Telegram Web Link
ግዕዝ ክፍል 1

ልሣነ ግእዝ
ክፍል 1


አቀድም አእኩቶቶ ለእግዚአብሔር...

ካለመኖር አምጥቶ እንዳመሰግነው የፈጠረኝ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን አሜን ::

እግዚአብሔር ቢፈቅድ እስከ ነሓሴ የግእዝ ቋንቋ እንከልሳለን።ከነሓሴ16 በኋላ ደግሞ ፍትሐነገሥት በጥልቀት እንማማራለን።ከዛሬ ጀምሮ ለ20 ክፍል የሚዘልቅ የግእዝን ቋንቋ እንማራለን።

በመጀመሪያ ግን ግእዝ ለምን ይጠቅማል የሚለውን ስናይ የቤተክርስቲያንን ምሥጢር በጥልቀት ለመረዳት በተለይ ቅዱሳት መጻሕፍትን ቅዳሴውን ማህሌቱን ምሥጢሩን ለመረዳት ይጠቅማል።ግእዝ የራሱ ፊደል ሥርዓተንባብ እና ቁጥር አለው።በቤተክርስቲያን ትምህርትም በዋናነት ቅኔ ለዚህ ተግባር የዋለና በሀገራችንም ስመጥር የታሪክ ምሁራን እነ ተክለጻድቅ መኩሪያ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ የፍቅር እስከ መቃብር ጸሐፊ ሐዲስ አለማየሁ የቤተክርስቲያን ሊቃውንትም ለዚህ ሙያ ጥልቅ እውቀት እንደነበራቸው በጻፏቸው መጻሕፍት እንረዳለን። ለዛሬ ከቁጥር እንጀምራለን ቁጥር በግእዝ አኀዝ ይባላል።ይኽውም አኀዘ ያዘ ቆጠረ ጀመረ ከሚለው ግስ የወጣ ነው።በግእዝ መስራች ቁጥሮች 20 ናቸው።

እነርሱን አንድ በአንድ እንመልከት እና ዛሬ እስከ 10000 በግእዝ መቁጠር የሚያስችለንን እንማራለን


1=፩=አሐዱ=አንድ=one
2=፪=ክልኤቱ=ሁለት=two
3=፫=ሠለስቱ=ሦስት=three
4=፬=አርባዕቱ=አራት=four
5=፭=ኀምስቱ=አምስት=five
6=፮=ስድስቱ=ስድስት=six
7=፯=ሰብዓቱ=ሰባት=seven
8=፰=ሰምንቱ=ስምንት=eight
9=፱=ተስዓቱ=ዘጠኝ=nine
10=፲=አሠርቱ=አስር=ten
20=፳=እሥራ=ሐያ=twenty
30=፴=ሠላሳ=ሠላሳ=thirty
40=፵=አርብዓ=አርባ=fourteen
50=፶=ኃምሳ=አምሳ=fifty
60=፷=ስድሳ/ስሳ=ስልሳ=sixty
70=፸=ሰብዓ=ሰባ=seventy
80=፹=ሰማንያ=ሰማንያ=eighty
90=፺=ተስዓ=ዘጠና=ninety
100=፻=ምእት=መቶ=hundred
10000=፼=እልፍ=አስር ሺ
ናቸው።በመካከል ያሉትን እንዴት መመስረት እንደሚቻል ቀጥሎ እንመለከታለን

1 ከ1 እስከ 100 ላሉት
ለምሳሌ1:-
25 ሲፃፍ 20+5 ታደርግና እሥራ ብለክ በመደመሩ ምትክ ወ አስገብተህ ኀምስቱ ትላለህ።ስለዚህ እስራ ወኀምሥቱ ትላለህ።
ምሳሌ 2:-
84=80+4=ሰማንያ ወ አርባእቱ ይላል

2 ከ100-10000 ላሉ ቁጥሮች
ምሳሌ1፦
108=100+8=፻+፰=፻፰=ምእት ወ እሥራ

ምሳሌ2፦
247=2×100+40+7=፪×፻+፵+፯=፪፻፵፯=ክልኤቱ ምእት አርብዓ ወ ሰብዓቱ

ምሳሌ3
801=8×100+1=፰×፻+፩=፰፻፩ሰመንቱ ምእት ወ አሐዱ

ምሳሌ4
1000=10×100=፲×፻=፲፻አሠርቱ ምእት

ምሳሌ5
1056=10×100+50+6=፲×፻+፶+፮=፲፻፶፮=አሠርቱ ምእት ኃምሳ ወስድስቱ

ምሳሌ6፦
2456=24×100+50+6=(20+4)×100+50+6=[፳×፬)×፻+፶+፮=፳፬፻፶፮=እስራ ወ አርባዕቱ ምእት ኃምሳ ወስድስቱ

ምሳሌ7፦
2007=20×100+7=፳×፻+፯=፳፻፯እሥራ ምእት ወሰብዓቱ

ምሳሌ8
9842=98×100+40+2=(90+8)×100+40+2=(፺+፰)×፻+፵+፪=፺፰፻፵፪=ተስዓ ወስምንቱ ምእት አርብዓ ወክልኤቱ ይላል።

መልመጃ/ምልማድ
የሚከተሉትን ቁጥሮች ከነ ንባባቸው ወደ ግእዝ ለውጥ
1፦ 99 ነገደ መላእክት
2፦ 2012 ዓመተ ምሕረት
3፦ 318 ሊቃውንት
4፦ 5000 ሕዝብ
5፦ 120 ቤተሰብ
..
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን ግእዝ መማር ለሚፈልጉ share ያድርጉ።

ክፍል 2 ይቀጥላል
........

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግዕዝ ክፍል 2

✟ልሣነ ግእዝ፤ክፍል 2✟

አቀድም አእኩቶቶ ለእግዚአብሔር
በክፍል 1 እስከ አስር ሺ እንዴት በግእዝ መጻፍና መቁጠር እንደሚቻል አይተናል አሁን ከዚያ በላይ ስላሉ ቁጥሮችና ስለፊደል እንማማራለን።

ከ10,000 በላይ ያሉ ቁጥሮች

ምሳሌ 1፦
10483=10000+4×100+80+3=፼+፬×፻+፹+፫=እልፍ ወ አርባእቱ ምእት ሰማንያ ወ ሠለስቱ ይላል።

ምሳሌ 2፦ 29347=2×10000+93×100+40+7=2×10000+(90+3)×100+40+7=፪×፼+(፺+፫)×፻+፵+፯=፪፼፺፫፻፵፯=ክልኤቱ እልፍ ተስዓ ወ ተስዓቱ ምእት አርብዓ ወ ሰብዓቱ ነው።
ሌላው
➤10000=እልፍ=አስር ሺ
➤100000=አሠርቱ እልፍ=አእላፍ=መቶ ሺ
➤1000000=አሠርቱ አእላፍ=አእላፋት=ሚልየን
➤10000000=ትእልፊት=አስር ሚልየን
➤100000000=ትእልፊታት=መቶ ሚልየን
➤1000000000=ምእልፊት=ቢልየን
➤10000000000=ምእልፊታት=አስር ቢልየን
ይላል።

ከዚያ በላይ ያሉ ቁጥሮችን በማዛረፍ እስከፈለግነው መቁጠር እንችላለን ለምሳሌ 20 ዜሮ ያለው ቁጥር ምእልፊተ ምእልፊታት ይባላል።

ምሳሌ 3፦
144000 ህፃናትን ሄሮድስ አስገደለ ይላል።ስለዚህ ይህን ቁጥር ወደ ግእዝ ስንቀይረው
144000=14×10000+40×100=(10+4)×10000+40×100=(፲+፬)×፼+፵×፻=፲፬፼፵፻=አሠርቱ ወ አርባእቱ እልፍ ወ አርብዓ ምእት ይላል።

በሌላ መልኩ 144000=100,000+4×10,000+40×100=፲፼+፬×፼+፵×፻=፲፼፬፼፵፻ ይላል ሲነበብም አእላፍ ወ አርባእቱ እልፍ ወ አርብዓ ምእት ይላል።ብዙ ጊዜ ይህ አልተለመደም።

ስለዚህ ሲጠቃለል በግእዝ ቁጥር እስከ ፈለገው መቁጠር እንችላለን ማለት ነው።

✤በተረፈ የግእዝ ቋንቋ መማሪያ በሚል በቅርብ በምርጥየ ወንድሞቼና እህቶቼ ብርታት ያሳተምኩት መጽሐፍ አዲስ አበባ 4 ኪሎ "ብራና መጻሕፍት ማከፋፍያ ማህበረ ቅዱሳን ህንፃ አጠገብ" ስላለ በጥልቀት ከዚያ ማየት ትችላላችሁ።

ፊደል
ከ ሀ እስከ ፐ ያሉት ፊደላት የግእዝ ፊደላት ናቸው። "ቸ፣ዠ፣ሸ፣ጀ፣ኸ፥ኘ፥ቨ፣" የግእዝ ፊደላት አይደሉም።
በግእዝ ቋንቋ የ "ሀ፣ሐ፣ኀ" "ጸ፥ፀ" "ሰ፥ሠ" አንድ ቃል ሲፃፍ የተለያየ ትርጉም ሰለሚሰጥ ጥንቃቄ ያስፈልጋል::
ለምሳሌ :-
"ሐለየ" እና "ኀለየ" የተለያየ ትርጉም አላቸው አንዱ አሰበ ማለት ሲሆን ሌላኛው ዘፈነ ማለት ነው።

"ሰአለ" እና "ሠዐለ" አንደኛው ሳለ ማለት ሲሄን አንደኛው ለመነ ማለት ነው።
ሰአሊ ለነ ቅድስት ሲል ቅድስት ሆይ ለምኝልን ሲል።ሥዕለ ተክለሃይማኖት ሲል የተክለሃይማኖት ሥዕል ማለት እንጂ የተክለሃይማኖት ልመና ማለት አይደለም።

ሰረቀ ማለት ሰረቀ ሌባ ሆነ ማለት
ሲሆን "ሠረቀ" ማለት ግን ወጣ ማለት ነው።

ምሥራቅ ስንል መውጫ ማለት ነው።ስለዚህ እኒህን መጠንቀቅ ያስፈልጋል።ለዚህም የአለቃ ኪዳነ ወልድ መዝገበ ቃላት ጥሩ ነው

መልመጃ

የሚከተሉትን ቁጥሮች የግእዙን ወደ አማርኛ(አረብኛ) የአማርኛውን ወደ ግእዝ ከነ ንባቡ ቀይር!

1). ፱፼፴፻፹፪

2). 623768

3). ስድሳ እልፍ ወስምንቱ ምእት የሚለውን በግእዝና በአማርኛ ቁጥሮች ፃፍ

4). 428 በግእዝ ጽፈህ በግእዝ አንብብ
5 )75623 በግእዝ ጽፈህ በግእዝ አንብብ

🙏ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን🙏

ሼር እያደረግን ለሁሉም እናዳርስ
መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
#50 (ሃምሳ) ላይክ ከደረሰ በኋላ ክፍል 3ን እንለቃለን!!!
👍👍👍👍👍👍👍👍👍👍
መሠረተ ግእዝ
የግስ ጥናት ክፍል ፱ የ - ነ -ግሶች ◦ሀይመነ ➺ አመነ ◦ሐዘነ ➺ አዘነ ◦ሐይደነ ➺ አበደ ◦መዝገነ ➺ አመሰገነ ◦ማሰነ ➺ ጠፋ ◦ወጠነ ➺ ጀመረ ◦ረበነ /ጠብቆ ይነበብ/ ➺ አስተማረ ◦የመነ ➺ ቀና ◦ጤገነ ➺ ጣደ ◦ድኅነ ➺ ዳነ ◦ተክህነ ➺ አገለገለ ◦ስእነ ➺ ደከመ ◦መነነ /ጠብቆ ይነበብ/ ➺ ናቀ ◦ለሰነ /ጠብቆ ይነበብ/ ➺ ተናገረ ◦ለጠነ ➺ አመሰገነ ◦ከፈነ ➺ ሸፈነ ◦ኮነ…
..
.
.
የቀጠለ...

የግስ ጥናት ክፍል ፲

የ - አ -ግሶች

◦ቦአ ➺ ገባ
◦ሞአ ➺ አሸነፈ ፤ ድል ነሳ
◦መጽአ ➺ መጣ
◦በልዐ ➺ በላ
◦መልአ ➺ መላ

◦ሰምዐ ➺ ሰማ
◦ተምዐ /ጠብቆ ይነበብ/ ➺ ተቆጣ
◦ቀጽአ ➺ ቀጣ
◦ቀብአ ➺ ቀባ
◦ተጋብአ ➺ ተሰበሰበ

◦ነቅዐ ➺ መነጨ
◦ነሥአ ➺ ያዘ
◦ወድአ /ጠብቆ ይነበብ/ ➺ ጨረሰ
◦ደርአ /ጠብቆ ይነበብ/ ➺ ታገሰ
◦ነድአ ➺ ነዳ

◦ዘንግዐ ➺ ዘነጋ
◦ጸልአ ➺ ጠላ
◦ጸምአ ➺ ተጠማ
◦ጸውአ /ጠብቆ ይነበብ/ ➺ ጠራ
◦ፈግአ /ጠብቆ ይነበብ/ ➺ ተደሰተ


🔷 የምታቁትን የ<አ> ግስ በአድራሻችን ላይ ከነትርጉሙ ጻፉ ፡፡

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግዕዝ ክፍል 3

✟ልሣነ ግእዝ፥ክፍል 3 ✟

መራሕያን

"መርሐ=መራ" ከሚል ግሥ የተገኘ ሁኖ መራሕያን ማለት መሪዎች ማለት ነው።በተለይ በግእዝ ቋንቋ ዋና ዋናዎቹ 10 ናቸው።

1). ውእቱ=እርሱ=he
2). ይእቲ=እርሷ=she
3). ውእቶሙ(እሙንቱ)=እነርሱ(ወንዶች)=they
4). ውእቶን(እማንቱ)=እነርሱ(ሴቶች)=they
5). አንተ=አንተ=you
6). አንቲ=አንቺ=you
7). አንትሙ=እናንተ(ወንዶች)=you
8 አንትን=እናንተ(ሴቶች)=you
9). አነ=እኔ=I
10). ንሕነ=እኛ=we
ይህ ከላይ ያለው ትርጉም መራሕያን የስም ምትክ ሁነው ሲያገለግሉ ያለው አተረጓጎም ነው።

ለምሳሌ ማርያም ተዐቢ እምኪሩቤል በሚለው ማርያም በሚለው ይእቲን ተክተን ይእቲ ተዐቢ እምኪሩቤል ቢል የስም ምትክ ይባላል ስለዚህ ሲተረጎም እርሷ ከኪሩቤል ትበልጣለች ይላል።

ብዙ ጊዜ የስም ምትክ ሁኖ ለመተርጎም ከግስ/verb በፊት መምጣት አለበት።ከዚህ ላይ ተዐቢ የሚለው ግስ ስለሆነ ነው እንዲህ ያለው።

ሌላኛው አተረጓጎም ነባር አንቀጽ (Auxiliary verb) ሁኖ ሲተረጎም
1). ውእቱ=ነው፥ነበር፥አለ=is,was
2). ይእቲ=ናት፥ነበረች፥አለች=is,was
3). ውእቶሙ=ናቸው፥ነበሩ፥አሉ=are,were
4). ውእቶን=-ናቸው፥ነበሩ፥አሉ=are,were
5). አንተ=ነህ፥ነበርክ፣አለህ=are,were(?)
6). አንቲ=ነሽ፥ነበርሽ፥አለሽ=are,were
7). አንትሙ=ናችሁ፥ነበራችሁ፥አላችሁ=are,were
8). አንትን=ናችሁ፥ነበራችሁ፥አላችሁ=-are,were
9). አነ=ነኝ፣ነበርኩ፥አለሁ= am,was
10). ንሕነ=ነን፥ነበርን፥አለን=are,were
ይላል።እንግዲህ መራሕያን ከዚህ በላይ ባለው ለመተርጎም ከ ዓረፍተ ነገር በኋላ ወይም ከስም በኋላ መምጣት አለባቸው።
ለምሳሌ:- ማርያም ይእቲ እመብርሃን ቢል።ማርያም የብርሃን እናት ናት ማለት ነው።አስተውል ይእቲ "እርሷ" ተብሎ ሳይሆን "ናት" ተብሎ የተተረጎመው ማርያም ከሚለው ስም በኋላ ስለመጣ ነው።

ሌላው መራሕያን አመልካች ቅጽል (Demonstrative pronoun??) ሁነው ያገለግላሉ።በዚህ ጊዜ የሚኖራቸው
1). ውእቱ=ያ
2). ይእቲ=ያች
3). ውእቶሙ=እነዚያ
4). ውእቶን=እነዚያ
5). አንተ=አንተ
6). አንቲ=አንቺ
7). አንትሙ=እናንተ
8). አንትን=እናንተ
9). አነ=እኔ
10). ንሕነ=እኛ ይላል
በዚህ ጊዜ አመልካች ቅጽል ሁነው ሲተረጎሙ ከስም(noun) በፊት ይመጣሉ።
ለምሳሌ:- ውእቱ ቃል ስጋ ኮነ ብል ያ ቃል ስጋ ሆነ ተብሎ ይተረጎማል።አስተውል ውእቱ "ያ" ተብሎ የተተረጎመ ቃል ከሚለው ስም በፊት ስለመጣ ነው።

ሌላው መራሕያን ተከታትለው ሲመጡ የመጀመሪያው የስም ምትክ ሁለተኛው ነባር አንቀጽ ሁነው ይተረጎማሉ።በነባር አንቀጽ ጊዜ ውእቱ ለ10ሩም መራሕያን ያስተረጉማል :: ይህም ማለት ለምሳሌ ጌታ አንትሙ ውእቱ ብርሃኑ ለዓለም ሲል።"አንትሙ እና ውእቱ" ተከታትለው ስለመጡ የመጀመሪያው እናንተ ተብሎ ይተረጎምና ሁለተኛው በነባር አንቀፅ "ናችሁ" ተብሎ ይተረጎማል።ውእቱ ናችሁ ተብሎ የተተረጎመበት ምክንያትም ለ10ሩም ይተረጎማል ስላልን ነው።ሌላው መራሕያን ሳይጠቀሱ በውስጠ አዋቂነት ይነገራሉ።ይህም በቅኔ ቤት ውእቱን ይመረምራሉ ይባላል።ምሳሌ መስቀል ኃይልነ ብለን መስቀል ኃይላችን ነው'' ብለን እንተረጉመዋለን "ነው" የሚለውን ትርጉም ያመጣው መራሕያን ሳይሆን ኃይልነ የሚለው ውእቱን መርምሮ ነው።


ጥያቄ:-
የሚከተሉትን መራሕያን አገልግሎታቸውን ለይ ተርጉም።
1). አነ ውእቱ ትንሳኤ ወሕይወት
2). ውእቱ ሚካኤል መና ዘአውረደ
3). አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም
4). መስቀል መድኃኒተ ነፍስነ
5). ገነት ይእቲ ምድረአክሱም

ወስብሃት ለእግዚአብሄር

ሼር እያደረግን ለሁሉም እናዳርስ
መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈

ከ 80 ላይክ👍👍👍👍👍 ክፍል 4 ይቀጥላል!!
መሠረተ ግእዝ
መዝገበ ቃላት እምነ ግእዝ ኃበ አማርኛ (፫) 🔹ቃና ➺ ዜማ ፤ ድምፅ 🔸ፀር ➺ ጠላት 🔹ጸዳል ➺ ብርሃን 🔸ፈርጽ ➺ ፈርጥ ፤ ዕንቁ 🔹ጽላል ➺ ጥላ ፤ ድባብ 🔸ቁር ➺ ብርድ 🔹ቀርን ➺ ቀንድ 🔸ጻማ ➺ ድካም 🔹ጸርቅ ➺ ጨርቅ 🔸ቀጸላ ➺ ጌጥ ፤ ሽልማት 🔹ቀስም ➺ ቅመም 🔸ቃሕዋ ➺ ቡና መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ መዝገበ ቃላት አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መሠረተ፡ግእዝ @learnGeez1 @learnGeez1…
የቀጠለ..
.
.
መዝገበ ቃላት እምነ ግእዝ ኃበ አማርኛ (፬)


🔹ረግን ➺ ታንኳ
🔸ምርጉዝ ➺ በትር
🔹መርሕብ ➺ ሜዳ
🔸መርዋሕት ➺ ቃጭል

🔹ርሙም ➺ ዝምተኛ
🔸ስንአሌ ➺ መሰናበት
🔹ስሙክ ➺ ጥገኛ
🔸ሰክም ➺ ሸክም

🔹ሳሕል ➺ ይቅርታ
🔸ሰዋስው ➺ መሰላል
🔹ሶከር ➺ ሸንኮራ
🔸ቀርን ➺ ቀንድ

መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ መዝገበ ቃላት አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግዕዝ ክፍል 4

👉ልሣነ ግእዝ፥ክፍል 4👈

.... ከመራሕያን የቀጠለ....
መራሕያን በተለያየ አከፋፈል ይከፈላሉ።

የመጀመሪያው
✟ሴት እና ወንድ✟
ውእቱ፥ውእቶሙ፥አንተ፥አንትሙ ለወንድ(masculine)
ይእቲ፥ውእቶን፥አንቲ፥አንትን ለሴት (feminine)
አነ፥ንሕነ ለሴትም ለወንድም ያገለግላ

አንድና ብዙ
ውእቱ፥ይእቲ፥አንቲ፥አነ፥አንተ ለአንድ ወይም ለነጠላ(singular)
ውእቶሙ፥ውእቶን፥አንትሙ፥ንሕነ፥አንትን ለብዙ (plural)

ቅርብና ሩቅ
አነ፥ንሕነ አንደኛ መደብ (1st person)
አንተ፥አንትሙ፥አንቲ፥አንትን ሁለተኛ መደብ (2nd person)
ውእቱ፥ውእቶሙ፥ይእቲ፥ውእቶን ሦስተኛ መደብ (3rd person) ይባላሉ።

አስተውል በግእዝ ቋንቋ ሴቶችን እናንተ እነርሱ ስንልና ወንዶችን እናንተ እነርሱ ስንል ይለያያል።ሴቶችን እናንተ እነርሱ ለማለት አንትን ውእቶን እማንቱ ስንል።ወንዶችን እናንተ እነርሱ ለማለት ግን አንትሙ ውእቶሙ እሙንቱ እንላለን።

ወንዶችና ሴቶች ተቀላቅለው እናንተ ወይም እነርሱ ለማለት ከፈለግን በወንዶች አንትሙ ውእቶሙ እንላለን ይህም ማለት ለምሳሌ ከ20 ሰዎች 2 ወንድ 18 ሴት ቢሆኑ ውእቶሙ እሙንቱ አንትሙ ይባላል እንጂ አንትን ውእቶን እማንቱ አይባልም።

ሌላው ከዚህ በታች ያሉትም ወደፊት ለምንማረው ግእዝ ወሳኝ ስለሆኑ እንከታተላቸው ተሳቢ መራሕያን ይባላሉ።
1). ኪያሁ=እርሱን=him
2). ኪያሆሙ=እነርሱን=them
3). ኪያሃ=እርሷን=her
4). ኪያሆን=እነርሱን(ለሴቶች)=them
5). ኪያከ=አንተን=you
6). ኪያክሙ=እናንተን=you
7). ኪያኪ=አንቺን=you
8). ኪያክን=እናንተን(ለሴቶች)=you
9). ኪያየ=እኔን=me
10). ኪያነ=እኛን=us
ይላል።ለምሳሌ ኪያከ እግዚኦ ንሴብሐከ ስንል በቅዳሴ አቤቱ አንተን እናመሰግንሃለን ማለት ነው።ሌላው ጌታ ሐዋርያትን ዘኪያክሙ ተወክፈ ኪያየ ተወክፈ ሲል እናንተን የተቀበለ እኔን ተቀበለ ማለቱ ነው።

ሌላው ድርብ መራሕያን የሚባሉት ደግሞ ከዚህ ቀጥለው ያሉት ናቸው።
1). ለልየ=እኔ ራሴ=I my self
2). ለሊሆሙ=ራሳቸው=themselves
3). ሊሊሃ=ራሷ=her self
4). ለሊሆን=ራሳቸው(ለሴቶች)=themselves
5). ለሊሁ=ራሱ=himself
6). ለሊከ=ራስህ=yourself
7). ለሊክሙ=ራሳችሁ=yourselves
8). ለሊኪ=ራስሽ=yourself
9). ለሊክን=ራሳችሁ(ለሴቶች)=yourselves

10). ለሊነ=ራሳችን=ourselves
ይላል።ለምሳሌ ለሊነ ነአምር ኩሎ ዘኮነ ቢል የሆነውን ሁሉ እኛ ራሳችን እናውቃለን ማለት ነው።



ጥያቄ ግእዙን ወደ አማርኛ አማርኛውን ወደ ግእዝ ተርጉም

1). ኪያየ ይሴብሑ(hint ይሴብሑ ያመሰግናሉ)
2). ለሊሁ መጽአ ውስተ ዓለም(hint፦መጽአ መጣ፥ውስተዓለም ወደ ዓለም)
3). ኪያክሙ ኢያርእየኒ-(hint፦ኢያርእየኒ አያሳየኝ)
4). እሷን እወዳታለሁ(hint፡-አፈቅራ እወዳታለሁ)
5). እኔ ራሴ እመጣለሁ(hint፦እመጣለሁ እመጽእ)

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
🙏የነገ ሰው ይበለን🙏

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግዕዝ ክፍል 5

👉ልሣነ ግእዝ፥ክፍል 5👈
አቀድም አእኩቶቶ ለእግዚአብሔር

✟ሥርዓተ ንባብ✟
የግእዝ ቋንቋ የራሱ የሆነ ሥርዓተ ንባብ(የአነባበብ ስልት አለው) ይህም ማንኛውም የግእዝ መጽሐፍ ከ4ቱ የንባብ ዓይነቶች አይወጣም።

አራቱ የንባብ ዓይነቶች የተባሉትም

1). ተነሽ፦የቃሉን ቅድመመድረሻ በማኅዘኒ ንባብ ጊዜ ይዞ የመጨረሻውን ቃል ረገጥ አድርጎ ይነበባል።ቆጣ ነዘር ተደርጎ ይነበባል
2). ሰያፍ፦እንደ ተነሽ ቆጣ ነዘር ተደርጎ ይነበባል በማህዘኒ ንባብ ጊዜ ቅድመ ቅድመ መድረሻውን ያዝ ተደርጎ የመድረሻውን ፊደል ሳይረግጥ ይነበባል።
3). ተጣይ፦በማህዘኒ ንባብ ጊዜ እንደ ተነሽ ቅድመ መድረሻውን ይይዛል የሚለየው መድረሻ ፊደሉን አይረግጥም።
4). ወዳቂ፦በማህዘኒ ንባብ ጊዜ መድረሻ ፊደሉን ረገጥ አድርጎ ይነበባል።

እኒህን አነባበባቸውን ለመለየት መምህራንን ብትጠይቁ ይሻላል።

ንባቡን በጽሑፍ ብቻ ለመግለፅ ግልፅ ላይሆን ስለሚችል ማለት ነው።

ንባቡን ከለመዳችሁት አንድን ቃል ከ4ቱ ንባባት በየትኛው ይነበባል የሚለውን ለመለየት ሁለት መሰረታዊ ነገሮች አሉ።
1ኛ መድረሻ ፊደሉ
2ኛ part of speech(የንግግር ክፍሉ፥ለጊዜው ከግስ ውጭ ያሉትን በአንድ ግስን በአንድ አድርገን እንየው) ይህም ማለት ተነሽ ቃላት በመድረሻ ፊደል በግእዝ በካዕብ በሳልስ በራብዕ በሳብዕ ይጨርሳል።

የቃል ክፍሉ ደግሞ ብዙ ጊዜ ግስ ነው።አንዳንድ ጊዜ ስሞችም ሲሳቡ(object) ሲሆኑ ተነስተው ይነበባሉ።ለምሳሌ ሕይወት ሲሳብ ሕይወተ ይላል ይህን ጊዜ ተነስቶ ይነበባል።ቀደሰ፣ቀደሱ፥ቀደስኪ፥ቀደሳ(ለሴቶች)፣ግበሮ(ስራው) ብሎ በ5ቱ ይጨርሳል

ወዳቂ ቃላት፦
የንግግር ክፍላቸው ከግስ ውጭ ያሉት ናቸው በብዛት ስሞች ቁጥሮች ናቸው።በግእዝ በካዕብ በሳልስ በራብእ በኃምስ በሳብዕ ይጨርሳሉ።አሐደ፥ክልኤቱ፥ሣሉሲ፥ሶስና፥ሙሴ፥መሰንቆ ይላል።በሳድስ "ዝ" የሚለው ፊደል ብቻ ነው ወዳቂ እንጂ በሳድስ የሚጨርስ ሌላ ወዳቂ የለም።

ሰያፍና ተጣይ መድረሻ ቀለማቸው ሁልጊዜም ሳድስ።ይህም ማለት መጨረሻው ሳድስ የሆነ ቃል ስታገኙ ሥርዓተ ንባቡ ሊሆን የሚችለው ተጣይ ወይም ሰያፍ ነው።ብዙ ጊዜ እኒህን የምንለያቸው በልምድ ነው።መምህራንን በመጠየቅ ማወቅ ይቻላል።
ለምሳሌ 2 ፊደል ሁኖ በሳድስ ከጨረሰ እና ሁሉም ሳድስ ከሆነ ተጣይ ነው።
ለምሳሌ ኖኅ፥ሴም፥ካም፣እስክንድር... የመሳሰለው።ብዙ ዓይነት ህጎች አሉት በጥልቀት "የግእዝ ቋንቋ መማሪያ" በሚለው መጽሐፌ ለማብራራት ሞክሬያለሁ ከዚያ ማየት ይቻላል።
ሌላው በግእዝ ቋንቋ ጠብቆ የሚነበብና ላልቶ የሚነበብ አለ።
ለምሳሌ ቀደሰ ስንል "ደ" ን አጥብቀን ነው።"መርሐ" ስንል ደግሞ አላልተን ነው።ይህንንም ቀስ በቀስ ማወቅ ቀላል ነው።

ስለዚህ በግእዝ ቋንቋ የሚጠብቀውን ካላላነው የሚላላውን ካጠበቅነው የትርጉም ለውጥ ስለሚያመጣ ማወቅ አለብን።ለምሳሌ "አፍቅራ የሚለውን ቃል "ራ"ን ካጠበቅነው ውደዳት ተብሎ ይተረጎማል።"ራ"ን ካላለው ደግሞ ውደዱ ተብሎ ይተረጎማል።

ከላይ ባሉት ሥርዓተ ንባቦችም የሚነሳውን ከጣልነው የሚጣለውን ካነሳነው የትርጉም ለውጥ ያመጣል።ለምሳሌ አእመራ የሚለውን ቃል አንስተን ስናነበው ብዙ ሴቶች አወቁ ተብሎ ይተረጎማል።በወዳቂ አነባበብ ዘዴ ስናነበው ግን አወቃት ተብሎ ይተረጎማል።አዳም አእመራ ለሔዋን ሲል።አዳም ሔዋንን አወቃት ተብሎ ይተረጎማል በወዳቂ ስናነበው።አንስተን ካነበብነው ግን meaningless ይሆናል አዳም ሄዋንን አወቁ ብትል ትርጉም አልባ ይሆናል።

ጥያቄ
የሚከተሉትን ቃላት ሥርዓተ ንባባቸውን ለይ
1 ዳንኤል
2 ተስዓቱ
3 ማርያም
4 ቅዳሴ
5 ወደሰ

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን አሜን

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግዕዝ ክፍል 6

⁺ልሣነ ግእዝ፥ክፍል 6⁺
አቀድም አእኩቶቶ ለእግዚአብሔር


ግስ(verb)

➤ግስ የአረፍተ ነገር መቋጫ የድርጊት መግለጫ ማሰሪያ አንቀጽ ነው።ይህም በግእዝ ቋንቋ የግስ ራሱን የቻለ መዝገበ ቃላት አለው።በራሱ በግሱ የምናገኘው የውእቱ(ወይም የእርሱ) ነው ይህም ማለት ቀደሰ ፣ ቀተለ ብህለ ስንል አመሰገነ ፣ገደለ አለ ማለት ነው።ትርጉሙ ስለዚህ ባለቤቱ እርሱ ወይም(ውእቱ) ነው ማለት ነው።ይህንን መነሻ አድርገን አሉ አመሰገኑ አመሰገነች አመሰገንሽ ወዘተ ለማለት የሚያገለግለን ዘዴ አለ።

እርሱም እንደሚከተለው ነው።

1ኛ). በውእቱ(እርሱ) ጊዜ እንዳለ ግሱ ነው።ይህም።ማለት ቀደሰ ቀተለ ብህለ አለ አመሰገነ ገደለ አለ ይላል።

2ኛ). በይእቲ(እርሷ) ጊዜ ከመጨረሻው ላይ "ት" ፊደልን መጨመር ነው።ይህም ቀደሰ ቀተለ ብህለ ይል የነበረው ቀተለት ብህለት ቀደሰት ይላል።ትርጉሙም አመሰገነች አለች ገደለች ማለት ነው።

3ኛ). በውእቶሙ(እነርሱ) ጊዜ የመጨረሻውን ፊደል ወደ ካዕብ መለወጥ ነው ይህም ማለት ቀተለ ይል የነበረው ገደሉ ለማለት ቀተሉ ይላል።ስለዚህ ቀተሉ ቀደሱ ብህሉ ይላል ትርጉሙም።አመሰገኑ አሉ ገደሉ ማለት ነው።

4ኛ). በውእቶን(እነርሱ ሴቶች) ጊዜ የመጨረሻውን ፊደል ወደ ራብዕ መቀየር ነው።ይህም።ማለት ቀተለ ቀደሰ ብህለ ይል የነበረው ቀተላ ቀደሳ ብህላ ይላል ትርጉሙም አሉ ገደሉ አመሰገኑ ማለት ነው።በግእዝ ሴቶች መጡ ስንልና ወንዶች መጡ ስንል ይለያያል።ለምሳሌ ማርያም ወማርታ ሮጻ ኀበ ክርስቶስ ሲል ማርያምና ማርታ ወደ ጌታ መቃብር ሮጡ ማለት ነው።ሮፃ አለ እንጂ ሮፁ አላለም ሴቶች ናቸውና።ከሁለት አንዱ ወንድ ቢሆን ግን የሚታሰረው በሮፁ ነው።

5ኛ). በአንተ ጊዜ የመጨረሻውን ፊደል ወደ ሳድስ ቀይረህ "ከ"ን መጨመር ነው ይህም ማለት ለምሳሌ ቀደሰ ከሚለው የመጨረሻው ፊደል "ሰ"ን ወደ "ስ" ቀይረህ "ከ"ን መጨመረ ነው ይህም ማለት ቀደስከ ይላል።ስለዚህ ቀተልከ ቀደስከ ብህልከ ይላል ትርጉሙ አመሰገንክ ገደልክ አልክ ማለት ነው።

6ኛ). በአንቲ(አንቺ) ጊዜ መጨረሻውን ወደ ሳድስ አድርገህ "ኪ"ን መጨመር ነው ስለዚህ ቀተለ ቀደሰ ብህለ ይል የነበረው ቀተልኪ ቀደስኪ ብህልኪ ይላል ትርጉሙ አልሽ አመሰገንሽ ገደልሽ ማለት ነው

7ኛ ). በአንትሙ(እናንተ) ጊዜ መጨረሽምውን።ወደ ሳድስ ቀይረህ "ክሙ"ን መጨመር ነው።ስለዚህ ቀተልክሙ ቀደስክሙ ብህልክሙ ይላል።ትርጉሙ ገደላችሁ አመሰገናችሁ አላችሁ ማለት ነው።

8ኛ ). በአንትን(እናንተ ሴቶች) ጊዜ መጨረሻውን።ሳድስ አድርገህ "ክን"ን መጨመር ነው ይህም ማለት ቀተልክን ቀደስክን ብህልክን ይላል ትርጉሙ ገደላችሁ አመሰገናችሁ አላችሁ ማለት ነው።በግእዝ እናንተ ሴቶች መጣችሁ ለማለትና ወንዶች መጣችሁ ለማለት እንደሚለያይ አስተውል

9ኛ). በአነ(እኔ) ጊዜ መጨረሻውን ወደ ሳድስ ቀይሮ "ኩ"ን።መጨመር ነው ስለዚህም ቀተልኩ ቀደስኩ ብህልኩ ይላል ትርጉሙ ገደልኩ አመሰገንኩ አልኩ ይላል

10ኛ). በንሕነ (በእኛ) ጊዜ መጨረሽምውን ወደ ሳድስ ቀይረህ "ነ"ን መጨመር ነው።ስለዚህ ቀተልነ ቀደስነ ብህልነ ይላል ትርጉሙ ገደልን አልን አመሰገንን ማለት ነው።

ማስታወሻ:- ሁለት ፊደል ያላቸው በ"አ" እና በ"ሀ" የሚጨርሱ ግሶችም አረባባቸው ከዚህ በላይ ባለው ዘዴ ነው።ይህም ማለት ቦአ ቦኡ ቦአት ቦኣ ቦእከ ቦእኪ ቦእክሙ ቦእክን ቦእኩ ቦእነ ይላል በ"ሀ" ሲሆን ሎሀ ሎሁ ሎሀት ሎሃ ሎህኩ ሎህነ ሎህክሙ ...... እያለ ይቀጥላል።ቦአ ገባ ማለት ነው።ሎሀ ጻፈ ማለት ነው።
ሦስትና ከዚያ በላይ ፊደል ያለው በ "አ" እና በ"ሀ" የሚጨርስ ግስ ግን የተለየ አረባብ አለው


ጥያቄ
"ኖኀ=ረዘመ" የሚለውን ከነትርጉሙ አርባ

🙏ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን አሜን🙏

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈

ለሁሉም ሼር አድርጉት!! ግእዝን እናስፋፋ!!!

ክፍል 7ን ይህ ክፍል 6 ከ500 ሰው ካጠናው በኋላ እንለቃለን!!
መሠረተ ግእዝ
የቀጠለ.... . ዕፅ - ተክል - Plant - ክፍል ፪ • ሮዛ ➜ ጽጌረዳ • ስጋድ ➜ ለውዝ • ሶጠስ ➜ ግራዋ • ቀቢላ ➜ ማሽላ • ቀይሕ ሥርው ➜ ቀይ ሥር • ሲሮብ ➜ እንቦጭ • ሰግላ ➜ ሾላ • ሶበርት ➜ ኮሶ • ስዝን ➜ ስንዴ • ሶመን ➜ ሳማ • ሴዋ ➜ ጌሾ • ሰገም ➜ ገብስ • ሰንጥ ➜ ሽምብራ • ሰንበልት ➜ ጦስኝ • ሰናፔ ➜ ሰናፍጭ ምንጭ ፦ ማዕደ ልሳናት መሠረተ፡ግእዝ…
.
.የቀጠለ...
.
.
ከዚህ የቀጠላ....


ዕፅ - ተክል - Plant

- ክፍል ፫

• በቀልት ➜ ዘንባባ
• በለን ➜ ዝግባ
• በድል ➜ ባቄላ
• ብርስን ➜ ምስር
• ብርዕ ➜ ሸንበቆ

• ተምር ➜ ሰሌን
• ተፋሕ ➜ ድንች
• ኆህ ➜ ኮክ
• አልቀር ➜ ቁልቋል
• አሜከላ ➜ እሾህ

• አርዘ ባሕር ➜ ባሕር ዛፍ
• አንሶት ➜ እንሰት
• አውልዕ ➜ ወይራ
• አዛብ ➜ እንዶድ
• አጽፋር ➜ አደይ አባ

ምንጭ ፦ ማዕደ ልሳናት
መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
መሠረተ ግእዝ
ግዕዝ ክፍል 6 ⁺ልሣነ ግእዝ፥ክፍል 6⁺ አቀድም አእኩቶቶ ለእግዚአብሔር ✟ግስ(verb)✟ ➤ግስ የአረፍተ ነገር መቋጫ የድርጊት መግለጫ ማሰሪያ አንቀጽ ነው።ይህም በግእዝ ቋንቋ የግስ ራሱን የቻለ መዝገበ ቃላት አለው።በራሱ በግሱ የምናገኘው የውእቱ(ወይም የእርሱ) ነው ይህም ማለት ቀደሰ ፣ ቀተለ ብህለ ስንል አመሰገነ ፣ገደለ አለ ማለት ነው።ትርጉሙ ስለዚህ ባለቤቱ እርሱ ወይም(ውእቱ) ነው…
ግዕዝ ክፍል 7

✟ልሣነ ግእዝ፥ክፍል 7✟

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።ቅድመ ዓለም የነበረ ዓለምን አሳልፎ የሚኖር የአባቶቻችን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን።

አቀድም አእኩቶቶ ለእግዚአብሔር።

"የግስ እርባታ የቀጠለ"
በክፍል ስድስት አንድን ግስ በ10ሩ መራሕያን እንዴት መዘርዘር እንደምንችል አይተናል።አሁን ደግሞ ከዚያ የተለየ አካሄድ ያላቸው(Exceptions) ስላሉ።
እነዚያን አንድ በአንድ እንመልከት።
✍️ ሦስትና ከዚያ በላይ ፊደል ያላቸው ቃላት ሁነው በ "ሀ እና አ" ከጨረሱ በአንደኛና በሁለተኛ መደብ ቅድመ መድረሻቸውን(ከመጨረሻው ፊደል በፊት ያለውን ወደ ራብእ ቀይረው ይዘረዘራሉ)
ምሳሌ:-
1 ውእቱ=በጽሐ=ደረሰ
2 ይእቲ=በጽሐት=ደረሰች
3 ውእቶሙ=በጽሑ=ደረሱ
4 ውእቶን=በጽሓ=ደረሱ
እኒህ ሦስተኛ መደብ ስለሆኑ በቀድሞው ህግ ይቀጥላሉ።ይህ ከዚህ የጠቀስነው አዋጅ የሚያገለግለው ለአንደኛና ለሁለተኛ መደብ ከዚህ ቀጥለው ላሉት ነው።
5 አንተ=በጻሕከ=ደረስክ(አስተውል ጽ ፊደል ወደ ራብዕ ጻ ተቀይሮ እንደረባ.... ከዚህ በታች ያሉትም እንዲሁ እያደረጉ ይዘረዘራሉ።
6 አንቲ=በጻሕኪ=ደረስሽ
7 አንትሙ=በጻሕክሙ=ደረሳችሁ
8 አንትን=በጻሕክን=ደረሳችሁ
9 አነ=በጻሕኩ=ደረስኩ
10 ንሕነ=በጻሕነ=ደረስን ይላል
።በ "አ" ፊደል የሚጨርሰው በዚሁ አካሄድ ይሄዳል።ገብአ ብሎ ገባእከ... እያለ ይሄዳል
✍️ሌላኛው አዋጅ በ"ነ" የሚጨርስ ግስ በንሕነ ጊዜ "ነ"ን አጥብቆ ይውጣታል።ይህም ማለት
1). ውእቱ=ወጠነ=ጀመረ
2). ይእቲ=ወጠነት=ጀመረች
3). ውእቶሙ=ወጠኑ=ጀመሩ
4). ውእቶን=ወጠና=ጀመሩ
5). አንተ=ወጠንከ=ጀመርክ
6). አንቲ=ወጠንኪ=ጀመርሽ
7). አንትሙ=ወጠንክሙ=ጀመራችሁ
8). አንትን=ወጠንክን=ጀመራችሁ
9). አነ=ወጠንኩ=ጀመርኩ
10). ንሕነ=ወጠንነ አይልም "ን"ን ይውጥና ወጠነ ይላል።ከ1ኛው ወጠነ የሚለየው በንባብ ይህኛው "ነ" ጠብቆ ይነበባል ትርጉሙም ጀመርን ማለት ነው።ያኛው ጀመረ ማለት ነው።በጠቅላላው ይህ ክፍል ስድስት ባለው አካሄድ ይሄድና በንሕነ ብቻ ይቀየራል።


ጥያቄ
1 ). መጽአ=መጣ የሚለውን በ10ሩ መራሕያን ከነትርጉሙ አርባው
2). ድኅነ=ዳነ የሚለውን በ10ሩ መራሕያን ከነትርጉሙ አርባው

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን አሜን

#ሼር አድርጉት

✍️መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
መሠረተ ግእዝ
.. . . የቀጠለ... የግስ ጥናት ክፍል ፲ የ - አ -ግሶች ◦ቦአ ➺ ገባ ◦ሞአ ➺ አሸነፈ ፤ ድል ነሳ ◦መጽአ ➺ መጣ ◦በልዐ ➺ በላ ◦መልአ ➺ መላ ◦ሰምዐ ➺ ሰማ ◦ተምዐ /ጠብቆ ይነበብ/ ➺ ተቆጣ ◦ቀጽአ ➺ ቀጣ ◦ቀብአ ➺ ቀባ ◦ተጋብአ ➺ ተሰበሰበ ◦ነቅዐ ➺ መነጨ ◦ነሥአ ➺ ያዘ ◦ወድአ /ጠብቆ ይነበብ/ ➺ ጨረሰ ◦ደርአ /ጠብቆ ይነበብ/ ➺ ታገሰ ◦ነድአ ➺ ነዳ ◦ዘንግዐ…
የቀጠለ...
.
.

የግስ ጥናት ክፍል ፲፩

የ - ከ -ግሶች

◦መለከ ➺ ገዛ
◦ሰበከ ➺ አስተማረ
◦ዘረከ ➺ ሰደበ
◦ማሕረከ ➺ ማረከ
◦ባረከ ➺ ባረከ

◦ደረከ ➺ ጸና
◦ሰበከ /ጠብቆ ይነበብ/ ➺ ጣዖት ሠራ
◦ሤረከ ➺ ብልኀተኛ ሆነ
◦ነሰከ➺ ነከሰ
◦ወሐከ ➺ አነሳሳ

◦ለአከ ➺ ላከ
◦ስሕከ ➺ ሻከረ
◦መሐከ ➺ ራራ
◦ለከከ ➺ ጻፈ
◦በተከ ➺ ቆረጠ

◦ሐከከ ➺ ተከራከረ
◦ሀወከ ➺ አወከ
◦አውከከ ➺ አጎደለ
◦አምለከ ➺ አመለከ
◦ወሰከ /ጠብቆ ይነበብ/ ➺ ጨመረ


ምልማድ ፩

ከለይ በተሰጠው ምሳሌ መሠረት ተጨማሪ የ<ከ> ቤት ግሶችን ዘርዝሩ ?

በመቀጠል በዘረዘራችሁት በአንዱ ግስ ዐረፍተ ነገር መሥርቱ ፡፡

መሠረተ፡ግእዝ

@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
መሠረተ ግእዝ
ግዕዝ ክፍል 7 ✟ልሣነ ግእዝ፥ክፍል 7✟ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።ቅድመ ዓለም የነበረ ዓለምን አሳልፎ የሚኖር የአባቶቻችን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን። አቀድም አእኩቶቶ ለእግዚአብሔር። "የግስ እርባታ የቀጠለ" በክፍል ስድስት አንድን ግስ በ10ሩ መራሕያን እንዴት መዘርዘር እንደምንችል አይተናል።አሁን ደግሞ ከዚያ የተለየ አካሄድ ያላቸው(Exceptions)…
ከክፍል7 የቀጠለ...
.
.
ግዕዝ ክፍል 8

✟ልሣነ ግእዝ፥ክፍል 8✟

አቀድም አእኩቶቶ ለእግዚአብሔር

✍️የግስ እርባታ የቀጠለ✍️
በክፍል 7 ላይ የተወሰኑትን የተለየ አካሄድ ወይም Exceptions ያላቸውን በጥቂቱ አይተናል።አሁን የቀሩትን እንመልከትና ወደ ክፍል 9 እንሄዳለን።
✍️ሌላው በግስ እርባታ ጊዜ በ "ቀ፣ከ፣ገ" የሚጨርሱ ግሶች "ከ"ን ውጠው ራሳቸው ጠብቀው ይነበባሉ።ይህም የሚሆነው በአንደኛ እና በሁለተኛ መደቦች ነው።
1). ውእቱ=ሰበከ=አስተማረ
2). ይእቲ=ሰበከት=አስተማረች
3). ውእቶሙ=ሰበኩ=አስተማሩ
4). ውእቶን=ሰበካ=አስተማሩ።

✍️አስተውሉ በግስ እርባታ ጊዜ ሦስተኛ መደቦች "ልሣነ ግእዝ ክፍል 6" ላይ ባየነው ህግ ነው የሚሄዱ Exception ለእነዚህ ሳይሆን ከዚህ ቀጥለው ላሉት ሁለተኛና አንደኛ መደቦች ነው።
5). አንተ=ሰበከ=አስተማርክ(አስተውል በድሮው ቢሆን ኑሮ ሰበክከ ይል ነበር ነገር ግን "ክ"ን ውጦ "ከ"ን አጥብቆ እንዲነበብ አድርጎታል። ቁጥር 1 ላይ ካለው ሰበከ የሚለየው የዚህ ከ ጠብቆ ይነበባል የዚያ ላልቶ ይነበባል)
6). አንቲ=ሰበኪ=አስተማርሽ (አስተውል ሰበክኪ አላለም ሰበኪ አለ እንጂ "ኪ" ጠብቆ ነው የሚነበብ)
7). አንትሙ=ሰበክሙ=አስተማራችሁ(ሰበክክሙ አላለም) ክ ጠብቆ ይነበባል
8). አንትን=ሰበክን=አስተማራችሁ(ክ ጠብቆ ይነበባል)
9). አነ=ሰበኩ=አስተማርኩ(ሰበክኩ አላለም ሰበኩ አለ እንጂ ቁጥር 3 ላይ ካለው ሰበኩ የሚለየው ይሄ ጠብቆ ነው የሚነበበው
10). ንሕነ=ሰበክነ=አስተማርን (ይህ ሕግ ንሕነ ላይ አይሰራም)


የ "ቀ፣ገ" እንዲሁ ነው።ሰጠቅከ ሰለማይል "ከ"ን ውጦ "ቅ"ን ወደ ቀ እየቀየረ ሰጠቀ ይላል።ሰጠቀ ሰጠቀት ሰጠቁ ሰጠቃ ሰጠቀ ሰጠቅሙ ሰጠቅን ሰጠቂ ሰጠቁ ሰጠቅነ ይላል።የኀደገም
ኀደገ ኀደጉ ኀደገት ኀደጋ ኀደግሙ ኀደግን ኀደጊ.... ብቻ ይህንኑ እየመሳሰለ በ "ከ" በሰራነው ላይ በ ከ ምትክ "ገ"ን "ቀ" እያስገባችሁ መስራት ነው።

ጥያቄ
የሚከተሉትን ግሦች በ10ሩ መራሕያን አርባ ከነትርጉማቸውም አስቀምጥ
1 አጥመቀ=አጠመቀ
2 ፈለከ=ፈጠረ
3 ሐገገ=ሕግ ሰራ

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን አሜን

መሠረተ፡ግእዝ

@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
መሠረተ ግእዝ
የቀጠለ.. . . መዝገበ ቃላት እምነ ግእዝ ኃበ አማርኛ (፬) 🔹ረግን ➺ ታንኳ 🔸ምርጉዝ ➺ በትር 🔹መርሕብ ➺ ሜዳ 🔸መርዋሕት ➺ ቃጭል 🔹ርሙም ➺ ዝምተኛ 🔸ስንአሌ ➺ መሰናበት 🔹ስሙክ ➺ ጥገኛ 🔸ሰክም ➺ ሸክም 🔹ሳሕል ➺ ይቅርታ 🔸ሰዋስው ➺ መሰላል 🔹ሶከር ➺ ሸንኮራ 🔸ቀርን ➺ ቀንድ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ መዝገበ ቃላት አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መሠረተ፡ግእዝ @learnGeez1 @learnGeez1…
የቀጠለ......
.
.

መዝገበ ቃላት እምነ ግእዝ ኃበ አማርኛ (፬)


🔹ሉዓሌ ➺ ከፍታ
🔸ኬደ ➺ ውል
🔹ኵለንታ ➺ ኹለመና
🔸ኵፌት ➺ ቆብ

🔹ክታብ ➺ ደብዳቤ
🔸ተንከተም ➺ መሸጋገሪያ ድልድይ
🔹ምዕራግ ➺ መሰላል
🔸ዕራይ ➺ እኩያ

🔹ዐርክ ➺ ጓደኛ ፣ ወዳጅ
🔸ዕቡይ ➺ ትዕቢተኛ ፣ ኩሩ
🔹ትዕግልት ➺ ግፍ ፣ በደል
🔸ፍግዕ ➺ ደስታ

መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ መዝገበ ቃላት አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ

መሠረተ፡ግእዝ

@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
መሠረተ ግእዝ
ከክፍል7 የቀጠለ... . . ግዕዝ ክፍል 8 ✟ልሣነ ግእዝ፥ክፍል 8✟ አቀድም አእኩቶቶ ለእግዚአብሔር ✍️የግስ እርባታ የቀጠለ✍️ በክፍል 7 ላይ የተወሰኑትን የተለየ አካሄድ ወይም Exceptions ያላቸውን በጥቂቱ አይተናል።አሁን የቀሩትን እንመልከትና ወደ ክፍል 9 እንሄዳለን። ✍️ሌላው በግስ እርባታ ጊዜ በ "ቀ፣ከ፣ገ" የሚጨርሱ ግሶች "ከ"ን ውጠው ራሳቸው ጠብቀው ይነበባሉ።ይህም የሚሆነው በአንደኛ…
የቀጠለ......
.
.

ግዕዝ ክፍል 9

✟ልሣነ ግእዝ፥ክፍል 9✟
ስብሐት ለእግዚአብሔር ዘፈጠረ ኪያነ ከመ ናምልኮ=እናመልከው ዘንድ እኛን ለፈጠረን እግዚአብሔር ምስጋና ይገባዋል።
........ የቀጠለ የግስ እርባታ.....
✍️ በገብረ ቤቶች ጊዜ በአንደኛና በሁለተኛ መደብ ቅድመ መድረሻቸውን ወደ ግእዝ ለውጠው ይዘረዘራሉ።እዚህ ላይ መጀመሪያ የግብረ ቤት ምንድን ነው የሚል ጥያቄ ሊፈጥርባችሁ ይችላል።(ገብረ ሲል መጀመሪያው "ገ" ግእዝ ቀጥሎ ያለው "ብ" ሳድስ ከዚያ የመጨረሻው "ረ" ግእዝ የሆነ) ይህን የመሰሉት የገብረ ቤት ይባላሉ።ምሣሌ ሰምረ የገብረ ቤት ይባላል የፊደል አቀማመጡ ልክ ገብረን ስለሚመስል የገብረ ቤት ይባላል።

ስለዚህ ሲዘረዘር:-
1 ውእቱ=ሠምረ=ወደደ
2 ይእቲ=ሠምረት=ወደደች
3 ውእቶሙ=ሠምሩ=ወደዱ
4 ውእቶን=ሠምራ=ወደዱ
Exception የሚሰራው ካሁን በኋላ ላሉት ነው።
5 አንተ=ሠመርከ=ወደድክ (አስተውል የግሱ ቅድመ መድረሻ "ም" ወደ "መ" ተቀይራ ነው የረባው።እስከ መጨረሻው አስተውላት)
6 አንቲ=ሠመርኪ=ወደድሽ
7 አንተ=ሠመርከ=ወደድክ
8 አንትሙ=ሠመርክሙ=ወደዳችሁ
9 አነ=ሠመርኩ=ወደድኩ
10 ንሕነ=ሠመርነ=ወደድን
ይላል ማለት ነው።
✍️ሌላው የመጨረሻው የብህለ ቤት ሁነው ግን በ "የ" ፊደል የሚጨርሱ ግሶች ሲዘረዘሩ በአንደኛና በሁለተኛ መደብ ቅድመ መድረሻቸውን ሣልስ አድርገው "የ"ን ጎርደው ይነበባሉ።መጀመሪያ የ ብህለ ቤት የሚባሉት በሳድስ ጀምረው መካከላቸውም ሳድስ ሁኖ መጨረሻቸው ግእዝ የሆኑ ናቸው።እነ ርእየ፥ጥዕየ ናቸው።
1 ውእቱ=ርእየ=አየ
2 ይእቲ=ርእየት=አየች
3 ውእቶሙ=ርእዩ=አዩ
4 ውእቶን=ርእያ=አዩ
5 አንተ=ርኢከ=አየህ(እየውልህ ተመልከተው ከዚህ "እ"ን ወደ ሣልስ "ኢ" ቀይሮ "የ"ን እንደጎረደ አስተውል ከዚህ በታች ያሉት እንዲሁ ይረባሉ)
6 አንቲ=ርኢኪ=አየሽ
7 አንትሙ=ርኢክሙ=አያችሁ
8 አንትን=ርኢክን=አያችሁ
9 አነ=ርኢኩ=አየሁ
10 ንሕነ=ርኢነ=አየን

ጥያቄ
የሚከተሉትን ግሦች በ10ሩ መራሕያን ከነትርጉማቸው አርባ
1 ገብረ=ሠራ
2 ጥዕየ=ዳነ

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን አሜን

መሠረተ፡ግእዝ

@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
#ግዕዝ ክፍል 10

✟ልሣነ ግእዝ፥ክፍል 10✟
ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ እስራኤል

፨፨የስም ዝርዝር በ10ሩ መራሕያን፨፨

እስካሁን ግስ ነው ያረባን ካሁን በኋላ ደግሞ ስሞችን እናረባለን ይህም ማለት ለምሳሌ ሀገር የሚል ስም አለ ይህን መነሻ አድርገን ሀገርህ ሀገርሽ ሀገራችሁ ሀገሬ.... እያልን እንዴት በግእዝ ማርባት እንደምንችል አሁን እንመለከታለን።ይህም ብዙ አዋጆች አሉት በዋናነት የመጀመሪያው አዋጅ
✍️ ስሞች ሁነው በሳድስ ከጨረሱ ማለትም ሀገር መንበር ሕይወት ወዘተ የሚሉት ለምሳሌ የመጨረሻ ፊደላቸው "ር፥ት" ሳድስ ናቸው ስለዚህ እኒህን የመሰሉት በ10ሩ መራሕያን ሲዘረዘሩ።
1ኛ). በውእቱ ጊዜ መድረሻቸውን ወደ ካእብ ይለውጣሉ።ለምሳሌ ሀገር ይል የነበረው "ር" ወደ "ሩ" ተቀይሮ ሀገሩ ይላል
2ኛ). በይእቲ ጊዜ መድረሻውን ወደ ራብእ ይቀይራል ይህም ሀገር ይል የነበረው ሀገራ ይላል።
3ኛ). በውእቶሙ ጊዜ የመጨረሻውን ፊደል ወደ ሳብዕ ቀይሮ "ሙ"ን ይጨምራል ሀገር ይል የነበረው ሀገሮሙ ይላል
4ኛ). በውእቶን ጊዜ የመጨረሻውን ፊደል ወደ ሳብዕ ቀይሮ "ን"ን ይጨምራል ስለዚህ ሀገሮን ይላል አስተውል "ር" ወደ ሳብእ "ሮ" ቀይሮ "ን"ን እንደጨመረ
5ኛ). በአንተ ጊዜ "ከ" ን መጨመር ነው ሀገር ይል የነበረው ሀገርከ ይላል።
6ኛ). በአንቲ ጊዜ "ኪ"ን መጨመር ነው ስለዚህ ሀገርኪ ይላል።
7ኛ). በአንትሙ ጊዜ "ክሙ"ን መጨመር ነው ሀገርክሙ ይላል ማለት ነው
8ኛ). በአንትን ጊዜ "ክን"ን መጨመር ሀገርክን ይላል
9ኛ). በአነ ጊዜ "የ"ን መጨመር ነው ሀገርየ ይላል
10ኛ). በንህነ ጊዜ "ነ"ን መጨመር ነው ሀገርነ ይላል።
ትዝ ይላችሁ ከሆነ በግስ እርባታ ጊዜ Exception ያላቸው ሁለተኛ እና አንደኛ መደቦች ነበሩ።ሦስተኛ መደብ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በመጀመሪያው ህግ ነው የሄደ የነበር።አሁን በስም ዝርዝር ደግሞ ወደ ፊት እንደምናገኘው ሦስተኛ መደቦች ናቸው Exception ያላቸው እንጂ ሁለተኛ እና አንደኛ መደቦች እስከ መጨረሻው በዚህኛው ህግ ይዘልቃሉ።ማለት ነው።
✍️እንግዲህ ከላይ ያየነው በሳድስ ለሚጨርሱ ስሞች አዋጅ ነበር አሁን ደግሞ ከሳድስ ውጭ ለሚጨርሱ ስሞች እንዴት በ10ሩ እንደሚዘረዘሩ እንመልከት።ከሳድስ ውጭ የሚጨርሱ እንደ መሰንቆ፦ሥጋ፥ቅዳሴ.... የመሳሰሉት ናቸው።እንደምታዩት የመጨረሻ ፊደላቸው ሳድስ አይደለም።ስለዚህ አረባባቸው እንደሚከተለው ነው።
1ኛ). በውእቱ ጊዜ "ሁ"ን መጨመር ነው ሥጋሁ ይላል ስጋው ለማለት
2ኛ). በይእቲ ጊዜ "ሃ"ን መጨመር ነው ሥጋሃ ይልላ ስጋዋ ለማለት
3ኛ). በውእቶሙ "ሆሙ"ን መጨመር ነው ሥጋቸው ለማለት ሥጋሆሙ መስንቆዋቸው ለማለት መሰንቆሆሙ ይላል
4ኛ). በውእቶን "ሆን" ን መጨመር ነው
።ከዚህ በኋላ ያሉት በመጀመሪያው አዋጅ የሚሄዱ ናቸው
5). አንተ=ሥጋከ
6). አንቲ=ሥጋኪ
7). አንትሙ=ሥጋክሙ
8). አንትን=ሥጋክን
9). አነ=ሥጋየ
10). ንሕነ=ሥጋነ
ይላል ማለት ነው።አንዳንድ ህግ የማይጠብቁ አሉ እነርሱን ክፍል 11 ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ እናያቸዋለን።

ጥያቄ
የሚከተሉትን ስሞች በ10ሩ መራሕያን ከነ ትርጉማቸው አርባ
1ኛ). መሰንቆ
2ኛ). ሕይወት

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን

መሠረተ፡ግእዝ

@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግዕዝ ክፍል 11

✟ልሣነ ግእዝ፥ክፍል 11✟

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

፨፨የስም ዝርዝር በ10ሩ መራሕያን፨፨።
እንግዲህ ሌላኛው አዋጅ ከዚህ የሚቀጥለው ነው።
✍️plural ስሞች ሲዘረዘሩ መድረሻ ፊደላቸውን ወደ ሣልስ ቀይረው ይዘረዘራሉ።ይህም ማለት ለምሳሌ መልአክ ነጠላ ነው መላእክት ሲል ግን plural ይሆናል ስለዚህ ይህ እና ይህን የመሰሉት ሲዘረዘሩ የመጨረሻ ፊደላቸውን ወደ ሳልስ ይቀይራሉ ለምሳሌ መላእክት ይል የነበረው "ት" ወደ "ቲ" ተቀይራ ይዘረዘራል
1 ውእቱ=መላእክቲሁ=መላእክቶቹ
2 ይእቲ=መላእክቲሃ=መላእክቶቿ
3 ውእቶሙ=መላእክቲሆሙ=መላእክቶቻቸው
4 ውእቶን=መላእክቲሆን=መላእክቶቻቸው
5 አንተ=መላእክቲከ=መላእክቶችህ
6 አንትሙ=መላእክቲክሙ=መላእክቶቻችሁ
7 አንትን=መላእክቲክን=መላእክቶቻችሁ
8 ንሕነ=መላእክቲነ=መላእክቶቻችን
9 አነ=መላእክትየ=መላእክቶቼ(በአነ ጊዜ ወደ ሣልስ አይቀይርም እንዳለ በሳድስ አድርጎ ይዘረዝራል)
10 አንቲ=መላእክትኪ=መላእክቶችሽ (ይህም እንደ አነ ወደ ሣልስ አይቀይርም።

ሌላው ግን በሳድስ ጨርሰውም በሳድስ የማይሄዱ አሉ እኒህ በልምድ ነው የሚታወቁት።ለምሳሌ አብ አባት አባቱ ለማለት አቡ አይልም አቡሃ ይላል እንደ ሁለተኛው አዋጅ ህጉን።አፍርሶ ነገር ግን አብዛኞች ስሞች ከላይ ባለው አዋጅ ስለሚሄድ ያንን ማስረጽ መልካም ይሆናል ብየ አስባለሁ።

ጥያቄ
የሚከተሉትን ስሞች በ10ሩ መራሕያን ዘርዝራቸው
1ኛ ሐዋርያት
2ኛ ጻድቃን
...
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን አሜን

መሠረተ፡ግእዝ

@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግዕዝ ክፍል 12

✟ልሣነ ግእዝ፥ክፍል 12✟
ስብሀት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር
✍️ንዑስ አገባብ(Adverb)✍️
እነዚህ ብዙ አንቀጽ አጎላማሽ ሁነው ያገለግላሉ።የሚያጎለምሱትም ግስን ነው ብዙ ጊዜ።የተወሰኑትን እንመልከታቸው
1ኛ ምንት=ምን=What
2ኛ መኑ=ማን=Who
3ኛ እፎ=እንዴት=How
4ኛ ማእዜ=ማቼ=When
5ኛ ለምንት=ለምን=Why
6ኛ አይቴ=የት=Where
7ኛ ናሁ፥ነዋ=እነሆ (በእንግሊዘኛ አላውቀውም)
8ኛ እስፍንቱ፥ስፍን=ስንት
እንግዲህ ስምህ ማን ነው ለማለት ብትፈልግ መኑ ስምከ ትላለህ።አገርህ የት ነው ለማለት አይቴ ውእቱ ሀገርከ ትላለህ።ለምን መጣህ ለማለት ለምንት መጻእከ ትላለህ...
እንዴት አደርክ ለማለት ስትፈልግ ደግሞ እፎ ኀደርከ ትላለህ...
...
በዚህ መልኩ ሰላምታ መለዋወጥ ይቻላል
✍️ሐዳስ፦እፎ ሀደርኪ እህትየ
✍️ሰሎሜ፦እግዚአብሔር ይሴባህ ወእፎ ሀደርከ እሁየ
✍️ሐዳስ፦መኑ ስምኪ
✍️ሰሎሜ፦ ስምየ ሰሎሜ ውእቱ
✍️ሐዳስ፦እስፍንቱ መዋእልኪ
✍️ሰሎሜ፦እስራ ወአሐዱ ውእቱ
✍️ሐዳስ፦ኀበ አይቴ ተሐውሪ
✍️ሰሎሜ፦ኀበ ቤተክርስትያን
...
እያልክ/ሽ መለማመድ ትችላለህ/ሽ

ጥያቄ
የሚከተሉትን ዓረፍተ ነገሮች ግእዙን ወደ አማርኛ አማርኛውን ወደ ግእዝ ለውጥ
1 እንዴት ቆየህ (hint:ጸንሐ=ቆየ)
2 አይቴ ቀበርክምዎ ለአልአዛር

ወስብሀት ለእግዚአብሔር አሜን

መሠረተ፡ግእዝ

@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
ግዕዝ ክፍል 13

✟ልሣነ ግእዝ፥ክፍል 13

አቀድም አእኩቶቶ ለእግዚአብሔር

፨፨ደቂቅ አገባብ(preposition)፨፨
1ኛ=በይነ፥በእንተ፥እንበይነ=ስለ
2ኛ=ኀበ፥መንገለ፥ውስተ=ውደ(to?)
3ኛ=ከመ=እንደ
4ኛ=እም፥እምነ=ከ(from)
5ኛ=እስከ፥እስከነ=እስከ(up to)
6ኛ=ዲበ፥ላእለ፥መልእልተ=በ....ላይ
7ኛ=ማዕከለ=መካከል
8ኛ=ውስተ=በ.....ውስጥ
9ኛ=ምስለ=ከ...ጋራ=with
ይላሉ እኒህም በአረፍተ ነገር ውስጥ እንደሚከተለው ቀርበዋል።
አምላክ ዲበ መስቀል ተሰቅለ==አምላክ በመስቀል ላይ ተሰቀለ
ማእከለባህር ቆመ=በባህር መካከል ቆሙ
ኀበ ሶርያ አሐውር=ወደሶርያ እሄዳለሁ
እምነ ረኃብ ይሄይስ ኲናት=ከረሀብ ጦር ይሻላል
በእንተማርያም መሐረነ ክርስቶስ=ስለማርያም ብለህ ማረን
...
ይህን ይህን በመሰለ መልኩ በዓረፍተ ነገር ይገባሉ ማለት ነው።

ጥያቄ
የሚከተሉትን ወደ ግእዝ ተርጉም ግእዙን ወደ አማርኛ ተርጉም።
1ኛ ወደ ዋሸራ ሄደ
2ኛ ከባሕረ ጊዮርጊስ መጣ
3ኛ ምስለ ጻድቅ ትጸድቅ

ወስብሀት ለእግዚአብሔር

መሠረተ፡ግእዝ

@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
#ግዕዝ_ክፍል_14

✟ልሣነ ግእዝ፥ክፍል 14✟
አቀድም አእኩቶቶ ለእግዚአብሄር
፨፨አርእስተ ግሥ፨፨
እኒህ ግሶች 8 ናቸው።ሌሎችን ግሶች በሙሉ ለማርባት እኒህን 8ቱን አርእስተ ግሥ ማወቅ አለብን።እነዚህም
1ኛ ቀተለ=ገደለ=ላልቶ ይነበባል
2ኛ ቀደሰ=አመሰገነ="ደ" ጠብቆ ይነበባል
3ኛ ተንበለ=ለመነ
4ኛ ዴገነ=ተከተለ
5ኛ ጦመረ=ጻፈ
6ኛ ክህለ=ቻለ
7ኛ ባረከ=አመሰገነ
8ኛ ማህረከ=ማረከ ናቸው።
የእነዚህ የራሳቸው አረባብ አላቸው።የእነዚህን አረባብ ከቻልን የሌላውን ግሥ አርእስቱን ካወቅነው እኒህን መሰረት አድርጎ ይረባሉ።
✍️ቀደሰ፦ይቄድስ=ያመሰግናል
ይቀድስ=ያመሰግን ዘንድ
ይቀድስ ያመስግን
ይላል ስለዚህ ለምሳሌ "ወደሰ" የቀደሰ ቤት ነው ስለዚህ አረባቡ ልክ ቀደሰን ይመስላል ወደሰ፦ይዌድስ ይወድስ ይወድስ ይላል ማለት ነው።ስለዚህ እኒህን መነሻ አድርገን ሌላውን ማርባት ስለምንችል ቀሪ 7ቶቹ ከዚህ በታች ባለው ይረባሉ።
ቀተለ=ገደለ
ይቀትል=ይገድላል
ይቅትል=ይገድል ዘንድ
ይቅትል=ይግደል
ክህለ=ቻለ
ይክህል=ይችላል
ይክሀል=ይቻል
ይክሀል=ይቻል
ባረከ=አመሰገነ
ይባርክ=ያመሰግናል
ይባርክ=ያመሰግን ዘንድ
ይባርክ=ያመስግን
ዴገነ=ተከተለ
ይዴግን=ይከተላል
ይዴግን=ይከተል ዘንድ
ይዴግን=ይከተል
ጦመረ=ጻፈ
ይጦምር=ይጽፋል
ይጦምር=ይጽፍ ዘንድ
ይጦምር=ይጻፍ
ተንበለ=ለመነ
ይተነብል=ይለምናል
ይተንብል=ይለምን ዘንድ
ይተንብል=ይለምን
...
አስተውል የባረከ የዴገነ የጦመረ ከካልዓይ እስከ ትእዛዝ ያለው በጽሑፍ ተመሳሳይ ነው።በንባብ ግን የመጀመሪያው ቅድመ መድረሻውን ያዝ እያደረገ ይነበባል።....
ከዚሁ ላይ
ቆመ=ቆመ
ይቀውም=ይቆማል
ይቁም=ይቆም ዘንድ
ይቁም=ይቁም
ሤመ=ሾመ
ይሠይም=ይሾማል
ይሢም=ይሾም ዘንድ
ይሢም=ይሹም
ገብረ=ሰራ
ይገብር=ይሰራል
ይግበር=ይሰራ ዘንድ
ይግበር=ይስራ
ይላል።የቆመ 2 ፊደል ሁኖ በሳብዕ ጀምሮ በግእዝ የሚጨርስ ነው።የሤመ ቤት በኃምስ ጀምሮ በግእዝ የሚጨርስ 2ፊደል ነው።የባረከ ቤት በራብእ የዴገነ ቤት በኃምስ የክህለ ቤት በሳድስ የጦመረ ቤት በሳብእ ስለሚጀምር ብዙም አይቸግርም።የቀተለ የቀደሰ የተንበለ ን ቤት ለመለየት ስመጥሩው ሊቅ ክቡር የኔታ ሊቀ ሊቃውንት ያሬድ ሽፈራው የጻፉት መጽሐፈ ግስ መልካም ነው።

ጥያቄ
የሚከተሉትን ቃላት በካልዓይ በዘንድ እና በትእዛዝ አንቀጽ ከነ ትርጉሙ ፃፍ
1ኛ፦ሖረ
2ኛ፦ሠምረ
..
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን

መሠረተ፡ግእዝ

@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
2024/10/02 06:21:23
Back to Top
HTML Embed Code: