦት=ችባሓ
አረቦናት=ፍትግ ክክ
አርዑት=ቀንበር
ዐራት=አልጋ
ዐራቦት=ሜዳ
እንጎት=ትርንጎ
ዐዘቅት=ጉድጓድ
ዕፍረት=ሽቱ
ኩሊት=ኲላሊት
ክሣቶት=መከዳ
ኮኮሞት=ዋምራ
ወዲፈት=ዳውጃ፥ግምጃ ጨርቅ
ዝፍት=ሙጫ
ደሴት=የባሕር ጥጋጥግ
ገራህት=እርሻ
ገነት=ጓሮ፥የአትክልት ቦታ
ግብነት=አይብ
ጥምዐት=እንሶስላ
ጽህርት=ጋን፤ድስት
ጾማዕት=ዋሻ
ፀበርት=ዘንባባ
ጽንጽንት=ነቀዝ
ጼዴኔት=ዔሊ
ጻጹት=ጫጭት
ጽፍነት=ስልቻ
ፍኅርት=ጫጩት
ፍኖት=ጎዳና
ቦኑ=በውኑ
መርሳኒ=ቀጋ
ቆብኒ=ቅማል
ቶብኒ=ትኋን
አቃኒ=ችፍርግ
አንጼዋ=አይጥ
ሆሳዕና=መድኃኒት
መና=እንጀራ
መዲና=ከተማ
ሰኮና=ተረከዝ
ቴሎግና=ቃለ እግዚአብሔር
ኦርና=ሚዳቋ
ጳውቄና=ጽድ
ጸደና=የጣዝማ ማር
ፍና=መንገድ
ፓና=መብራት
ልብኔ=ልምጭ
ቊንቊኔ=ነቀዝ


መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
የግእዝ ቋንቋ ክፍል 28
የግእዝ ስሞች (nouns)
ኀጺን=ብረት
ሜሮን=ቅብዐ ቅዱስ
መንገን=አሽክላ፥መኪና
ስኂን=ሽቱ
ሥን=ደም ግባት
ሲላን=አብሽ
ሶመን=ሳማ
ሰሳን=ኮሶ
ሰራግልዮን=አሳማ
ሰኪኖን=እንዶድ
ሰውሳን=ሱፍ
ሰጥረጲሎን=ዋንዛ፥ሽነት
ራምኖን=ዶግ
ቀርን=ቀንድ፥ነጋሪት፥ከበሮ
ቄድሮን=ዋንዛ
ቅጥራቅጥሬን=ድንቢጥ
ቆጶን=ጫማ
ባላን=ግራር
ተመን=ዘንዶ
ተርሜን=ደደሆ፥ክትክታ
ቴፈን=ወይፈን
አስከሬን=ሣጥን፥ከረጢት
ኤርሞን=ሰማይ
ዐረቦን=መያዣ፥ፈለማ፥የስጦታ መጀመርያ
አርጋኖን=ምስጋና፥መሰንቆ
አቅላሜዶን=ቁልቋል
ዕቀን=ተቀጽላ
ዕቋን=ወገሚት
ዕብን=ድንጋይ
እቶን=ምድጃ
እዝን=ጆሮ
ዓይን=ዓይን
ከሙን=ተልባ
ከሜን=ፌጦ
ከርሜን=ደድሆ
ኪሮግልዮን=ዐሣማ
ወይን=ወይን፥ጠላ
ዘባን=ጀርባ
ዘይቶን=ዘይቶነ
ዙዝዮን=አለቅት
የማን=ቀኝ
ዱሐን=ዳጉሳ
ደራጎን=ዘንዶ
ጤገን=ብረት ምጣድ
ጳልቃን=ርኩም
ጵርዮን=መጋዝ
ጽንጒን=ጭቃ
ሰገኖ=ሰጎን
ደርከኖ=ሰማያዊ
ሙራኡ=ሽንጥ
ሰንብኡ=ሳንባ
ደርፍኡ=ሻኛ
ገርድኡ=ዳኛ
እንዳኢ=እንጃ
ገባኢ=ምንደኛ፥ሠራተኛ
ገዛኢ=ሚዜ
መርዓ=ሙሸራ ጫጉላ
እንግድዓ=ደረት
መሥኤ=መንሽ
ቊልኤ=ወዳጅ
ጒርዔ=ጉረሮ
መሐስእ=ጠቦት
መጒድዕ=መዶሻ
ሠምዕ=ሠም
ሰንቡዕ=ሳንባ
ቄርነናዕ=እንቁራሪት
ቆብዕ=ቆብ
ቋዕ=ቁራ
ብርዕ=መቃ፥ሸምበቆ፥ጭራሮ
በግዕ=በግ
ተላዕ=ፍሪንባ
እንቋዕ=እሰይ
ኲርናዕ=ክንድ
ከርካዕ=ሎሚ
ድርዕ=የጦር ልብስ
ድኩዕ=ፋንድያ
ጠባይዕ=ባሕርይ፥ጠባይ
ፀዐዕ=ብልጭታ
ፀፍዕ=አዛባ
ኮራኪ=ምስጥ
መንካ=ማንኪያ
መስቴካ=ጨጓራ
ሶቤቃካ=ጅግራ
ታዕካ=አዳራሽ
አጥሬስካ=ተዝካር
ፔርካ=ሽንብራ
ሰናፔ=ሰናፍጭ
ሐሰክ=ተምች
ሐኒክ=አፈር
ማዕከክ=ማሰሮ፥ቶፋ
ሦክ=እሾህ
ደደክ=ደጋ
አድራማሌክ=ጉጉት
ፋሌክ፥ፈለክ=ሰማይ
ሴዋ=ጌሾ
ጣዕዋ=ጥጃ
ሠርዌ=ጭፍራ፥ጉድፍ
አርዌ=አውሬ
ማህው=ብርጭቆ
ሰዋስው=መሰላል
እዳው=ትቢያ
አፈው=ሽቱ
ዘብድው=ሌጦ
ተከዚ=ጎርፍ
ሮዛ=ጽጌ ረዳ
ጉዛ=ጭላት
ጠረጴዛ=ወንበር
ተከዜ=ፈሳሽ ውሃ
ሕምዝ=መርዝ
ሐርመዝ=ዝኆን
ሐንገዝ=ብብት
ቅንፉዝ=ጃርት
ቤዝ=ኮከብ
አርዝ=ዛፍ
ፒርልዩ=ቀንጠፋ
ሐራውያ=ከርከሮ፥አሳማ
መንኮብያ=አውራ ጣት
ሰፌልያ=ድጅኖ፥መዶሻ
ትንንያ=ትንኝ
ሆባይ=ዝንጀሮ
ሐጋይ=በጋ
ማይ=ውሃ
ሙዳይ=ሙዳይ፥አገልግል
ሥርናይ=ስንዴ
ብዕራይ=በሬ
ንዋይ=ገንዘብ
ፀሐይ=ፀሐይ

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
የግእዝ ቋንቋ ክፍል 29
የግእዝ ስሞች (nouns) ክፍል 4

ሳይዳ=ቆንጆ
ተስጴዳ=ጥንቸል
ተቅዳ=ድንብላል
ጋዳ=እጅ መንሻ
ዴዴ=ደጃፍ
ስጒርንድ=ሽንኩርት
ብድብድ=ቸነፈር
ዐምድ=ምሰሶ
ክሣድ=አንገት
ከብድ=ሆድ
ድድ=መሰረት
ጒጋ=ቁንጫ
ጋጋ=ዛንጀር፥የእግር ብረት
ሐርጌ=ጊደር
ነጌ=ዝኆን
ሐረግ=አረግ
ሰፍነግ=እንጉዳይ
ሰፍነግ=የውሃ መምጠጫ
ዔረግ=ቀፎ
ዐንግ=ጉትቻ
አድግ=አህያ
ንግምስምስጤ=ወግ፥ታሪክ
ሑሱጱ=አሽክት
ጸያጴ=እንሽላሊት
መላጺ=ምላጭ
ኆጻ=አሸዋ
ፋጻ=ፉጨት
ፃፄ=ብል፥ነቀዝ
ሐርገፅ=አዞ
ሐጽ=ጦር
መቅረጽ=መቀስ
ቊይጽ=ጭን
አንቀፅ=ደጃፍ፥በር
ዕፅ=እንጨት
ጎጻጉጽ=ሸካራ፥ገረገንቲ መንገድ
ገጽ=ፊት
ማዕፆ=መዝጊያ
መንፌ=ወንፊት
መትከፍ=ትክሻ
አንፍ=አፍንጫ
አውቃፍ=አምባር
አፍ=አፍ
ዖፍ=ወፍ
ክንፍ=ክንፍ
ዲፓ=ሽመቃ

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
የግእዝ ቋንቋ ክፍል 30
በግእዝ ናልኝ ኑሪልኝ መጣብኝ ወዘተ ለማለት የሚጠቅሙን የበ እና የለ ዝርዝሮች።
ሊተ=ልኝ......ነዓ ሊተ=ናልኝ
ለነ=ልን.....ሰአሊ ለነ.....ለምኝ ልን
ሎሙ=ላቸው
ለከ=ልህ
ለኪ=ልሽ
ለክሙ=ላችሁ
ይላል።ይህ ከግሡ በኋላ ሲመጣ የሚኖራቸው ትርጉም ነው።
ብየ=ብኝ.....በጽሐ ብየ....ደረሰብኝ
ብነ=ብን
ብክሙ=ባችሁ
ብከ=ብህ
ብኪ=ብሽ
ቦሙ=ባቸው
ቦቱ=በት
ባቲ=ባት.....መጽአ ባቲ....መጣባት ይላል ይህ ከግስ በኋላ ሲመጣ የሚኖረው ትርጉም ነው።
ናሁ=እነሆ
ነያ=እነኋት
ነዮሙ=እነኋቸው እያለ በ10ሩ መራሕያን ይረባል።

ከላይ ያየናቸው የበ እና የለ ሌላ ዓይነት መንገድም አላቸው።
ሎቱ=ለእርሱ..ይገባዋል
ላቲ=ለእርሷ....ይገባታል
ለኪ=ለአንቺ...ይገባሻል
እያለ በ10ሩ ይረባል።ሎቱ ስብሀት ስንል ምስጋና ይገባዋል ማለት ነው።ሰላም ለኪ ሲል ደግሞ ሰላም ለአንቺ ማለት።ተጨማሪ ሰፊ ትርጉም አላቸው።ለጊዜው ይህንን እንያዝ።
ቦቱ=በእርሱ
ብኪ=በአንቺ
እያለም በ10ሩ ይረባል።ምሳሌ ብኪ ድኅነ ዓለም ሲል በአንቺ ዓለም ዳነ ማለት ነው።

ጥያቄ
የሚከተሉትን ተርጉም
1, ገብረ ለከ (ገብረ=ሰራ)
2, አሌ ለክሙ (አሌ=ወዮ)
3, ሕየው ሊተ (ሕየው=ኑር)
4, ሰረቀ ቦቱ
5, በዝኀ ብነ

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግእዝ ክፍል 31
አገናዛቢ ቅጽል (possessive adjective)
ዚኣየ=የእኔ=My
ዚኣነ=የእኛ=our
ዚኣሁ=የእርሱ=his
ዚኣሃ=የእርሷ=her
ዚኣሆሙ=የእነርሱ=their
ዚኣከ=የአንተ=your
ዚአክሙ=የእናንተ=your
ዚአኪ=የአንቺ=your
ዚአክን=የእናንተ=your (ሴቶች)
ዚኣሆን=የእነርሱ=their (ሴቶች)
አገናዛቢ ቅጽሎች በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ ከስሙ በፊት እየመጡ ይነገራሉ።ይህም ማለት ለምሳሌ የእኔ ሀገር my countries ይላል።በግእዝ ሀገረ ዚአየ ይላል።የእናንተ ሀገር ለማለት በእንግሊዘኛ your country ይላል። በግእዝ ደግሞ ሀገረ ዚአክሙ ይላል።እንዲህ እንዲህ እያለ ይሄዳል።በዓረፍተ ነገር እንመልከት

ኢትዮጵያ የእኛ ሀገር ናት.................አማርኛ
Our country is Ethiopia............English
ኢትዮጵያ ይእቲ ሀገረ ዚአነ.................ግእዝ

ጥያቄ
ግእዙን ወደ አማርኛ አማርኛውን ወደ ግእዝ ተርጉም።
1 የእኔ መጽሐፍ
2 የእኛ ነገር
3 የእርሷ ደስታ
4 ጸረ ዚአነ መስቴማ ውእቱ (hint፦ጸር=ጠላት።መስቴማ=ሰይጣን)
5 የእኛ ሀገር በሰማይ ነው።
6 ማርያም እመ ዚአነ (hint፦እም=እናት)

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግእዝ ክፍል 32
Possessive Pronoun (አገናዛቢ ተውላጠስም)
ዚአሆሙ=የእነርሱ=theirs
ዚኣሆን=የእነርሱ=theirs (ሴቶች)
ዚአክሙ=የእናንተ=yours
ዚአክን=የእናንተ=yours (ሴቶች)
ዚአነ=የእኛ=ours
ዚአየ=የእኔ=mine
ዚአከ=የአንተ=yours
ዚአኪ=የአንቺ=yours
ዚኣሁ=የእርሱ=his
ዚኣሃ=የእርሷ=hers
አስተውል አገናዛቢ ተውላጠ ስም (possessive pronoun) ከአገናዛቢ ቅጽል (possessive adjectives) የሚለዩት አገናዛቢ ተውላጠ ስሞች ተሳቢ (object) ሲሆኑ ብቻቸውን ይነገራሉ።አገናዛቢ ቅጽሎች ግን ብቻቸውን አይነገሩም።ቅጽል ስለሆኑ ከእነርሱ ቀጥሎ ስም ያስፈልጋል።ልዩነታቸውን በምሳሌ እንመልከት።

Possessive pronoun
ታላቁ ወንዝ ግዮን የእኛ ነው...............አማርኛ
The great river Ghion is ours....English
ዚአነ ውእቱ ፈለገ ግዮን ዐቢይ..............ግእዝ

Possessive adjective
የእኛ ወንዝ ግዮን ታላቅ ነው...........አማርኛ
Our river Ghion is great..........English
ፈለገ ዚአነ ግዮን ዐቢይ ውእቱ...........ግእዝ

በነገራችን ላይ ከላይ ያሉት ዝርዝሮች የዘ ዝርዝሮች ይባላሉ።ለሴትም ለወንድም ለአንድም ለብዙም ይችላል።ትርጉሙ ልክ እንደ ዘ ሆኖ ለሴት ብቻ የሚያገለግል እንዲሁም ለብዙ ብቻ የሚያገለግል አለ።ለሴት እንተ ነው።ለብዙ እለ ነው።ዝርዝራቸውን ቀጥለን እንመልከት።
እንቲአሁ=የእርሱ
እንቲአሃ=የእርሷ
እንቲአሆሙ=የእነርሱ
እንቲአሆን=የእነርሱ (ሴቶች)
እንቲአከ፥እንቲአኪ፥እንቲአክሙ፥እንቲአክን፥እንቲአየ፥እንቲአነ እያለ በ10ሩ ይረባል።እለም በተመሳሳይ እሊአሁ፥እሊአሃ፥እሊአሆሙ፥እሊአሆን፥እሊአከ፥እሊአኪ፥እሊአክሙ፥እሊአክን፣እሊአየ፥እሊአነ እያለ በ10ሩ ይረባል።ትርጉሙ ተመሳሳይ ነው።ልዩነቱን ከዚህ ቀጥለን እንመልከት።

ቅዱሳን የእኛ ናቸው ለማለት።ባለቤቶቹ ቅዱሳን ብዙ (Plurals) ስለሆኑ።ዘ ለሴት ለወንድ ለአንድ ለብዙ ስለሚችል።ዚአነ እሙንቱ ቅዱሳን። ይላል።እንተ ግን ለሴት ያውም ለነጠላ እንጂ ለብዙ ስለማያገለግል እንቲአነ እሙንቱ ቅዱሳን አይልም።እለ ግን ለብዙ ስለሚያገለግል እሊአነ እሙንቱ ቅዱሳን እንላለን።እንተ ለሴት ያገለግላል ያልነው የእኔ ፍቅር እርሷ ናት ሲል በግእዝ ይእቲ ይእቲ ፍቅርተ እንቲአየ ይላል ወይም ይእቲ ይእቲ ፍቅርተ ዚአየ ይላል።

ጥያቄ
የሚከተሉትን ግእዙን ወደ አማርኛ አማርኛውን ወደ ግእዝ ቀይር

1 ዚአየ ውእቱ ገለአድ
2 እሊአነ እሙንቱ መላእክት
3 ማርያም የእኛ እናት ናት።
4 ቅዱሳን የእኛ ወዳጆች ናቸው።
5 ኢትዮጵያ የእኛ ናት።

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግእዝ ክፍል 33
አመልካች ተውላጠ ስሞች (Demonstrative pronouns) እና አመልካች ቅጽሎች (Demonstrative Adjectives)
ዝንቱ፥ዝ=ይህ=this
ዛቲ፥ዛ=ይህች=this
ዝስኩ፥ዝኩ፥ዝክቱ=ያ=that
እንታክቲ፥እንትኩ=ያች=that
እልክቱ፥እልኩ=እነዚያ=those
እልኮን፥እልክቶን=እነዚያ=those (ሴቶች)
እሉ፥እሎንቱ=እነዚህ=these
እላ፥እሎን፥እላንቱ=እንዚህ=these (ሴቶች)
እነዚህ አመልካች ቅጽልም አመልካች ተውላጠ ስምም ሆነው ሲያገለግሉ ትርጉማቸው ይኽው ነው።ነገር ግን አመልካች ቅጽልና አመልካች ተውላጠ ስም ሆነው ሲያገለግሉ በአረፍተ ነገር የተለያየ አቀማመጥ አላቸው።እርሱን ቀጥለን እንመልከት።

አመልካች ቅጽል ከሆነ ከስም በፊት ሆነው ነው የሚያገለግሉን።ይህም ማለት ይህ ሀገር እነዚያ ሀገሮች ያች ሀገር እያለ ይሄዳል በእንግሊዘኛም ቢሆን this country,those countries,that country እያለ ይሄዳል።አስተውል ከስም በፊት ነው የመጣው።
ምሳሌ
ዛ አንቀጽ እንተ እግዚአብሄር ቢል ይች ደጅ የእግዚአብሄር ናት ይላል።አስተው ዛ የምትለው አንቀጽ ከሚለው ስም በፊት እንደመጣ።ምሳሌ
እነዚያ ነቢያት ቅዱሳን ነበሩ..............አማርኛ
Those prophets were saints....English
እልክቱ ነቢያን ቅዱሳን እሙንቱ...........ግእዝ

አመልካች ተውላጠ ስም ሲሆን ግን ራሱን ችሎ ተሳቢ (object) ይሆናል።ለምሳሌ
እናቴ ይህች ናት......................አማርኛ
This is my mother.............English
ዛቲ ይእቲ እምየ........................ግእዝ

እያለ ይሄዳል ማለት ነው።

ጥያቄ
የሚከተሉትን ግእዙን ወደ አማርኛ አማርኛውን ወደ ግእዝ ተርጉም።
1 ዛቲ ዓለም ኀላፊት ይእቲ
2 ዝ ውእቱ ጊዜ ባርኮት
3 ሀብ መንፈቆ ለእንታክቲ (hint መንፈቆ=ግማሹን ሀብ=ስጥ)
4 እነዚያ ሰዎች የተባረኩ ናቸው
5 ይህ ሰውየ አብዷል (አብደ=አበደ)

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግእዝ ክፍል 34
©ዘ፥እንተ፥እለ እንደ ቅጽል©
ዘ፥እለ እና እንተ ቅጽል ይሆናሉ።ምሳሌ አቡነ ዘበሰማያት ይትቀደስ ስምከ ሲል።በሰማያት ያለ አባታችን ተብሎ ይተረጎማል።"ዘ" የአቡነ ቅጽል ይባላል።በምስጢር ደረጃ ስንመለከተው ከ Relative pronoun ጋር ይመሳሰላል።በሰፊው እንየው።
ዘመጽአ=የመጣ
ዘመጽአት=የመጣች
ዘመጻእከ=የመጣህ
ዘመጻእኪ፥ዘመጻእክሙ፥ዘመጻእኩ እያለ በ10ሩ ይዘረዘራል።ዘ ለአንድ ለብዙ ለሴት ለወንድ ይቀጸላል።ይህም ማለት ማርያም ዘወለደት አምላከ ሲል አምላክን የወለደች ማርያም ይልና ዘ የማርያም ቅጽል ይባላል።እንተ ለሴት ብቻ ማርያም እንተ ወለደት አምላከ ይላል።እለ ለብዙ ሐዋርያት እለ ሰበኩ ወንጌለ ብሎ ወንጌልን የሰበኩ ሐዋርያት ይላል።እለ ለብዙዎች ሐዋርያት የተቀጸለ እንደሆነ አስተውል። በእንግሊዘኛው
Who,whose,whom.....ለሰው
Which..........................ለነገር
That..............................ለነገርም ለሰውም

ነገሩ ግልጽ እንዲሆንልን በአረፍተ ነገር ብንመለከተው መልካም ነው።

ኢትዮጵያን ያስተማረ ዮሐንስ የጌታ ደቀመዝሙር ነው።
John is the disciple of Christ who preachs Ethiopia።
ዮሐንስ ውእቱ ረድአ ክርስቶስ ዘሰበከ ኢትዮጵያ ይላል።

ኦሪት ዘጸአትን የጻፈ ሙሴ ሞተ
Moses who write the Exodus is dead
ሞተ ሙሴ ዘጸሐፈ ኦሪተ ዘጸአት

አሚናዳብ የገዛት መኪና ጥሩ ናት።
The car which/that Aminadab bought is good.
ሰናይት ይእቲ ሠረገላ ዘአጥረያ አሚናዳብ።

እያለ ይሄዳል።

ጥያቄ
ግእዙን ወደ አማርኛ አማርኛውን ወደ ግእዝ ተርጉም።
1 ዕፅ እንተ ርእያ ሙሴ
2 መስቀል ዘተሰቅለ ቦቱ ክርስቶስ
3 የምወዳት ሀገሬ
4 ለቅዱሳን የተሰጠች ሃይማኖት
5 ቤተ ክርስቲያን እንተ ናፈቅራ


መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
2024/10/02 02:30:25
Back to Top
HTML Embed Code: