Telegram Web Link
Channel created
መ ሠ ረ ተ ግ እ ዝ


🔸የግእዝ ቋንቋ ታሪክና አመጣጥ
ክፍል ፩(1)

ቋንቋ ማለት መግባቢያ ማለት ነው ፡፡ የግእዝ ቋንቋ አመጣጥ ከአንዳንድ ቀደምት የታሪክ ጸሓፊዎችና የግእዝ ቋንቋ መጻሕፍትን ጽፈው ካስረከቡን ቀደምት የቤተ ክርስቲያን አባቶችና የቋንቋው ባለቤቶች እንደምንረዳው፦ የግእዝ ቋንቋ አመጣጥ በኢትዮጵያ መነሻ ሊሆነን የሚችለው ክርስቶስ ከመወለዱ ከ800 ዓመት ጀምሮ ነገደ ሴም (የሴም ዘሮች/ወገኖች) ቋንቋቸውን ይዘው ወደ ኢትዮጵያ ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ ሴማዊ ቋንቋ በኢትዮጵያ ሀገራዊ ቋንቋ ሆነ፡፡ ነገደ ሴም ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣታቸው በፊት ቋንቋቸውን በመግባቢያነት አሳድገው፣ ሥነ ጽሑፋቸውን አስፋፍተው በባቢሎን ፣ በአካድና በአሶር ይኖሩ ነበር፡፡ በኋላ ግን ለሁት ተከፍለው ግማሾቹ ሴማውያን ሰሜንና ምስራቅ እስያን፣ ግማሾቹ ሴማውያን ደግሞ ደቡብ እስያን ይዘው ይኖሩ ነበር፡፡

የሰሜን እስያ ሴማውያን ቋንቋ (የአካድ ቋንቋ)፦ አማራይክ፣ ዕብራይስጥን እና ፊንቄን ሲያስገኝ የደቡብ እስያ ሴማውያን ቋንቋም (አካድ ቋንቋ)፦ ሳባን ግእዝንና የተለያዩ በኢትዮጵያ ውስጥ በመግባቢያነት የምንጠቀምባቸውን ሴማውያን ቋንቋዎች አስግኝቷል፡፡ በደቡብ እስያ ይኖሩ የነበሩ ነገደ ሴም በተለያየ ምክንያት እየፈለሱ ወደ ደቡብ ዐረብ ወደ የመንና ወደ አካባቢዋ መጥተዋል ከዝያም ፈልሰው ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በአክሱምና በአካባቢዋ ሰፍረው ይዘዋቸው ከመጡት ቋንቋዎቻቸው መካከል በታሪክ ጎልተው የሚታወቁና አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩትና በአሁኑ ሰዓትም በአገልግሎት ላይ የሚገኙት ቋንቋዎች የሳባ እና የግእዝ ቋንቋዎች ናቸው፡፡
@learnGeez1
@learnGeez1

ነገደ ሴም(ሴማውያን) ቋንቋዎቻቸውን /ሳባና ግእዝን/ ከነገደ ካም ቋንቋ ጋር አስማምተው በመያዝ ሁሉንም ቋንቋዎች ሲናገሩዋቸው ኖረው ነበር፡፡ በኋላ ግን ሳባና ግእዝ እየተለመዱና እየተስፋፉ እየዳበሩም ከመሄዳቸው የተነሣ የነገደ ካምን ቋንቋ እየዋጡት መጥተው ሁለቱ ሳባ እና ግእዝ ቋንቋዎች ብቻ ሀገራዊ ቋንቋዎች ይሆኑ ጀመር እየቆዩ ግን ሁለቱ (ሳባና ግእዝ) በጣም ተመሳሳይና ተቀራራቢ በመሆናቸው እንደ አንድ ቋንቋ ሆነው ይነገሩ ጀመር፡፡ ይኸም ጽሑፉ (ፊደሉ) በሳባ እንዲጻፍ እና መነጋገሪያ ቋንቋውን ደግሞ በግእዝ እንዲሆን በመደረጉ ነው፡፡ ነገደ ሴም በሳባ ቋንቋቸው ፥ሳባውያን፥ በግእዝ ቋንቋቸው ደግሞ ፥አግአዝያን፥ ተብለው የሚጠሩት ከዚህ መነሻነት ነበር፡፡

ለዚህም መረጃ የሚሆኑን ሳባና ግእዝ ቋንቋዎች ተጽፈውባቸው የሚገኙት ጥንታውያን የኢትዮጵያ ቅርሶች እንደ የአክሱምና የላሊበላ ሐውልቶች በየሐ እና በአዱልስ ወዘተ….. የተለያዩ በድንጋይ ላይ የተቀረጹ ጽሑፎችና ቅርጻ ቅርጾች እስከ አሁን ቆመው የሚገኙ የዚህ ቋሚና ግልጽ ማስረጃዎች ናቸው፡፡ የሳባና የግእዝ ቋንቋዎች በዚህ ሁኔታ እስከ 324 ዓ.ም. አካባቢ ድረስ አብረው ሲነገሩ ቆይተዋል በኋላ ግን የሳባ ቋንቋ እየተዳከመና በግእዝ ቋንቋ እየተዋጠ ይሄድ ጀመር እንደ ምንም እየተንገዳገደ እስከ 350 ዓ.ም. ቆይቶ ከዚህ በኋላ ከሥነ – ጽሑፍ ከመነጋገሪያነትም ፈጽሞ ቀረ የግእዝ ቋንቋ ግን ከ324 ዓ.ም ጀምሮ ብቸኛ ሀገራዊ ቋንቋ በመሆን እስከ 12ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ማለትም የአማርኛ ቋንቋ ብሔራዊ ቋንቋ ሆኖ ሲያገለግል እንደ ነበር የታሪክ ጸሐፊዎች በግልጽ አስቀምጠውታል፡፡


ዮም ፈጸምነ ዘይእዜ ትምህርት ሠናይ ሶቤ ይኲን ለኲልኲሙ ፡፡
🔸ይቀጥላል...

#መጀመሪያ #ግእዝ_ታሪክ
🔸▢▭🔅▭▢🔸
◊ መ ሠ ረ ተ ግ እ ዝ ◊
@learnGeez1
🔸የግእዝ ቋንቋ ታሪክና አመጣጥ
ክፍል ፪(2)


በዓለም ላይ ፊደልና ቁጥር ካላቸው ጥቂት ቋንቋዎች መካከል ጥንታዊውና ታሪካዊ የሆነ የራሱ ጽሕፈትና የንባብ ሥርዓት ያለው ቋንቋ ግእዝ ነው።

ግእዝ ማለት መጀመሪያ ማለት ነው። ግእዝ እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን የፈጠረበት አዳማዊ ቋንቋ ነው።
ኦሪት ዘፍጥረት ፲ ፩፥፩
"ወኮነ ኲሉ ምድር አሐተ ከንፈረ ወአሐደ ነገረ።" <ሰው ሁሉ በአንድ ቋንቋ ይናገር ነበር፡፡>


ይህም ከአዳም እስከ ባቢሎን ድረስ ይነገር የነበረው ቋንቋ ግእዝ እንደነበረ አብዛኛዎቹ የቤተክርስቲያናችን መምህራን ይስማማሉ፡፡በተቃራኒው ደግሞ ግእዝ አዳማዊ ቋንቋ አይደለም ብለው የሚከራከሩ መምህራን አሉ፡፡ ነገር ግን አዳማዊ ቃንቋ ነው ስንል ግእዝ እንደሌሎቹ ቋንቋዎች ሀገርን ወይም ነገድን የተከተለ አደለም፡፡
ለምሳሌ
- እብራይስጥ (ኤቦር ) እብራውያን ያስታውሰናል
- ሮማይስጥ (ሮም) ሮማውያንን መሰረት ያረገ ቋንቋ ነው ፡፡
- ዐረብኛ (ዐረብ)ን ወይም ዐረባውያንን የሚያስታውሰን ቋንቋ ነው ፡፡

ዓለም ላይ ያሉትን ሁሉንም ቋንቋዎች ብንመለከት ሀገርን ፣ ነገድን ፣ አካባቢን የሰዎችን ስም የያዘና በዛ ላይ የተመሰረተ ነው።
#ግእዝ ግን ከዚህ ሁሉ ነጻ ነው ፡፡
የቃሉን ትርጉም እንኳን ብንመለከት ግእዝ ማለት፦ ነፃነት ፤ ማንነት ማለት ነው ፡፡
ለምሳሌ ስሞችን ስንመለከት ፦
#አዳም፦ (አደመ) አማረ ፣ ተዋበ ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ ነው፡፡
#ሔዋን፦ (ሐይውዳነ) በሕይወት ኖረ ማለት ነው።
#ሴት፦ (እሴትየ) ዋጋዬ ምትኬ ማለት ነው ፡፡
ስለዚህ የመጀመሪያው ፍጡር አዳም የስሙ ስያሜ የመጣው ከግእዝ በመውጣቱ ግእዝ አዳማዊ ቋንቋ ተብሏል ፡፡

በተጨማሪ የግእዝ ንባብ ሲጀመር የሚጀመረው ከግእዝ ንባብ ነው በመቀጠል ፣ ውርድ ንባብ ፣ ቁም ንባብ እያለ የቀጥላል ፡፡

የቅዱስ ያሬድን ዜማ ስንመለከት፦ ግእዝ ፣ ዕዝል እና አራራይ ናቸው። የጀመሪያወን ዜማ ያረገው ግእዝን ነው።
የፊደላትን ስም ስንመለከት የመጀመሪያዎቹ ወደታች የተደረደሩት ቋላት ግእዝ ይባላሉ።
ለምሳሌ
- ሀ፣ለ፣ሐ፣... ፦ ግእዝ
- ሁ፣ሉ፣ሑ፣... ፦ ካዕብ
- ሂ፣ሊ፣ሒ፣... ፦ ሣልስ
- ሃ፣ላ፣ሓ፣... ፦ ራብዕ
- ሄ፣ሌ፣ሔ፣... ፦ ሐምስ
- ህ፣ል፣ሕ፣... ፦ ሳድስ
- ሆ፣ሎ፣ሖ፣... ፦ ሳብዕ ይባላሉ ፡፡

በአጠቃላይ የሀገራችን ቀደም ሲል የነበረው ስልጣኔ ሥነ ጽሑፍ ሊታወቅ የቻለው፦ በድንጋይ ሐውልቶች ፣ በየዋሻዉ ፣ በገዳማት የተገኙ ብራናዎች የሐውልት ላይ ጽሑፎች በግእዝ ነው ተጽፈው የተገኙት ከትውልድ ትውልድ በመተላለፋቸው ግእዝን ቀዳማዊ ቋንቋ እንለዋለን።


፨ ሠናይ ሶቤ ይኲን ለኲልክሙ ፨
🔸 ይቀጥላል...


#ግእዝ_ታሪክ
🔸 ▢▭🔅▭▢ 🔸
መ ሠ ረ ተ ግ እ ዝ
@learnGeez1
🔸የግእዝ ቋንቋ ታሪክና አመጣጥ
ክፍል ፫


የዓለም ቋንቋ ኹሉ በየነገዱ ሲጠራ ግእዝ ብቻ በማንም ነገድ ስም አልተጠራም ፤ በራሱ በገንዘቡ እንጂ ግእዝ ማለት ፩ኛ መጀመሪያ ማለት ነው። (አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ)

የብሉይ ኪዳን ሊቃውንትና ይልቁንም የጀርመኑ ሊቅ ሲዲ ጳውሎስ ግእዝ አዳማዊ ቋንቋ ነው በማለት ዘፍ. ፲፫ ፥ ፩ ላይ ያለውን ያነሳል፡፡

በተጨማሪ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በዕብራይስጥ ሲያስተምር ለሕዝቡ ግን መንፈስ ቅዱስ ለእያንዳዱ ሰው በእራሱ ቋንቋ ና ፊደል ያሰማቸው ነበር ፡፡

ከኢትዮጵያም ለፋሲካ በዓል ፈላሾችና አይሁዶች የጰራቅሊጦስ ዕለት የጴጥሮስን ስብከት በግእዝ ቋንቋ ሰምተው አምነው ተጠምቀዋል። ከ 3000 አርድእት ተቆጥረዋል።
ከባቢሎን ግንብ በኋላ አንድ የነበረው ፊደልና በቋንቋ ሲለያዩ ቋንቋቸውንም እንደሀገራቸው በየስማቸው ሰይመዋል ፡፡

ግእዝ ግን በ600 ዓመተ ዓለም ሳይፈጸም በያዕቆብ ዘመን ከእስያ ክፍል ከየመን ፈልሰው እንደአንበጣ ሳባንና አቢስን ለመውረስ ወደ ምድረ ካም የገቡ ሲሆን ግእዝ የነገደ ሴም ቋንቋ ነው።

ግእዝ የቋንቋና የፊደል ስም ሲሆን በአልፋው "አ" እንጂ በዓይኑ "ዐ" አይጻፍም ፡፡ በዓይኑ "ዐ" ሲጻፍ ትርጎሜው ሌላ ነው ፡፡ ግእዝን ና ግዕዘን ብንመለከት ከጌታችን ልደት በፊት በብሉይ ኋላም በሐዲስ እስከ አብርሐ ወአጽብሐ ዘመን ድረስ ካዕብ ፣ ሣልስ ፣ ራብዕ ፣ ኃምስ አልነበረም በግእዙ ብቻ ይጣፍ ስለነበር ግእዝ ተብላል ፡፡

በአፄ ቴዎድሮስ ጊዜ የተቃጠሉትና ተዘርፈው የሄዱት በግራኝ ጊዜም የጠፋት የግእዝ መጻሕፍት በኢንግሊዝ ብቻ በአይነቱ የተለያዩ ፫፻፸፭ (3075) የሚሆን መጽሐፍ ወስደዋል ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ ብዙ የግእዝ መጻሕፍቶች ወደ አውሮፓ ተሻግረዋል ፡፡
የግእዝ መጻሕፍት ያልሄዱበት ሀገር የለም ግእዙን ከእኛ ይልቅ የውጭ ሀገር ሰዎች ጠግበውታል ፡፡

የጀርመኑ ሊቅ ዲልማን እንኳ ፮፻(600) መጻሕፍትን በማንበብ የግስ መጽሐፍ ጽፏል፡፡ #እኛስ ? የግእዝ ቋንቋ የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቋንቋ ብቻ ሳይሆን የሀገራችን የኢትዮጲያ ታሪክ ፣ ቅርስ መሆኑን ተረድተን ልንጠቀምበት ያስፈልጋል ፡፡

( ምንጭ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ መዝገበ ቃላት አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ )

፨ ሠናይ ሶቤ ይኲን ለኲልክሙ ፨
🔸 ይቀጥላል
#ግእዝ_ታሪክ
🔸 ▢▭🔅▭▢ 🔸
መ ሠ ረ ተ ግ እ ዝ
@learnGeez1
መሠረተ ግእዝ


🔹ስለ ግእዝ ፊደላት
ክፍል ፩


ፊደል ማለት ፈደለ ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ፦ ጻፈ ፣ ጽሕፈት ፣ አጻጻፍ ማለት ነው፡፡

የግእዝ ቋንቋ ልዩ የሚያደርገው የራሱ የሆነ ፊደል ስላለው ነው።

የፊደል ቅርጽ የተጀመረው በሄኖስ ዘመን ነው። ሄኖስ የሴት ልጅ ሲሆን የአዳም የልጅ ልጅ ነው። ነቢዩ እግዚአብሔርን በማገልገሉና በመገዛቱ የሕግ ማሰሪያ የሆነው የፊደልን አጻጻፍ በጸፍጸፍ ሰማይ እግዚአብሔር ገልጦለታል።

ፊደላቱ ፳፮ (26) ሲሆኑ በእብራይስጥ ቋንቋ አሌፋት በመባል ይታወቁ ነበር። ከጊዜ ወደ ጊዜ ግን ቅርጻቸውና ድምፃቸውን በመለወጥ ወደ ኢትዮጵያ የሳባና የግእዝ ፈደላት በመባል ተሰይመዋል።
እነሱም ፦
አ የ ቀ
በ ከ ረ
ገ ለ ሰ
ደ መ ተ
ሀ ነ ጰ
ወ ሠ ፐ
ዘ ዐ
ሐ ፈ
ኀ ጸ
ጠ ፀ

ፊደላቱን ከ አ በ ገ ደ ... ወደ አሁኑ አቀማመጥ ያዘጋጁት የመጀመሪያው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን (324 ዓ.ም) ከአክሱም ሊቃውንተ ቤተክርስትያን ጋር በመሆን ነው፡፡

በድሮ ጊዜ ግእዝ ይጻፍ የነበረው ከቀኝ ወደ ግራ ነበር አሁን ግን ከግራ ወደ ቀኝ እንዲጻፍ አርገዋል።
በመቀጠል አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ግእዝ ቋንቋ ወደ አንድ ቤት ብቻ ነበር ወደታችም ወደ ጎንም የሚጻፈው። ወደ ጎን 6 ፊደል በመጨመር ባለ 7 ቤት እንዲሆን አድርገዋል፡፡
ምሳሌ፦ ከ'ሀ' 6ቱ 'ሁ፣ሂ፣ሃ፣ሄ፣ህ፣ሆ' ረብተዋል።
ይህን ሲያረጉ ግን በዛው ቅርጹን ሳይለቅ ቅጥያዎችን ብቻ በመጨመር ፊደላቱን ሰርተዋል።

ሀ ኀ ገ
ለ አ ጠ
ሐ ነ ጰ
መ ከ ጸ
ሠ ወ ፀ
ረ ዐ ፈ
ሰ ዘ ፐ
ቀ የ
በ ደ

የግእዝ ቃላት ከላይ የተዘረዘሩት ፳፮ (26)ቱ ብቻ ናቸው ፡፡
በግእዝ ፈደላት ውስጥ እነ
'ሸ ፣ ቸ ፣ ኘ ፣ ጨ ፣ ጀ ፣ ዠ ፣ ቨ ፣ ኸ'
አይካተቱም ከግእዙ ላይ ያሉ ቃላትን በማሻሻል ለአማርኛው ፊደል የተጨመሩ ናቸው ፡፡


🔹ሠናይ ሶቤ
ይቀጥላል...
#መጀመሪያ #ፊደላት
◈◌◊◊◍ 🔆 ◍◊◊◌◈
መሠረተ ግእዝ
@GeezEnemar
🔹ስለ ግእዝ ፊደላት
ክፍል ፪


የግእዝ ፊደላት ከሌሎች ቋንቋዎች ፊደል የሚለየው ፊደላቱ እያንዳንዳቸው የራሳቸው ትርጉም ስላላቸው ነው።
ለምሳሌ፦


- ማለት የአብ አኗኗሩ ከዓለም በፊት ነው፡፡
- ብሂል ሀልዎቱ ለአብ እም ቅድመ ዓለም።

- ማለት የእኛን ሥጋ ለበሰ።
- ብሂል ለብሰ ሥጋ ዚአነ።

- ማለት ስለእኛ ታሞ ሞተ።
- ብሂል ሐመ ወሞተ በእንቲአነ።

- ማለት የእግዚአብሔር ስራው ድንቅ ነው፡፡
- ብሂል መንክር ግብሩ ለእግዚአብሔር።

- ማለት ከድንግል በሥጋ ተወለደ(ተገለጠ)
- ብሂል ሠረቀ በሥጋ እምድንግል፡፡

- ማለት በጥበቡ ፤ ሰማይና ምድር ረጋ።
- ብሂል ረግዓ ሰማይ ወምድር፡፡

- ማለት እንደእኛ ሰው ሆነ።
- ብሂል ሰብአ ኮነ ከማነ።

- ማለት በመጀመሪያ ቃል ነበረ።
- ብሂል ቀዳሚሁ ቃል ውእቱ።

- ማለት ለዓለም ሁሉ ቤዛነት በትሕትናው ወረደ፡፡
- ብሂል በትሕትናሁ ወረደ ለቤዛ ኩሉ ዓለም።

- ማለት ፍፁም ሰው ሆነ።
- ብሂል ተሰብአ ወተሰገወ።

- ማለት ራሱን (ባህሪውን )ሰወረ (ሸሸገ)
- ብሂል ኀብአ ርእሶ።

- ማለት ደዌያችንን ያዘል ሕማማችንንም ተሸከመልን።
- ብሂል ነስአ ደዌነ ወፆረ ሕማመነ።

- ማለት እግዚአብሔርን ፈፅሞ አመሰግነዋለሁ።
- ብሂል አአኲቶ ወእሴብሖ ለእግዚአብሔር።

- ማለት እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ነው፡፡
- ብሂል ከሃሊ እግዚአብሔር።

- ማለት ከሰማያት ወረደ።
- ብሂል ወረደ እምሰማያት።

- ማለት እግዚአብሔር ታላቅ ነው።
- ብሂል ዐቢይ እግዚአብሔር።

- ማለት እግዚአብሔር ሁሉን የሚይዝ (የሚገዛ ነው)።
- ብሂል ዘኲሎ ይእኅዝ እግዚአብሔር።

- ማለት የእግዚአብሔር ቀኝ ኀይልን አደረገች።
- ብሂል የማነ እግዚአብሔር ገብረት ኀይለ።

- ማለት መለኮቱን ከሥጋችን ጋር አንድ አደረገ።
- ብሂል ደመረ መለኮቶ ምስለ ሥጋነ፡፡

- ማለት ምድርና ሰማያትን የፈጠረ ነው፡፡
- ብሂል ገባሬ ሰማያት ወምድር።

- ማለት እግዚአብሔር ጠቢብ ነው፡፡
- ብሂል ጠቢብ እግዚአብሔር።

- ማለት ጰራቅሊጦስ የእውነት መንፈስ ነው፡፡
- ብሂል ጰራቅሊጦስ መንፈሰ ጽድቅ ፡፡

- ማለት እግዚአብሔር ጸጋና እውነት ነው።
- ብሂል ጸጋ ወጽድቅ እግዚአብሔር፡፡

- ማለት እግዚአብሔር የእውነት ፀሐይ ነው።
- ብሂል ፀሐየ ጽድቅ እግዚአብሔር፡፡

- ማለት በጥበቡ ዓለምን ፈጠረ።
- ብሂል ፈጠረ ዓለመ በጥበቡ።

- ማለት የእግዚአብሔር ስሙ ፓፓኤል ነው፡፡
- ብሂል ፓፓኤል ስሙ ለእግዚአብሔር።


ይቀጥላል...
#ፊደላት
◈◌◊◊◍ 🔆 ◍◊◊◌◈
መሠረተ ግእዝ
@GeezEnemar
🔹ስለ ግእዝ ፊደላት
ክፍል ፫(3)


ሞክሼ ፊደላት

ሞክሼ ፊደላት የሚባሉት አንድ አይነት ድምጽ ያላቸው ነገር ግን በቅርጽ እና በስራቸው የተለያዩ ፊደላት የሆኑ ናቸው።

በድሮ ጊዜ ግን አባቶቻችን ን ከ ... ፊደሎችን በድምጽ አወጣጥ ይለዮአቸው ነበር።

እኝህ ፊደላት በቁጥር ፱(9) ሰሆኑ
ሀ ፣ ሐ ፣ ኀ ፣ ሠ ፣ ሰ ፣ አ ፣ ዐ ፣ ጸ ፣ ፀ ናቸው።

➺ ሃሌታው "ሀ" ይባላል።
◦ሃሌ ሉያ ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው ይህን ፊደል ስለሆነ ሃሌታው "ሀ" ተብሏል።

➺ ሐመሩ "ሐ" ይባላል።
◦ሐመር ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው በዚህ ፊደል ስለሆነ ነው።

➺ ብዙኀኑ "ኀ" ይባላል
◦ብዙህ ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው ይህን ስለሆነ ነው።

➺ አልፋው "አ" ይባላል።
◦አልፋ ኦሜጋ ብለን ስንጽፍ የምንጠቀምበት ስለሆነ ነው።

➺ ዓይኑ "ዐ" ይባላል።
◦ዓይኑ ብለን ስንጽፍ የምንጠቀምበት ስለሆነ ነው።

➺ ንጉሡ "ሠ" ይባላል።
◦ንጉሥ ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው ይሄን ፊደል ስለ ሆነ ነው።

➺ እሳቱ "ሰ" ይባላል።
◦እሳት ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው ይህን ስለሆነ ነው።

➺ ጸሎቱ "ጸ" ይባላል።
◦ጸሎት ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው ይሄን ፊደል ስለሆነ ነው።

➺ ፀሐዩ "ፀ" ይባላል።
◦ፀሐይ ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው ይህን ፊደል ነው።

እነዚህ ሞክሼ ፊደላት አንዱ በአንዱ ቦታ መግባት የለበትም ምክንያቱም የትርጉም ለውጥ ያመጣሉ።
ለምሳሌ
➺ ሠረቀ = ወጣ
ሰረቀ = ሰረቀ
➺ አመት = አገልጋይ
ዓመት = ዘመን
➺ ሰዐለ = ስዕል ሳለ
ሰአለ = ለመነ
➺ መሀረ = አስተማረ
መሐረ = ይቅር አለ
➺ ኀለየ = አመሰገነ
ሐለየ = አሰበ
➺ ፈጸመ = ጨረሰ
ፈፀመ = ነጨ
➺ ማኅሌት = ማመስገን
ማሕሌት = ማሰብ

◈ይቀጥላል...
#ፊደላት
◈◌◊◊◍ 🔆 ◍◊◊◌◈
መሠረተ ግእዝ
@learnGeez1
⚪️ ስለ ግእዝ አኃዝ ( ቁጥሮች )
ክፍል ፩


አኀዝ ማለት አኀዘ ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ ሲሆን ያዘ ፣ ቆጠረ ፣ ጀመረ ማለት ነው ትርጉሙም ቁጥር ማለት ነው፡፡

አኀዝ ብለን ስንጽፍ ነጠላ ቁጥር ሲሆን አኃዝ ብለን በራብዕ ስንጽፍ ደግሞ ቁጥሮች ይሆናል።

በሥነ ጽሑፍ ግእዝን ምሉዕ ካደረጉት አንዱ ግእዝ የራሱ ቁጥር ስላለው ነው።
በአንድ ቋንቋ ውስጥ ቁጥር ትልቅ ድርሻ አለው። የግእዝ ቋንቋም የራሱ የሆነ አኃዝ (ቁጥሮች) አሉት።

የግእዝ ቁጥሮች በኢትዮጵያውያን ዘንድ ሰፊ ሥፍራ አላቸው፡፡ የግእዝ ቋንቋ እንደ ማንኛውም ቋንቋ እራሱን የቻለ የቁጥር አጻጻፍ ስልቶች አሉት።
ለምሳሌ

1 ➺ ፩ 10 ➺ ፲
2 ➺ ፪ 20 ➺ ፳
3 ➺ ፫ 30 ➺ ፴
4 ➺ ፬ 40 ➺ ፵
5 ➺ ፭ 50 ➺ ፶
6 ➺ ፮ 60 ➺ ፷
7 ➺ ፯ 70 ➺ ፸
8 ➺ ፰ 80 ➺ ፹
9 ➺ ፱ 90 ➺ ፺
100 ➺ ፻
10000 ➺ ፼

የግእዝ ቁጥሮች ከላይ የተመለከትናቸው ሃያው መደበኛ ቁጥሮች ሲሆን ከነዚህ ቁጥሮች ተነስተን እስከፈለግነው ድረስ መጻፍ እንችላለን።

በግእዝ ዜሮ የለም ፤ 'አልቦ' ይባላል እንጂ ይህም የሆነው በግእዝ አሥር እራሱ የቻለ አሥር ቁጥር ስላለ ነው ፡፡

የግእዙም ሆነ አሁን እኛ የምንጠቀምበት ቁጥር ማለትም ከዐ/ዜሮ/ ጀምረን የምንጽፈው የአማርኛ ቁጥር ሳይሆን ስያሜው ከየት እንደመጣ ትክክለኛ መረጃዎች ባይኖሩም 0፣ 1፣ 2፣ 3….. እየተባሉ የሚዘረዘሩት ቁጥሮች የዐረብኛ ቁጥሮች ተብለው እንደሚጠሩ በተለያዩ መጻሕፍት ተጽፈው እናገኛለን፡፡

በኢትዮጵያ የቀን አቆጣጠር /የቀን መቁጠሪያ/ ላይ የምናገኛቸውን በየወቅቱ የሚከበሩትን ሃይማኖታዊ በዓላትንና ብሔራዊ በዓላትን ለማክበር የምጠቀመው የቀን አቆጣጠር የግእዝ ቁጥር /ኢትዮጵያዊ/ ቁጥር እንደሆኑ በግልጹ ልንረዳውና ተገቢውን ስያሜ አውቀን በስሙ ልንጠራው ይገባናል፡፡

የግእዝ ቁጥሮችን ከነስያሜያቸው በዝርዝር ጽፈን መጨረስ ባንችልም ከብዙ በጥቂት በ ክፍል ፪ እንመለከታለን


ሠናይ ሶቤ
#አኃዛተ_ግእዝ
፻፻፻፻፻ ፬፬ ፻፻፻፻፻፪
^ ~ መሠረተ ግእዝ ~ ^
▢□ @learnGeez1□▢
⚪️ ስለ ግእዝ አኃዝ ( ቁጥሮች )

ክፍል ፪

የግእዝ ቁጥሮችን በዝርዝር ጽፈን መጨረስ ባንችልም ከብዙ በጥቂት እንመልከት


አኀዝ በፊደል - በዓረብኛ - በአማርኛ

(አልቦ) 0 (ዜሮ)

፩ (አሐዱ) 1 (አንድ)

፪ (ክልኤቱ) 2 (ሁለት)

፫ (ሠለስቱ) 3 (ሶስት)

፬ (አርባዕት) 4 (አራት)

፭ (ኃምስቱ) 5 (አምስት)

፮ (ስድስቱ) 6 (ስድስት)

፯ (ሰብዓቱ) 7 (ሰባት)

፰ (ሰመንቱ) 8 (ስምንት)

፱ (ተስዐቱ) 9 (ዘጠኝ)

፲ (ዐሠርቱ) 10 (አስር)

፳ (እስራ) 20 (ሃያ)

፴ (ሠላሳ) 30 (ሠላሳ)

፵ (አርባ) 40 (አርባ)

፶ (ሃምሳ) 50 (ሃምሳ)

፷ (ስሳ) 60 (ስድሳ)

፸ (ሰብዓ) 70 (ሰብዓ)

፹ (ሰማንያ) 80 (ሰማንያ)

፺ (ተስዓ) 90 (ዘጠና)

፻ (ምእት) 100 (መቶ)

፲፻ (ዐሠርቱ ምእት) 1000 (አንድ ሺህ)

፼ (እልፍ) 10,000 (አስር ሺህ)

፲፼ (ዐሠርቱ እልፍ) 100,000 (መቶ ሺህ)

፼፻ (አእላፋት) 1000,000 (አንድ ሚሊየን)

፲፼፻ (ትእልፊት) 10,000,000 (አስር ሚሊየን)

፻፼፻ (ትልፊታት) 100,000,000 (መቶ ሚሊየን)

፲፻፼፻ (ምእልፊት) 1,000,000,000 (አንድ ቢልየን)


#አኃዛተ_ግእዝ
፩፪፫፬፭፮፯፰፱፲
^ ~ መሠረተ ግእዝ ~ ^
▢□@learnGeez1 □▢
2024/10/03 19:32:37
Back to Top
HTML Embed Code: