Telegram Web Link
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 9🌹
ተናባቢ ቃላት እና ተሳቢ
ሁለት ቃላት በአንድነት ሲጣመሩ ተናባቢ ቃላት ይባላሉ።ለምሳሌ "ቤተ መንግሥት" ስንል ቤት እና መንግሥት ከሚሉ ቃላት የተዋቀረ ነው።ይህ ደግሞ የራሱ ሕግ ስላለው እርሱን ዛሬ እንመለከታለን። መንግሥት የቤት ዘርፍ ይባላል።
>>ሳድስ ቃላት ወደ ግእዝ
>>ሣልስ ቃላት ወደ ኃምስ
>>ራብዕ ቃላት አይለወጡም
>> ኃምስ ቃላት አይለወጡም
>>ሳብዕ ቃላት አይለወጡም
ይህም ማለት ለምሳሌ "ቤት" የሚለው ቃል "መንግሥት" ከሚለው ቃል ጋር ሲናበብ የመጨረሻ ፊደሉ "ት" ወደ "ተ" ተለውጦ "ቤተመንግሥት" ይባላል። ሣልስ ቃላት ወደኃምስ ይለወጣሉ ያልነው ደግሞ ለምሳሌ "መጋቢ" የሚለው ቃል "ሐዲስ" ከሚለው ቃል ጋር ሲናበብ ሣልሷ "ቢ" ወደ ኃምስ "ቤ" ትቀየርና "መጋቤ ሐዲስ" ይላል ማለት ነው። ተናባቢ ቃላት በአንድ ትንፋሽ እንጂ ተነጣጥለው አይነበቡም።ራብዕ ቃላት አይለወጡም ያልነው ደግሞ ለምሳሌ "መና" የሚለው ቃል "እስራኤል" ከሚለው ቃል ጋር ሲናበብ "ና" ባለበት ሆኖ "መና እስራኤል" ይላል ማለታችን ነው። ኃምስ አይለወጥም ያልነውም ለምሳሌ "ቅዳሴ" የሚለው ቃል እና "መላእክት" የሚለው ቃል ሲናበቡ "ሴ" ባለበት ኃምስ ሆኖ "ቅዳሴ መላእክት" ይላል ማለታችን ነው። ሳብዕ ቃላት አይለወጡም ያልነውም ለምሳሌ "አእምሮ" እና "ሊቃውንት"ን ብናናብባቸው ባለበት "አእምሮ ሊቃውንት" ይላል ማለታችን ነው።
ቃላት ሲናበቡ ብዙ ጊዜ "የ" የሚል ትርጉምን ይይዛሉ።ለምሳሌ ሕዝብ እና ኢትዮጵያ ሲናበቡ ሕዝበ ኢትዮጵያ ይላል። ትርጉሙ የኢትዮጵያ ሕዝብ ማለት ነው። በእንግሊዘኛ "Of" የሚል ትርጉም ማለት ነው። People of Ethiopia ይላል።
#ተሳቢ #ቃላት
በግእዝ ቋንቋ አንድ ቃል እንደባለቤትነት ወይም "Subject" ሲያገለግልና እንደ ተሳቢነት "Object" ሲያገለግል የተለያየ የፊደል መዋቅር አለው። ለምሳሌ በአማርኛ ኤዶም እንጀራ በላች። ስንል እና "እንጀራ ይበላል" ብንል እንጀራ የሚለው ቃል በመጀመሪያው ተሳቢ ሲሆንና ቀጥሎ ባለቤት ሲሆን ምንም ዓይነት ለውጥ አላመጣም። በግእዝ ቋንቋ ግን ለውጥ አለው። ኤዶም በልዐት ኅብስተ ይላል። እንጀራ ይበላል ለማለት ግን ኅብስት ይትበላዕ ይላል። አስተውል ተሳቢ ሲሆን "ኅብስተ" ብሎ ባለቤት ሲሆን ግን "ኅብስት" ይላል።መድረሻ ቀለሙ እንደተለያየ አስተውል። የመጀመሪያው ግእዝ "ተ" ሁለተኛው ሳድስ "ት" ሆኗል።ስለዚህ ቃላት ተሳቢ ሲሆኑ ሕግ አላቸው።

<<ሳድስ ቃላት ሲሳቡ ግእዝ
<<ካዕብ ቃላት ሲሳቡ ሳብዕ
<<ሣልስ ቃላት ሲሳቡ ኃምስ
<<ራብዕ ቃላት ሲሳቡ አይለወጡም
<<ኃምስ ቃላት ሲሳቡ አይለወጡም
<<ሳብዕ ቃላት ሲሳቡ አይለወጡም
<<የሀገር ስሞችና ተናባቢ ቃላት ሲሳቡ አይለወጡም
<<የሰው ስም ሲሳብ መድረሻው ላይ "ሃ" ፊደልን ይጨምራሉ።

ለምሳሌ "ቤቱ" ይል የነበረው ሲሳብ "ቤቶ" ይላል።ቱ ካዕብ ነበረ ሲሳብ ግን ቶ ሳብ ዕ ሆነ ማለት ነው። ጸሓፊ ይል የነበረው ሲሳብ "ጸሓፌ" ይሆናል።ፊ ሣልስ ወደ ኃምስ ፌ መለወጧን አስተውል። "ሀገር" ይል የነበረው ሲሳብ "ሀገረ" ይላል። ር ሳድስ ወደ ግእዝ ረ መለወጧን አስተውል።ራብዕ፣ኃምስ እና ሳብዕ ቃላት ሲሳቡ አይለወጡም ማለት ለምሳሌ "ውዳሴ፣እንዚራ፣መሰንቆ" የሚሉት ቃላት ሲሳቡም ባሉበት "ውዳሴ፣እንዚራ፣መሰንቆ" ይላሉ ምንም ዓይነት የፊደል ለውጥ አያመጡም ማለት ነው።የሀገር ስሞችና ተናባቢ ቃላትን ተሳቢ ሲሆኑ ምንም ዓይነት ለውጥ አያመጡም። "ቤተመንግሥት" ሲሳብ ያው ባለበት "ቤተመንግሥት" ይላል ማለት ነው።ጎጃም፣ጎንደር፣ትግራይ የሚሉ ቃላትም ሲሳቡ እዚያው ባሉበት ጎጃም፣ጎንደር፣ትግራይ ይላሉ ማለት ነው።የሰው ስም ሲሳብ "ሀ" የሚል ፊደልን ይጨምራሉ።ለሴት ሲሆን "ሃ"ን እንጨምራለን። ለምሳሌ እኛ ማርያምን እንወዳለን የሚለው ንሕነ ናፈቅር ማርያምሃ ይላል። ማርያም የክርስቶስ እናት ናት ሲል ግን ባለቤት ስለምትሆን ባለበት ማርያም ይእቲ እሙ ለክርስቶስ ይላል ማለት ነው።

ጥያቄ
የሚከተሉትን ቃላት ተናባቢ አድርጉ
1, ውዳሴ እና ማርያም
2, መሰንቆ እና ዳዊት
3, ዝማሬ እና መላእክት
4, መጋቢ እና አእላፍ
5, ሊቅ እና ምሁራን
የሚከተሉትን ቃላት ተሳቢ አድርጉ
6 ሰማይ
7 መንግሥተሰማያት
8 ፈጣሪ
9 ሀገሩ
10 ጸዐዳ
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 10🌹
ከክፍል 1 እስከ ክፍል 9 የተማራችሁ በሉ ለማስታወስ የሚከተሉትን 15 ጥያቄዎች መልሱ።

1) ስለ ግእዝ ቋንቋ ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ, የራሱ የሆነ ፊደል አለው
ለ,የራሱ የሆነ ቁጥር አለው
ሐ,የራሱ ሥርዓተ ንባብ አለው
መ,ሁሉም
2) "44" የሚለው ቁጥር በግእዝ.....ነው
ሀ,፬፬
ለ,፵፬
ሐ,፵፵
መ,፬፵
3) "ኤርምያስ" የሚለው ቃል ሥርዓተ ንባቡ ምንድን ነው?
ሀ, ሰያፍ
ለ, ተነሽ
ሐ, ወዳቂ
መ, ተጣይ
4) ከመራሕያን ውስጥ ሦስተኛ መደብ ሴት እና ነጠላ የሆነች የትኛዋ ናት?
ሀ,አንቲ
ለ,ይእቲ
ሐ,ንሕነ
መ, ሀ እና ለ
5) "እነዚያ" የሚለውን የአማርኛ ቃል የሚተካ የግእዝ ቃል የትኛው ነው?
ሀ,እሉ
ለ,እላ
ሐ,እልክቱ
መ,እሎን
6) ከሚከተሉት ውስጥ በትክክል የተናበበው ቃል የቱ ነው?
ሀ, መጋቢ ብሉይ
ለ, ሊቀ ጠበብት
ሐ, መልአከ ብርሃን
መ, ለ እና ሐ
7) "ዳንኤል" የሚለው ቃል ተሳቢ ሲሆን እንዴት ነው?
ሀ, ዳንኤልሀ
ለ, ዳንኤለ
ሐ, ዳንኤል
መ. ዳንኤልሃ
8) "8645" የሚለው ቁጥር ወደ ግእዝ ሲለወጥ ምን ይሆናል።
ሀ,፹፻፮፻፵፭
ለ,፹፮፻፵፭
ሐ,፰፮፻፵፭
መ,ሀ እና ለ
9) "ሃይማኖት እንበለ ምግባር ምውት ይእቲ" ከሚለው ዓረፍተ ነገር "ይእቲ" አገልግሎቷ ምንድን ነው?
ሀ, የስም ምትክ
ለ, ነባር አንቀጽ
ሐ, አመልካች ቅጽል
መ, ተውላጠ ስም
10) "አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም" ከሚለው ዓረፍተ ነገር ውስጥ የውእቱ ትርጉም ምንድን ነው?
ሀ) ነሽ
ለ) ነው
ሐ) ናት
መ) ነኝ
11) ከሚከተሉት ውስጥ ትክክለኛው የቱ ነው።
ሀ, ሠዐለ....ለመነ
ለ, ሰዐለ.....ሳለ
ሐ, ሠአለ.....ሳለ
መ, ሰአለ......ለመነ
12) "አቤቱ አንተን እናመሰግንሀለን" የሚለው የግእዝ ቃል ወደ ግእዝ ሲተረጎም እንዴት ነው?
ሀ) ለሊነ እግዚኦ ነአኲት
ለ) ኪያነ እግዚኦ ነአኲት
ሐ) ኪያከ እግዚኦ ነአኲት
መ) ለሊከ እግዚኦ ነአኲት
13) "የእኔ መመኪያ እግዚአብሔር ነው" የሚለው የአማርኛ ዓረፍተ ነገር ወደ ግእዝ ሲተረጎም ምን ይሆናል?
ሀ, እግዚአብ ሔር ውእቱ ትምክህተ ዚኣየ
ለ, ትምክህት በእግዚአብሔር ዚኣየ ውእቱ
ሐ, ትምክህት ዘዚኣየ እግዚአብሔር ውእቱ።
መ, ሀ እና ሐ
14) "ለሊነ ነአምር ኲሎ ዘኮነ" ከሚለው ዓረፍተ ነገር የለሊነ ትርጉም ምንድን ነው?
ሀ, እነርሱ ራሳቸው
ለ, እናንተ ራሳችሁ
ሐ, እኛ ራሳችን
መ, አንቺ ራስሽ
15) ውእቱ ብሎ እርሱ ካለ ...... ብሎ እነርሱ ይላል።
ሀ) እማንቱ
ለ) ውእቶሙ
ሐ) ውእቶን
መ) እሙንቱ
ሠ) ሁሉም

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1 👈
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 11🌹
ግእዝ አማርኛ
ውእቱ ቀደሰ አመሰገነ
ውእቶሙ ቀደሱ አመሰገኑ
ይእቲ ቀደሰት አመሰገነች
ውእቶን ቀደሳ አመሰገኑ (ሴቶች)
አንተ ቀደስከ አመሰገንክ
አንትሙ ቀደስክሙ አመሰገናችሁ
አንቲ ቀደስኪ አመሰገንሽ
አንትን ቀደስክን አመሰገናችሁ (ሴቶች)
አነ ቀደስኩ አመሰገንኩ
ንሕነ ቀደስነ አመሰገንን

እንግዲህ አንድን ግሥ በአሥሩም መራሕያን ለማርባት የራሱ የሆኑ ሕጎች አሉት።

#በውእቱ ጊዜ የሚጨመርም ሆነ የሚለወጥ ፊደል የለም። ቀደሰ

#በውእቶሙ ጊዜ የመጨረሻ ፊደሉን ወደ ካዕብ ይለውጣል። ቀደሱ (ሰ ወደ ሱ መለወጡን አስተውል)።

#በይእቲ ጊዜ መጨረሻ ላይ "ት" ፊደልን መጨመር ነው። ቀደሰት (ት እንደተጨመረ አስተውል)።

#፬በውእቶን ጊዜ መጨረሻ ፊደሉ ወደ ራብዕ መለወጥ ነው። ቀደሳ (ሰ ወደ ሳ እንደተለወጠ አስተውል)።

#፭በአንተ ጊዜ መድረሻውን ወደ ሳድስ ቀይሮ "ከ" ፊደልን መጨመር ነው። ቀደስከ (ሰ ወደ ሳ ድስ ስ ተቀይራ ከዚያ ከ እንደተጨመረ አስተውል)

#፮በአንትሙ ጊዜ መድረሻውን ወደ ሳድስ ቀይሮ "ክሙ" ፊደልን ይጨምራል። ቀደስክሙ

#፯በአንቲ ጊዜ መድረሻውን ወደ ሳድስ ቀይሮ "ኪ" ፊደልን ይጨምራል። ቀደስኪ።

#፰በአንትን ጊዜ መድረሻውን ወደ ሳ ድስ ቀይሮ "ክን" ፊደልን ይጨምራል። ቀደስክን

#፱በአነ ጊዜ መድረሻውን ወደ ሳድስ ቀይሮ "ኩ" ፊደልን መጨመር ነው። ቀደስኩ

#፲በንሕነ ጊዜ መድረሻውን ወደ ሳድስ ቀይሮ "ነ" ፊደልን ይጨምራል። ቀደስነ

አስተውል አንደኛ መደቦችና ሁለተ ኛ መደቦች ሲዘረዘሩ መድረሻቸው ፊደላቸውን ወደ ሳድስ ለውጠው ከዚያ ባዕድ በመጨመር ነው። ሦስተኛ መደቦች ሁልጊዜም ከላይ በጻፍነው ሕግ ሲጸኑ ሁለተኛና አንደ ኛ መደቦች የተለያዩ አካሄዶች አሏቸው።እነርሱን በቀጣይ ክፍል እንመለከታለን።

የውእቶን እና የአንትን ዝርዝር ተጥለው ይነበባሉ። የይእቲ ዝርዝር ተሰይፎ ይነበባል።የሌሎቹ ዝርዝር ተነስቶ ይነበባል።

ጥያቄ
የሚከተሉትን ቃላት በአሥሩ መራሕያን ዘርዝር
1, ዘገበ (ሰበሰበ)
2, ፈከረ (ተረጎመ)
3, ሰከበ (ተኛ)
4, ፈጠረ (ፈጠረ)
5, ኖመ (ተኛ)


መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
ግእዝ ክፍል ፲፩
መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
መሠረተ ግእዝ
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 11🌹 ግእዝ አማርኛ ውእቱ ቀደሰ አመሰገነ ውእቶሙ ቀደሱ አመሰገኑ ይእቲ ቀደሰት አመሰገነች ውእቶን ቀደሳ አመሰገኑ (ሴቶች) አንተ ቀደስከ አመሰገንክ አንትሙ ቀደስክሙ አመሰገናችሁ…
ክፍል ፲፩ የጥያቄዎች መልስ


1 ውእቱ → ዘገበ
ይእቲ → ዘገበት
ውእቶሙ → ዘገቡ
ውእቶን → ዘገባ
አንተ → ዘገብከ
አንቲ → ዘገብኪ
አንትሙ → ዘገብክሙ
አንትን → ዘገብክን
አነ → ዘገብኩ
ንሕነ → ዘገብነ


2ኛ ውእቱ → ፈከረ
ይእቲ → ፈከረት
ውእቶሙ → ፈከሩ
ውእቶን → ፈከራ
አንተ → ፈከርከ
አንቲ → ፈከርኪ
አንትሙ → ፈከርክሙ
አንትን → ፈከርክን
አነ → ፈከርኩ
ንሕነ → ፈከርነ



3ኛ ውእቱ → ሰከበ
ይእቲ → ሰከበት
ውእቶሙ → ሰከቡ
ውእቶን → ሰከባ
አንተ → ሰከብከ
አንቲ → ሰከብኪ
አንትሙ → ሰከብክሙ
አንትን → ሰከብክን
አነ → ሰከብኩ
ንሕነ → ሰከብነ


4ኛ ውእቱ → ፈጠረ
ይእቲ → ፈጠረት
ውእቶሙ → ፈጠሩ
ውእቶን → ፈጠራ
አንተ → ፈጠርከ
አንቲ → ፈጠርኪ
አንትሙ → ፈጠርክሙ
አንትን → ፈጠርክን
አነ → ፈጠርኩ
ንሕነ → ፈጠርነ


5ኛ ውእቱ → ኖመ
ይእቲ → ኖመት
ውእቶሙ → ኖሙ
ውእቶን → ኖማ
አንተ → ኖምከ
አንቲ → ኖምኪ
አንትሙ → ኖምክሙ
አንትን →ኖምክን
አነ → ኖምኩ
ንሕነ → ኖምነ

ግእዝ ክፍል ፲፩
መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 12🌹

በ"ሀ" እና በ"አ" የሚጨርሱ ግሦች
እነዚህ ግሦች ሲዘረዘሩ በአንደኛና በሁለተኛ መደቦች ቅድመ መድረሻቸውን ወደ ራብዕ ቀይረው ይዘረዘራሉ።

ግእዝ አማርኛ
ውእቱ መጽአ መጣ
ውእቶሙ መጽኡ መጡ
ይእቲ መጽአት መጣች
ውእቶን(ሴ) መጽኣ መጡ
አንተ መጻእከ መጣህ
አንትሙ መጻእክሙ መጣችሁ
አንቲ መጻእኪ መጣሽ
አንትን(ሴ) መጻእክን መጣችሁ
አነ መጻእኩ መጣሁ
ንሕነ መጻእነ መጣን
በሀ ፊደል የጨረስም እንደዚሁ መርሐ መራ ብሎ መርሐ፣ መርሑ፣ መርሐት፣ መርሓ፣ መራሕከ፣ መራሕክሙ፣ መራሕኪ፣ መራሕክን፣ መራሕኩ፣ መራሕነ ይላል።ማለት ነው። ሦስተኛ መደቦች ላይ ባለፈው እንዳየነው ባሉበት ናቸው። ሁለተኛና አንደ ኛ መደቦች ግን "ጽ"ን ወደ ራብእ "ጻ" ቀይረው እንደተዘረዘሩ አስተውል። ይህ ሕግ ሦስትና ከዚያ በላይ ፊደል ባላቸው እንጂ ሁለት ፊደል ባላቸው በሀ እና በአ በሚጨርሱ ግሦች አይሠራም።በምሳሌ ለመመልከት ያህል።

ግእዝ አማርኛ
ውእቱ ሦዐ ሰዋ
ውእቶሙ ሦዑ ሰው
ይእቲ ሦዐት ሰዋች
ውእቶን ሦዓ ሰው (ሴ)
አንተ ሦዕከ ሰዋህ
አንትሙ ሦዕክሙ ሰዋችሁ
አንቲ ሦዕኪ ሰዋሽ
አንትን ሦዕክን ሰዋችሁ
አነ ሦዕኩ ሰዋሁ
ንሕነ ሦዕነ ሰዋን
ይላል ማለት ነው።ሁለት ፊደል ሆኖ በሀ የጨረሰ ግሥም እንዲሁ ነው። ሎሀ ጻፈ ብሎ ሎሀ፣ ሎሁ፣ ሎሀት፥ ሎሃ፣ ሎህከ፣ ሎህክሙ፣ ሎህኪ፣ ሎህክን፥ ሎህኩ፥ ሎህነ ይላል ማለት ነው።


ጥያቄ
የሚከተሉትን ቃላት በ10ሩ መራሕያን ከነትርጉማቸው አርባ።

1 ባልሐ (አዳነ)
2 ተፈሥሐ (ተደሰተ)
3 ሞዐ (አሸነፈ)


መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
መሠረተ ግእዝ
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 12🌹 በ"ሀ" እና በ"አ" የሚጨርሱ ግሦች እነዚህ ግሦች ሲዘረዘሩ በአንደኛና በሁለተኛ መደቦች ቅድመ መድረሻቸውን ወደ ራብዕ ቀይረው ይዘረዘራሉ። ግእዝ አማርኛ ውእቱ መጽአ መጣ ውእቶሙ መጽኡ መጡ ይእቲ መጽአት መጣች ውእቶን(ሴ) መጽኣ…
የግእዝ ክፍል 12 ጥያቄዎች መልስ

1ኛ ውእቱ ባልሐ አዳነ
ውእቶሙ ባልሑ አዳኑ
ይእቲ ባልሐት አዳነች
ውእቶን ባልሓ አዳኑ
አንተ ባላሕከ አዳንክ
አንትሙ ባላሕክሙ አዳናችሁ
አንቲ ባላሕኪ አዳንሽ
አንትን ባላሕክን አዳናችሁ
አነ ባላሕኩ አዳንኩ
ንሕነ ባላሕነ አዳንን


2ኛ ውእቱ ተፈሥሐ ደስ አለው
ውእቶሙ ተፈሥሑ ደስ አላቸው
ይእቲ ተፈሥሐት ደስ አላት
ውእቶን ተፈሥሓ ደስ አላቸው
አንተ ተፈሣሕከ ደስ አለህ
አንትሙ ተፈሣሕክሙ ደስ አላችሁ
አንቲ ተፈሣሕኪ ደስ አለሽ
አንትን ተፈሣሕክን ደስ አላችሁ
አነ ተፈሣሕኩ ደስ አለኝ
ንሕነ ተፈሣሕነ ደስ አለን


3ኛ ውእቱ ሞዐ አሸነፈ
ውእቶሙ ሞዑ አሸነፉ
ይእቲ ሞዐት አሸነፈች
ውእቶን ሞዓ አሸነፉ
አንተ ሞዕከ አሸነፍክ
አንትሙ ሞዕክሙ አሸነፋችሁ
አንቲ ሞዕኪ አሸነፍሽ
አንትን ሞዕክን አሸነፋችሁ
አነ ሞዕኩ አሸነፍኲ
ንሕነ ሞዕነ አሸነፍን


መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1

አስተያየትና ጥቆማዎትን እንዲሁም ድጋፍ ለማድረግ ከፈለጉ @learnGeezbot ይጠቀሙ
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 13🌹

በ "ቀ፥ከ፣ገ" የሚጨርሱ ግሦች
በእነዚህ ቃላት የሚጨርሱ ግሦች ሲዘረዘሩ ፊደሉን ይውጡታል። ለምሳሌ "ሰበከ" አስተማረ ይላል። አስተማርክ ለማለት "ሰበክከ" አይባልም።"ክ" ይዋጥና "ከ" ጠብቆ "ሰበከ" ይላል።ከመጀመሪያው ሰበከ የሚለየው ይህኛው ጠብቆ በመነበቡ ነው።በምሳሌ እንመልከተው።
ግእዝ አማርኛ
ውእቱ ሰበከ አስተማረ
ውእቶሙ ሰበኩ አስተማሩ
ይእቲ ሰበከት አስተማረች
ውእቶን(ሴ) ሰበካ አስተማሩ
አንተ ሰበከ አስተማርክ
አንትሙ ሰበክሙ አስተማራችሁ
አንቲ ሰበኪ አስተማርሽ
አንትን ሰበክን አስተማራችሁ
አነ ሰበኩ አስተማርኩ
ንሕነ ሰበክነ አስተማርን
አስተውል በአንደኛና በሁለተኛ መደቦች ያለው የ"ከ፣ቀ፥ገ" ዘር ሁሉ ጠብቆ ይነበባል።ይህ ሕግ የንሕነ ቤት አያካትትም።በቀ "ሠረቀ" ወጣ ይልና ሠረቀ፣ ሠረቁ፣ ሠረቀት፣ ሠረቃ፣ ሠረቀ፣ ሠረቅሙ፣ ሠረቂ፣ ሠረቅን፣ ሠረቁ፣ ሠረቅነ ይላል። በገ ደግሞ "ኀደገ" ተወ ብሎ ኀደገ፣ ኀደጉ፣ ኀደገት፣ ኀደጋ፣ ኀደገ፣ ኀደግሙ፣ ኀደጊ፣ ኀ ደግን፣ ኀደጉ፣ ኀደግነ ይላል። አስተውል። ውእቶሙ ኀደጉ ስትልና አነ ኀደጉ ስትል የሚለያየው በንባብ ነው። ውእቶሙ ኀደጉ ስትል "ጉ" ላልቶ ይነበባል። አነ ኀደጉ ስትል ግን "ጉ" ጠብቆ ይነበባል። ውእቱ ኀደገ ሲልም "ገ" ላልቶ ይነበባል። አንተ ኀደገ ስትል ግን "ገ" ጠብቆ ይነበባል።

ስለዚህ የግሡ መድረሻ "ቀ፣ከ፣ገ" ከሆነ ስለሚውጥ ጠንቅቀህ ማየት አለብህ። ኀደግከ ሰጠቅከ ሰበክከ አይልም።ከዚያ ይልቅ ኀደገ፣ ሠጠቀ፣ ሰበከ፣ ይላል ። ኀደግኩ፣ ሰጠቅኩ፣ ሰበክኩ አይባልም ከዚያ ይልቅ ሰበኩ፣ ሰጠቁ፣ ኀደጉ ይላል። ሰበክክሙ፣ ኀደግክሙ፣ ሠጠቅክሙ፣ አይልም።ሰበክሙ፣ ኀደግሙ፣ ሰጠቅሙ ይላል እንጂ። እንዲህ እንዲህ እያለ ይቀጥላል። በ"ነ" ፊደል የሚጨርስ ግሥ ደግሞ በተለየ በንሕነ ብቻ "ነ"ን ይውጣል። ለምሳሌ ወጠነ ጀመረ ካለ በኋላ እኛ ጀመርን ለማለት "ወጠንነ" አይልም። "ን"ን ውጦ ወጠነ ተብሎ ይነበብና "ነ"ን ያጠብቀዋል።ወጠነ፣ ወጠኑ፣ ወጠነት፣ ወጠና፣ ወጠንከ፣ ወጠንክሙ፣ ወጠንኪ፣ ወጠንክን፣ ወጠንኩ፣ ወጠነ ይላል ማለት ነው።

ጥያቄ
የሚከተሉትን ቃላት በ10ሩ መራሕያን ከነትርጉማቸው ዘርዝር።

1 አስተብረከ (ሰገደ)
2 ደደቀ (ተጣላ)
3 ኮነ (ሆነ)
4 ነሰገ (ቆለፈ)


መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1

አስተያየትና ጥቆማዎትን እንዲሁም ድጋፍ ለማድረግ ከፈለጉ @learnGeezbot ይጠቀሙ
ግእዝ ክፍል ፲፪&፲፫
መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
መሠረተ ግእዝ
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 13🌹 በ "ቀ፥ከ፣ገ" የሚጨርሱ ግሦች በእነዚህ ቃላት የሚጨርሱ ግሦች ሲዘረዘሩ ፊደሉን ይውጡታል። ለምሳሌ "ሰበከ" አስተማረ ይላል። አስተማርክ ለማለት "ሰበክከ" አይባልም።"ክ" ይዋጥና "ከ" ጠብቆ "ሰበከ" ይላል።ከመጀመሪያው ሰበከ የሚለየው ይህኛው ጠብቆ በመነበቡ ነው።በምሳሌ እንመልከተው። ግእዝ አማርኛ ውእቱ ሰበከ …
#የግእዝ #ክፍል13 #ጥያቄዎች #መልስ


#አስተብረከ
ውእቱ፣አስተብረከ፣ሰገደ
ውእቶሙ፣አስተብረኩ፣ሰገዱ
ይእቲ፣አስተብረከት፣ሰገደች
ውእቶን፣አስተብረካ፣ሰገዱ
አንተ፣አስተብረከ፣ሰገድክ
አንትሙ፣አስተብረክሙ፣ሰገዳችሁ
አንቲ፣አስተብረኪ፣ሰገድሽ
አንትን፣አስተብረክን፣ሰገዳችሁ
አነ፣አስተብረኩ፣ሰገድኩ
ንሕነ፣አስተብረክነ፣ሰገድን


#ደደቀ
ውእቱ፥ደደቀ፥ተጣላ
ውእቶሙ፥ደደቁ፥ተጣሉ
ይእቲ፤ደደቀት፥ተጣላች
ውእቶን፥ደደቃ፥ተጣሉ
አንተ፥ደደቀ፥ተጣላህ
አንትሙ፥ደደቅሙ፥ተጣላችሁ
አንቲ፥ደደቂ፥ተጣላሽ
አንትን፥ደደቅን፥ተጣላችቱ
አነ፥ደደቁ፤ተጣላሁ
ንሕነ፥ደደቅነ፣ተጣላን


#ኮነ
ውእቱ፣ኮነ፣ሆነ
ውእቶሙ፣ኮኑ፣ሆኑ
ይእቲ፣ኮነት፣ሆነች
ውእቶን፣ኮና፣ሆኑ
አንተ፣ኮንከ፣ሆንክ
አንትሙ፣ኮንክሙ፣ሆናችሁ
አንቲ፣ኮንኪ፣ሆንሽ
አንትን፣ኮንክን፣ሆናችሁ
አነ፣ኮንኩ፣ሆንኩ
ንሕነ፣ኮነ፣ሆንን


#ነሰገ
ውእቱ፥ነሰገ፥ቆለፈ
ውእቶሙ፥ነሰጉ፥ቆለፉ
ይእቲ፥ነሰገት፥ቆለፈች
ውእቶን፥ነሰጋ፥ቆለፉ
አንተ፥ነሰገ፥ቆለፍክ
አንትሙ፥ነሰግሙ፥ቆለፋችሁ
አንቲ፥ነሰጊ፥ቆለፍሽ
አንትን፥ነሰግን፥ቆለፋችሁ
አነ፥ነሰጉ፥ቆለፍኩ
ንሕነ፥ነሰግነ፣ቆለፍን

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 14🌹
"የገብረ ቤቶች፣ እና የብህለ ቤቶች በየ ሲጨርሱ"
የገብረ ቤቶች የሚባሉት "ግእዝ፣ሳድስ፣ግእዝ" የፊደል አወቃቀር ያላቸው ናቸው።ለምሳሌ ገብረን ስናይ "ገ" ግእዝ "ብ" ሳድስ "ረ" ግእዝ ነው። ስለዚህ 3 ፊደል ሆነው መካከላቸው ሳድስ ሆኖ መጀመሪያውና መጨረሻው ግእዝ የሆነ የገብረ ቤት ይባላል።እና እነዚህ የገብረ ቤቶች በ10ሩ መራሕያን ሲዘረዘሩ ቅድመ መድረሻቸው ሳድሱ ቀለም ወደ ግእዝ ቀለም ተለውጦ ይዘረዘራል። ይህም በአንደኛና በሁለተኛ መደቦች ነው።እሱን እንደሚከተለው እንይ፦
ግእዝ አማርኛ
ውእቱ ገብረ ሠራ
ውእቶሙ ገብሩ ሠሩ
ይእቲ ገብረት ሠራች
ውእቶን ገብራ ሠሩ
አንተ ገበርከ ሠራህ
አንትሙ ገበርክሙ ሠራችሁ
አንቲ ገበርኪ ሠራሽ
አንትን ገበርክን ሠራችሁ
አነ ገበርኩ ሠራሁ
ንሕነ ገበርነ ሠራን
ይላል።አስተውል በአንደኛና በሁለተኛ መደቦች ሳድስ የነበረው "ብ" ወደ "በ" ተቀይሮ እንደተዘረዘረ አስተውል።የብህለ ቤት የሚባሉት ደግሞ "ሳ ድስ፣ሳድስ፣ግእዝ" የፊድል አወቃቀር ያላቸው ሦስት ፊደል ያላቸው ቃላት ናቸው።ብህለ ስንል "ብ" ሳድስ "ህ" ሳድስ "ለ" ግእዝ መሆኑን ልብ ማድረግ ነው። እና የብህለ ቤት ሆነው መጨረሻ ፊደላቸው "የ" የሆኑ ግሦች ሲዘረዘሩ በአንደኛና በሁለተኛ መደቦች ቅድመ መድረሻቸውን ወደ ሣልስ ቀይረው "የ"ን ጎርደው ይነበባሉ። ለምሳሌ ጥዕየ ዳነ ማለት ነው። እኔ ዳንኩ ለማለት ጥዒኩ እላለሁ። አስተውል ቅድመ መድረሻው "ዕ" ወደ ሣልስ "ዒ" ተቀይሮ "የ" ደግሞ ጠፍቶ ተዘርዝሯል።ቀሪዎችን ከዚህ ቀጥለን እንያቸው።
ግእዝ አማርኛ
ውእቱ ጥዕየ ዳነ
ውእቶሙ ጥዕዩ ዳኑ
ይእቲ ጥዕየት ዳነች
ውእቶን ጥዕያ ዳኑ
አንተ ጥዒከ ዳንክ
አንትሙ ጥዒክሙ ዳናችሁ
አንቲ ጥዒኪ ዳንሽ
አንትን ጥዒክን ዳናችሁ
አነ ጥዒኩ ዳንኩ
ንሕነ ጥዒነ ዳንን
ይላል ማለት ነው።አስተውል ለውጡ ያለው አንደኛ መደቦች ላይ እና ሁለተኛ መደቦች ላይ ነው።የብህለ ቤቶች መጨረሻቸው "የ" ከሆነ ነው እንደዚህ የሚረቡት። "የ" ካልሆነ ግን "ግእዝ ክፍል 11" ላይ ባለው ሕግ ይዘረዘራሉ።

ጥያቄዎች
የሚከተሉትን ቃላት ከነትርጉማቸው በ10ሩ መራሕያን ዘርዝር

1 ርእየ (አየ)
2 ሠምረ (ወደደ)

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
ክፍል- ፲፬

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
መሠረተ ግእዝ
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 14🌹 "የገብረ ቤቶች፣ እና የብህለ ቤቶች በየ ሲጨርሱ" የገብረ ቤቶች የሚባሉት "ግእዝ፣ሳድስ፣ግእዝ" የፊደል አወቃቀር ያላቸው ናቸው።ለምሳሌ ገብረን ስናይ "ገ" ግእዝ "ብ" ሳድስ "ረ" ግእዝ ነው። ስለዚህ 3 ፊደል ሆነው መካከላቸው ሳድስ ሆኖ መጀመሪያውና መጨረሻው ግእዝ የሆነ የገብረ ቤት ይባላል።እና እነዚህ የገብረ ቤቶች በ10ሩ መራሕያን ሲዘረዘሩ ቅድመ መድረሻቸው ሳድሱ ቀለም…
የግእዝ ክፍል 14 (፲፬) ጥያቄዎች መልስ

ውእቱ፣ርእየ፣አየ
ውእቶሙ፣ርእዩ፣አዩ
ይእቲ፣ርእየት፣አየች
ውእቶን፣ርእያ፣አዩ
አንተ፣ርኢከ፣አየህ
አንትሙ፣ርኢክሙ፣አያችሁ
አንቲ፣ርኢኪ፣አየሽ
አንትን፣ርኢክን፣አያችሁ
አነ፣ርኢኩ፣አየሁ
ንሕነ፣ርኢነ፣አየን

ውእቱ፣ሠምረ፣ወደደ
ውእቶሙ፥ሠምሩ፥ወደዱ
ይእቲ፥ሠምረት፥ወደደች
ውእቶን፥ሠምራ፥ወደዱ
አንተ፥ሠመርከ፥ወደድክ
አንትሙ፥ሠመርክሙ፥ወደዳችሁ
አንቲ፥ሠመርኪ፥ወደድሽ
አንትን፥ሠመርክን፥ወደዳችሁ
አነ፥ሠመርኩ፥ወደድኩ
ንሕነ፥ሠመርነ፥ወደድን

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 15🌹
የስም ዝርዝር በመራሕያን
ግእዝ አማርኛ
ውእቱ ፍቅሩ ፍቅሩ
ውእቶሙ ፍቅሮሙ ፍቅራቸው
ይእቲ ፍቅራ ፍቅሯ
ውእቶን ፍቅሮን ፍቅራቸው
አንተ ፍቅርከ ፍቅርህ
አንትሙ ፍቅርክሙ ፍቅራችሁ
አንቲ ፍቅርኪ ፍቅርሽ
አንትን ፍቅርክን ፍቅራችሁ
አነ ፍቅርየ ፍቅሬ
ንሕነ ፍቅርነ ፍቅራችን
እያለ በ10ሩ መራሕያን ይዘረዘራል። ይህ ሲሆን የራሱ የሆነ ሰዋስዋዊ ሕግ አለው። እርሱም ሦስት አካሄዶች አሉት። በዚህ አንደኛውብ አካሄድ አይተን በቀጣይ ክፍሎች ደግሞ ሌሎቹን እንመለከታለን።

አንደኛው አካሄድ በሳድስ የሚጨርሱ ስሞች የሚዘረዘሩበት ሲሆን ከላይ ያለውን ይመስላል። ለምሳሌ "ፍቅር" የሚለው ቃል የመጨረሻ ፊደሉ "ር" ሳድስ ነው። ስለዚህ በሳድስ የሚጨርሱ ስሞች ሲዘረዘሩ እንደሚከተለው ነው።

1) በውእቱ ጊዜ መድረሻ ፊደሉን ወደ ካዕብ መቀየር ነው። ፍቅሩ እንዲል።

2) በውእቶሙ ጊዜ መድረሻ ፊደሉን ወደ ሳብዕ ቀይረን ከዚያ "ሙ" ፊደልን መጨመር ነው።ፍቅሮሙ እንዲል።

3) በይእቲ ጊዜ መድረሻ ፊደሉን ወደ ራብዕ መቀየር ነው።ፍቅራ እንዲል።

4) በውእቶን ጊዜ መድረሻ ፊደሉን ወደ ሳብዕ ቀይሮን "ን" ፊደልን መጨመር ነው። ፍቅሮን እንዲል።

5) በአንተ ጊዜ መጨረሻ ላይ "ከ" ፊደልን መጨመር ነው።ፍቅርከ እንዲል።

6) በአንትሙ ጊዜ መጨረሻ ላይ "ክሙ" ፊደልን መጨመር ነው። ፍቅርክሙ እንዲል።

7) በአንቲ ጊዜ መጨረሻ ላይ "ኪ" ፊደልን መጨመር ነው። ፍቅርኪ እንዲል።

8) በአንትን ጊዜ መጨረሻ ላይ "ክን" ፊደልን መጨመር ነው። ፍቅርክን እንዲል።

9) በአነ ጊዜ መጨረሻ ላይ "የ" ፊደልን መጨመር ነው።ፍቅርየ እንዲል።

10) በንሕነ ጊዜ መጨረሻ ላይ "ነ" ፊደልን መጨመር ነው።ፍቅርነ እንዲል።

በሳድስ የሚጨርሱ ስሞች በዚህ ሕግ ይዘረዘራሉ ማለት ነው።

የእለቱ ጥያቄዎች
የሚከተሉትን ስሞች በአሥሩ መራሕያን ከነትርጉማቸው ዘርዝሩ።
1 እም (እናት)
2 ሀገር (ሀገር)
3 ትእግስት



መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
ክፍል- ፲፭

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
መሠረተ ግእዝ
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 15🌹 የስም ዝርዝር በመራሕያን ግእዝ አማርኛ ውእቱ ፍቅሩ ፍቅሩ ውእቶሙ ፍቅሮሙ ፍቅራቸው ይእቲ ፍቅራ ፍቅሯ ውእቶን ፍቅሮን ፍቅራቸው አንተ ፍቅርከ ፍቅርህ አንትሙ ፍቅርክሙ ፍቅራችሁ…
የግእዝ ክፍል 15 ጥያቄዎች መልስ

ውእቱ፥እሙ፥እናቱ
ውእቶሙ፥እሞሙ፥እናታቸው
ይእቲ፥እማ፥እናቷ
ውእቶን፥እሞን፥እናታቸው
አንተ፥እምከ፥እናትህ
አንትሙ፥እምክሙ፥እናታችሁ
አንቲ፥እምኪ፥እናትሽ
አንትን፥እምክን፥እናታችሁ
አነ፥እምየ፥እናቴ
ንሕነ፥እምነ፥እናታችን

ውእቱ፥ሀገሩ፥አገሩ
ውእቶሙ፥ሀገሮሙ፥አገራቸው
ይእቲ፥ሀገራ፥አገሯ
ውእቶን፥ሀገሮን፥አገራቸው
አንተ፥ሀገርከ፥አገርህ
አንትሙ፥ሀገርክሙ፥አገራችሁ
አንቲ፥ሀገርኪ፥አገርሽ
አንትን፥ሀገርህን፥አገራችሁ
አነ፥ሀገርየ፥አገሬ
ንሕነ፥ሀገርነ፥አገራችን

ውእቱ፥ትእግስቱ፥ትግስቱ
ውእቶሙ፥ትእግስቶሙ፥ትግስታቸው
ይእቲ፥ትእግስታ፥ትግስቷ
ውእቶን፥ትእግስቶን፥ትግስታቸው
አንተ፥ትእግስትከ፥ትግስትህ
አንትሙ፥ትእግስትክሙ፥ትግስታችሁ
አንቲ፥ትእግስትኪ፥ትግስትሽ
አንትን፥ትእግስትን፥ትግስታችሁ
አነ፥ትእግስትየ፥ትግስቴ
ንሕነ፥ትእግስትነ፥ትግስታችን

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን


መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
🌹ግእዝ ቋንቋ ክፍል 16🌹
የስም ዝር ዝር በመራሕያን ክፍል 2
ግእዝ አማርኛ
ውእቱ መሰንቆሁ መሰንቆው
ውእቶሙ መሰንቆሆሙ መሰንቋቸው
ይእቲ መሰንቆሃ መሰንቆዋ
ውእቶን መሰንቆሆን መሰንቋቸው
አንተ መሰንቆከ መሰንቆህ
አንትሙ መሰንቆክሙ መሰንቋችሁ
አንቲ መሰንቆኪ መሰንቆሽ
አንትን መሰንቆክን መሰንቋችሁ
አነ መሰንቆየ መሰንቆየ
ንሕነ መሰንቆነ መሰንቋችን
ይላል።ከሳድስ ውጭ የሚጨርሱ ስሞች ከላይ ባለው መንገድ ይረባሉ። ለምሳሌ መሰንቆ ስንል የመጨረሻ ፊደሉ "ቆ" ከሳድስ ውጭ ስለሆነ አረባቡ የተለየ ነው። ከሳድስ ውጭ የሚጨርሱ ግሦች በዚህ መልኩ ይረባሉ።በሁለተኛ እና በአንደኛ መደብ ክፍል 15 ላይ እንደተመለከትነው ነው። የተለየ ነገር የለውም።በሦስተኛ መደቦች ግን የተለየ ነገር አለ።ይኽውም፦

በውእቱ ጊዜ መድረሻው ላይ "ሁ" ፊደልን መጨመር ነው።መሰንቆሁ እንዲል።

በውእቶሙ ጊዜ መድረሻው ላይ "ሆሙ" የሚለውን መጨመር ነው። መሰንቆሆሙ እንዲል።

በይእቲ ጊዜ መድረሻው ላይ "ሃ" ፊደልን መጨመር ነው።መሰንቆሃ እንዲል።

በውእቶን ጊዜ መድረሻው ላይ "ሆን" ፊደልን መጨመር ነው። መ ሰንቆሆን እንዲል።

የእለቱ ጥያቄዎች
የሚከተሉትን ቃላት በአሥሩ መራሕያን ዘርዝሩ።
1) እንዚራ
2) ቅዳሴ
3) ፈጣሪ


ክፍል- ፲፮

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
ክፍል- ፲፮

መሠረተ፡ግእዝ
@learnGeez1
@learnGeez1
@learnGeez1
2024/10/01 15:30:31
Back to Top
HTML Embed Code: