Telegram Web Link
መሠረተ ግእዝ
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 16🌹 የስም ዝር ዝር በመራሕያን ክፍል 2 ግእዝ አማርኛ ውእቱ መሰንቆሁ መሰንቆው ውእቶሙ መሰንቆሆሙ መሰንቋቸው ይእቲ መሰንቆሃ መሰንቆዋ ውእቶን መሰንቆሆን መሰንቋቸው አንተ መሰንቆከ መሰንቆህ አንትሙ መሰንቆክሙ መሰንቋችሁ አንቲ መሰንቆኪ መሰንቆሽ…
የግእዝ ክፍል 16 ጥያቄዎች መልስ

ውእቱ፥እንዚራሁ
ውእቶሙ፥እንዚራሆሙ
ይእቲ፥እንዚራሃ
ውእቶን፥እንዚራሆን
አንተ፥እንዚራከ
አንትሙ፥እንዚራክሙ
አንቲ፥እንዚራኪ
አንትን፥እንዚራክን
አነ፥እንዚራየ
ንሕነ፥እንዚራነ

ውእቱ፣ቅዳሴሁ
ውእቶሙ፣ቅዳሴሆሙ
ይእቲ፣ቅዳሴሃ
ውእቶን፣ቅዳሴሆን
አንተ፣ቅዳሴከ
አንትሙ፣ቅዳሴክሙ
አንቲ፣ቅዳሴኪ
አንትን፣ቅዳሴክን
አነ፣ቅዳሴየ
ንሕነ፣ቅዳሴነ

ውእቱ፥ፈጣሪሁ
ውእቶሙ፥ፈጣሪሆሙ
ይእቲ፥ፈጣሪሃ
ውእቶን፥ፈጣሪሆን
አንተ፥ፈጣሪከ
አንትሙ፥ፈጣሪክሙ
አንቲ፥ፈጣሪኪ
አንትን፥ፈጣሪክም
አነ፥ፈጣሪየ
ንሕነ፥ፈጣሪነ

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 17🌹
የስም ዝርዝር በመራሕያን ክፍል 3
ግእዝ አማርኛ
ውእቱ ሐዋርያቲሁ ሐዋርያቱ
ውእቶሙ ሐዋርያቲሆሙ ሐዋርያቶቻቸው
ይእቲ ሐዋርያቲሃ ሐዋርያቶቿ
ውእቶን ሐዋርያቲሆን ሐዋርያቶቻቸው
አንተ ሐዋርያቲከ ሐዋርያቶችህ
አንትሙ ሐዋርያቲክሙ ሐዋርያቶቻችሁ
አንቲ ሐዋርያትኪ ሐዋርያቶችሽ
አንትን ሐዋርያቲክን ሐዋርያቶቻችሁ
አነ ሐዋርያትየ ሐዋርያቶቼ
ንሕነ ሐዋርያቲነ ሐዋርያቶቻችን
ይላል።ይህኛው ደግሞ ብዙ ስሞች (plurals) ሲዘረዘሩ በአነ እና በአንቲ ጊዜ በአነ "የ" ፊደልን ብቻ መጨመር ነው። በአንቲ ደግሞ "ኪ" ፊደልን ብቻ መጨመር ነው። ሐዋርያት በሚለው ሐዋርያትየ እና ሐዋርያትኪ እንዳለው ማለት ነው። በቀሪዎቹ ስምንቱ መራሕያን ጊዜ ግን የመጨረሻውን ፊደል ወደ ሣልስ ቀይሮ እንደሚዘረዘር አስተውል። ይኽውም ሐዋርያት ከሚለው ቃል ውስጥ የመጨረሻው ፊደል "ት" ወደ ሣልስ "ቲ" ተቀይሮ እንደተዘረዘረ አስተውል።አስተውል ዘመድ ቢል በውእቱ ጊዜ ዘመዱ ይላል። ብዙ ወይም plural ሲሆን አዝማድ ሲል ግን አ ዝማዲሁ ይላል። ከላይ ያለውን መስሎ ይረባል ማለት ነው።

ሌላው አንዳንድ ሕገ ወጥ ስሞች አሉ። ለምሳሌ "አብ" የሚለው ስም የመጨረሻ ፊደሉ "ብ" ሳድስ ነው። ነገር ግን ክፍል 15 ላይ እንዳየነው ዓይነት አይረባም።"ብ"ን ወደ ካእብ ቀይሮ ይዘረዘራል።ይኽውም አቡሁ፣ አቡሆሙ፣ አቡሃ፣ አቡሆን፣ አቡከ፣ አቡክሙ፣ አቡኪ፣ አቡክን፣ አቡየ፣ አቡነ ይላል ማለት ነው።

የእለቱ ጥያቄዎች
የማከተሉትን ቃላት በአሥሩ መራሕያን ዘርዝር
1) ሕገጋት
2) አድባራት
3) መላእክት

#ሼር


መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
ክፍል- ፲፯

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 18🌹
በጣም አስፈላጊ የሆኑ የግእዝ ቃላት

ግእዝ አማርኛ English
ወ እና And
አው ወይም Or
ምንት ምን What
መኑ ማን Who
እፎ እንዴት How
አይቴ የት Where
ማእዜ መቼ When
እስፍንቱ ስንት How many
ለምንት ለምን Why
ለ ለ For
በ በ By
አመ/ሶበ/ጊዜ በ...ጊዜ When
እንዘ ሲ፣ሳ፣እየ While
እመ በ፣ቢ፣ባ፣ብ If
እስመ/አምጣነ/አኮኑ ና
ተብለው ይተረጎማሉ።በምሳሌ እንደሚከተለው አቀርባቸዋለሁ። በመካከል ነጠብጣብ ያስገባሁባቸው ቃል ስለሚገባባቸው ነው ምሳሌ አመ ብየ በ....ጊዜ ያልኩት።አመ ተሰቅለ ቢል በተሰቀለ ጊዜ ስለሚል በበ እና በጊዜ መካከል ተሰቀለ የሚል ቃል ገብቷል።እና በዚህ እይታ መሆኑን ተረዱልኝ።

#ወ (እና)፦ ሚካኤል ወገብርኤል ሰአሉ በእንቲኣነ።ሚካኤል እና ገብርኤል ሆይ ስለእኛ ለምኑልን።

#አው (ወይም)፦ ግእዛን አው ሞት። ነጻነት ወይም ሞት።

#ምንት (ምን)።ምንት ውእቱ ሃይማኖትከ።ሃይማኖትህ ምንድን ነው?

#እፎ (እንዴት)።እፎ ኀደርከ።እንዴት አደርክ።

#ለምንት (ለምን)። ለምንት ትሰድደኒ።ለምን ታሳድደኛለህ?

#አይቴ (የት)።አይቴ አሐውር። የት ወይም ወዴት እሄዳለሁ?

#ማእዜ (መች)።ማእዜ ትመጽእ ኀቤየ።ወደ እኔ መቼ ትመጣለህ።

#ስፍን (ስንት)። ስፍን መዋእሊከ። እድሜህ ስንት ነው?

#መኑ (ማን)።መኑ ስምከ።ስምህ ማን ነው?

#ለ (ለ)። ለእግዚአብሔር ንሰግድ። ለእግዚአብሔር እንሰግዳለን።

#በ (በ)። በክርስቶስ ነአምን። በክርስቶስ እናምናለን።

#አመ/ሶበ/ጊዜ (በ...ጊዜ)። አመ ተሰቅለ ክርስቶስ ፀሐይ ጸልመ። ክርስቶስ በተሰቀለ ጊዜ ፀሐይ ጨለመ።

#እንዘ (ሲ፣ሳ፣እየ)።ሳ ሲሆን ንግበር ሰናየ እንዘ ኢይመጽእ ክርስቶስ ዳግመ። ክርስቶስ ዳግመኛ ሳይመጣ መልካም ሥራን እንስራ።ሲ ሲሆን ይትፌሥሑ ጻድቃን እንዘ ይመጽእ ክርስቶስ።ክርስቶስ ሲመጣ ጻድቃን ይደሰታሉ። እየ ሲሆን እንዘ ይበልዕ ሞተ። እየበላ ሞተ።

#እመ/እም (በ፣ቢ፣ባ፣ብ)። ብ ሲሆን እመ ተናገርኩ ጽድቀ ሰብአ ዛቲ ዓለም ይጸልኡኒ። እውነትን ብናገር የዚች ዓለም ይጠሉኛል። ቢ ሲሆን እመ ይመጽእ ይምጻእ።ቢመጣ ይምጣ። ባ ሲሆን ምስለ ሰብአ ሮሜ ወግብጽ ለእመ ነበርከ።እም አምለኩ በኮከብ ዓይንከ።ከሮም እና ከግብጽ ሰዎች ጋር ብትኖር ኖሮ።በኮከብ ዓይንህ ባመለኩ ነበር ማለት ነው።

#እስመ/አምጣነ/አኮኑ (ና)። ናፈቅሮ ለክርስቶስ እስመ/አምጣነ/አኮኑ አድኃነነ እሞት። ከሞት አድኖናልና ክርስቶስን እንወደዋለን።

የእለቱ ጥያቄዎች
የሚከተሉትን ዓረፍተ ነገሮች ግእዙን ወደ አማርኛ አማርኛውን ወደ ግእዝ ተርጉሙ።

1) ጊዮርጊስና ፊቅጦር ሰማእት ናቸው።
2) እንዘ አሐዱ ሠለስቱ
3) ምንት ውእቱ ሃይማኖት
4) እንዴት ዋልክ (ወዐለ፦ዋለ)
5) ኢትፍራህ እስመ ትድኅን።


መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 19🌹
ግእዝ አማርኛ English
ምስለ ከ.....ጋር With
እንበለ ያለ፣በቀር፣ሳ
ዘ/እንተ/እለ የ
ውስተ በ....ውስጥ In
ታሕተ በ....ታች Under
ማእከለ በ...መካከል betwen
ዲበ/ላእለ/መልእልተ በ...ላይ On
እም/እምነ ከ From
እስከ/እስከነ እስከ Upto
ከመ እንደ as
ኀበ/መንገለ ወደ To
በይነ/በእንተ/እንበይነ ስለ because of
ተብለው ይተረጎማሉ።እኒህም በዓረፍተ ነገር ምን እንደሚመስሉ ከዚህ ቀጥለን እንመለከታለን።

#ምስለ (ከ...ጋር) ፦ንዒ ማርያም ምስለ ሚካኤል።ማርያም ሆይ ከሚካኤል ጋር ነይ።

#እንበለ (በቀር፣ያለ፣ሳ)። በቀር ሲሆን ከእናታችን ማርያም በቀር ሁሉም በድሏል።ኩሉ ጌገየ እንበለ ማርያም እምነ ይላል። ያለ ሲሆን ኢትመውዕ ዘእንበለ ረድኤተ እግዚአብሔር።ያለ እግዚአብሔር ረድኤት አታሸንፍም። ሳ ሲሆን ኢትብልዑ ሥጋ ዘእንበለ ዓሣ።ዓሣ ሳይቀር ሥጋ አትብሉ ማለት ነው።

#ዘ/እለ/እንተ። ዘማርያም ንጽሕና። የማርያም ንጽሕና። እለ ለብዙ ሰዎች ያገለግላል። ሐዋርያት እለ ክርስቶስ የክርስቶስ ሐዋርያት ማለት ነው። እንተ ለሴት ያገለግላል። ማርያም እንተ እፍረት። የሹቱዋ ማርያም ይላል።ዘ ለወንድም ለሴትም ለአንድም ለብዙም ይችላል።

#ውስተ (ውስጥ)። ሀሎ ማይ ውስተ ሄላ። ውሃ በጉድጓድ ውስጥ አለ።

#ታሕተ (በ/ከ...ታች)። አልቦ ሐዳስ ነገር ታሕተ ሰማይ።ከሰማይ በታች አዲስ ነገር የለም።

#ማእከለ (በ...መካከል)። ተሰቅለ ማእከለ ፈያት።በሽፍቶች መካከል ተሰቀለ።

#ዲበ/ላእለ/መልእልተ (በ...ላይ)። ተሰቅለ ዲበ/መልእልተ/ላእለ መስቀል።በመስቀል ላይ ተሰቀለ።

#እም/እምነ (ከ)። እምነ ረኃብ ይኄይስ ኲናት።ከረኀብ ጦር ይሻላል።

#እስከ/እስከነ። እምነ ምድር እስከ ሰማይ።ከምድር እስከ ሰማይ።

#ከመ(እንደ)። ከመ ሐሊብ ዘእጎልት ወከመ ወይን ዘገነት።ስምከ ይጥእም ጊዮርጊስ ሰማእት። እንደ ገነት ወይን እንደ ጊደር ወተት። ስምህ ይጣፍጣል ጊዮርጊስ ሰማእት።

#ኀበ/መንገለ (ወደ)። ንሑር ኀበ አክሱም። ወደ አክሱም እንሂድ።

#በይነ/በእንተ/እንበይነ (ስለ)። በእንተ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ።ክርስቶስ ሆይ ስለማርያም ብለህ ይቅር በለን።

እነዚህ ከላይ ያየናቸው በ10ሩ መራሕያን ይዘረዘራሉ። ሲዘረዘሩም መድረሻ ቀለማቸውን ወደ ኃምስ ቀይረው የሚዘረዘሩ አሉ። ለምሳሌ ምስለ፦ምስሌሁ ይላል። ለ ወደ ሌ እንደተቀየረች አስተውል። ምስሌሁ ከእርሱ ጋር፣ ምስሌሃ ከእርሷ ጋር፣ ምስሌሆሙ ከእነርሱ ጋር እያለ በ10ሩ መራሕያን ይዘረዘራል። እምኔሁ፣ እምኔሃ፣ እምኔሆሙ፣ እምኔሆን፣ እምኔከ፣ እምኔክሙ፣ እምኔክን፣ እምኔየ፣ እምኔነ ይላል። እስከነ ደግሞ እስከኔሁ እስከኔሃ እያለ በ10ሩም ዝለቅ። ዲበ/ላእለ/መልእልተ ያለውም ዲቤሁ ላእሌሁ መልእልቴሁ ዲቤከ ዲቤነ ላእሌነ ወዘተ እያለ በ10ሩም ይዘልቃል። ማእከለም ማእከሌሁ ማእከሌሃ እያለ በ10ሩ መራሕያን ይዘልቃል። ኀበ እና መንገለም እንዲሁ ኀቤከ ኀቤሁ ኀቤሃ መንገሌሃ መንገሌከ እያለ ይዘረዝራል። እንበለም እንበሌሁ እንበሌሃ እያለ ይዘልቃል።

በእንተ እና ዘ እለ እንተ ደግሞ መድረሻቸውን ሣልስ ያደርጉና "ኣ" ፊደልን ጨምረው ይዘረዘራሉ። በእንቲኣሁ በእንቲኣሃ በእንቲኣከ እያለ በ10ሩ ይተረጎማል። ዘ ደግሞ ዚኣሁ ዚኣሃ እያለ ይሄዳል።እለም እሊኣሁ እሊኣከ ወዘተ እያለ ይዘረዘራል። እንተም እንቲኣሁ እንቲኣሃ እያለ ይዘልቃል። "ከመ" በተለየ የመጨረሻ ፊደሉ ወደ ራብዕ ቀይሮ ይዘረዘራል። ከማሁ ከማከ እያለ ይዘልቃል።

የእለቱ ጥያቄዎች
የሚከተሉትን ዓረፍተ ነገሮች ግእዙን ወደ አማርኛ አማርኛውን ወደ ግእዝ ተርጉሙ።

1) እምተናግሮ ይኄይስ አርምሞ (አርምሞ፦ዝምታ፣ ይሄይስ፦ይሻላል፣ ተናግሮ፦መናገር)
2) ገብርኤል ከማርያም ጋር ወደ ገነት ሄደ (ሄደ፦ሖረ)
3) ጥዑም ከመ መዓር
4) ብርሃነከ ፈኑ ዲቤነ
5) ማእከለ አኃውየ (አኃውየ፦ወንድሞቼ)


መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 20🌹
ማጠቃለያ ጥያቄዎች
1) ማርያም ወማርታ.......ኀበ ክርስቶስ
ሀ, ሮጹ
ለ, ሮጸ
ሐ, ሮጻ
መ, ሮጽክሙ
2) ያሬድ......... እምነ አክሱም ኀበ ዋሸራ።
ሀ, መጽኣ
ለ, መጽአኪ
ሐ, መጽኡ
መ, መጽአ
3) ራሄል ወማርያም ...... በእንተ ወሉዶን።
ሀ, አንብዓ
ለ, አንብዑ
ሐ, አንብዐ
መ, አንባዕክሙ
4) ፈጠረ ብሎ ፈጠርኩ ካለ መጽአ ብሎ ምን ይላል?
ሀ, መጻእኩ
ለ, መጸእኩ
ሐ,መጽኢኩ
መ, መጻኢኩ
5) ሠምረ ብሎ ሠመርክሙ ካለ ርእየ ብሎ ምን ይላል?
ሀ,ርእይክሙ
ለ,ርኢይክሙ
ሐ,ርኢክሙ
መ,ርእክሙ
6) .......ተሰቅለ ክርስቶስ ፀሐይ ጸልመ ወወርኅ ደመ ኮነ
ሀ, አመ ለ, ጊዜ ሐ,ሶበ መ, ሁሉም
7) ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ, ሐዋርያትክሙ
ለ, ሐዋርያትከ
ሐ, ሐዋርያትየ
መ, ሐዋርያትነ
8) ሚካኤል.....ገብርኤል መጽኡ ይትራድኡነ
ሀ, ወ
ለ, ምስለ
ሐ, ላእለ
መ, ማእከለ
9) ወደ ኢየሩሳሌም ሄድኩ የሚለው ወደ ግእዝ ሲተረጎም ምን ይሆናል?
ሀ, ኀበ ኢየሩሳሌም ሖርኩ
ለ, መንገለ ኢየሩሳሌም ሖርኩ
ሐ, እምኢየሩሳሌም ሖርኩ
መ, ሀ እና ለ
10) ሕገ ሰዋሰውን የጠበቀ ዓረፍተ ነገር የትኛው ነው?
ሀ, ሠራዊተ መላእክትሁ ለመድኃኔዓለም ይሰግዱ
ለ, አእኑስ ሦዓ መሥዋእተ ለእግዚአብሔር
ሐ, አእኑስ ሦዑ መሥዋእተ ለእግዚአብሔር
መ, ይቤሎሙ ወሬዛ ለአእኑስ ይሴኒ ሥእርትክሙ።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን


መሠረተ፡ግእዝ

@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1

ለመልክትዎ መላኪያ ይህንን ይጫኑ @learnGeezbot
@learnGeezbot
@learnGeezbot
መሠረተ ግእዝ
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 17🌹 የስም ዝርዝር በመራሕያን ክፍል 3 ግእዝ አማርኛ ውእቱ ሐዋርያቲሁ ሐዋርያቱ ውእቶሙ ሐዋርያቲሆሙ ሐዋርያቶቻቸው ይእቲ ሐዋርያቲሃ ሐዋርያቶቿ ውእቶን ሐዋርያቲሆን ሐዋርያቶቻቸው አንተ ሐዋርያቲከ ሐዋርያቶችህ አንትሙ ሐዋርያቲክሙ ሐዋርያቶቻችሁ አንቲ ሐዋርያትኪ…
የግእዝ ክፍል 17 ጥያቄዎች መልስ

ውእቱ፣ሕገጋቲሁ
ውእቶሙ፣ሕገጋቲሆሙ
ይእቲ፣ሕገጋቲሃ
ውእቶን፣ሕገጋቲሆን
አንተ፣ሕገጋቲከ
አንትሙ፣ሕገጋቲክሙ
አንቲ፣ሕገጋትኪ
አንትን፣ሕገጋቲክን
አነ፣ሕገጋትየ
ንሕነ፣ሕገጋቲነ

ውእቱ፣አድባራቲሁ
ውእቶሙ፣አድባራቲሆሙ
ይእቲ፣አድባራቲሃ
ውእቶን፣አድባራቲሆን
አንተ፣አድባራቲከ
አንትሙ፣አድባራቲክሙ
አንቲ፣አድባራትኪ
አንትን፣አድባራቲክን
አነ፣አድባራትየ
ንሕነ፣አድባራቲነ።

ውእቱ፣መላእክቲሁ
ውእቶሙ፣መላእክቲሆሙ
ይእቲ፣መላእክቲሃ
ውእቶን፣መላእክቲሆን
አንተ፣መላእክቲከ
አንትሙ፣መላእክቲክሙ
አንቲ፣መላእክትኪ
አነ፣መላእክትየ
ንሕነ፣መላእክቲነ

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
መሠረተ ግእዝ
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 18🌹 በጣም አስፈላጊ የሆኑ የግእዝ ቃላት ግእዝ አማርኛ English ወ እና And አው ወይም Or ምንት ምን What መኑ ማን Who እፎ እንዴት …
የግእዝ ክፍል 18 ጥያቄዎች መልስ

1) ጊዮርጊስ ወፊቅጦር ሰማእታት እሙንቱ (ውእቶሙ)
2) አንድ ሲሆን ሦስት
3) ሃይማኖት ምንድን ነው?
4) እፎ ወዐልከ
5) ትድናለህና አትፍራ

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
መሠረተ ግእዝ
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 19🌹 ግእዝ አማርኛ English ምስለ ከ.....ጋር With እንበለ ያለ፣በቀር፣ሳ ዘ/እንተ/እለ የ ውስተ በ....ውስጥ In ታሕተ በ....ታች Under ማእከለ በ...መካከል betwen ዲበ/ላእለ/መልእልተ በ...ላይ On እም/እምነ…
የግእዝ ክፍል 19 ጥያቄዎች መልስ

1) ከመናገር ዝም ማለት ይሻላል
2) ገብርኤል ምስለ ማርያም ሖረ ኀበ ገነት
3) እንደማር የጣፈጠ
4) ብርሃንህን በእኛ ላይ ላክ
5) በወንድሞቼ መካከል

ረድኤተ እግዚአብ ሔር አይለየን።

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 21🌹
#ውእቱ #አስሩን #መራሕያን #ሲያውቃቸው
አእመሮ፣አወቀው፣He knows him
አእመሮሙ፣አወቃቸው፣He knows them
አእመራ፣አወቃት፣He knows her
አእመሮን፣አወቃቸው፣He knows them.
አእመረከ፣አወቀህ፣He knows you
አእመረክሙ፣አወቃችሁ፣He knows you
አእመረኪ፣አወቀሽ፣He knows you
አእመረክን፣አወቃችሁ፥He knows you
አእመረኒ፥አወቀኝ፣He knows me
አእመረነ፣አወቀን፣He knows us

ውእቱ አእመረ አወቀ ይል የነበረው ውእቱን ሲያውቀው አእመሮ ተብሎ የመጨረሻ ፊደሉ ወደ ሳብዕ "ሮ" እንደተለወጠ አስተውል። እነርሱን አወቃቸው ሲል ደግሞ መጨረሻውን ሳብዕ አድርጎ "ሙ" ፊደልን ጨምሯል። እርሷን አወቃት ለማለት ደግሞ የመጨረሻ ቃሉ ወደ ራብዕ "ራ" መቀየሩን አስተውል።ብዙ ሴቶችን አወቃቸው ሲል ደግሞ መጨረሻ ፊደሉን ወደ ሳብዕ "ሮ" ቀይሮ "ን" ፊደልን መጨመሩን አስተውል። በአንተ ጊዜ "ከ"ን በአንትሙ ጊዜ "ክሙ"ን በአንቲ ጊዜ "ኪ"ን በአንትን ጊዜ "ክን"ን ይጨምራል።በአነ ጊዜ "ኒ"ን በንሕነ ጊዜ "ነ" ፊደልን መጨመር ብቻ ነው።

#ውእቶሙ #አስሩን #መራሕያን #ሲያውቃቸው
አእመርዎ፣አወቁት፣They know him
አእመርዎሙ፣አወቋቸው፣They know them
አእመርዋ፣አወቋት፣They know her
አእመርዎን፣አወቋቸው፣They know them
አእመሩከ፣አወቁህ፣They know you
አእመሩክሙ፣አወቋችሁ፣They know you
አእመሩኪ፣አወቁሽ፣They know you
አእመሩክን፥አወቋችሁ፣ They know you
አእመሩኒ፣አወቁኝ፣They know me
አእመሩነ፣አወቁን፣They know us

ውእቶሙ አእመሩ።እነርሱ አወቁ ይል የነበረው።እርሱን ሲያውቁት መጨረሻ ፊደሉን ወደ ሳድስ ቀይሮ "ዎ" ፊደልን መጨመር ነው። እነርሱን ሲያውቋቸው "ዎሙ"ን መጨመር ነው።እርሷን ሲያውቋት "ዋ"ን መጨመር ነው።እነርሱን ሴቶችን ሲያውቋቸው "ዎን"ን ይጨምራል። ሁለተኛ መደቦችንና አንደኛ መደቦችን ግን ቀጥታ አእመሩ ባለው ቃል ላይ "ከ፣ኪ፣ ክሙ፣ ክን፣ ኒ፤ ነ" መጨመር ነው።


መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
ክፍል- ፳፩

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 22🌹
#ይእቲ #አስሩን #መራሕያን #ስታውቃቸው
አእመረቶ፣አወቀችው፣She knows him
አእመረቶሙ፣አወቀቻቸው፣She knows them
አእመረታ፣አወቀቻት፣She knows her
አእመረቶን፣አወቀቻቸው፣She knows them
አእመረተከ፣አወቀችህ፣She knows you
አእመረተክሙ፣አወቀቻችሁ፣She knows you
አእመረተኪ፣አወቀችሽ፣She knows you
አእመረተክን፣አወቀቻችሁ፣She knows you
አእመረተኒ፣አወቀችኝ፣She knows me
አእመረተነ፣አወቀችን፣She knows us
.
ይላል አስተውል ይእቲ አእመረት እርሷ አወቀች She knows ይላል። እርሷ እርሱን ስታውቀው "ት" ወደ ሳብዕ "ቶ" ይቀየራል። እነርሱን ስታውቃቸው ደግሞ ወደ ሳብዕ ተቀይሮ "ሙ" ፊደልን ይጨምራል። እርሷ እርሷን ስታውቃት ወደ ራብዕ "ታ" ይቀየራል። ሴቶችን እነርሱን ስታውቃቸው ደግሞ ወደ ሳብዕ ቀይሮ "ን" ፊደልን ይጨምራል። በሁለተኛ እና በአንደኛ መደቦች ጊዜ "ት" የነበረው ወደ ግእዝ "ተ" ተቀይሮ በአንተ ከን በአንትሙ ክሙን በአንቲ ኪን በአንትን ክንን በአነ ኒን በንሕነ ነን መጨመር ነው።

#ውእቶን #አስሩን #መራሕያን #ሲያውቋቸው
አእመራሁ፣አወቁት፣They know him
አእመራሆሙ፣አወቋቸው፣They know them
አእመራሃ፣አወቋት፣They know her
አእመራሆን፣አወቋቸው፣They know them
አእመራከ፣አወቁህ፣They know you
አእመራክሙ፣አወቋችሁ፣They know you
አእመራኪ፣አወቁሽ፣They know you
አእመራክን፥አወቋችሁ፣ They know you
አእመራኒ፣አወቁኝ፣They know me
አእመራነ፣አወቁን፣They know us
ይላል።ውእቶን አእመራ እነርሱ አወቁ ይል የነበረው።እርሱን ሲያውቁት "ሁ" ፊደልን ጨምሯል። እነርሱን ሲያውቋቸው "ሆሙ" ፊደልን ጨምሯል።እርሷን ሲያውቋት "ሃ" ፊደልን ጨምሯል። እነርሱን ሲያውቋቸው "ሆን" ፊደልን ጨምሯል። በአንደኛና በሁለተኛ መደቦች እንደተለመደው "ከ፣ ኪ፣ ክሙ፣ ክን፣ ኒ፣ ነ" ፊደልን መጨመር ነው።


መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 23🌹
#አንተ #ስድስቱን #መራሕያን #ሲያውቃቸው
አእመርኮ፣አወቅከው፣You know him
አእመርኮሙ፣አወቅካቸው፣You know them
አእመርካ፣አወቅካት፣You know her
አእመርኮን፣አወቅካቸው፣You know them
አእመርከኒ፣አወቅከኝ፣You know me
አእመርከነ፣አወቅከን፣You know us.
አንተ አእመርከ You know ይል የነበረው በውእቱ ጊዜ "ከ" ወደ ሳብዕ "ኮ" ይቀየራል። በእነርሱ ጊዜ ደግሞ ወደ ሳብዕ ተቀይሮ "ሙ"ን ይጨምራል፣ በእነርሱ ሴቶች ጊዜ ወደ ሳብዕ ተቀይሮ "ን"ን ይጨምራል፣ በእርሷ ጊዜ ወደ ራብዕ ይቀይራል።

#አንትሙ #ስድስቱን #መራሕያን #ሲያውቃቸው
አእመርክምዎ፣አወቃችሁት፣You know him
አእመርክምዎሙ፣አወቃችኋቸው፣You know them
አእመርክምዋ፣አወቃችኋት፣You know her
አእመርክምዎን፣አወቃችኋቸው፣You know them
አእመርክሙኒ፣አወቃችሁኝ፣You know me
አእመርክሙነ፣አወቃችሁን፣You know us.
አንትሙ አእመርክሙ You know አወቃችሁ ይል የነበረው።በእርሱ ጊዜ መጨረሻው "ሙ" ወደ ሳድስ "ም" ተቀይሮ "ዎ" ፊደልን መጨመር ነው።በይእቲ "ዋ"ን መጨመር ነው። በውእቶሙ ጊዜ "ዎሙ"ን መጨመር ነው። በውእቶን ጊዜ "ዎን"ን መጨመር ነው። በአነ ጊዜ "ኒ"ን መጨመር ነው። በንሕነ ጊዜ "ነ"ን መጨመር ነው።

#አነ #ስምንቱን #መራሕያን #ሳውቃቸው
አእመርክዎ፣አወቀዋለሁ፣I know Him
አእመርክዎሙ፣አውቃቸዋለሁ፣I know them
አእመርክዋ፣አወቅኳት፣I know her
አእመርክዎን፣አወቅኳቸው፣I know them
አእመርኩከ፣አወቅኩህ፣I know you
አእመርኩክሙ፣አወቅኳችሁ፣I know you
አእመርኩኪ፣አወቅኩሽ፣I know you
አእመርኩክን፣አወቅኳችሁ፣I know you
አነ አእመርኩ እኔ አወቅሁ I know ይል የነበረው በውእቱ ጊዜ "ኩ" ወደ ሳድስ ተቀይሮ "ዎ"ን መጨመር ነው። በውእቶሙ ጊዜ "ዎሙ"ን መጨመር ነው።በይእቲ ጊዜ "ዋ"ን መጨመር ነው። በውእቶን ጊዜ "ዎን"ን መጨመር ነው።በሁለተኛ መደቦች እንደተለመደው "ከ፣ ኪ፣ ክሙ፣ ክን" መጨመር ነው።


መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 24🌹
#ንሕነ #ስምንቱን #መራሕያን ስናውቃቸው
አእመርናሁ፣አወቅነው፣We know him
አእመርናሆሙ፣አወቅናቸው፣We know them
አእመርናሃ፣አወቅናት፣We know her
አእመርናሆን፣አወቅናቸው፣We know them
አእመርናከ፣አወቅንህ፣We know you
አእመርናክሙ፣አወቅናችሁ፣We know you
አእመርናኪ፣አወቅንሽ፣We know you
አእመርናክን፣አወቅናችሁ፣We know you
ንሕነ አእመርነ እኛ አወቅን We know ይል የነበረው በውእቱ ጊዜ መድረሻውን ወደ ራብዕ "ና" ቀይሮ ከዚያ "ሁ"ን መጨመር ነው። በውእቶሙ "ሆሙ"ን፣ በውእቶን "ሆን"ን፣ በይእቲ "ሃ"ን፣ በአንተ "ከ"ን በአንትሙ "ክሙ"ን በአንቲ "ኪ"ን በአንትን "ክን"ን መጨመር ነው።

#አንቲ #ስድስቱን #መራሕያን #ስታውቃቸው
አእመርኪዮ፣አወቅሽው፣You know him
አእመርኪዮሙ፣አወቅሻቸው፣You know them
አእመርኪያ፣አወቅሻት፣You know her
አእመርኪዮን፣አወቅሻቸው፣You know them
አእመርኪኒ፣አወቅሽኝ፣You know me
አእመርኪነ፣አወቅሽን፣You know us.
አንቲ አእመርኪ አንቺ አወቅሽ You know ይል የነበረው በውእቱ ጊዜ "ዮ"ን፣ በውእቶሙ "ዮሙ"ን፣ በይእቲ "ያ"ን፣ በውእቶን "ዮን"ን፣ በአነ ጊዜ "ኒ"ን፣ በንሕነ ጊዜ "ነ"ን መጨመር ነው።

#አንትን #ስድስቱን #መራሕያን #ሲያውቃቸው
አእመርክናሁ፣አወቃችሁት፣You know him
አእመርክናሆሙ፣አወቃችኋቸው፣You know them
አእመርክናሃ፣አወቃችኋት፣You know her
አእመርክናሆን፣አወቃችኋቸው፣You know them
አእመርክናኒ፣አወቃችሁኝ፣You know me
አእመርክናነ፣አወቃችሁን፣You know us.
አንትን አእመርክን እናንተ ሴቶች አወቃችሁ You know ይል የነበረው በውእቱ ጊዜ የመጨረሻዋ ፊደል "ን" ወደ ራብዕ "ና" ተቀይራ በውእቱ ጊዜ "ሁ"ን፣ በውእቶሙ ጊዜ "ሆሙ"ን፣ በይእቲ ጊዜ "ሃ"ን፣ በውእቶን ጊዜ "ሆን"ን፣ በአነ ጊዜ "ኒ"ን በንሕነ ጊዜ "ነ"ን ይጨምራል። የውእቱ፣ የአንተ፣ የአንቲ፣ የንሕነ ተደራቢ አረባብ አላቸው። ማደናገር እንዳይሆንብኝ አልፌዋለሁ። ምናልባት በስፋት ከነተደራቢው "የግእዝ ቋንቋ መማሪያ" በሚለው መጽሐፌ ስላለ ገዝታችሁ ማንበብ ትችላላችሁ።መጽሐፏን አዲስ አበባ "ብራና መጻሕፍት መደብር" ታገኟታላችሁ።


መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 25🌹

8ቱ የግሥ አርእስት።የእነዚህን አረባብ በደንብ ከተረዳን ግእዝ ቀላል ይሆንልናል።እነሆ፦
1) ቀተለ=ገደለ
2) ቀደሰ=አመሰገነ
3) ተንበለ=ለመነ
4) ባረከ=አመሰገነ
5) ዴገነ=ተከተለ
6) ክህለ=ቻለ
7) ጦመረ=ጻፈ
8) ማሕረከ=ማረከ
እነዚህ የግሥ አርእስት ይባላሉ። የጦመረ ቤት የሚባሉት መጀመሪያ ፊደላቸው ሳብዕ ነው። ጦመረ ስንል "ጦ" ሳብዕ መሆኑን ልብ ይሏል። የክህለ ቤቶች ደግሞ መጀመሪያ ፊደላቸው ሳድስ ነው። ክህለ ሲል "ክ" ሳድስ መሆኑን አስተውል። የዴገነ ቤቶች ደግሞ መነሻ ፊደላቸው ኃምስ ነው።ዴገነ ሲል "ዴ" ኃምስ መሆኑን ልብ ይሏል። የባረከ ቤቶች ደግሞ መነሻ ፊደላቸው ራብዕ ሆኖ ሦስት ፊደል ብቻ የሆኑ ናቸው። የማሕረከ ቤት የሚባሉት ደግሞ መነሻ ፊደላቸው እንደ ባረከ ሁሉ ራብዕ ሲሆን ነገር ግን አራትና ከዚያ በላይ ፊደላት ያላቸው ናቸው።የቀደሰ ቤቶች ጠብቀው ይነበባሉ። ቀደሰ ስንል "ደ" ጠብቆ ይነበባል። መነነ ስንል መካከለኛው "ነ" ጠብቆ ይነበባል። ሌሎች ላልተው ይነበባሉ።የተንበለ ቤቶች ደግሞ መነሻው ግእዝ ሆኖ ከመነሻው ቀጥሎ ያለው ፊደል ደግሞ ሳድስ የሆኑ ናቸው። ለምሳሌ ተንበለን ብታይ መነሻው "ተ" ግእዝ ሆኖ ቀጥሎ ያለው "ን" ሳድስ ነው።ሌላው ግእዝ ነው። ይህንን የመሰለ ሌላ "አእመረ" አለ። 5 ፊደል ባለው ግሥ ደግሞ መካከለኛዋ "ሳድስ" ሆና ሌላው ግእዝ የሆነ ነው። ለምሳሌ "አመድበለ" ቢል መካከለኛዋ "ድ" ሳድስ ሆና ሌላው ግእዝ መሆኑን አስተውል።

ሌላው ወደፊትም በግሥ እርባታ ጊዜ ከላይ ካየናቸው በተጨማሪ የሚጠቅሙን ቤቶች አሉ እነዚህም፦
1) ሤመ=ሾመ
2) ቆመ=ቆመ
3) ገብረ=ሠራ
ናቸው።የሤመ ቤቶች የሚባሉት በኃምስ ተነስተው ሁለት ፊደል ያላቸው ግሦች ናቸው። የቆመ ቤት የሚባሉት ደግሞ በሳብዕ ተነስተው ሁለት ፊደል ብቻ የሆኑ ግሦች ናቸው።የገብረ ቤት የሚባሉት ደግሞ ሦስት ፊደል ያላቸው ግሦች ሆነው መነሻና መድረሻቸው ግእዝ ሆኖ መካከላቸው ሳድስ የሆኑ ግሦች ናቸው።


መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
2024/10/01 13:29:21
Back to Top
HTML Embed Code: